የመብራት ሃይል ምሰሶዎች በወቅቱ አለመነሳታቸው የመንገድ ግንባታው በተያዘለት ጊዜ እንዳይጠናቀቅ ስጋት ሆኗል።

Written by on February 14, 2018

የካቲት 7 2010

የመብራት ሃይል ምሰሶዎች በወቅቱ አለመነሳታቸው የመንገድ ግንባታው በተያዘለት ጊዜ እንዳይጠናቀቅ ስጋት ሆኗል።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በራስ ሃይል ከሚያስገነባቸው የአዲስ አስፋልት መንገድ ግንባታ  ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የየካ ሚካኤል በግ ተራ ሚሊኒየም መንገድ ፕሮጀክት ከወሰን ማስከበር ስራው ጋራ ተያይዞ የመብራት ሃይል ምሰሶዎች በወቅቱ ከመንገድ ወሰን ውስጥ ተነስተው ባለማጠናቀቃቸው  የመንገድ ግንባታ ስራው በተያዘለት ጊዜ እንዳይጠናቀቅ ስጋት ሆኗል ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የራስ ሃይል መንገድ ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ኢንጅነር ሙህዲን ረሻድ እንደገለፁት ፕሮጀክቱ አጠቃላይ 500 ሜትር ርዝመት በ25 ሜትር ስፋት የእግረኛ መንገድን ጨምሮ የሚገነባ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ግንባታው በ8 ወራት ጊዜ ለማጠናቀቅ ታስቦ በህዳር 2010 ዓ.ም የተጀመረ ቢሆንም በመሰረተ ልማት ዘርጊ ተቋማት ያሉ የወሰን ማስከበር ስራዎች ባለመጠናቀቃቸው ፕሮጀክቱ በታሰበለት ፍጥነት እየተከናወነ አይደለም፡፡

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት በአቋራጭነት እንዲያገለግል ተብሎ እየተገነባ ሲሆን ከሾላ ወደ ሚሊንየም መንገድ በቀላሉ ለመውጣት እንዲያስችል ተብሎ የሚገነባ ነው፡፡

 


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]