የሩሲያው አውሮፕላን አየር ላይ ነደደ ።

Written by on February 12, 2018

የሩሲያው አውሮፕላን አየር ላይ ነደደ ።

ከሞስኮ 1000 ማይልስ ርቃ ወደምትገኘው ኦርስክ ከተማ ለመጓዝ የተነሳው የበረራ ቁጥር AN148 የሆነው ይህ አውሮፕላን በተነሳ በ10 ደቂቃ ውስጥ ከራዳር እይታ ውጪ በመሆን በአየር ላይ እንዳለ በአሰቃቂ ሁኔታ ጋይቷል ።
በውስጡ የበረራ ቡድኑን ጨምሮ 71 ተጓዦችን ይዞ የነበረ ሲሆን ከአደጋው የተረፈ አንድም ሰው የለም ።
እንደ ኢንተር ፋክስ የዜና አውታር ገለፃ ከሩሲያ የፖስታ ድርጅት አውሮፕላን ጋር ተጋጭቶ ነው የሚል ያልተረጋገጠ መረጃ የወጣ ቢሆንም ከዚህ አደጋ በስተጀርባ ስላለው ነገር አልታወቀም ።

በአሁኑ ሰአት የሟቾችን አስክሬን ማንነት ለመለየት የDNA ምርመራ እየተካሄደ ነው፡፡
የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት የክስ መዝገብ የተከፈተ ሲሆን ከሟቾቹ ውስጥ አንድ የስዊዘርላንድ ዜጋ እንደነበር ታውቋል፡፡


No automatic alt text available.

 ምንጭ : አልጀዚራ

 

Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]