የእንቦጭ አረምን ለመቆጣጠር 2 ሚሊየን ብር ተመደበ፡፡

Written by on December 29, 2017

የእንቦጭ አረምን ለመቆጣጠር 2 ሚሊየን ብር ተመደበ፡፡

በታላቁ የጣና ሀይቅ ላይ ተንሰራፍቶ ጀልባዎችን አላንቀሳቅስ አሳዎችን አላስተነፍስ ያለውና ኢትዮጲያውያንን ስጋት ላይ የጣለውን የእንቦች አረም ለመከላከል የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለመንቀሳቀሻ የሚሆን 2 ሚሊየን ብር መበጀቱን ይፋ አድርጓል ፡፡በክልሉ መንግሥት፣ በበጎ ፈቃደኛ ወጣቶችና በክልሉ ውስጥ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የእንቦጭ አረም ከተከሰተ ወዲህ ለመከላከል ጥረት እየተደረገ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ሙሉ በሙሉ ሐይቁን መታደግ አልተቻለም፡፡

የአረም ስርጭቱን ለመቆጣጠር የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የእንቦጭ አረምን በሳይንሳዊ ዘዴ ለማስወገድ 150 የሚሆኑ እንቦጭን ብቻ የሚመገቡ ጢንዚዛዎችን ከወንጂ ስኳር ኮርፖሬሽን የምርምር ማዕከል በማምጣት የተለያዩ የሙከራ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱንና ጎንደር ዩንቨርስቲ አረሙን የሚያጭድ ማሽን ስራ ላይ ማዋል ቢቻልም ውጤቱ የተገመተውን ያህል ውጤታማ መሆን አልቻለም፡፡
የክልሉ መንግስት ግን እንቦጭን በ10 ቀናት ውስጥ እስከ ታህሳስ 30 ከጣና ላይ አጠፋለው ብሏል፡፡

Image may contain: mountain, grass, nature and outdoor
Image may contain: plant, outdoor and nature

Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]