ኢትዮ ቴሌኮም ምርትና አገልግሎቶቹን ለማቅረብ ልዩ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች ሊመርጥ ነው፡፡

Written by on December 21, 2017

በኢትዩጲያ የቴሌኮም አገልግሎቶችን በብቸኝነት የሚያቀርበው ኢትዩ ቴሌ ኮም በሀገሪቱ ከተሞች 94 ምርቶቹን እና አገልግሎቶቹን የሚያቀርብባቸው ለመሸጥ ልዩ ፈቃድ ያላቸውን ሱቆች ለመክፈት አቅዷል፡፡ እነዚህን ድርጅቶቹን ለመምረጥም ጨረታ አውጥቷል፡፡

በጨረታው አሸናፊ ሆነው የሚመረጡት 94 አገልግሎት ሰጪዎች አሁን ኢትዮ ቴሌ ኮም በማእከሎቹ የሚሰጠውን ተመሳሳይ አገልግሎት የሚያቀርቡ ናቸው፡፡
ሱቆቹ ከአገልግሎቶች በተጨማሪም የኢትዩ ቴሌኮምን ተንቀሳቃሽ ስልኮች፤ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች እና ታብሌቶች መሸጥም ይኖርባቸዋል፡፡
አሁን ለተጫራቾች የቀረበው ጨረታ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ታህሳስ 27 የሚያበቃ ሲሆን ጥር 3 ላይ ለቴክኒካዊ ጉዳዩች ምዘና የድርጅቶቹ ዶክመንቶች ይከፈታሉ፡፡


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]