ህጋዊ ፍቃድ ሳያገኙ ስልጠና በሚሰጡ የትምህርት ማሰልጠኛዎች ላይ እርምጃ ሊወሰድ ነዉ፡፡

Written by on December 20, 2017

ህጋዊ ፍቃድ ሳያገኙ ስልጠና በሚሰጡ የትምህርት ማሰልጠኛዎች ላይ እርምጃ ሊወሰድ ነዉ፡፡

በተለያዩ ጊዜያት ትክክለኛ የሆነ ህጋዊ ፍቃድ ሳያገኙና ያልተገባ የትምህርት ክፍያ በሚጠይቁ የግልና የክረምት ስልጠና በሚሰጡ ተቋማት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ኤጀንሲ አስታዉቋል፡፡

ከዚህ ቀደም ሲል የበጋዉን ወራት በትምህርት አሳልፈዉ በክረምት ወራት የማጠናከሪያ ትምህርት ለሚወስዱ ተማሪዎች ክረምቱን አልፎ በመደበኛ የትምህርት ጊዜ ትምህርት በሚሰጡ ተቋማት ላይ ፍቃድ ከመሰረዝ እስከ ማገድ እርምጃ እንደወሰደ የገለፀዉ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ኤጄንሲ አሁን ደግሞ ህጋዊ ፍቃድ በሌላቸዉና ያለ አግባብ ክፍያን በሚያስከፍል የማጠናከርያ ትምህርት ብሎም አጫጭር ስልጠና በሚሰጡ ተቋማት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ተናግሯል፡፡


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]