የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የህጻናት ማቆያ ማእከል ከሌሎች ሴክተር መስሪያ ቤቶች ቀድሞ ቢገነባም እስካሁን ስራ አልጀመረም፡፡

Written by on November 29, 2017

የኢፌድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በዋናው መስሪያ ቤት ህንፃ ላይ የቀድሞው የጤና ጥበቃ ሚኒስተር ዶ/ር ቴውድሮስ አድሃኖም ስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት የህፃናት ማቆያ ምእከል ግንባታ ቢጀመርም አሁንም እናቶች ልጆቻቸውን ወደ ስራ ቦታ ይዘው መጥተው በነፃነት ስራቸውን መስራት አልቻሉም ሲሉ የጤና ጥበቃ ሚኒስተር የስርዓተ ፆታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ላምሮት ተናግረዋል፡፡

በኢፌድሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአገሪቱ ደረጃ የህፃናት ማቆያን በማስገንባት ቀዳሚ ሆናችሁ በአተገባበር ኃላ ቀርታችኃል የሴክተር መስሪያ ቤቶች እንቅስቃሴስ ምንድነው ተብለው ለተነሳላቸው ጥያቄ ወ/ሮ ላምሮትም በበኩላቸው ችግሩ በዘላቂነት እስኪፈታ ድረስ እናት ሰራተኞች ላይ የሚደርሰውን ጫና ለመቀነስ በኪራይ ቦታዎች ላይም ቢሆን የህፃናት ማቆያው መገንባት አለበት ሲሉ መ/ቤቱን አሳስበዋል፡፡


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]