የውጭ ዜና

Page: 4

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት የሀገሪቱን ደሴት የቋንቋ ጥያቄ ውድቅ አደረጉ፡፡ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በሜድትሪያንያን የፈረንሳይ ደሴት የሆነችውን ግዛት ይፋዊ የስራ ቋንቋ የኮርሲካን እንዲሆን እውቅና እንዲሰጡ የቀረበላቸውን ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ከዚህ በተጨማሪም የኮርሲካን ግዛት ዜጎች ያቀረቡላቸውን የልዩ መኖሪያ ፈቃድ ይሰጠን ጥያቄም ሳይቀበሉ ቀርተዋል፡፤ ነገር ግን ማክሮን ለደሴቷ ነዋሪዎች የበለጠ ኢንቨስትመንትን ለማቅረብ ቃል ሲገቡ ለግዛቷ ባለስልጣናት የሚሰጡትን […]

የጃፓን የቴክኖሎጂ ኩባንያ ከመፀዳጃ ቤት የሚወጡ ድምፆችን የሚያስቀር ስማርት ቴክኖሎጂ መሥራቱን ይፋ አደረገ፡፡ ጃፓናውያን ለሰዓት እና ለሥራ ያላቸው ክብር ትልቅ የመሆኑን ያክል በጣም ትሁት እና ሥነ-ምግባር የተላበሱ ህዝቦች እንደሆኑ ይገልጻል፡፡ ሮላንድ የተባለ የጃፓን የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሰሞኑን የሀገሪቷን ህዝብ ወግና ልማድን መሠረት ያደረገ የቴክኖሎጂ ውጤት ይዘው ብቅ ማለታቸውን አስታውቀዋል፡፡ የቴክኖሎጂ ኩባንያው በጃፓናውያን ዘንድ ነውር የሆነውን ከመፀዳጃ […]

በታይዋን የመሬት መንቀጥቀጥ አሁንም ቀጥሏል ፡፡ የ4 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው እንዲሁም ለ220ዎች ጉዳት ምክንያት የሆነው ከፍተኛ የታይዋን መሬት መንቀጥቀጥ አሁንም እንደቀጠለ ነው። ይህ 6.4 ሬክተር ስኬል ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ወደ እኩለ ሌሊት ሲሆን በከፍተኛ ሁኔታም በምስራቅ የምትገኘውን የባህር ዳርቻ ደሴቷን የሁሉየን ከተማ ተፅእኖ አድርሶባታል። የሁሉየን ከተማ ነዋሪዎች ከፈራረሱ ቤቶቻቸው እንዲርቁ የተነገራቸው ሲሆን ይህንንም ተከትሎ 800 […]

የሰሜን ኮሪያው ፕሬዝዳንት እህት በደቡብ ኮሪያ የኦሎምፒክ ጨዋታ ላይ ሊገኙ ነው፡፡ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ተፅእኖ ፈጣሪ እህት ደቡብ ኮሪያ በምታዘጋጀው የኦሎምፒክ ጨዋታ ላይ ሊገኙ መሆኑ ብዙዎችን እያነጋገረ ሲሆን እስከ ባለፈው ዓመት ፍፃሜ ድረስ የሀገሪቱን የፖሊት ቢሮ ለማስተዋወቅ የሰሩ ጠንካራ ሴት እንደሆኑ በብዙዎች ይመሰከርላቸዋል፡፡   2ቱ ኮሪያዎች በኦሎምፒክ ጨዋታዎች ላይ በአንድ ሰንደቅ አላማ […]

በጥንት ጊዜ እንግሊዛውያን ጥቁር ቆዳ እንደ ነበራቸው አንድ ጥናት ይፋ አደረገ፡፡ ከአንድ የዘረመል ቅንጣት ላይ ተወስዶ በተደረገ ጥናት ከ10ሺህ አመታት በፊት እንግሊዛውያን ጥቁር ፊትና ሰማያዊ ዓይን እንዳላቸው የተረጋገጠ ሲሆን ጥናቱ የተካሄደው ለንደን ከሚገኘው የተፈጥሮ ታሪክ ሙዚየም ውስጥ በተገኘ ቅሪተ አካል ላይ ነው፡፡እንደ ጥናቱ መሪ ገለፃ በሙዚየሙ የተገኘው ቅሪተ አካል የተሟላ አካል ያለው ሲሆን በ1909 የተገኘ […]

የደቡብ ሱዳን ወጣቶች በጸረ-አሜሪካ ተቃውሞ ላይ የነበሩ ጋዜጠኞች ላይ ጥቃት አደረሱ፡፡ የደቡብ ሱዳን ወጣቶች አሜሪካ በቅርቡ በሀገሪቱ ላይ የጣለችውን ማእቀብ ተቃውመው ማክሰኞ እለት የተቃውሞ ሰልፍ አድርገው ነበር፡፡ በጁባ የተደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ ለመዘገብ በቦታው የተገኙ ጋዜጠኞች ላይ ጥቃት አድርሰዋል፡፡ ተቃውሞው የሀገሪቱ ገዢ ፖለቲካ ፓርቲ የደቡብ ሱዳን ህዝቦች ነጻነት እንቅስቃሴ ወጣቶች ሊግ አባላት እና ሌሎችም በርካታ ወጣቶች […]

የኬንያ መንግስት የናሳ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ከፍተኛ መሪዎችን ፓስፖርት ይዞባቸዋል፡፡ የኬንያ ሞምባሳ ገዢ ሀሰን ጆሆ፤ የሲያ ከተማ ተወካይ ህግ አውጪ ጄምስ ኦሬንጎ እና ቀድሞ የህግ አውጪ አባል ጆንሰን ሙታማ በሀገሪቱ ፓስፖርታቸው ከተያዘባቸው የናሳ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች መካከል ናቸው፡፡ የሀገሪቱ መንግስት ከእነዚህ በተጨማሪም ሌሎች የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲው ቁልፍ አባላትን ፓስፖርት በጊዜያዊነት ነው ሲል ይዟል፡፡ ይህ እርምጃ […]

ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ ውጥረት ውስጥ ናቸው፡፡ ፕሬዚዳንቱ ከፓርቲያቸው ኤ ኤን ሲ ፓርቲ አባላት ጋር በምን ጉዳዮች ላይ እንደተወያዩ ግልጽ ባይደረግም የፓርቲው መሪዎች ሰኞ ጥር 28 አስቸኳይ ስብሰባ መቀመጣቸው ታውቋል፡፡ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ ሰሞኑን ከፓርቲያቸው ኤ ኤን ሲ ፓርቲ አባላት ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ ስልጣን እንዲለቁ ከፍተኛ ጫና እየደረሰባቸው መሆኑን ተነግሯል ፡፡ ተንታኞች እንደሚሉት […]

በሩሲያ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ላይ ፑቲን በተወዳዳሪነት ስማቸዉ ሰፈረ:: የወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት የሆኑት ቭላድሚር ፑቲን በመጪዉ የፈረንጆቹ መጋቢት 18 በሚካሄደዉ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንደሚወዳደሩ የሀገሪቱ ማዕከላዊ የምርጫ ኮሚሽን አስታዉቋል፡፡ፑቲን ባካሄዱት ዘመቻም ከ 1.6 ሚሊየን በላይ የድጋፍ ፊርማ አሰባስበዋል፡፡ የምርጫ ኮሚሽኑ እንዳለዉ በፓርላማ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሚወክሉ እንደ ፑቲን የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ የማይጠበቅባቸዉ 2 ተፎካካሪዎችን ስለመመዝገቡ የተናገረ ሲሆን […]

በግብጽ የሲና ከተማ መኪና ላይ በተጠመደ ቦምብ 15 የግብጽ ፖሊሶች እንደተገደሉ የሀገሪቱ የደህንነት ምንጭ ያመላክታል፡፡ ፖሊሶቹ ህይወታቸውን ያጡት ከሲና ከተማ ከባል አል አብድ ወደ ሰሜናዊው ከተማ አል አራሽ በሚጓዙበት ወቅት እንደነበርም የተገለፀ ሲሆን ከተጎዱት መካከል ከፍተኛ ማእረግ ያላቸው የፖሊስ አባላትም እንዳሉበትም በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡ የትኛውም አካል ለዚህ አደጋ ተጠያቂ እንደማይሆን እንዲሁም የግብጽ መንግስትም ማንንም ተጠያቂ እንዳላደረገ […]


[There are no radio stations in the database]