መስከረም 15/2007

በሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ2007 ዓ.ም ፕሮግራሙ ሲወጣ ከ17 ዓመት በታች እንዲራዘም ተደርጓል፡፡ ዛሬ በነበረው ውይይት የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የማዕከላዊ ሰሜን ዞን ክለቦች የወልዲያ ከነማ ሳይረጋገጥ 10 ሆነዋል፡፡ አዲስ ክለብ ፕሪምየር ሊጉን የተቀላቀለው እቴጌ የተባለው ቡድን ሆኗል፡፡

የደበብ ምስራቅ ዞን የነበሩት እንደሚቀጥሉ ተረጋግጧል፡፡

ፕሪምየር ሊጉ ቀድሞ ጥቅምት 29/2007 ይጀመራል ተብሎ ቀን የተቆረጠለት ሲሆን ዛሬ ክለቦች ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ለአንድ ሳምንት እንዲራዘም ተወስኗል፡፡ በዚህም መሰረት ህዳር 6 ወይም ህዳር 7 ይጀመራል ተብሏል፡፡

በወጣው ፕሮግራም መሰረት በመጀመሪያው ሳምንት

   በማዕከላዊ ሰሜን ዞን

-ቅድስተማሪያም ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

-ቅ/ጊዮርጊስ ከ ዳሽን ቢራ

-መከላከያ ከ ደደቢት

-ኢትዮጵያ መድን ከ ኢትዮጵያ ቡና

-አዲስ መጪው እቴጌ ከ መብራት ሀይል ይጫወታሉ፡፡

በደቡብ ምስራቅ ዞን

-አዳማ ከነማ ከ ሀረር ቢራ

-ሲዳማ ቡና ከ ሀዋሳ ከነማ

-ወላይታ ዲቻ ከ ሙገር ሲሚንቶ

-ድሬዳዋ ከነማ ከ አርባምንጭ ይጫወታሉ፡፡

ከ17 ዓመት በታች የፕሪምየር ሊግን በተመለከተ፡-

በአዲስ አበባ ክለቦች ብቻ የተጀመረው ውድድር በዘንድሮ ዓመት ክልሎችን በማሳተፍ ውድድሩን ለማስጀመር እንደታሰበ ተገልጧል፡፡ በዚህም ምክንያት የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓትም እንዲቆይ ተደርጓል፡፡

የተጫዋጮች የእድሜ ማጣራትን በተመለከተም የMRI ምርመራው በአንድ ቦታ ላይ ሁሉም ክለቦች እንዲያደርጉ ይደረጋል ተብሏል፡፡ (አርያት ራያ)

በዛሬው እለት የኮሚቴ አባላቱ በአዲስ አበባ በካፍ ድጋፍ በሲ ኤም ሲ አካባቢ የተገነባውን የወጣቶች አካዳሚን ጎብኝተዋል ፕሬዘዳንቱ ኢሳ ሀያቱ አንዲሁም የካፍ ዋና ፀሀፊ ኢሻም አል ኤምራኒን ጨምሮ የማእከሉ ዳይሬክተር የቀድሞ የኢትዮጵያ የእግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ ሳህሉ ገብረወልድ ተገኝተዋል፡፡

አካዳሚው ያልተጠናቀቁ ስራዎች ሲኖሩት ስራዎቹ ተጠናቀው የፊታችን ሰኔ ወር በተሟላ ሁኔታ ታዳጊዎችን ተቀብሎ ስልጠና መስጠት ይጀምራል ተብሏል፡፡ስልጠና መስጠት ሲጀምር 40 ያህል ታዳጊዎችን በአንዴ ተቀብሎ እንደሚያሰለጥን ዋና ፀሀፊው ኢሻም  አል ኢምራኒ አረጋግጠዋል ፡፡ ጠቅላላ ጉባኤውም የፊታችን ቅዳሜ ይጠናቀቃል የ2019 እና የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጆችንም ያሳውቃል በነገው እለትም ለማዘጋጀት ጥያቄ ያቀረቡ ሀገራት እቅዳቸውን ለጠቅላላ ጉባኤው ያሳውቃሉ፡፡ ከሊብያ አዘጋጅነት የተነጠቀው የ2017ቱ አዘጋጅ ግን ቅዳሜ ግልፅ አይሆንም ምክንያቱም ሌሎች የሚያዘገጁ ሀገራት ካሉ ይጠበቃሉ ተብሏል፡፡ (አርያት ራያ)

welayta Dicha

መስከረም 07/2007

ለአዲሱ የውድድር ዓመት 4 ተጫዋቾችን ከሆሳእና ከነማ፣ ከድሬደዋ ከነማ፣ ከዳሸን ቢራና ሱሉልታ ሲያመጡ ሁለት ተጫዋቾች ቡድኑን ለቀዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በልምምድ ላይ የሚገኘው ቡድኑ የአዲሱ ዓመት ጨዋታቸውን በወላይታ ሶዶ ሜዳው ለማድረግ ዝግጅቱን የማጠናቀቅ ስራ ላይ ይገኛል፡፡

አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ለዛሚ 90.7 ኤፍ ኤም እንደገለፁት ከደጋፊው፣ ከከተማው አስተዳደርና ከክለቡ ባለቤት የወላይታ ልማት ማህበር ድጋፎች ተደርገውለታል፡፡ የውድድር ዓመቱ እንደተጀመረም ከክልሉ ቃል የተገባለት የስፖርተኞች ሰርቢስም እስከ ጥቅምት 30 ይገባል መባላቸውን ገልፀዋል፡፡

አሰልጣኙ በ2006 ዓ.ም ያሳየውን ጥሩ አቋምም ለመድገም እየሰራን ነው ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

(አርያት ራያ)

walyawochu

ሶስት (3) ተጫዋቾችተጠርተዋል፤እንደአዲስቡድኑንየተቀላቀለውየመከላከያውፍሬውሰለሞን (ጣቁሩ) ሲሆንየኢትዮጵያቡናውዳዊትእስጢፋኖስእናየዳሸንቢራውአስራትመገርሳበድጋሚተጠርተዋል፡፡


ግብጠባቂዎች:~ጀማልጣሰው
ታሪክጌትነትሲሳይባንጫ

ተከላካዮች:~አሉላግርማ
አበባውቡጣቆብርሃኑቦጋለ
ቶክጀምስአክሊሉአየነው
አንዳርጋቸውይላቅሰላሀዲንባርጊቾአንተነህተስፋዬዋሊድአታ

አማካዮች፡
አስራትመገርሳምንተስኖትአዳነ
ሽመልስበቀለታደለመንገሻ
አዳነግርማምንያህልተሾመ
ናትናኤልዘለቀዳዊትእስቲፋኖስ
ፍሬውሰለሞንዩሱፍሳላ
ኤፍሬምአሻሞ
አጥቂዎች :~ኡመድኡኩሪ
ሰላሀዲንሰኢድጌታነህከበደ
ዳዋአቲሳአሚንኦስካርናቸው፡፡

ዋና አሰልጣኙ ማሪያኖ ባሬቶ በአሁኑ ሰዓት ሀገራቸው ፖርቹጋል የሚገኙ ሲሆን መች እንደሚመለሱና ብሄራዊ ቡድኑም ጥቅምት 1 ከማሊ ለሚያደርገው ጨዋታ ዝግጅቱን መች እንደሚጀምር የተረጋገጠ ነገር የለም፡፡

(አርያት ራያ)

ነሐሴ 23/2006

                                                                                                          

በግብፅ የሚገኘው አጥቂው ሳላዲን ሰአድና በሱዳን የነበረው አዲስ ህንፃ ቡድኑን ተቀላቅለዋል፡፡

ብሄራዊ ቡድኑ ዛሬ 9 ሰዓት ሁለተኛ የአዲስ አበባ ልምምዱን ይሰራል፡፡ አሰልጣኝ ማሪያኖባሬቶ 3 ተጫዋቾችን ቀንሰው የ30 ተጫዋቾችን ስም ይፋ አድርገዋል፤

ግብ ጠባቂዎች-

ሲሳይ ባንጫ

ታሪኩ ጌትነት

ጀማል ጣሰው

ተከላካይ-

አሉላ ግርማ፣ ስዩም ተስፋዬ፣ አበባው ብጣቆ፣ ብርሃኑ ቦጋለ፣ አክሊሉ አየነው፣ ቶክ ጀምስ፣ ግርማ በቀለ፣ አንዳርጋቸው ይላቅ፣ሰላሃዲን ባርጌቾ

አማካዮች-

ጋቶች ፓኖም፣አስራት መገርሳ፣አዲስ ህንፃ፣ምንተስኖት አዳነ፣ሽመልስ በቀለ፣ታደለ መንገሻ፣አዳነ ግርማ፣ ምንያህል ተሾመ፣ናትናኤል ዘለቀ፡፡

አጥቂዎች-

በሃይሉ አሰፋ፣ኡመድ ኡክሪ፣ሰላሃዲን ሰኢድ፣ጌታነህ ከበደ፣ፍፁም ገ/ማሪያም፣የሱፍ ሰላህ፣ዳዋ ሆትሴ ፣ኤፍሬም አሻሞ

ዳዊት ፍቃዱን መሱድ መሀመድ ሽመልስ ተገኝ ከቡድኑ የተቀነሱ ተጫዋቾች ሲሆኑ አሉላ ግርማና ስዩም ተስፋዬ በድጋሚ ተቀላቅለዋል፡፡

በአርያት ራያ

images

ሊቨርፑል ሪያል ማድሪድ ማንቺስተር ሲቲ ባየርሙኒክ አርሴናል ቦሩሲያዶርትሙንድ ቸልሲ ሻልካ 04 ተገናኝተዋል

በምድብ 1                                      ምድብ 2

ጁቬንቱስ                                          ባዝል

አትሌቲኮ ማድሪድ                                /ማድሪድ

ኦሊምፒያኮስ                                    ሊቨርፑል

ማልሞ                                            ሉዶጎሬት

ምድብ 3                                        ምድብ 4

ዜኒትፒተርስበርግ                                 ዶርትሙንድ

ቤኔፊካ                                             አርሴናል

ሊቨርኩሰን                                      ጋላታሰራይ

ሞናኮ                                               አንደርሌክት

ምድብ 5                                          ምድብ 6

ማንችስተርሲቲ                                     PSG

ባየርሙኒክ                                         ባርሴሎና

CSK ሞስኮ                                        አያክስ

ሮማ                                                  አፖንኒኮሲያ

ምድብ 7                                           ምድብ 8

ሻልካ 04                                         ሻካታርዶንቴክስ

ቸልሲ                                               ፖርቶ

ስፖርቲንግሊዝበን                                 አት/ቢልባኦ

ማርሊበርን                                         ባቴቦሪሶቭ

 አሪያት ራያ

 

hand bal team

ለአራት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 20 አመት በታች የዞን አምስት የእጅ ኳስ ሻምፒዮና በኢትዮጲያ የበላይነት ተጠናቀቀ

4ቀናት ሲካሄድ በቆየው ሻምፒዮና ትላንት በፍፃሜው ኢትዮጲያ ሱዳን ተገናኝተው 48 12 አሸንፈው ነው የዋንጫው ባለቤትነታቸውን ያረጋገጡት

ከትላንት በስቲያ በሴቶች በተከናወነው የዋንጫ ጨዋታ የኢትዮጲያ ሴቶች ሶማሊያን አሸንፈው ዋንጫውን አንስተዋል

በነዚህ አራት ቀናት ጕንለጕን የአሰልጣኝነትና የዳኝነትስልጠናወች በአለም አቀፊ የእጅ ኳስ ፌዴሬሽን ተሰጥቷል ስልጠናውን ከወሰዱት መካከልም በዳኝነት 8 በአሰልጣኝነት ደግሞ 14 ኢትዮጲያዊያን ሆነዋል

አሪያት ራያ

                               

Ethiopian Hand ball

በዓለም አቀፍ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን እሁድ የጀመረው የዞን 5 ሀ የእጅ ኳስ ሻምፒዮና እንደ ቀጠለ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ እየተካሄደ ባለው ሻምፒዮና በመክፈቻው የኢትዮጵያ የሴቶች ቡድን ከሶማሊያ አቻው ተገናኝቶ 32 ለ11 ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡

ትላንት በተመሳሳይ በወንዶቹ ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ተጫውተው ኢትዮጵያ 37 ለ15 አሸንፈዋል፡፡

ዛሬ ቀጥሎ ሲካሄድ በሴቶች ኢትዮጵያ ከሶማሊያ በድጋሚ ይገናኙና የሁለቱ ጨዋታ አሸናፊ ሻምፒዮን ይሆናል፡፡ በወንዶቹ ሱዳን ከኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ይጫወታሉ፤ሱዳኖች እሁድ ሶማሊያን 23 ለ20 አሸንፈዋል፡፡

ሻምፒዮናው በነገው ዕለት በኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ ፍፃሜውን ያገኛል፡፡

a52153726f8889146a759b4351534192eb7734b56908cba99b6dd24e6c29a781

ብራዚል ዝግጅት ሲያደርግ የሰነበተው የኢትዮጲያ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ ምሽት 2:45 አዲስ አበባ ይገባል:: ዋሊያወቹ በብራዚሉ ቆይታቸዉ 5 አራተኛ ዲቪዚዮን ከሚገኙ ቡድኖች ጋር የአቋም መለኪያ ጫወታዎች አድርጎ 3 ሲሸነፍ በሁለቱ አቻ ተለያይቷል በዚህም 7 ግቦችን ሲያስተናግድ 3 ግቦችን አስቆጥሯል

በመጀመሪያው ጨዋታ በሬሞ 1 0 በሁለተኛው ጋማ 1 1 ሲለያይ ሉዚያና 1 0 ብራዚሊያንሴ

2 0 በመጨረሻው 1948 ከተመሰረተው አናፓሊና ተጫውቶ

2 2 ተለያይቷል

ብሄራዊ ቡድኑ ዛሬ ይገባና ጳጉሜ 2 የአዲስ አበባ ስቴድየም አልጄሪያ ጫወታ ዝግጅቱን አጠናክሮ ይቀጥላል 

ዘንድሮ ፕሪምየር ሊጉን የተቀላቀሉት አዳማ ከነማና ወልዲያ ከነማ የመጀመሪያ ጫወታቸውን ከቅ/ጊዮርጊስና ደደቢት ያደርጋሉ፡፡

አዳማ ከነማ በሜዳው ቅ/ጊዮርጊስን ሲያስተናግድ ወልድያ ከነማ አዲስ አበባ መጥቶ ከደደቢት ይጫወታል፡፡

-    ሀዋሳ ከነማ ከ አርባ ምንጭ ከነማ

-    ወላይታ ዲቻ ከ ዳሽን ቢራ

-    ሲዳማ ቡና ከ ሙገር ሲሚንቶ

-    መከላከያ ከ መብራት ሀይል

-    ኢትዮጵያ ቡና ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመጀመሪያው ሳምንት ጫወታዎች ናቸው፡፡ ፕሪምየር ሊጉ ግን መች እንደሚጀምር አልተገለፀም፡፡