ህዳር 24/2007 ዓ.ም

ቢቢሲ በየዓመቱ ምርጥ የአፍሪካ የዓመቱን ኮከብ እግር ኳስ ተጫዋች በድረ-ገፁ አማካኝነት እንደሚያስመርጥና እንደሚሸልም ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት እጩ ካደረጋቸው አምስት ተጫዋቾች በስፖርት ድረ-ገፅ በዓለም ዙሪያ ያሉ እግር ኳስ አፍቃሪዎች ዘንድሮ ምርጥ የሚሉትን ኮከብ ተጫዋች እንዲመርጡ በማድረግ አሸናፊዎችን ይፋ አድርጓል፡፡ ያሲን ብራሂሚም በአጠቃላይ የምርጫ ውጤት የናይጄሪያዊውን ግብ ጠባቂ ቪሰንት ኢኒያማን ቀድሞ የኮከብነት ሽልማቱን አንስቷል፡፡

የፓርቹጋሉ ፖርቶ ክለብ የክንፍ ተጫዋች እና የ24 ዓመቱ ያሲን ብራሂሚ በዘንድሮው ሽልማት የመጀመሪያው አልጄሪያዊ በቢቢሲ የተመረጠ የአፍሪካ ምርጥ ኮከብ ተጫዋች መሆን አስችሎታል፡፡

‹‹ይህን ሽልማት መቀበሌና አሸናፊ መሆን መቻሌ ለእኔ ትልቅ ክብር ነው፤ በእኔ ብቃት ተማርኮ እኔን የመረጠኝን የሀገሬ ህዝብ እንዲሁም ሁሉንም የአፍሪካ ህዝቦች ላመሰግናቸው እወዳለሁ››ብሏል፡፡ ያሲን ብራሂሚ ከሽልማቱም በኋላ ደስታውን እየገለፀ ነው፡፡ አያይዞም ‹‹ይህ ሽልማት ይበልጥ መልካም ስራንና የተሻለ እንቅስቃሴን እንዳደርግ ጥንካሬን ይሰጠኛል፡፡ ራሴን ለማሻሻልና የበለጠ ለመስራት እንደ ትልቅ አጋጣሚ ነው የምጠቀምበት፤ የተሻለ ለመስራት አሁን ያለሁበትን ምርጥ አቋም ማስቀጠል ይኖርብኛል›› በማለትም አስተያየቱን ለቢቢሲ ሰጥቷል፡፡

ብራሂሚ በ2014 ለሀገሩ ብሄራዊ ቡድን እና ለክለቡ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ላይ ምርጥ ብቃቱን አሳይቷል፡፡ ሀገሩ አልጄሪያን በብራዚሉ የዓለም ዋንጫ እስከ 16 እንድትደርስ ምርጥ ብቃቱን ተጠቅሞ የበኩሉን አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡ በመድረኩም የጀመሪያውን ኢንተርናሽናል ግቡን አልጄሪያ ደቡብ ኮሪያን 4ለ2 በረታችበት ጨዋታ ላይ አስቆጥሯል፡፡ ያሲን ብራሂሚ በስፔኑ ክለብ ግራናዳ ያሳየው እንቅስቃሴም በሀገሪቱ የአፍሪካ ምርጥ ተጫዋች አሰኝቶታል፤ ወደ ፖርቶ እንዲዘዋወር እድሉን የፈጠረለትንም ብቃት ያሳየበትም ነው፡፡

ብራሂሚ በአዲሱ ክለቡ ፖርቶ በ15 ጨዋታዎች ተሰልፎ 6 ግቦችን በማስቆጠር ስኬታማ የሚባል እንቅስቃሴ ማሳየት ችሏል፡፡ ተጫዋቹ በኢኳቶሪያል ጊኒ በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ቀዳሚ የአልጄሪያ ተመራጭ ተጫዋች ሆኗል፡፡ (አርያት ራያ)

ህዳር 22/2007 ዓ.ም

ቅዳሜና እሁድ በክልል እና በአዲስ አበባ ጨዋታዎቹ ተከናውነዋል፡ወደ ይርጋለም የተጓዘው /ጊዮርጊስ ሲዳማ ቡናን ነጥብ ሲያስጥል፤ ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በዳሽን ቢራ በሜዳው ተሸንፏል፡፡ቅዳሜ እለት አስቀድሞ ከፍተኛ ግምት በተሰጠው የመከላከያ ከደደቢት ጨዋታ መከላከያዎች ፍጹም የበላይ ሆነው አምሽተዋል፤በዘንድሮዉ የውድድር አመት ምርጥ ብቃታቸውን እያሳዩ ከሚገኙ የመከላከያ ተጫዋቾች መሀከል አንዱ የሆነው ዩሀንስ ሀይሉ (ኩባ) ከቅ/ጊዮርጊስ በነበረው ጨዋታ ያሳየውን አቋም በመድገም የጨዋታው ኮከብ ሆኗል፡፡
እስካሁን ባደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች አሸናፊ የነበሩት ደደቢቶች የጅብሪል አህመድ አለመኖር መሀሉ እዲሰበር እና ተከላካዩ እንዲጋለጥ ሆኖባቸዋል፡፡መከላከያዎች 32 ደቂቃ ላይ ሙሉአለም ጥላሁን ባስቆጠረው ግብ አንድ ለባዶ አሸንፈው 5 ጨዋታ  2 ንጹ ግብ 9 ነጥብ ይዘው ከመሪው ደደቢት በግብ ክፍያ ተበልጠው ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
ሌላው ቅዳሜ ት በክልል በተከናወነ ጨዋታ ሀዋሳ ከነማ ወልዲያ ከነማን 2 1 አሸንፏል፡፡
ለሃዋሳ ግቦቹን ታፈሰ ተስፋዬ እና አንተነህ ተሻገር ለወልዲያ ብቸኛዋን ግብ የቀድሞው የመከላከያው ተጫዋች በዳሶ ሆራ አስገኝቷል፡፡
ፕሪሜር ሊጉ ትላንት ቀጥሎ በአዲስ አበባ ስታዲየም ዳሽን ቢራን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተሻ ግዛው ከርቀት ያሻገራት ከኳስ በቀጥታ መረቡ ላይ አርፋ ዳሽኖች 3 ነጥብ ይዘው ወጥተዋል፡፡ 1130 ላይ በአራተኛው ሳምንት ጨዋታ ወደ አሸናፊነት የመጡት ኢትዮጵያ ቡናዎች አርባምንጭ ከነማን 3 1 አሸንፈዋል ፡፡ አርባምንጮች 7ተኛው ደቂቃ ላይ በረከት /ጻዲቅ ባስቆጠራት ግብ አስቀድመዉ መምራት ቢችሉም ቢኒያም አሰፋ 18ተኛው ደቂቃ ላይ የአቻነቷን ግብ አስገኝቶ የመጀመሪያው አጋማሽ 1 1 ተጠናቀቀ፤በሁለተኛው 45 የተጫዋች ለውጥ በማድረግ ወደ ሜዳ የተመለሱት ቡናዎች 75ኛው ደቂቃ ላይ በድጋሚ ቢኒያም አሰፋ 84ተኛው ደቂቃ ጥላሁኝ ወልዴ አስቆጥረው ጨዋታቸውን 3 1 አሸንፈዋል፡፡
በክልል ወደ ይርጋለም የተጓዙት /ጊዮርጊሶች በጥሩ አቋም ላይ የሚገኘውን ሲዳማ ቡናን በሜዳዉ 2 0 ረትተዋል ግቦቹንም አዳነ ግርማ እና በሀይሉ አሰፋ አስገኝተዋል፡፡
በሌላ ጨዋታ አሰላ ላይ መብራት ሀይል ሙገርን 3 2 ሲያሸንፍ ለሙገር ክንደአምላክ ፈቀደ እና ሄኖክ ፍሰሀ ለመብራት ደግሞ ማንኮቀዌሳ፣ወንድምአገኝ ዘሪሁን እና ራምኬል ሎክ አስቆጥረዋል፡፡
የወላይታ ዲቻ ከአዳማ ከነማ በዲቻ 3 2 የበላይነት ሲጠናቀቅ ግቦቹን ለወላይታ ዲቻ ባዬ ገዛኸኝ ሁለቱን፤ አንደኛዋን አልአዛር ፋሲካ የአዳማን ግቦች ደግሞ ቢኒያም አየለ ዳኛቸው በቀለ አስቆጥረዋል፡፡ (አርያት ራያ)

ማዕከላዊ ዞን ሀ                                   ማዕከላዊ ዞን ለ

  1. አራዳ ክ/ከተማ                             1. አዲስ ከተማ ክ/ከተማ

  2. ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ                   2. ቦሌ ክ/ከተማ   

  3. አዲስ አበባ ከተማ                          3. የካ ክ/ከተማ

  4. ካሳንችስ አቧሬ ሀይኮፍ                      4. ባዮስ ኮልጅ

  5. ቦሌ ገርጂ                                 5. አ.አ ዩኒቨርሲቲ

  6. ፌ/ፖሊስ                                  6. ኢትዮጲያ መድህን

  7. ኢት/ውሀ ስፖርት                          7. አ.አ ፖሊስ

  8. ልደታ ከ/ከተማ                            8. ቡራዩ ከተማ

  9. ሰበታ ከተማ                                9. ዱከም ከተማ

  10. ሱሉልታ ከተማ                           10. ለገጣፎ ከተማ

  11. ቢሾፍቱ ከተማ                           11. ሆለታ ከተማ

  12. ዋዜማ                                  12. ደብረ ብረሀን ከተማ

  13. መቂ ከተማ                             13. ጨፌ ዶንሳ ከተማ

 

 

ምዕራብ ዞን ሀ                                  ምዕራብ ዞን ለ

 

 1. ቡታጅራ ከተማ                         1. ጅማ ከተማ
 2. ወራቤ ከተማ                           2. ጅማ አባቡና
 3. ዓለም ገበያ ከተማ/ሳንኩራ                3. መቱ ከተማ
 4. ሆሳእና ከተማ                          4. ካፋ ቡና
 5. አስሚድ ከተማ                         5 . ሚዛን አማን
 6. ባቱ ከተማ                             6. ነቀምቴ ከተማ
 7. አምበሪቾ ከተማ/ዶምበያ/                 7. ጋምቤላ ከተማ
 8. ሃላባ ከተማ                             8. አሶሳ ከተማ
 9. ወሊሶ ከተማ
 10. ወልቂጤ ከተማ
 11. ላንፎር ከተማ

 

 

ሰሜን  ዞን ሀ                             ሰሜን ዞን ለ                           

 

 1. ፋሲል  ከተማ                   1. መቀሌ ከተማ
 2. ባህርዳር ከተማ                  2. ጥቁር አባይ ትራንስፓርት
 3. ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ         3. ኮምቦልቻ ከተማ
 4. አማራ ውሀ ስራ                 4. ሶሎዳ አድዋ
 5. አዊ እምፒልታቅ                5. ወልዋሎ
 6. አማራ ፖሊስ                   6. ደሴ ከተማ
 7. ሴቲት ሁመራ                  7. ሱሁል ሽሬ እንደስላሴ
 8. ደብረ ማረቆስ ከተማ            8. አክሱም ከተማ
 9. ዳሞት ከተማ                   9. አርሶአደር እንደመሆኔ
 10. አምባ ጊዮርጊስ/ወገራ/           10. ትግራይ ውሀ ስራ
 11. ዳባት ከተማ                   11. ዋልታ ፖሊስ

 

 

ምስራቅ ዞን                          ደቡብ ዞን 

 

 1. ሀረር ሲቲ                   1. ሻሸመኔ
 2. ድሬደዋ ከተማ               2. ደቡብ ፖሊስ
 3. ድሬደዋ ፖሊስ               3. ጅንካ ከተማ
 4. ናሽናል ሲሚንት             4. ዲላ ከተማ
 5. ምስራቅ አየር ምድብ         5. ሮቤ ከተማ
 6. መተሀራ ስኳር               6. ኮንሶ ኒዮርክ
 7. ሪፍት ቫሊ ዩ.ኮሌጅ          7. ነገሌ ቦረና
 8. ወንጂ ስኳር                 8. አዶላ ወዩ ከተማ
 9. ጅግጅጋ ከተማ              9. ቡሌሆራ
 10. ሰመራ ከተማ               10. አርሲ ነገሌ
 11. ሞጆ ከተማ                 11. ጋርዱላ ከተማ
 12. ሼር ኢትዮጲያ

 

ውድድሩ ታህሳስ 4 ተጀምሮ ሰኔ 30 ይጠናቀቃል ተብሏል ፡፡

 

 

 

 

 

 

ህዳር 17/2007 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ስታዲየም ዘጠኝ ሰአት ላይ የተገናኙት በዘንድሮዉ የዉድድር አመት ጠንካራ ስብስብ ይዞ የመጣዉ ደደቢት ከ ወላይታ ዲቻ ነበሩ፡፡ ጥሩ ፉክክር በታየበት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ደደቢት 20ኛዉ እና 27ኛዉ ደቂቃ ላይ ሳሙኤል ሳኑሚ ባስቆጠራቸዉ ግቦች እየመራ የመጀመሪያዉ 45 ቢጠናቅቅም በሁለተኛዉ 45 የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረግ የቻሉት ዲቻዎች 50ኛዉ እና 57ኛዉ ደቂቃ ላይ አልአዛር ፋሲካ ግቦችን አስቆጥሮ አቻ ሆኑ፤ ብዙም ሳይቆይ ግን ከቅ/ጊዮርጊስ ዘንድሮ ደደቢትን ተቀላቅሎ ጥሩ ብቃቱን እያሳየ የሚገኘዉ ሳኑሚ 64 ደቂቃ ላይ የማሸነፊያዋን ግብ አስቆጥሮ ጨዋታው 3 ለ 2 ተጠናቋል፡፡

11፡30 ላይ ጨወታቸውን ያደረጉት መከላከያ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ሲሆኑ ሁለቱ ቡድኖች ማራኪ የሆነ ጨዋታ አሳይተዋል፡፡ ከእረፍት በፊት ተመጣጣኝ የሚባል እንቅስቃሴ ያደረጉ ሲሆን በሁለተኛው አጋማሽ መከላከያ የተሻለ ተንቀሳቅሷል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ  በዘጠነኛው ደቂቃ  ያገኘውን ቅጣት ምት ደጉ ደበበ መትቶ የግቡ አግዳሚ የመለሰውን ሳላዲን በርጌቾ በጭንቅላቱ በመግጨት ግሩም ግብ አስቆጥሯአል፡፡ አንድ ለባዶ እየተመሩ የመጀመሪያውን አርባ አምስት ያጠናቀቁት መከላከያዎች ከእረፍት መልስ ተጭነው በመጫወት በግምት ከሰላሳ ሜትር አካባቢ ያገኙትን ቅጣት ምት መሃመድ ናስር አሳምሮ በመጠቀም የቀድሞ ክለቡ ላይ በግሩም ሁኔታ አስቆጥሮ ጨዋታውን በአንድ አቻ ውጤት አጠናቀዋል ፡፡

በክልል ወደጎንደር የተጓዘው ኢትዮጵያ ቡና ዳሽንን ሁለት ለ አንድ አሸንፎ የመጀመሪያውን ሶስት ነጥብ አስመዝግቧል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና በዘንድሮ የውድድር ዓመት ጥሩ የሚባል ጅማሮ ያላሳየ ሲሆን ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች ተሸንፏል፡፡ ትላንት በፋሲለደስ ስታዲም ዳሽንን 2 ለ 1 ሲያሸንፍም የተከላካይ መስመር ተጫዋቹን ሮብል ግርማን እና ግብ ጠባቂዉን ሙሴ ገ/ኪዳንን በቀይ ካርድ አጥቶ ነዉ፡፡ በእለቱ ጨዋታ ለኢትዮጵያ ቡና ሁለቱንም ጎሎች ቢኒያም አሰፋ ሲያስቆጥር ለዳሽን ቢራ ብቸኛዋን ገብ የተሻ ግዛው አስገኝቷል፡፡ (አርያት ራያ)

ህዳር 15/2007 ዓ.ም

ትናንት በአዲስ አበባ ስቴድየም 10፡00 ሰዓት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመብራት ሃይል የተገናኙ ሲሆን ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ አሳይተው አንድ አቻ ውጤት ጨዋታቸውን አጠናቀዋል ግቦቹን ለመብራት ሃይል ዊሊያም አሴንጆ ለባንኮች ደግሞ ፊሊፕ ዳውዚ አስቆጥረዋል፤ በክልል በተከናወኑ ጨዋታዎች አዳማ ላይ አዳማ ከነማ ከሃዋሳ ከነማ ባደረጉት ጨዋታ በረከት አዲሱ ለአዳማ እንዲሁም ተመስገን ተክሌ ለሃዋሳ ግብ አስገኝተው ጨዋታቸውን በ1 ለ 1 አቻ ውጤት ሲያጠናቅቁ፤ ከሃዋሳ ግርማ በቀለ በቀጥታ ቀይ ካርድ ከአዳማ ከነማ አብዱልከሪም አባ ፎጊ በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ ወጥተዋል፡፡

በሌሎች የክልል ጨዋታዎች አርባ ምንጭ ከሲዳማ ቡና ባዶ ለባዶ ሲለያዩ ወደ ወልዲያ የተጓዘው ሙገር ሲሚኒቶ 1 ለ 1 ጨዋታውን አጠናቋል፡፡ ለወልዲያ አብይ በየነ ለሙገር ሲሚንቶ መርዋን ራያ ግብ አስቆጣሪዎች ናቸው፡፡ ፕሪሜር ሊጉ በነገው ዕለት ቀጥሎ ሲካሄድ በአዲስ አበባ ስታዲየም 9፡00 ሰዓት ላይ ደደቢት ከወላይታ ዲቻ 11፡30 መከላከያ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ሲጫወቱ ጎንደር ላይ ዳሸን ቢራ ኢትዮጵያ ቡናን ያስተናግዳል፡፡

በሌላ በኩል የማዕከላዊ ሰሜን ዞን የሴቶች ፕሪሜር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜና እሁድ ተከናውኗል ዛሬም በሁለት ጨዋታዎች ቀጥሎ ይውላል፡፡

ቅዳሜ ዕለት ደደቢት ከእቴጌ ባደረጉት ጨዋታ ዘንድሮ ሊጉን የተቀላቀሉት እቴጌዎች ከአንደኛው ሳምንት የተሻለ ማራኪ እንቅስቃሴ አሳይተው በደደቢት 3 ለ 0 አሸንፈዋል፡፡

ለደደቢት ግቦቹን ዘንድሮ ከሃዋሳ ከነማ ደደቢትን የተቀላቀለችው ሎዛ አበራ ሁለቱን ግቦች ስታስቆጥር ሰርካለም አሊ አንደኛዋን ግብ አስገኝታለች ትላንት ወደ ጎንደር የተጓዙት መከላከያዎች በዳሸን ቢራ 1 ለ 0 ሲሸነፍ ብቸኛዋን ግብ ብርቱካን ገ/ክርስቶስ አስቆጥራለች፡፡ ፕሪሜር ሊጉ ቀጥሎ ኢትዮጵያ ቡና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ ባንኮች ቡናን 4 ለ 0 ሲያሸንፈው፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅድስተ ማሪያምን 3 ለ 1 አሸንፏል፡፡ (አርያት ራያ)

ህዳር 15/2007 ዓ.ም

‹‹አገርን ለማልማት ሴቶችን እናሳትፍ›› በሚል መሪ ቃል ዘንድሮ በድምቀት የተካሄደው 14ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 40ሺ ሰዎችን አሳትፎ በሴቶች ውዴ አያሌው ለ3ኛ ጊዜ አሸናፊነቷን ስታረጋግጥ በወንዶቹ አዝመራው አንደኛ ሆነው በማጠናቀቅ የ40ሺ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን ጨምሮ ታዋቂ አትሌቶችና በርካታ ኢትዮጵያዊያን የተሳተፉበት የዘንድሮው ታላቁ ሩጫ በጃንሜዳ መነሻ እና መድረሻውን አድርጎ ሲካሄድ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ 40ሺ ሰዎች የተሳተፉበት ውድድር ለተከታታይ ዓመት በሰላም መጠናቀቁ በሀገሪቱ የተዘረጋውን አስተማማኝና ዘላቂ ፀጥታ ያረጋገጠ ነው ሲል የውድድሩ የበላይ ጠባቂ እና መስራች ዶ/ር ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ስላሴ ተናግረዋል፡፡

የዘንድሮውን ውድድር በሴቶች ከዚህ ቀደም በ2008 እና በ2009 ሁለት ጊዜ ሻምፒዮን የሆነችው ውዴ አያሌው ታላቁ ሩጫን 3 ጊዜ በማሸነፍ ኮከብነቷን አረጋግጣለች፡፡ በ34 ደቂቃ 03 ሰከንድ ከ04 ማይክሮ ሰከንድ በመግባትም የ40 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላታል፡፡

ነፃነት ጉደታ በ34 ደቂቃ 09 ሰንድ ከ04 ማይክሮ ሰከንድ ለሁለተኛ፤ እንዲሁም ገበያነሽ አየለ በ34 ደቂቃ 17 ሰከንድ ከ06 ማይክሮ ሰከንድ ሶስተኛ ሆነው ተከታትለው ገብተዋል፡፡

በተመሳሳይ በወንዶች የ2010 አሸናፊ የነበረው አዝመራው በቀለ 30 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ ከ01 ማይክሮ ሰከንድ አንደኛ ሆኗል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ አዝመራው መንግስቱ በ30 ደቂቃ ከ13 ሰከንድ ከ09 ማይክሮ ሰከንድ ሲያጠናቅቅ አዱኛ ታከለ በ30 ደቂቃ ከ17 ሰከንድ ከ09 ማይክሮ ሰከንድ ሶስተኛ ሆነው ጨርሰዋል፡፡

በ2012 የትራይትሎን ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ያጠለቀው ታዋቂው አትሌት አሊስተን ብሮንሊ በውድድሩ ተካፋይ ሲሆን በማራቶን ዓለም ሻምፒዮናዋ ኬንያዊቷ ኤዲና ኪፕ ላጋት ደግሞ ተጋባዥ እንግዳ በመሆን በውድድሩ ላይ ተገኝታለች፡፡ (አርያት ራያ)

ህዳር 09/2007 ዓ.ም

አዲስ ሊጉን የተቀላቀለው እቴጌ በመብራት የ 7 ለ 1 ሽንፈትን ሲያስተናግድ የአምናው ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅድስተ ማርያምን 5 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ቅዳሜ በአዲስ አበባ ስታዲየም ፕሪሚየርሊጉ ሲጀመር 9፡00 ላይ የተገናኙት ለብሄራዊ ቡድን በርካታ ተጫዋቾችን ያስመረጠውና የአምናው ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከቅድስተ ማርያም ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች 5 ለ 0 ቅድስተ ማርያምን በመክፈቻ ጨዋታቸው አሸንፈዋል፡፡ ለባንኮች ግቦቹን ረሂማ ዘርጋና ሽታዬ ሲሳይ ሁለት ሁለት ሲያስቆጥሩ አንደኛዋን ግብ ብሩክታይት ግርማ አስገኝታለች፡፡

11፡30 በሁለተኛው ጨዋታ የተገናኙት ቅ/ጊዮርጊስና ዳሸን ቢራ ሲሆኑ ተመጣጣኝ እንቅስቃሴን አሳይተው በአንድ አቻ ውጤት ጨዋታቸውን አጠናቀዋል፡፡ የዳሸን ቢራን ግብ ሜሮን አብዱ  ስታስቆጥር ለቅ/ጊዮርጊስ የተመዘገበውን ግብ የዳሽኗ ተከላካይ ስምረት ሃይሉ በራሷ መረብ ላይ  አሳርፋለች፡፡

እሁድ እለት በተከናወነው ቀሪ ጨዋታዎች ደደቢት መከላከያን 5 ለ 1 ኢትዮጵያ ቡና ኢትዮጵያ መድህንን 2 ለ 1 አሸንፈዋል፡፡ ሰኞ እለት በተከናወነው ብቸኛው ጨዋታ ሊጉን ዘንድሮ የተቀላቀለው እቴጌ በመብራት ሃይል የ7 ለ 1 ሽንፈትን አስተናግዷል፡፡

በመአከላዊ ስምን ዞን የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች በወጣዉ መርሀግብር መሰረት የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም ሰኞ ቀጥለዉ ሲካህዱ የደቡብ ምስራቅ ዞን ጨዋታዎች ቤርጋለም ወላታ እና በድርደዋ ምዳዎች ይጀመራሉ፡፡ (አርያት ራያ)

ህዳር 02/2007 ዓ.ም

በወዳጅነት ጨዋታው መጠነኛ ጉዳት ያጋጠማቸው ሰለሃዲን በርጌቾና ዋሊድ አታ ከጉዳታቸው አገግመው አብረው እንደሚጓዙ ታውቋል፡፡

የፊታችን ቅዳሜ በ2015ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከአልጀሪያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ብሊዳ ላይ  የመልስ ጨዋታውን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሐሙስ ምሽት 3፡00 ወደ ስፍራው ይጓዛል፡፡

አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ በውጭ ሀገር ክለቦች የሚጫወቱትን ጨምሮ 26 ተጫዋቾችን ይዘው ትናንትና ልምምዳቸውን ሰርተዋል፡፡ ዛሬ እንደታወቀው ደግሞ ወደ ስፍራው የሚጓዙ ተጫዋቾች 20 መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡

በዚህም መሰረት

ግብ ጠባቂዎች፡- ጀማል ጣሰውና ታሪክ ጌትነት

ተከላካዮች፡- ብርሃኑ ቦጋለ፣ ቢያድግልኝ ኤልያስ፣ ሰለሃዲን በርጌቾ፣ ግርማ በቀለ፣  ዋሊድ አታ፣ አበባው ቡጣቆ

አማካዮች፡- ምንተስቶት አዳነ፣ አንዳራጋቸው ይላቅ፣ ታደለ መንገሻ፣ ናትናኤል ዘለቀ ፋሲካ አስፋው፣ ሽመልስ በቀለ  ኤፍሬም አሻሞ፣ ዩሱፍ ሳላህ

አጥቂዎች፡- ዳዋ ሁጤሳ፣ ዳዊት ፍቃዱ፣ ራምኬል ሎክ፣ ኡመድ ኡክሪ ሆነዋል፡፡

በአጠቃላይም ወደ ስፍራው የሚጓዘው የልዑካን ቡድን 31 እንደሆነም ታውቋል፡፡

(አርያት ራያ)

ህዳር 01/2007 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ስታዲየም 9:00 ላይ አርባ ምንጭ ከነማን ያስተናገደው መከላከያ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ጨዋታውን አጠናቋል፡፡
11:30 ላይ የተገናኙት ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ እና ሙገር ሲሚንቶ ጨወዋታቸውን 2 2 ሲያጠናቅቁ ማራኪ እቅስቃሴን አሳይተዋል። ባንኮች በፊሊፕ ዳውዚ እና አዲሱ ሰይፊ ግቦች 2 0 እስከ 72ኛው ደቂቃ ድረስ መምራት ቢችሉም በሁለተኛው 45 የተጫዋች ለውጥ አድርገው የተሻለ እንቅስቃሴ ማሳየት የቻሉት ሙገሮች 72ተኛው እና 93ተኛው ደቂቃ ላይ አካካፓ ጌዲዬን ባስገኛቸው ግቦች ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል
በክልል ~ ወደ ይርጋለም የተጓዘው ዳሽን ቢራ 2 1 ሽንፈትን ሲያስተናግድ ሁለቱን ከብሄራዊ ሊግ ያደጉት አዳማ ከነማ እና ወልዲያ ከነማን ያገናኘው የአዳማው አበበ ቢቂላ ስታዲየም 3 1 ውጤት ተመዝግቦበታል በባለሜዳው አዳማ አሸናፊነት።
(አርያትራያ
)

ህዳር 1/2007 ዓ.ም

ጋናዊዉን ፒር ኢመሪክ አቡሚያን ግከቦሪሲያዶርትሙንድ
ከአልጀሪያ ያሲን ብራሂሚ ከፖርቶ
ከናይጄሪያ ግብ ጠባቂውን ቪሴንት ኤኒያማ ከሊል
ከኮትዲቯር ዠርቪኒኆ ከሮማ
ከዚያው ከኮትዲቯር ያያ ቱሬን ከማንችስተር ሲቲ ምርጥ አምስት ውስጥ ተካተዋል፡፡ ቢቢሲ የአፍሪካ ምርጥ እግርኳስ ተጫዋች እያለ 2000 ጀምሮ ሲሸልም መሃመድ ባረካት 2005 መሃመድ አቡታሪካ 2008 ከግብፁ አልሃሊ አንደሬ አዩ ከጋና የቶጎው አዲባየር 2007 አረሰናል እያለ እንዲሁም የናይጄሪያው ኮከብ ጄይ ጄይ ኦኮቻ 2003 እና 2004 አሸናፊ ነበሩ፡፡የአምናው 2013ቱ አሸናፊ ደግሞ የዘንድሮ አምስት ውስጥ የተካተተው የሲቲው ያያቱሬ ነበር፤ ቢቢሲ እስከ ህዳር 14 ደጋፊዎች በአጭር የፁሁፍ መልዕክት ድምፅ እንዲሰጥ ክፍት ያደረገ ሲሆን ህዳር 22 አሸናፊውን ይፋ ያደርጋል፡፡

(አርያት ራያ)