የካቲት 12/2007 ዓ.ም

14 ክለቦችን የሚያሳትፈው የኢትዮጵ ፕሪሜር ሊግ ጥቅምት 15/2007 ጅማሮውን አድርጎ በተስተካካይ የሚደረጉ ጨዋታዎችን ጨምሮ ጥር 24 በሲዳማ ቡና መሪነት ተጠናቋል ፡፡

በዚህ በመጀመሪያው ዙር በተደረጉ 91 ጨዋታዎች 356 ግቦች ከመረብ አርፈዋል፤ 368 ቢጫ ካርዶች ሲመዘዙ 25 የቀይ ካርዶች ታይተዋል ፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ በዮርዳኖስ ሆቴል የክለብ ተወካዮች እና አሰልጣኞች በተገኙበት የመጀመሪያውን ዙር ግምገማ አድርጓል ፡፡

በፌዴሬሽኑ በቀረበው ሪፖርት መሰረት የተዘረዘሩትን ጠንካራ ጎኖች ሲል አስቀምጧል፡

 1. የውድድር ተሳትፎና ፉክክር ካለፉት ዓመታት የተሻለ ሆኖ መገኘቱ
 2. ውድድሩ የተመልካች ህብረተሰቡን ቀልብ እየሳበ መምጣቱ
 3. ተተኪ ወንድ ተጨዋቾች ስፖርተኞች እየተገኙ መሆኑ
 4. ለወንድ ተጨዋቾች የሥራ መስክ እየሆነ መምጣቱና ከፍተኛ የገንዘብ ክፍያም እየተከፈላቸው ገቢያቸው እየጨመረ መምጣቱ
 5. ሁሉም ክለቦች ምዝገባና የቴሲራ ዝግጅት በሰዓቱ ማከናወናቸው
 6. ውድድሩን ከመጀመሩ በፊት ለዳኞችና ኮሚሽነሮች ስልጠና መስጠቱ
 7. ተወዳዳሪ ክለቦች ለወንዶች ውድድር ትኩረት በመስጠት መሳተፋቸው
 8. የፀጥታ ሀይሎች በየሜዳው ያደርጉት የነበረው ክትትል በጣም ጥሩ መሆኑ
 9. ክለቦች በውድድራቸው ወቅት የሜዳ ገቢ ማግኘታቸው ፡፡
 10. የኮሚኒኬ ግንኙነት አልፎ አልፎ መዘግየት፣
 11. በአንዳንድ ጨዋታዎች ላይ በስታዲየም የሚገኘው ተመልካች ቁጥሩ አነስተኛ መሆኑ፣
 12. አልፎ አልፎ በተጨዋቾች ላይ እየታየ ያለው የዳኛን ውሳኔ በፀጋ አለመቀበል ችግር
 13. አልፎ አልፎ ዳኝነት ስህተቶች መኖራቸው
 14. የኮሚቴው አባላት በተሟላ ሁኔታ ውድድሮች በሚካሄዱበት ቦታዎች ተገኝተው አለመከታተል፣
 15. አንዳንድ ክለቦች የደጋፊያቸው ቁጥር አነስተኛ መሆን
 16. አንዳንድ ክለቦች በውድድሩ ደንብ መሰረት ማሟላት የሚገባቸውን ጉዳዮች አሟልተው አለመገኘት /ለምሳሌ ፡- ኳስ፣ ኳስ አቀባይ፣ ቃሬዛ፣ አምቡላንስ፣ ሐኪም/
 17. በአንዳንድ ሜዳዎች የቁጥጥር መላላት
 18. የውድድር ሰዓት አለማክበር
 19. የማወዳደሪያ ሜዳ በተሟላ መልኩ ማግኘት አለመቻል

በደካማ ጎኖች

 የተወሰዱ የመፍትሔ ዕርምጃዎች ሲል ደግሞ

    1. በተቻለ መጠንና ባለው የሰው ሃይል በ2 ሳምንት ኮሚኔኬ እንዲደርስ ማድረግ  

    2. ከተለያዩ ቋሚ ኮሚቴዎች ጋር ከብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ከዲስፕሊን ኮሚቴ ጋር

       በመሆን ችግሮችን መፍታት

    3. ክለቦች ለውድድሩ የሚያስፈልጉ ነገሮችን እንዲያሟሉ በስልክ በደብዳቤ በኮሚኒኬ

መጠየቅ

4. ከፀጥታና ስፖርታዊ ጨዋነት ኮሚቴ ጋር በሜዳ ደህንነት ዙሪያ በጋራ መስራት

በክለቦቹ ከዚህ ቀደም እደሚደመጠው ዛሬም

 • የፕሮግራም መቆራረጥ
 • የጫዋታ ሰአት ምቹ አለመሆን አንድ አንድ ክለቦች በተደጋጋሚ የ9 ሰአት ጨዋታ እንዲጫወቱ መደረግ
 • የክልል ሜዳዎች የጸጥታ ችግር
 • በሁሉም ክለቦች ደግሞ ዳኝነት ላይ ጨዋታን የመምራት የአቅም ችግር በስፋት መታየቱን እና የጨዋታ ውጤት የሚቀይሩ ዳኞች መታየታቸው እንዲሁም የኮሚሽነር ምደባ በምን መልኩ ነው የሪፖርታቸው ተአማኒነት ጥያቄ የሚያስነሳ ነው የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል ከዚህ ባለፈም የጥሎ ማለፉ ፕሮግራም አወጣጥ ለምን በዕጣ አልሆነም የምድብ አባት ሆነው የመጀመሪያውን ጨዋታ እዲያርፉ የተደረጉት ቅ/ጊዮርጊስ የፕሪሜር ሊጉ ሻምፒዮን በመሆን የኢትዮጵያ ቡና በምን ምክንያት ነው የሚሉትም ተጠይቀዋል

በመጨረሻም በዚህኛው የታዩ ክፍተቶች ላይ በሁለተኛው ዙር እንደሚሰራባቸው ተገልጧል፡፡

የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎችም ሲልም ፌዴሬሽኑ እነዚህን ነጥቦች አስቀምጧል፡

 1. የሚወጡ ፕሮግራሞች በተያዘላቸው ፕሮግራም መሰረት እንዲከናወኑ

በትኩረት መሰራት 

  2. ውድድሩ ተመልካች እንዲኖረው ክለቦችም ፌዴሬሽኑም ከሚዲያ አካላት ጋር

      በመሆን ጠንክሮ መስራት

  3. የ2ኛው ዙር በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ጠንክሮ መስራት

  4. ከተለያዩ ቋሚ ኮሚቴዎች ጋር ጠንካራ የስራ ግንኙነት መፍጠር

  5. ክለቦች በወንዶች ጨዋታ ላይ የሜዳ ገቢ የሚያገኙበት ሁኔታ እያሰለመደ መምጣት ናቸው፡፡

የ2ኛው ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ መጋቢት 5 ይጀመራል፡፡

(አርያት ራያ)

የካቲት 10/2007 ዓ.ም

በማዕከላዊ ሰሜን ዞን ንግድ ባንክ በመሪነቱ ሲቀጥል የደቡብ ምስራቅ ዞንን ድሬደዋ መምራት ጀምሯል፡፡

በማዕከላዊ ሰሜን ዞን ቅዳሜ በተደረገ ጨዋታ እቴጌ ከ ቅ/ማሪያም 1 ለ 1 ሲለያዩ ኢት/ንግድ ባንክ ኤሌክትሪክን 6 ለ 0 አሸንፏል ፡፡

እሁድ በተከናወኑ ሁለት ጨዋታዎች ኢት/መድህን ከ ዳሽን ቢራ ተገናኝተው ዳሽኖች ከጨዋታ ብልጫ ጋር 5 ለ 1 ሲያሸንፉ ደደቢቶች ደግሞ ኢትዮጵያ ቡናን 4 ለ 0 ረተዋል ፡፡

በእለተ ሰኞ በተከናወነ ብቸኛ ጨዋታ መከላከያ ቅ/ጊዮርጊስን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

እሁድ በተከናወኑ የደቡብ ምስራቅ ዞን ጨዋታዎች ደግሞ አዳማ ከነማ ከ ወላይታ ዲቻ እንዲሁም ሀዋሳ ከነማ ከ ድሬደዋ ከነማ በተመሳሳይ 1 ለ 1 ሲለያዩ ሙገር ሲሚንቶ ከ አርባ ምንጭ ከነማ 0 ለ 0 ተለያይተዋል ፡፡

ደረጃውን ስንመለከት የማዕከላዊ ሰሜን ዞንን ኢት/ንግድ ባንኮች በ 39 ነጥብ ይመራሉ፤ ደደቢቶች በ 36 ሁለተኛ ናቸው ፡፡

የደቡብ ምስራቅ ዞንን ደግሞ ድሬደዋ በ 14 ነጥብ 5 ንጹ ግቦች ይዘው ሲመሩ ሙገሮች በ 14 ነጥብ በ2 የግብ እዳ ሁለተኛ ሆነዋል፡፡ (አርያት ራያ)

የካቲት 06/2007 ዓ.ም

በታላቁ ሩጫ በኢትዬጵያ አዘጋጅነት በየአመቱ የሚካሄደው ቅድሚያ ለሴቶች የ5ኪሜ ሩጫ ዘንድሮ ለ12ጊዜ ነው የሚካሄደው፡፡

በዘንድሮው ውድድር ከ10 ሺህ በላይ ሴቶች የሚሳተፉ ሲሆን ባለፈው አመት በተጀመረው “ተምሳሌት ሴቶች” ዘርፍ በተለያዩ ሙያዎች ተሰማርተው ስኬታማ የሆኑ ሴቶች እንደ ሰአሊ ደስታ ሀጎስ ፤ ወ/ሮ የትነበርሽ ንጉሴ እና ወ/ሮ ሰሎሜ ታደሰን ጨምሮ ሌሎች ስኬታማ ሴቶችም ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡

መጋቢት 6/2007 ለሚካሄደው ውድድር ከፊታችን ሰኞ የካቲት 9 ጀምሮ በእናት ባንክ ሶስት ቅርንጫፎች እንዲሁም በታላቁ ሩጫ ቢሮ ምዝገባው እንደሚካሄድ ተገልጧል፡፡ (አርያት ራያ)

የካቲት 02/2007 ዓ.ም

ከኢቦላ ወርሽኝ ስርጭት ጋር ተያይዞ በስጋት ታጅቦ ከሞሮኮ ወደ ኢኳቶሪያል ጊኒ ያመራው 30ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በፍፃሜ ኮትዲቯርን ከ ጋና አገናኝቷል ፡፡

በውድድሩ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ምርጥ ብቃታቸውን ያሳዩት ጋናዎች በግል ችሎታቸው ተጠቅመው ቡድናቸውን ለፍጻሜ ካደረሱት ኮትዲቯሮች ያደረጉት ጨዋታው መደበኛው ሰአት 0 ለ 0 ተጠናቆ ወደተጨማሪ  30 ደቂቃ ቢያመሩም ጨዋታቸውን በአቻ ውጤት በማጠናቀቃቸው  በተሰጡ የመለያ ምቶች ኮትዲቯር 9 ለ 8 አሸንፋ ሻምፒዮና ሆናለች።

ኮትዲቯር በሴኔጋል አዘጋጅነት በተካሄደው የ1992 የአፍሪካ ዋንጫ በተመሳሳይ ከጋና ጋር ተገናኝታ በተሰጡ የመለያ ምቶች 11 ለ 10 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነበር ዋንጫውን ያነሳችው የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ዋንጫውን ስታነሳ፡፡

ከዚያ ውጭ በ2006 እና 2012 በተዘጋጁ የአፍሪካ ዋንጫዎች በኮከብ ተጫዋቾቿ ታግዛ ማጣሪዎችን በጥሩ በማለፍ ለፍፃሜ ብትቀርብም ዋንጫውን ማንሳት ሳትችል ቀርታለች።

ትናንት ምሽት ወርቃማው ትውልድ እየተባሉ የሚነሱት የኮትዲቯር ተጨዋቾች ድሉን ተጎናጽፈዋል፡፡ አሰልጣኛቸውም ፈረንሳዊው ሄርቬሬናርድ በ3አመት የአፍሪካ ቆያታቸው ሁለተኛ ድላቸውን አስመዝግበዋል በ2012 ከዛምቢያ አሁን ደግሞ ከኮትዲቯር ጋር በዚህም ለሁለተኛ ጊዜ ኮከብ አሰልጣኝ ሲባሉ በኮከብ ተጫዋችነት የቀድሞው የቸልሲው ተጫዋች አሁን ኤቨርተን የሚገኘው ክሪስቲያን አትሱ ክብሩን ሲያገኝ፤ በኮከብ ግብ አስቆጣሪነት 5 ተጫዋቾች እኩል ሶስት ሶስት ግቦችን ቢያስቆጥሩም አንድሬ አዩ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ ሆኗል፡፡

ለደረጃ በተደረገው የኢኳቶሪያል ጊኒ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጨዋታ መደበኛው መደበኛው ሠአት በአቻ ውጤት ተጠናቆ፤ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ኢኳቶሪያል ጊኒን 4 ለ 2 በማሸነፍ የሶስተኝነት ደረጃን አግኝታለች።

በዚህ በ30ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የተመዘገቡ ቅጣቶችን ስንመለከት ኢኳቶሪያል ጊኒ ለፍፃሜ ለማለፍ ከጋና በነበረው ጨዋታ የአስተናጋጇ አገር ደጋፊዎች ያስነሱትን ብጥብጥ ተከትሎ ካፍ የኢኳቶሪያል ጊኒ እግርኳስ ማህበርን የ100 ሺህ ዶላር ቅጣት ሲጥል በብጥብጡ ጉዳት ለደረሰባቸው 36 ደጋፊዎች የህክምና ወጪ እዲሸፈን አዟል።

ሌላው የቅጣት ሰለባ የቱኒዚያ ቡድን ነው ግማሽ ፍጻሜ ለመግባት ከአዘጋጅዋ ኢኳቶሪያል ጊኒ ጋር በነበረው ጨዋታ ያለአግባብ በተሰጡብኝ ሁለት ፍ/ቅጣት ምቶች ከውድድር እንድወጣ ሆኛለሁ በማለት ባሰሙት ቅሬታ እና ፕሬዝዳንቱ ከካፈፍ የስራ አስፈጻሚነት እራሴን አገላለሁ በማለታቸው እርሳቸው በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቁ፤ እንዲሁም ቡድኑ የ50 ሺህ ዶላር ቅጣት ተጥሎበታል፡፡ የእለቱ ሞሪሸሳዊ ዳኛም ለ6ወር ጨዋታ እናዳይመሩ ታግደዋል፡፡ (አርያት ራያ)

 

ጥር 26/2007 ዓ.ም

ትላንት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ደደቢቶች እቴጌን 12 ለ 1 አሸንፈዋል፡፡ ግቦቹን ሎዛ አበራ 5ቱን በስሟ ስታስመዘግብ፤ ሰናይት ባሩዳ 3፣ ሰናይት ቦጋለ 2፣ ቅድስት 1ኛውን ያስቆጠሩ ናቸው፡፡ የእቴጌን ብቸኛ ግብ ደግሞ ፍቅርተ ከተማ አስገኝታለች፡፡ በሌላኛው ጨዋታ ቅ/ጊዮርጊስ ከ ቅ/ማሪያም ተገናኝተው ቅ/ጊዮርጊሶች በመቅደስ ማስረሻ ግብ 1 ለ 0 አሸንፈዋል፡፡

እሁድ በተደረገ አንድ ጨዋታ ኤሌክትሪክ ኢት/መድህንን 3 ለ 1 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

ጨዋታው ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይቀጥልና 8፡00 ሰዓት ላይ መከላከያ ከዳሽን ቢራ እንዲሁም 10፡00 ሰዓት ላይ መሪው ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ከኢትዮጲያ ቡና ይጫወታሉ፡፡ (አርያት ራያ)

ጥር 26/2007 ዓ.ም

በኢትዮጲያ አትሌቲክስ ማህበር የመነሻ ሀሳብ አዘጋጅነት እና አስተባባሪነት ትላንት በብሄራዊ ሆቴል ማህበሩ በይፋ ተመስርቷል፡፡

7 ክልሎች አትሌቶቻቸውን የሚወክሉ አትሌቶችን መርጠው ልከዋል፤ እያንዳንዱ ክልልም ድምጽ እንዲሰጥ 6 አትሌቶችን ነው ያስመዘገበው፡፡ በዚህ መሰረት ለፕሬዝዳንትነት

 # አዲስ አበባ በሀይሉ አለምእሸትን

 # ሀረሪ አሊ አብዶሽ

 # ትግራይ ገብረእግዚሀብሄር ገብረማሪያም

 # ኦሮሚያ ስለሺ ስህን

 # ደቡብ ወጠረ ገልቻ

 # አማራ የኔው አላምረው

 # ሶማሌ ከድር ኢብራሂምን አቅርበው ስለሺ ስህን ከፍተኛውን ድምጽ አግኝቶ የፕሬዝዳንትነት  ማዕረጉን በሌለበት አግኝቷል፡፡

በስራ አስፈጻሚነት ከቀረቡት 7 እጩዎች ደግሞ 6ቱ ተመርጠዋል፡፡

መሰረት ደፋር አዲስ አበባን ወክላ ከኦሮሚያው ማርቆስ ገነቲ እኩል ድምጽ በማግኘት ምክትል ፕሬዝዳንት ስትሆን ማርቆስ ገነቲ የማህበሩ አቃበ ነዋይ ፤ የማነ ጸጋዬ ከትግራይ ጸሀፊ፣ ፋንቱ ሜጌሶ ከደቡብ ክልል እና ሞስነት ገረመው ከአማራ እንዲሁም መቶአለቃ ግርማይ ብርሀኔ ከሀረሪ የስራ አስፈጻሚው አባል ሆነዋል፡፡ (አርያት ራያ)

ጥር 25/2007 ዓ.ም

ወደ  ሀዋሳ ተጉዞ ሀዋሳ ከነማን የገጠመው ደደቢት በ ብርሀኑ ቦጋለ እና በዳዊት ፍቃዱ ግቦች ሀዋሳ ከነማን በሜዳው 2 ለ 0 አሸንፎታል ቦዲቲ ላይ ወላይታ ዲቻ ከ ቅ/ጊዮርጊስ 0 ለ 0 ሲለያዩ በአበበ ቢቂላ ስታዲም ኤሌክትሪክ ኢትዮጲያ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፎታል ለመብራት ብቸኛዋን ግብ ፒተር ንዋድኬ 67 ደቂቃ ላይ አስገኝቷል ፡፡

 በ13ተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ኢትዮጲያ ቡና ወልዲያ ከነማን 5 ለ 2 ሲያሸንፍ ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ከ ሲዳማ ቡና 1 ለ 1 በተመሳሳይ ኤሌክትሪክ ከ ወላይታ ዲቻ 1 ለ 1 ቅ/ጊዮርጊስ ደደቢትን 2 ለ 0 አሸንፎታል በክልል አሰላ ላይ ሙገር ሲሚንቶ መከላከያን 1 ለ 0 ዳሸን ቢራ ሀዋሳ ከነማን 2 ለ 1 አርባ ምንጭ ከነማ ከ አዳማ ከነማ 0 ለ 0 በሊጉ የመጨረሻ ጨዋታ ሆነው የተመዘገቡ ውጤቶች ናቸው፡፡

በአንደኛው ዙር በኮከብ ግብ አግቢነት # ቢኒያም አሰፋ ከኢትዮጲያ ቡና በ 11 ግቦች ሲመራ

# ሳሙኤል ሳኑሚ ደደቢት 8

# ፊሊፕ ዳውዚ ከንግድ ባንክ 6

# ባዩ ገዛኸኝ ከወላይታ ዲቻ 5

# ቢኒያም አየለ ከአዳማ ከነማ 5

# መሀመድ ናስር ከመከላከያ 4

# አስቻለው ግርማ ከ ኢ፣ ቡና 4

# ዊሊያም ኤሴንጆ ከኤሌክትሪክ 4

# ታፈሰ ተስፋዬ ከ ሀዋሳ ከነማ 3

 የደረጃ ስንመለከት

 1. ሲዳማ ቡና…….. በ27  ነጥብ  6 ግቦች አሉት
 2. ቅ/ጊዮርጊስ ……. በ24 ነጥብ  10 ግቦች አሉት
 3. ወላይታ ዲቻ…… በ22 ነጥብ  3 ግቦች አሉት
 4. ኢት/ቡና ……… በ21 ነጥብ  5 ግብ
 5. አዳማ ከነማ……. በ19 ነጥብ  3 ግብ
 6. አርባ ምንጭ……..በ19 ነጥብ  1 ግብ
 7. ደደቢት ……….. በ18  ነጥብ  4 ግብ
 8. ኤሌክትሪክ………በ17 ነጥብ   - 1 እዳ
 9. ንግድ ባንክ………በ16 ነጥብ  2 ግብ
 10. መከላከያ ………..በ16ነጥብ   - 2 እዳ
 11. ዳሽን ቢራ……….በ16 ነጥብ  - 2 እዳ
 12. ሙገር ሲሚንቶ…በ13 ነጥብ   - 3 እዳ
 13. ሀዋሳ ከነማ………በ10ነጥብ    - 6 እዳ
 14. ወልዲያ ከነማ…..በ5 ነጥብ    - 20 እዳ

(አርያት ራያ)

ጥር 11/2007 ዓ.ም

ቅ/ ጊዮርጊስ ከሜዳው ውጭ ድል ሲቀናው አዳማ ከነማ ሲዳማ ቡና ሀዋሳ ከነማ እና ወላይታ ዲቻ በሜደቸው አሸንፈዋል።

በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም በተከናወነው የአዳማ ከነማ ከዳሽን ቢራ ጨዋታ የመጀመሪያው 45 በሁለቱም ቡድኖች ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ ታይቶበ 0ለ0 ተጠናቋል ። 

በሁለተኛው 45 የሜዳቸውን ነጥብ አሳልፈው መስጠት ያልፈለጉት የአዳማው አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ተጫዋቾችን መቀየር ጀምረዋል ተቀይረው ከገቡት ተጫዋቾ መካከል ወንደሰን ቦጋለ 81ኛው ደቂቃ ላይ ከበረከት የተሻገረለትን ኳስ አክርሮ መታ መስመር ማለፊ በግልፅ ያልታየው አወዛጋቢው ኳስ በእለቱ ረዳት ዳኛ ዳንኤል ታይቶ ነበርና ለአዳማዎች ግብ ሆኖ ተመዘገበ በዚህ ሰአት አምነው መቀበል ያቃታቸው የዳሸን ቢራ ተጫዋቾች ውሳኔውን ተቃውመው ጨዋታው በውዝግብ ለ16 ደቂቃዎች እንዲቋጭ ሆኗል ። 

ከጨዋታው በሀላ የዳሽን ቢራው አሰለጣኝ ሳምሶን አየለ የክልል ጨወታዎች ልክ እንደ አዲስ አበባ ሜዳ እኩል ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ሲሉ የእለቱን ዳኝነት ተችተዋል። የአዳማው አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ በበኩላቸው በርካታ የጎል እድሎችን ፈጥረናል ውጤቱን ይዘን ለመውጣት ያደረግነው ጥረት ተሳክቶልናል ብለዋል።

በሌሎች ጨዋታዎች መሪው ሲዳማ ቡና ኢትዮጲያ ቡናን 1ለ0 ሲያሸንፍ ሀዋሳ ከነማ ኤሌክትሪክን 2ለ1 ወላይታ ዲቻ ሙገር ሲሚንቶን 1ለ0 ወልዲያ ከነማ ደግሞ በሜዳው በቅ/ጊዮርጊስ 3 ለ 0 ተሸንፏል።
በዚሁ በ12ተኛው ሳምንት ቅዳሜ በአዲስ አበባ መከላከያ በንግድ ባንክ የ3 ለ 1 ሽንፈት ሲያስተናግድ ደደቢት ከ አርባ ምንጭ ከነማ 1 ለ 1 መለያየቱ ይታወሳል።

ኘሪምየር ሊጉ የመጀመሪያው ዙር ሊጠናቀቅ የአንድ ሳምንት ጨዋታ ብቻ ይቀራል ከተስተካካይ ውጭ የደረጃ ሰንጠረጁን ሲዳማ ቡና በ 26 ነጥብ ሲመራ የኮከብ ግብ አግቢነቱን ቢኒያም አሰፋ ከኢት/ቡና ሳሙኤል ሳኑሚ ከደደቢት በእኩል 8 ግቦች ይመሩታል። (አርያት ራያ)

ጥር 05/2007 ዓ.ም

የአለምአቀፉ እግር ኳስ መሀበር /ፊፋ/ በየአመቱ በውድድር ዘመኑ ምርጥ ብቃታቸውን ያሳዩ ተጫዋቾችን እያወዳደረ ይሸልማል፡፡

ከወር በፊት የ3 ተጫዋቾችን ስም ይፋ ማድረጉ ይታወሳል ከጀርመን ብሄራዊ ቡድን ጋርየዓለምዋንጫንባየርሙኒክጋር ደግሞ የሻምፕዮንስሊግክብርንያገኛው ግ/ጠባቂው ማኑኤልኑየርለሶስትጊዜያትሽልማቱንየተቀዳጀውየአርጄንቲናእናየባርሴሎናውግብ አዳኝሊዮኔልሜሲ፤ እንዲሁም በውድድር አመቱ ከሪያል ማድሪድ ጋር ምርጥ ብቃቱን ማሳየት የቻለው ክርስቲያኖሮናልዶ ድምጽ ተሰጥቶባቸው ትላንት ምሽት በሲውዘርላንድ  ዙሪክ ይፋ ሲደረግ ክርስቲያኖሮናልዶ የወርቅ ኳሱን አግኝቷል፡፡

በሴቶች የጀርመኗ እና የወልፍስበርጓ አማካይ ናንዲ ኬስለር፤ ከአሰልጣኞች ደግሞ ጀርመንን ለአለም ዋንጫ ድል ያበቁት ዮሀኪምሎ፤

በፑሽካሽ አዋርድ የአመቱ ምርጥ ጎል በመሆን ደግሞ በአለም ዋንጫው ሀሜስ ሮድርጌስ ለኮሎምቢያ ዑራጋይ ላይ ያስቆጠረው ግብ የተመረጠ ሲሆን የተሻለ ስራ የሰሩ በሚለው ዘርፍ የ89 አመቱ የጃፓኑ ጋዜጠኛ ሄሮሽ ካጋዋ ተሸልመዋል፡፡

በእለቱ ምርጥ 11 ተጫዋቾችም ይፋ ተደርገዋል በግ/ጠባቂ ማኑኤልኑየር፤ ተከላካዮች ፊሊፕ ለሀም፣ ዴቪድ ሉዊዝ፣ ቲያጎ ሲልቫ ሰርጂዎ ራሞስ፤ አማካይ አንድሬ ኢኔሽታ፣ ቶኒ ክሩስ እና ዲማሪያ፤ በአጥቂ ሥፍራ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ፣ ሊዮኔልሜሲ እና አሪያን ሮበን የአመቱ ምርጥ 11 ተብለዋል፡፡ (አርያት ራያ)

ታህሳስ 20/2007 ዓ.ም

9፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ወልዲያን ያስተናገደው መከላከያ 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡ 31ኛው ደቂቃ ላይ ተስፋዬ በቀለ፣ 38ኛው ደቂቃ ላይ ደግሞ ሀመድ ናስር በፍፁም ቅጣት ምት ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡

11፡30 ላይ ቅ/ጊዮርጊስ ከኤሌክትሪክ ባደረጉት ጨዋታ 1 ለ 0 ጊዮርሶች አሸንፈዋል፡፡ አዳነ በክልል ሙገር ሲሚንቶ ደደቢትን 2 ለ 1፣ ሲዳማ ቡና ወላይታ ዲቻን 2 ለ 0፣ ዳሽን ቢራ አርባ ምንጭ ከነማን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ በትናንትናው እለት በአዲስ አበባ ስታዲየም በተከናወኑ ሁለት ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀዋሳ ከነማ 1 ለ 1፣ በተመሳሳይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ አዳማ ከነማ 1 ለ 1 ጨዋታቸውን አጠናቀዋል፡፡ (አርያት ራያ)