ጥር 14/2008 ዓ.ም

በ2008 ዓ.ም ሀገራችንን በመወከል የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ላይ ይካፈላል፡፡ በቅድሚያ በወጣው የጨዋታ ድልድልም ኢትዮጵያዊው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ከሲሸልሱ ቅዱስ ሚካኤል ቡድን ጋር ይጋጠማል፡፡ የመጀመሪያ ጨዋታቸውንም በየካቲት ወር አዲስ አበባ ላይ ተጫውተው ከሁለት ሳምንት በኋላ ሲሽልስ ላይ የመልስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ እና ውጤታማ ለመሆን ዝግጅቱን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ለዚህም ይረዳው ዘንድ በአሁን ወቅት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ከሚጫወቱት ሦስት የውጭ አገር ተጫዋቾች ግብ ጠባቂው ሮበርት፣ ተከላካዩ አይዛክ፣ አጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ብራየን ከሦስቱ ኡጋንዳዊ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋቾች በተጨማሪ የውጭ ሀገር ተጫዋች ቡድኑ ተቀላቅለው እንዱጫወቱ ሙከራ ተደርጐ ቆይቷል፡፡ ለሙከራ ከመጡት የውጭ ተጫዋቾች መካከል ናይጄሪያዊው የፊት አጥቂ ስፍራ ተጫዋች ጎድዋን ቺካ በችሎታው ብቁ ሆኖ በመገኘቱ ለቡድኑ ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል፡፡ ናይጄሪያዊው የፊት አጥቂ መሰመር ተጨዋች ጎድዊን የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር 80ኛ አመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ በሚገኝበት ወቅት ከዝግጅቱ አንዱ አካል በሆነው ኢንተርናሽል የወዳጅነት ጨዋታ በቅድሚያ የሱዳኑ ኤልሜሪክ ክለብ አንድ ለዜሮ በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሲሆን ተቀያሪ ወንበር ላይ ተቀምጦ ጨዋታውን የተከታተለ ሲሆን ሁለተኛውን ኢንተርናሽናል የወዳጅነት ጨዋታ ከኬንያው ጉርማሃያ ጋር ሲጫወትም ጎድዊን ቺካ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ተሰልፎ ተጫውቷል፡፡

ምንጭ፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ

ጥር 12/2008 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ የምድቡን ሁለተኛ ጨዋታ ምሽት 1:00 ሰዓት ከካሜሮን ጋር ያደርጋል። ብሔራዊ ቡድኑ በውድድር ለመቆየት ይህንን ጨዋታ ማሸነፍ ይጠበቅበታል።
አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ በመጀመሪያው ጨዋታ የነበረውን ክፍተት እና ለዛሬው ጨዋታም ቡዱኑ ያደረገውን ዝግጅት ነግረውናል።

ቡድኑ ከመጀመሪያው ጨዋታ በኋላ ግምገማ አድርጓል፤ ደካማ ጎኑንም ለይቷል ካሉ በኋላ ባለጋራ ቡድን አለማወቃቸው አንዱ ክፍተት እንደነበር ተናግረዋል፡፡ አስቀድመን ያሰብነው የመጀመሪያዎቹን 15 ደቂቃዎች ቡድኑን አይተን ከዛ ወጥተን ለመጫወት ነበር እቅዳች ግን አልተሳካም ያሉት አሰልጣኙ የመጀመሪያው 45 ሊጠናቀቅ ሲል የተቆጠረብን ግብ የስነልቦና ክፍተት ፈጥሮብናል ብለዋል፡፡

በቪዲዮ ጨዋታውን ተመልክተን ተነጋግረንበታል፤ የጨዋታውንም መረጃዎች ለሁሉም ተጫዋቾች ሰጥተናቸው አይተውታል፤ እያንዳንዱ ተጫዋች ምን አይነት እንቅስቃሴ እንዳደረገም አይተዋል፤ እንዴት እንደሚነበብም እንዲያውቁ አድርገናል፤ ልምምዳችንን መስራት የጀመርነውም ከዚህ በመነሳት ነው ብለዋል፡፡

ከምድቡ ካሜሮን እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሶስት ሶስት ነጥብ አላቸው፤ ነጥቡ ያስፈልገናል፤ ይሄ ሌላ ቡድን ነው ያለን አማራጭ ማሸነፍ ብቻ ነው ወጥተን ሙሉ ለሙሉ በማጥቃት እንጫወታለንም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ (አርያት ራያ)

ህዳር 08/2008 ዓ.ም

አትሌት ገንዘቤ ዲባባ የ2015 የአመቱ ምርጥ አትሌት ተብሎ ለመመረጥ የመጨረሻዎቹ 3 ዝርዝር ዉስጥ ገብታለች፡፡
IAAF ይፋ እንዳደረገው መረጃ የ 2015 በሴቶች ምርጥ 3 አትሌቶችን ስም ለይቻለሁኝ ያለ ሲሆን፤ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ለአመቱ ምርጥ አትሌትነት ዝርዝር ዉስጥ ከገቡት መካከል አንዷ ሆናለችም ብሏል፡፡ ከገንዘቤ ጋር ፓላንዳዊቷ አሎሎ ወርዋሪ አኒታ ሎድዛይክ እና ኔዘርላንዳዊቷ የ200 ሜትር ሯጭ ዳፈን ሺፐርሰ በምርጥ 3 ውስጥ ተካተዋል፡፡

የወንዶች የመጨረሻዉ ዝርዝርም እየተጠበቀ ይገኛል፡፡

ምንጭ፡- iaaf.org

ነሐሴ 17/2007 ዓ.ም

ከሀምሌ 25 ጀምሮ በ24 ከለቦች መካከል ሲካሄድ የቆየው የብሄራዊ ሊግ የክለቦች ሻምፒዮና ዛሬ በድሬዳዋ ከነማ እና በሆሳዕና ከነማ መካከል በተካሄደ ጨዋታ ፍጻሜውን አግኝታል።ድሬዳዋ ከነማ ከጨዋታ ብልጫ ጋር ሆሳዕና ከነማን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዓመቱን ጉዞ በድል አጠናቋል።

ሁለቱም ቡድኖች በ2008 ዓ.ም የፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ ሲሆኑ ሻምፒዮናው ድሬዳዋ ከነማ አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተዘጋጀለትን የዋንጫ እና የ50 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆናል።

በሁለተኝነት ያጠናቀቀው ሆሳዕና ከነማ 40 ሺህ ብር ሶስተኛው ሀላባ ከተማ የ30 ሺህ ብር ሽልማት አግኝተዋል። 
በድሬዳዋ በነበረው ሻምፒዮና ኮከብ በመሆን ያጠናቀቁ ተጫዋች፣ አሰልጣኝና ዳኞችም ተሸልመዋል።
ይሁን እንዳሻው በኮከብ ተጫዋችነት በላይ አባይነህ በኮከብ ግብ አግቢነት በስድስት ግቦችን ከድሬዳዋ ከነማ የ10 ሺህ ብር ተሸላሚ ሲሆኑ በኮከብ ግብ ጠባቂነት ተክለማርያም ሻንቆ ከሃላባ ከተማ 8 ሺህ ብር ተሸልማል።
ድሬዳዋን ከሶስት ዓመት በሃላ ከብሄራዊ ሊግ ወደ ፕሪሚየር ሊግ የመለሠችው ብቸኛዋ እንስት አሰልጣኝ መሰረት ማኒ ኮከብ አሰልጣኝ በመሆን የ10 ሺህ ብር ስትሸለም የዕለቱን የፍጻሜ ጨዋታ በብቃት የመሩት ፌዴራል ዋና ዳኛ ጌቱ ተፈራ 6 ሺህ ብር ፤ፌዴራል ረዳት ዳኛ አስቻለ ወርቁ የ5 ሺህ ብር ተሸላማ ሆነዋል። (አርያት ራያ)

ነሐሴ 15/2007 ዓ.ም

ሆሳህና ከሀላባ ከቀኑ 8፡00 ሰአት ያደረገውን የዛሬውን የፍፃሜ ጨዋታ ለማየት የሀላባ ክለብ ደጋፊዎች ከሀላባ ተነስተው መንገድ ጀምረው አሰበ ተፈሪ ላይ ሲደርሱ ከባድ የመኪና አደጋ ደርሶ ሹፌሩን ጨምሮ 4 ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ 18 የሚጠጉ ደጋፊዎቸ ከፍተኛ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑ ታውቋል።

ነሐሴ 11/2007 ዓ.ም

የፊታችን አርብ በ16/12/2007 ለሊት በሚጀመረው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በተለያ የውድድር መድረኮች ተጽኖ መፍጠር የቻሉ አትሌቶች ሀገራቸውን ይወክላሉ፡፡የኢትጵያ አትሌቲክ ፌዴሬሽን በየርቀቱ የውድድሩን መግቢያ ያሟሉ አትሌቶችን ከአንድ ወር በፊት ሆቴል በማስገባት የተጠናከረ ልምምድ እንሰሩ አድርጓል፡፡አትሌቶቹም ዝግጅታቸውን በብቃት ሲያደርጉ ቆይተው ትናንት ምሽት ባረፉበት በአራራት ሆቴል አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ አለባቸው ንጉሴን ጨምሮ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በስነ-ስርአቱ ላይ የተገኙ ሲሆን ፕሬዝዳንቱ ጥሩ ተዘጋጅተናልየተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ወደ ስፍራው እናመራለን ብለዋል፡፡ አትሌቶቹም በተወካዮቻቸው አማካኝነት ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ መሰናዳቸውን የገለጹ ሲሆን በዝግጅት ሰአቱ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ እና ሀጎስ ገ/ህይወት ከአትሌቶቹ ጋር አብረው ልምምድ አልሰሩም በሽኝቱም ላይ አልተገኙም እዚያው ቤንጂንግ ቡድኑን እንደሚቀላቀሉ ነው ተነገረው፡፡37 አትሌቶችን ጨምሮ በአጠቃላይ 61 የልዑካን ቡድን ያካተተው የኢትዮጵያ ቡድን ትናንት ምሽት ወደስፍራው መጓዝ ጀምሯል፡፡በአለም አቀፉ የአትሌቲክ ማህበር የኮንግረንስ ጉባኤ ላይ የሚሳተፉት ፕሬዝዳንቱ አቶ አለባቸው ንጉሴ የጽ/ቤት ሀላፊው አቶ ቢልልኝ ንጉሴ እና የቴክኒክ ዳይሬክተሩ አቶ ዱቤ ጅሎ እንዲሁም በኮንግረንሱ ላይ ለስራ አስፈጻሚ እጩ ሆነው የሚወዳደሩት ብቸኛዋ ተወካይ ወ/ሮ ብስራት ጋሻውጠና ወደስፍራው የተጋዙ ሲሆን አትሌቶቹ ከነገ ማክሰኞ ጀምረው እንደውድድር ፕሮግራማቸው ያመራሉ፡፡የመጀመሪያው ኢትዮጵውያን አትሌቶች የሚጠበቁበት የወንዶች ማራቶን አርብ ሊት 8፡35 ሰዓት መክፈቻው ይደረጋል፤ ሌሊሳ ዲሳሳ የማነ ጸጋዮ እና ለሚ ብርሀኑ ይሳተፋሉ ፡፡ (አርያት ራያ)

ሐምሌ 26/2007 ዓ.ም

በ2008 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ የሚሳተፉ ሁለት ቡድኖችን ለመለየት 24 ቡድኖች በ4 ምድብ ተደልድለዋል፡፡ ሻምፒዮናው እስከ ነሀሴ 17/2007 ሲቆይ ዛሬ በመክፈቻው አስተናጋጁ ድሬደዋ ከነማ አርሲ ነገሌን 2 ለ 0 አሸንፎ የመጀመሪያውን 3 ነጥብ አግኝቷል። 

በዚሁ በመክፈቻው በየዞኑ ሻምፒዮን ሆነው ያጠናቀቁ ክለቦች ከፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚዎች የዋንጫ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል፡፡ (አርያት ራያ)

ሰኔ 26/2007 ዓ.ም

ዋሊያዎቹ ትናንት ናይሮቢ ሲደርሱ በኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዲሁም በኬንያ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጥሩ አቀባበል ቢደረግላቸውም በኬኒያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተጫዋቾች ሰርቪስ ካለማቅረብ ጀምሮ መልካም የሚባል አቀባበል እንዳልተደረገላቸው እና የመጀመሪያ ልምምዳቸውንም ምሽት ላይ ምቹ ባልሆነ መንገድ በካሜራ ብርሀን ታጅበው መስራታቸውን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያው ጨዋታ ባህርዳር ላይ በአስቻለው ግርማ እና በጋቶች ፓኖም ግቦች 2 ለ 0 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

የመልሱ ጨዋታ ነገ ቅዳሜ በ10፡00 ሰዓት የሚያደርግ ሲሆን በደርሶ መልሱ ጨዋታ ኬንያን የሚያሸንፍበትን ውጤት ካስመዘገበ በ2016ቱ ሩዋንዳ በምታስተናግደው የቻን አፍሪካ ለመሳተፍ የመጨረሻ ማጣሪያውን ከ ብሩንዲ እና ጅቡቲ አሸናፊ ጋር ተጫውቶ ማሸነፍ ይጠበቅበታል፡፡ (አሪያት ራያ)

ሰኔ 15/2007 ዓ.ም

በወንጂ ስታዲየም በ10 ክለቦች መካከል ሲከናወን በሰነበተው የፕሪሜር ሊጉ የማጠቃለያ ጨዋታ ለፍጻሜ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዳሸን ቢራ ተገናኝተው 90 ደቂቃውን በ 1 ለ 1 አቻ ውጤት አጠናቀው በመለያ ምት ባንኮች 4 ለ 2 በማሸነፍ ዋንጫውን አንስተዋል፡፡

ለደረጃ በተደረገው የደደቢት ከሲዳማ ቡና ጨዋታ ደደቢቶች 2 ለ 0 አሸንፈው ሶስተኛ ሆነዋል፡፡ በእለቱ በኮከብ አሰልጣኝነት የባንኩ ብርሀኑ ግዛው ሲሸለም፤  ኮከብ ተጫዋች የዳሽኗ ብርቱካን ገ/ክርስቶስ፤ በኮከብ ግብ አስቆጣሪነት ደግሞ ሎዛ አበራ ወንጂ ላይ ባስቆጠረቻቸው 5 ግቦች ኮከብ ተብላለች፡፡ (አርያት ራያ)

ሰኔ 15/2007 ዓ.ም

ሰኔ 7/2007 ዓ.ም በ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የሌሴቶ አቻቸውን 2 ለ 1፤ ትናንት ሰኔ 14 ደግሞ በቻን አፍሪካ ተሳታፊ ለመሆን በመጀመሪያው ማጣሪያ ኬንያን አስተናግደው 2 ለ 0 አሸንፈዋል፡፡ ዋሊያዎቹ ሩዋንዳ በምታስተናግደው የ2016ቱ ቻን አፍሪካ ተሳታፊ ለመሆን በደርሶ መልስ ኬንያን ከረቱ ከ ጅቡቲ እና ብሩንዲ አሸናፊ ተገናኝተው ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች ትናንት በአቻ ውጤት ጨዋታቸውን አጠናቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድኑ ነገ አዲስ አበባ ይገባል፡፡ ከሁለት ሳምንት በኋላ ኬንያ ናይሮቢ ላይ ለሚያደርገው የመልስ ጨዋታ ዝግጅት ለማድረግ ረቡዕ ወደ ሀዋሳ ይጓዛል፡፡

ኢንስትራክተር ዮሀንስ ሳህሌ ከጨዋታ በኋላ ውጤቱን አናስብም፤ 0 ለ 0 አስበን ነው የምንነሳው፤ ለመልሱ ሙሉ ትኩረት በመስጠት እንዘጋጃለን ብለዋል፡፡ 

ፌዴሬሽኑ በየጨዋታው ካሸነፋችሁ ሲል ቃል የገባውን የማበረታቻ ሽልማትም እንደሚያበረክት የቡድን መሪው አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ አረጋግጠዋል፡፡ (አርያት ራያ)