Friday, 29 August 2014 11:35

የጀርመን መንግሥት የኢራቅ ኩርዶችን ለማስታጠቅ መወሰኑ በሀገሪቱ በስፋት እያነጋገረ ይገኛል፡፡

ነሐሴ 23/2006

ፈረንሳይን የመሳሰሉ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ታጣቂ ቡድኑን አይ ኤስ አይ ኤስ ለመፋለም ያስችላቸው ዘንድ ለኩርድ ሃይሎች የጦር መሳሪያ እናቀርባለን በሚሉበት ወቅት ጀርመን ወደ ኢራቅ የጦር መሳሪያዎችን እንደማትልክ አስታውቃ ነበር፡፡ ጀርመን ሰብዓዊ እርዳታን ብቻ ለኢራቅ እንደምትሰጥ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየርም ተናግረው ነበር፡፡ ምንም እንኳን የመንግሥት ባለስልጣናት ይህንን አቋማቸውን ሲያንፀባርቁ ቢቆዩም አሁን ግን ታጣቂ ሃይሉን ለሚዋጉ የኢራቅ ኩርድ ፔሽሜርጋ ተዋጊዎች ጀርመን በልዩ አስተያየት ለማስታጠቅ መወሰኗን አስታውቃለች፡፡ ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረግ መንገድ ላይ ነን፤ የትጥቅ እርዳታም ያስፈልጋል፤ የኩርድ ሃይሎች ከአሜሪካ እና ከሌሎች ጋር ሆነው ጥቃቱን እየመከቱ ነው እኛም የድርሻችንን መወጣት አለብን ሲሉ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ተናግረዋል፡፡ ይህም ደግሞ ለጀርመናዊያኑ የመነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ የሆነ ሲሆን በእርዳታ የሚሰጡ የጦር መሳሪያዎች ከታሰበላቸው ቦታና ኢላማ ውጭ መዋል አለመዋላቸው አሳሳቢ ጉዳይ ነው እየተባለ ይገኛል፡፡ ዘገባው የዩሮ ኒውስ ነው፡፡    

ነሐሴ 23/2006

                                                                                                          

በግብፅ የሚገኘው አጥቂው ሳላዲን ሰአድና በሱዳን የነበረው አዲስ ህንፃ ቡድኑን ተቀላቅለዋል፡፡

ብሄራዊ ቡድኑ ዛሬ 9 ሰዓት ሁለተኛ የአዲስ አበባ ልምምዱን ይሰራል፡፡ አሰልጣኝ ማሪያኖባሬቶ 3 ተጫዋቾችን ቀንሰው የ30 ተጫዋቾችን ስም ይፋ አድርገዋል፤

ግብ ጠባቂዎች-

ሲሳይ ባንጫ

ታሪኩ ጌትነት

ጀማል ጣሰው

ተከላካይ-

አሉላ ግርማ፣ ስዩም ተስፋዬ፣ አበባው ብጣቆ፣ ብርሃኑ ቦጋለ፣ አክሊሉ አየነው፣ ቶክ ጀምስ፣ ግርማ በቀለ፣ አንዳርጋቸው ይላቅ፣ሰላሃዲን ባርጌቾ

አማካዮች-

ጋቶች ፓኖም፣አስራት መገርሳ፣አዲስ ህንፃ፣ምንተስኖት አዳነ፣ሽመልስ በቀለ፣ታደለ መንገሻ፣አዳነ ግርማ፣ ምንያህል ተሾመ፣ናትናኤል ዘለቀ፡፡

አጥቂዎች-

በሃይሉ አሰፋ፣ኡመድ ኡክሪ፣ሰላሃዲን ሰኢድ፣ጌታነህ ከበደ፣ፍፁም ገ/ማሪያም፣የሱፍ ሰላህ፣ዳዋ ሆትሴ ፣ኤፍሬም አሻሞ

ዳዊት ፍቃዱን መሱድ መሀመድ ሽመልስ ተገኝ ከቡድኑ የተቀነሱ ተጫዋቾች ሲሆኑ አሉላ ግርማና ስዩም ተስፋዬ በድጋሚ ተቀላቅለዋል፡፡

በአርያት ራያ

images

ሊቨርፑል ሪያል ማድሪድ ማንቺስተር ሲቲ ባየርሙኒክ አርሴናል ቦሩሲያዶርትሙንድ ቸልሲ ሻልካ 04 ተገናኝተዋል

በምድብ 1                                      ምድብ 2

ጁቬንቱስ                                          ባዝል

አትሌቲኮ ማድሪድ                                /ማድሪድ

ኦሊምፒያኮስ                                    ሊቨርፑል

ማልሞ                                            ሉዶጎሬት

ምድብ 3                                        ምድብ 4

ዜኒትፒተርስበርግ                                 ዶርትሙንድ

ቤኔፊካ                                             አርሴናል

ሊቨርኩሰን                                      ጋላታሰራይ

ሞናኮ                                               አንደርሌክት

ምድብ 5                                          ምድብ 6

ማንችስተርሲቲ                                     PSG

ባየርሙኒክ                                         ባርሴሎና

CSK ሞስኮ                                        አያክስ

ሮማ                                                  አፖንኒኮሲያ

ምድብ 7                                           ምድብ 8

ሻልካ 04                                         ሻካታርዶንቴክስ

ቸልሲ                                               ፖርቶ

ስፖርቲንግሊዝበን                                 አት/ቢልባኦ

ማርሊበርን                                         ባቴቦሪሶቭ

 አሪያት ራያ

 

hand bal team

ለአራት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 20 አመት በታች የዞን አምስት የእጅ ኳስ ሻምፒዮና በኢትዮጲያ የበላይነት ተጠናቀቀ

4ቀናት ሲካሄድ በቆየው ሻምፒዮና ትላንት በፍፃሜው ኢትዮጲያ ሱዳን ተገናኝተው 48 12 አሸንፈው ነው የዋንጫው ባለቤትነታቸውን ያረጋገጡት

ከትላንት በስቲያ በሴቶች በተከናወነው የዋንጫ ጨዋታ የኢትዮጲያ ሴቶች ሶማሊያን አሸንፈው ዋንጫውን አንስተዋል

በነዚህ አራት ቀናት ጕንለጕን የአሰልጣኝነትና የዳኝነትስልጠናወች በአለም አቀፊ የእጅ ኳስ ፌዴሬሽን ተሰጥቷል ስልጠናውን ከወሰዱት መካከልም በዳኝነት 8 በአሰልጣኝነት ደግሞ 14 ኢትዮጲያዊያን ሆነዋል

አሪያት ራያ

                               

ነሐሴ 21/2006- ስነ-ምግባር ከጎደለው አለባበስና የቋንቋ አጠቃቀም ጀምሮ ራቁት ዳንስ ቤቶችና የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት እስከ መመስረት የሚዘልቁ የራሳችን ያልሆኑ እና ከሀገራችን ባህል ታሪክና ሞራል ጋር የሚጣረሱ ድርጊቶች ይፈፀማሉ፡፡ ጉዳዩ የሚመለከተው የከተማዋ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በበኩሉ ችግሩ መሰረተ-ሰፊ ብቻም ሳይሆን ዓለም አቀፍ ይዘት ያለው ከቴክኖሎጂና ከግል ስነ-ምግባርም ጭምር የተያያዘ ስለሆነ በኛ አቅም ብቻ ሊፈታ አይችልም ብሏል፡፡ የቢሮው ሃላፊ አቶ ገብረ-ፃድቅ ሀጎስ ለዛሚ 90.7 ኤፍ ኤም እንደገለፁት ከአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ ከህግ አካላት እና በዋነኝነት  ከነዋሪው ህብረተሰብ ጋር ከፍተኛ ድጋፍና ትብብር ያስፈልገናል ብለዋል፡፡ ያም ሆኖ ቢሮአቸው የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ላይ በተለይም ከባህል ለውጥ ጋር በተገናኘ ከህብረተሰቡ ጋር መድረኮችን እየፈጠረ እያወያየ ነው ሲሉ ሃላፊው ገልፀዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በቅርቡ የተጠና ጥናት ተጠናቆ እነዚህ ቤት ያላቸው መጤ ባህሎችን ማስቀረት የሚቻልበትን የተቀናጀ አሰራር ለመጀመር በዝግጅት ላይ እንገኛለን ሲሉ አቶ ገብረ-ፃድቅ አስታውቀዋል፡፡

ነሐሴ 20/2006- ወጣት ደረጀ ለማና ወ/ሪት ደስታ ሙልጌታ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ነዋሪዎች ናቸው፡፡ ታድያ ወ/ሪት ደስታ ለጊዜው መቼ እንደሆነ ባልታወቀ ቀን ደብረዘይት ሄዳ ለመዝናናት እንቅስቃሴዋንም በፎቶ ማስቀረት ትፈልጋለች፡፡ ግና የፈለገችውን የፎቶግራፍ ማንሻ ባለማግኘቷ 8ሺ ብር የሚያወጣውን የወጣት ደረጀን ሞባይል ተውሳ ትሄዳለች፡፡

ጉዳይዋን ጨርሳ ስትመጣ ከሁለት ጓደኞቿ ጋር በመሆን አመስግና ንብረቱን ትመልሳለች፡፡ ከቀናት በኋላ ግን የተነሳሁት ፎቶ ታጥቦ ይደርስልኛል ብላ ስታስብ በምትኩ የፖሊስ መጥሪያ ይሰጣታል፡፡ ጉዳዩንም ስትመለከት ወጣት ደረጀ በእምነት ማጉደል ወንጀል እንደከሰሳትና የሰጣትን ሞባይል እንዳልመለሰችለት መግለፁን ትመለከታለች፡፡ ወዲያውም ፖሊስ ጣቢያ ቀርባ ንብረቱን መመለሷን ትናገራለች፡፡

ፖሊስም ጉዳዩን ከፌዴራል አቃቤ ህግ ጋር በመሆን መመርመር ይጀምራል፤ ምርመራውን እንዳጠናቀቀም አስፈላጊውን የሰነድ ማስረጃ አጠናቅሮ የወንጀሉን ክስ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቃቂ ቃሊቲ ፈጣን ምድብ ችሎት ያቀርባል፡፡ ፍርድ ቤቱም የቀረበውን ክስና ማስረጃ መርምሮ ከሳሽ የነበረውን ወጣት ደረጄ ለምን በሀሰት ሰውን በመወንጀል አንቀፅ 447 ንዑስ /ሀ/ መሰረት ጥፋተኛ ነው በማለት በአንድ ዓመት ፅኑ እስራት እና አንድ ሺ ብር እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡ተሀ