ጥር 26/2008 ዓ.ም

በአለማችን 36.9 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ እንደሚኖር ቢነገርም ተመርምረው ራሳቸውን ያወቁት ግን 54 ከመቶዎቹ ብቻ ናቸው፡፡ ዛሬም ድረስ በየአመቱ 2 ሚሊዬን የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ ይያዛሉ፡፡ በሃገራችን ኢትዮጲያ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ እንደሚኖር ያረጋገጡ ሰዎች ቁጥር 741,000 ሆኗል፡፡ በየአመቱ ደግሞ ከ24000 በላይ ሰዎች በቫይረሱ ይያዛሉ። ይሄ ቁጥር ሲታይ ከቀድሞዎቹ አመታት አንጻር የቀነሰ ቢመስልም ዝምታው ካልተሰበረና የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራው በፍጥነት ካልተሰራ ቁጥሩ ሊያሻቅብ እንደሚችል የተናገሩት ዶክተር አቻምየህ አለባቸው የፌዴራል ኤች አይ ቪ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት የእቅድ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር ናቸው፡፡ የቫይረሱ የስርጭት መጠን በሃገራችን ዛሬ ላይ ወደ 1.2 ከመቶ ቢቀንስም በአንዳንድ የክልል ከተሞች ስርጭቱ ዛሬም ድረስ አሳሳቢ መሆኑን ዶክተሩ ተናግረዋል፡፡ በቫይረሱ ስርጭት ጋንቤላ በ5.3 ከመቶ አዲስ አበባ በ4.53 ከመቶ እና ድሬዳዋ በ3.26 ከመቶ ቀዳሚውን ስፍራ ይዘዋል፡፡ በቤንሻንጉል የቫይረሱ ስርጭት ዝቅተኛ ነው ተብሎ በ0.7 ከመቶ ቢቀመጥም በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ስርጭቱ አሳሳቢ ነውም ብለዋል፡፡ ሃገራችን ኢትዮጲያ እስከ 2020 የፈረንጆቹ አመት የሚፈጸም ሶስቱ ዘጠናዎች የሚል እቅድ ማዘጋጀቷን ሰምተናል፡፡ እስከ 2020 ዘጠና ከመቶ የሚሆኑት ሰዎች ተመርምረው ራሳቸውን ያውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ 90 ከመቶ የሚሆኑና ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ሰዎች እስከ 2020 ድረስ የART ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ ሌላኛው እቅድ ደግሞ እስከ 2020 ድረስ አዲስ ለቫይረሱ ተጋላጭ የሚሆኑ ሰዎች በ90 ከመቶ ይቀንሳሉ ተብሏል፡፡ በ2030 በአጠቃላይ የኤች አይ ቪ ቫይረስ ስርጭቱን ዜሮ ለማድረስ እነዚህ የ 2020 ሶስቱ ዘጠናዎች ተግባራዊ መሆን እንዳለባቸው ተነግሯል፡፡ (እንየው ቢሆነኝ)

ጥር 25/2008 ዓ.ም

ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ከአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት ግንባታ ጋር ተያይዞ ከስፍራው ተነስቶ የነበረው የአርበኛው ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ጥር 29 ቀን 2008 ዓ.ም በታላቅ ክብር በአርበኝነት እና በሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓት ወደ ቦታው ይመለሳል፡፡

ጥር 25/2008 ዓ.ም

ከስዋዚላንድ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የልምድ ልውውጥ ተሞክሮ ለማድረግ ለመጡት የልዑካን ቡኑ አባላት የፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ከበደ ወርቁ በኢትዮጵያ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም አፈጻጸም ዙሪያ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ገልጸው በሽታዎችን በመከላከል፤ በመቆጣጠርና በመቀነስ ረገድ ለውጦች ተመዝግበዋል ብለዋል፡፡

በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም አፈጻጸሙ በየደረጀው የተለያዩ አደረጃጀቶች መኖራቸውን የገለጹት ዶ/ር ከበደ በተለይ የሴቶች የልማት ቡድንና የጤና ልማት ሠራዊት አደረጃጀት ለእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎት መሻሻል የጎላ ድርሻ ማበርከቱን ገልጸዋል፡፡

የስዋዚላንድ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሲለቦነሌ ዲሌሌ (Slbonglle Ndlela) እንደተናገሩት ከዚህ በፊት ለእንደዚህ አይነት ተግባር ወደ አሜሪካና ሌሎች የአውሮፓ አገራት ያቀኑ እንደነበር አስታውሰው አሁን ግን በአህጉራችን አፍሪካ ጥሩ አፈጻጸም መገኘቱ የሚያነቃቃ ነው ብለዋል፡፡

በዋናነትም ኢትዮጵያ ተላላፊ በሽታዎችን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ ያስመዘገበችውን ውጤት ያደነቁት ሚኒስትሯ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም አፈጻጸሙን ለማየት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ግምቢቹ ወረዳ ያከናወኑት ጉብኘት የተሳከ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

-    ምንጭ- የፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስቴር

ጥር 25/2008 ዓ.ም

 

ይሄን ያሉት የፌዴራል ኤች.አይ.ቪ መከላከያ ጽህፈት ቤት ምክትል ዳይሬክተር አቶ አለሙ አኑ ናቸው፡፡ ጽህፈት ቤቱ በ2030 ሃገራችን ኢትዮጲያ የኤች.አይ.ቪ ስርጭትን ለመግታት የሚዲያዎች ሚና ምን መሆን አለበት በሚል ለሚዲያ ባለሙያዎች በአዳማ ከተማ ባዘጋጀው ስልጠና ላይ ሚዲያዎች በቫይረሱ ስርጭት ላይ የሚሰሯቸው የመማሪያ ፕሮግራሞች መቀዛቀዛቸውን አሳውቀዋል፡፡ የሚዲያዎች ሚና ላይ ትኩረቱን ያደረገውን ስልጠና የፌዴራል ኤች አይ ቪ መከላከያ ቢሮ በአለም አቀፍ ደረጃ በቤተሰብ ጤና ላይ ከሚሰራው FHI360 ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር ያዘጋጀው መሆኑ ታውቋል፡፡ ግብረ ሰናይ ድርጅቱ ከ37 አመታት በላይ በቤተሰብ ጤና ላይ የሰራ ሲሆን መሰረቱ ከወደ አሜሪካ ነው ተብሏል፡፡ በሃገራችን ኢትዮጲያ ከ15 አመታት በፊት በተለያዩ ክልሎች ላይ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ሲሰራ መቆየቱን የ FHI360 የኢትዮጲያ ቅርንጫፍ አስተባባሪ ዶክተር ማሞ ገብረጻዲቅ ለዛሚ ተናግረዋል፡፡ (እንየው ቢሆነኝ)

ጥር 25/2008 ዓ.ም

ይሄን ያሉት የፌዴራል ኤች.አይ.ቪ መከላከያ ጽህፈት ቤት ምክትል ዳይሬክተር አቶ አለሙ አኑ ናቸው፡፡ ጽህፈት ቤቱ 2030 ሃገራችን ኢትዮጲያ የኤች.አይ.ቪ ስርጭትን ለመግታት የሚዲያዎች ሚና ምን መሆን አለበት በሚል ለሚዲያ ባለሙያዎች በአዳማ ከተማ ባዘጋጀው ስልጠና ላይ ሚዲያዎች በቫይረሱ ስርጭት ላይ የሚሰሯቸው የመማሪያ ፕሮግራሞች መቀዛቀዛቸውን አሳውቀዋል፡፡ የሚዲያዎች ሚና ላይ ትኩረቱን ያደረገውን ስልጠና የፌዴራል ኤች አይ መከላከያ ቢሮ በአለም አቀፍ ደረጃ በቤተሰብ ጤና ላይ ከሚሰራው FHI360 ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር ያዘጋጀው መሆኑ ታውቋል፡፡ ግብረ ሰናይ ድርጅቱ 37 አመታት በላይ በቤተሰብ ጤና ላይ የሰራ ሲሆን መሰረቱ ከወደ አሜሪካ ነው ተብሏል፡፡ በሃገራችን ኢትዮጲያ 15 አመታት በፊት በተለያዩ ክልሎች ላይ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ሲሰራ መቆየቱን FHI360 የኢትዮጲያ ቅርንጫፍ አስተባባሪ ዶክተር ማሞ ገብረጻዲቅ ለዛሚ ተናግረዋል፡፡ (እንየው ቢሆነኝ)

ጥር 24/2008 ዓ.ም

እንስሳቶቹ የተገኙት በኢትዮጲያና ሱዳን ድንበር አቅራቢያ በአማራ ክልል በሚገኘው የአልጣሽ ብሄራዊ ፓርክ ነው፡፡ እንስሳቶቹ ከዚህ በፊት በዚህ ቦታ ይኖሩ እንደነበር ምንም የታወቀ መረጃ የለም፡፡ አናብስቶቹም ምናልባት አመቱን ሙሉ በፓርኩ የሚቆዩ ወይንም ቦታውን ለቀው የሚሄዱ ስለመሆናቸው ባለሙያዎች ጥናት እያደረጉ ነው፡፡ የአልጣሽ ብሄራዊ ፓርክ 10,000 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን ከዚህ በፊት ቁጥራቸው ከ27-54 የሚሆኑ አናብስት መኖሪያ ሆኖ ቆይቷል፡፡ አሁን ላይ በአፍሪካ የሚገኙት አናብስት ከ20,000 እንደማይበልጡ ይነገራል፡፡ (እንየው ቢሆነኝ)

ጥር 23/2008 ዓ.ም

እንደ ፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር በ1990 የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት የነበሩትን ሄስኒ ሃብሬን ከስልጣን አስወግደው መንበረ መንግስቱን የተቆጣጠሩት ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ የህብረቱ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡

የሊቢያ፣ የሩዋንዳ፣ የቤኒን፣ የቻድ እና የዙምባቡዌ መሪዎች በእጩነት ቀርበው ነበር፡፡ የ2015 የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሆነው ያገለገሉት የዙምባቡዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ስልጣናቸውን ለኢድሪስ ዴቢ አስረክበዋል፡፡ በህብረቱ ጉባኤ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ሮበርት ሙጋቤ የአለም መንግስታት ድርጅት ለአፍሪካ መሪዎች ተገቢውን ክብር ሊሰጥ እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡ አፍሪካውያን በህብረቱ ቋሚ የጸጥታው ምክር ቤት አባልነት ይገባቸዋል ብለዋል፡፡ 54 የአፍሪካ ሀገራት ቋሚ መቀመጫ በሌላቸው ሁለት ሃገራት ብቻ ሊወከሉ አይገባም ነው ያሉት ሮበርት ሙጋቤ፡፡ ሙጋቤ አክለውም ከ3.5 ቢሊዮን ህዝብ በላይ ላላቸው አፍሪካና የእስያ ሀገራት ተገቢ ክብር ሊሰጥ ይገባልም ብለዋል፡፡ አዲሱ የህብረቱ ሊቀመንበር ኢድሪስ ዴቢ የ2063 አጀንዳን ለማሳካት፤ አፍሪካን በአንድ መሰረተ ልማት ለማስተሳሰር፤ ሰብአዊ መብቶችን ለማስክበርና የአፍሪካ ሰላምና መረጋጋት እውን እንዲሆን እሰራለሁ ብለዋል፡፡ (እንየው ቢሆነኝ)