መስከረም 28/2007 ዓ.ም

ቅዳሜ ብሄራዊ ቡድኑ በአዲስ አበባ ስቴድየም ከማሊ ጋር ለሚያደርገው የማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅቱን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

በውጭ ሀገራት የሚጫወቱት ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ዋሊድ አታ፣ የሱፍ ሳላህና አሚር አስካር ቡድኑን በተቀላቀሉበት ቀን ከኢትዮጵያ ባንክ በነበረው የአቋም መለኪያ ጨዋታ ገብተው ተጫውተዋል፡፡

አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶም አዳዲስ በቡድኑ የተቀላቀሉ  ተጨዋቾችንም ተመልክተዋል፡፡ በዛሬው እለት ደግሞ 4 ተጨዋቾችን ሲቀንሱ በብሄራዊ ቡድኑ ቀድሞ ትልቅ ድርሻ የነበረውን አዳነ ግርማን ጨምሮ አሉላ ግርማ ከአርባ ምንጭ ከነማ የተጠራው አንተነህ ተስፋዬ እና ዘግይቶ ቡድኑን የተቀላቀለው ግብ ጠባቂውን ዩሃንስ ሽኩርን ቀንሰውታል፡፡

ብሄራዊ ቡድኑ በምድብ 2 ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች ተሸንፎ ምንም ነጥብ የለውም፡፡ ቅዳሜ በ10 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚያደርገው 3ኛ የማጣሪያ ጨዋታ የመጀመሪያውን ነጥብ ለማግኘት ወደ ሜዳ እንደሚገቡ አሰልጣኙ ከአቋም መለኪያ ጨዋታው በኋላ ተናግረዋል፡፡ (አርያት ራያ) 

መስከረም 27/2007 ዓ.ም

ለግጭቱ መንስኤ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ከ12 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው የማጣራት ስራው እየተሰራ ነው፡፡

ከአካባቢው የተሰወሩ ተጠርጣሪዎችን ግን የመከታተል ስራው መቀጠሉን የፌዴራል ጉዳዮች የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አበባ ወርቁ ለዛሚ 90.7 ኤፍ ኤም ገልፀዋል፡፡ በወቅቱ ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በቦታቸው መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡ የሃይማኖት አባቶች ከፌዴራልና ከመከላከያ ሰራዊትና ከክልሉ መንግሥት ጋር በጋራ ነዋሪዎችን የማወያየት ስራ እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀው፤ በሰላማዊ መንገድ መህበራዊ ጉዳዮችም እየተከናወኑ መሆኑን ተጠቁሟል፡፡ (ታሪክ አዱኛ)

Tuesday, 07 October 2014 09:14

የላይቤሪያ የህትመት ሚዲያ ህብረት የሀገሪቱ መንግሥት በኦቦላ በሽታ ላይ የሚሰሩ ዘገባዎችን እያገደ እንደሆነ አስታወቀ፡፡

መስከረም 27/2007 ዓ.ም

በሱዳን በኢቦላ ዙሪያ የሚሰሩ ዘገባዎች ይታገዱ መባሉን የሚያመላከተው ዘገባ መውጣቱን ተከትሎ፤ የላይቤሪያ የህትመት ሚዲያ ህብረትም ተመሳሳይ ችግር መኖሩን አመላክቷል፡፡ የህብረቱ አባላት መንግሥት በሽታውን ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት ከማጠናከር ይልቅ ዘገባዎችን ማገዱ አግባብ አይደለም ሲሉ ወቀሳቸውን እየሰነዘሩ ነው፡፡

የሀገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በበኩሉ በዚህ ዙሪያ የሚተላለፉ ጉዳዮች መስመር እየሳቱ ነው የሚል አስተያየት አለው፡፡ ለማገገሚያነት በተሰሩ የጤና ማዕከላት ውስጥ የሚነሱ ፎቶግራፎች፣ የሚሰሩ ቃለ-መጠይቆችና ተያያዥ ጉዳዮች የህሙማንን መብት መጋፋት እንደሆነም እየተነገረ ነው፡፡ የሚዲያዎችን ነፃነት የሚጋፉ ተግባራት ተመልስው መምጣታቸው የሀገሪቱን ዴሞክሲያዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው መባሉን VOA ዘግቧል፡፡

Tuesday, 07 October 2014 09:14

የእስራኤል ታጣቂ ቡድን የሆነ እና በአንፃሩ አይ ኤስ ተብሎ የሚጠራው ቡድን የሽብር ጥቃቱን ለማስፋት እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተነገረ፡፡

መስከረም 27/2007 ዓ.ም

የአሸባሪ ቡድኑ አባላት የሆኑ ኮማንዶዎቹን በስደተኞች ስም ወደ ምዕራብ አውሮፓ በመላክ የሽብር ጥቃት ለማድረስ እያሴረ መሆኑን ጀርመን የተናገረች ነው፡፡ አራት አባላት ያሉት የሽብር ቡድን በሶሪያና ቱርክ ድንበር ሰርጎ በመግባት እና በተጭበረበረ የጉዞ ሰነድ ወደተለያዩ የምዕራብ አውሮፓ ሀገራት ለመግባት ማቀዱ ነው የታወቀው፡፡ የሽብር ቡድኑም ጀርመን ለኩርድ ወታደሮች ድጋፍ ማድረጓን ተከትሎ የሽብር ጥቃት ለመሰንዘር አስቧል፡፡ ምንም እንኳን ጀርመን እንዲህ ብትልም የአሜሪካ የደህንነት አባላት እንዳስታወቁት ከሆነ በአየር ማረፊያዎች እጅግ ጥብቅ ቁጥጥር በመኖሩ አሸባሪዎች አውሮፕላኖችን እንደማይጠቀሙ ተናግረዋል፡፡

የተረጋገጠ የሽብር ጥቃት ፍንጭ ባይኖርም ጀርመን የአሸባሪዎች ቀጣይ የጥቃት ኢላማ ናት ሲሉ የጀርመን የሀገር አስተዳደር ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ተናግረዋል፡፡ ዘገባው የሮይተርስ ነው፡፡

መስከረም 26/2007 ዓ.ም

ፕሬዝዳንቱ በዛሬው ዕለት የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አምስተኛ የስራ ዘመን የመጀመሪያ የጋራ ስብሰባ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡

በአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ ማደስ ፕሮግራም ባለፈው በጀት ዓመት ሶስት ሺህ ታቅዶ ስድስት መቶ አርባ ሶስት መንደሮችና ከተሞች የኤሌክትሪክ ሀይል እንዲያገኙ መደረጉን ገልፀው፤ ከሀይል አቅርቦት አንፃር ግዙፍና ከኤሌክትሪክ ሀይል በላይም ፋይዳ ያለው፤ መንግስትና መላው የሀገሪቱ ህዝቦች እየተረባረቡበት የሚገኘው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በተያዘለት መርሀ ግብር እየተከናወነ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም 40 ከመቶ ገደማ ደርሷል ብለዋል፡፡

የግልገል ግቤን፤ የገናሌ ዳዋና ሌሎችም የንፋስና የጂኦተርማል እንዲሁም የውሀ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች በተያዙላቸው መርሀ ግብር መሰረት በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

እነዚህ ሰፋፊ ፕሮጀክቶችን የጠቀሱት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ በታላላቅ ከተሞች ከተፈጠረው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኀይል ፍላጎት አንፃር ካለው የማስተላለፊያ እና ማሰራጫ መስመሮች እንዲሁም በተቋሙ ከቆየው የመልካም አስተዳደር ችግር ተዳምሮ ህዝባችንና ልማታዊ ባለሀብቱ በቂና የማይቆራረጥ ኃይል እያገኙ እንዳልሆነ መንግስት እንደሚገነዘብ ገልፀዋል፡፡

በመሆኑም የአጭር፣ የመካከለኛ እና የረዥም ጊዜ እቅድ ይዘን እየተረባረብን ነው፡፡ በዚሁ አጋጣሚ ለተፈጠረው መስተጓጎል በታላቅ አክብሮት ይቅርታ እንጠይቃለን ብለዋል፡፡

(ሱራፌል ዘላለም)

መስከረም 26/2007 ዓ.ም

ለአንጋፋው የሙዚቃ ሰው ክቡር አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ 74ኛ ዓመት መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ቀርበዋል፡፡ በርካታ ወጣቶች ህብረ ዝማሬ ያቀረቡ ሲሆን የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓትና የተለያዩ የኪነ-ጥበብ ስራዎችም ለታዳሚው ቀርበዋል፡፡ አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ በህይወት ቢኖር ኖሮ ትናንት ልክ 74ኛ ዓመቱን ያከብር እንደነበርና በኖረባቸው ዘመናት ታላቅ ሰው መሆኑን የሙያ አጋሮቹና ጓደኞቹ ተናግረዋል፡፡

በዝግጅቱ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ አንጋፋ የጥበብ ሰዎችና ተጋባዥ እንግዶችም ተገኝተዋል፡፡ (እንደገና ደሳለኝ)