ጥቅምት 25/2007 ዓ.ም

በኢፌዴሪ ህገ-መንግሥት አንቀፅ 82/1/ የተቋቋመው የህገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ፅ/ቤት ማንኛውም ህግ ልማዳዊ አሰራር ወይም የመንግሥት ውሳኔ እንዲሁም የባለስልጣን ውሳኔ ከህገ-መንግሥቱ ጋር ይቃረናል የሚል ጥያቄ በፅሁፍ ሲቀርብለት አጣርቶ ውሳኔ የሚሰጠው ጉባዔው ህገ-መንግሥቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ከ1,200 በላይ መዝገቦችን መርምሮ ምላሽ መስጠቱን ለዛሚ 90.7 ኤፍ ኤም የገለፁት የኢፌዴሪ የህገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ደሳለኝ ወይሳ ናቸው በተለይ በ2006 ዓ.ም ከ150 በላይ መዝገቦችን መርምረው ውሳኔ መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡ በፌዴራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ክስ የተመሰረተባቸው ከፍተኛ የመንግሥት ሃላፊዎች የእነ አቶ መላኩ ፈንታ ጉዳይን በተመለከተም በፌዴራል ከ/ፍ/ቤት መዳኘት እንዳለባቸው ጉባዔው መርምሮ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ማቅረባቸውን አስታውሰዋል፡፡ በያዝነው በ2007 ዓ.ም ከህገ-መንግሥት ጋር ይፃረራሉ ወይም ይቃረናሉ ተብለው የሚቀርቡ መዝገቦችን በፈጣን ሁኔታ ምላሽ እንደሚሰጡም ገልፀዋል፡፡ (ታሪክ አዱኛ)

Tuesday, 04 November 2014 10:54

ቻይና እና ኳታር ወዳጅነታቸውን በተለያዩ ዘርፎች ለማጠናከር ተስማሙ፡፡

ጥቅምት 25/2007 ዓ.ም

የኳታር ንጉስ በቻይና ባደረጉት ጉብኝት ነው ሀገራቱ ከስምምነት የደረሱት፡፡ የኳታር ንጉስ በትላንትናው ዕለት ነበር ወደ ቻይና ያቀኑት፡፡ ሁለቱ የሀገር መሪዎች በአጠቃላይ ግንኙነታቸው ዙሪያ ሰፊ ሰዓት ወስደው እንደተነጋገሩ ዘገባዎች አመላክተዋል፡፡ የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ቺን ፒንግ ከኳታር ጋር ያላቸው ግንኘነት ማደጉ ለሁለቱም ሀገራት ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እድገት እና ትስስር ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ተናግረዋል፡፡ ዘገባው የኤዥያን ታይምስ ነው፡፡

Tuesday, 04 November 2014 10:49

በኢቦላ ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድተዋል ከተባሉ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የሚመጡ ዜጎች ላይ ከበድ ያለ የቪዛ ህግ ማስቀመጧን ሲንጋፖር አስታውቃለች፡፡

ጥቅምት 25/2007 ዓ.ም

ወደ ሲንጋፖር የሚገቡት ላይ የሚደረገው ይኸው ቁጥጥር ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ የሚደረገው ከረቡዕ ጀምሮ መሆኑም ታውቋል፡፡ የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት በጊኒ፣ ላይቤሪያና ሴራሊዮን ዜጎች ላይ የሚደረገው ይኸው ቁጥጥር በተሻለ መልኩ ደህንነቱን ለማስጠበቅ ያለመ ነው፡፡ የሲንጋፖር መገናኛ ብዙሃን 2 በኢቦላ የተጠረጠሩ ሰዎች መኖራቸውን ይፋ አድርገው የነበረ ቢሆንም ሁለቱም በተደረገላቸው ምርመራ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ ዜናው የቢቢሲ ነው፡፡

ጥቅምት 25/2007 ዓ.ም

ተከሳሽ ዩሃንስ ንጉሴ በነሃሴ ወር 2005 ዓ.ም በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው ሳሚት ኮንደሚኒየም ውስጥ የ11 ዓመት እድሜ ያላትን የገዛ ልጁን የእናቷን መውጣት ተከትሎ አስገድዶ ደፍሯታል በሚል ነው በአቃቤ ህግ ክስ የተመስረተበት፡፡ በዚህም መሰረት ሐምሌ 26/2006 ዓ.ም የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 7ኛ ወንጀል ችሎት በወንጀለኛ ህግ አንቀፅ 82/1/ሀ/ መሰረት በ16 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

አቃቤ ህግ ተበዳይዋን፣ እህቷን እና እናቷን በሰው ምስክርነት፤ የጋንዲ ሆስፒታል የህክምና ማስረጃን በሰነድ ማስረጃነት ያቀረበ ቢሆንም ተከሳሹ ለፍርድ ቤቱ ክሱ ባለቤቴ በቅናት ተነሳስታ ያቀረበችው ነው ሲል ይግባኝ አቅርቧል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በእህትማማቾቹ ምስክርነት አሰጣጥ ላይ የቦታና የሁኔታ ልዩነት አለ ስለሆነም ፍ/ቤቱ ይህንና ይህን መሰል ክፍተቶችን ከግምት ሳያስገባ ነው የወሰነብኝ ብሏል፡፡ ፍርድ ቤቱም ይግባኙን ለመስማት ለህዳር 12/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ (ቴድሮስ ብርሀኑ)

gebre

ጥቅምት 24/2007 ዓ.ም

በውድድሩ ተሳታፊ የነበሩት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ለአሸናፊነቱ ቅድመ ግምት ቢሰጣቸውም የ2013ቱ የበርሊን ማራቶን አሸናፊውና 2014 የለንደን ማራቶንን በበላይነት ያጠናቀቀው ኬንያዊው ዊልሰን ኪፕሰንግ በ2፡10፡55 በአንደኛነት ውድድሩን አጠናቋል፡፡

የ2013 የቦስተን ማራቶን አሸናፊው ሌሊሳ ዲሳሳ በ 11፡06 ሁለተኛ ሲሆን የ2010 የኒዮርክ ማራቶን አሸናፊው ገ/እግዚያብሄር ገ/ማርያም በ2፡12፡13 ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ፈፅሟል፡፡

በሴቶቹ በተደረገው ውድድር ኬኒያዊቷ ሜሪ ኪታኒ በ2፡25፡07 የሀገሯን ልጅ ጀሚማ ሰማጎንግ አስከትላ ስታጠናቅቅ ኢትዮጵያዊያኖቹ ፍሬሂወት ዳዶ 7ኛ ብዙነሽ ዳባ 9ኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን አጠናቀዋል፡፡ (አርያት ራያ)

ጥቅምት 24/2007 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክትር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከግብፁ አቻቸው ጋር ትናንት በፅ/ቤታቸው ባደረጉት ውይይት የኢትዮጵያና የግብፅ የንግድና ኢንቨስትመንት ልውውጥ የሚጠበቀውን ያህል አለማደጉን መገምገማቸውንና በምን መልኩ መሻሻል አለበት የሚለውን መነጋገራቸውን ለጋዜጠኞች ገልፀዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በሁለቱ ሀገር ያለው የንግድ መጠን ከ150 ሚሊዮን ዶላር የማይበልጥ ሲሆን በጋራ መስራት ከተቻለ ግብፅ ከህንድ አውስትራሊያና ደቡብ አሜሪካ የሚያመጧቸውን እቃዎች ከኢትዮጵያ መውሰድ እንደሚችሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም አብራርተዋል፡፡ ሁለቱ ሚኒስትሮች የህዳሴውን ግድብ ጨምሮ በሌሎች የጋራ ጉዳዮቻቸው ላይ የማጠናከሪያ ውይይት ያደረጉ መሆኑንና በምስራቅ አፍሪካ ያሉ ግጭቶችን ከመፍታትና ኢቦላን ከመከላከል አንፃርም በጋራ ለመስራት መነጋገራቸውንም ገልፀዋል፡፡ ውይይቱ ሌሎች ሚኒስትሮችን አካቶ ዛሬ በሰፊው ቀጥሎ እንደሚውል ተገልጧል፡፡ (እንደገና ደሳለኝ)