Monday, 14 August 2017 08:29

የቲቤት መንፈሳዊ መሪ ዳላይ ላማ ወደ አፍሪካዊቷ አገር ቦትስዋና ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞ ሰረዙ፡፡

የቲቤት መንፈሳዊ መሪ ዳላይ ላማ ወደ አፍሪካዊቷ አገር ቦትስዋና ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞ ሰረዙ፡፡
መንፈሳዊው መሪ ዳላይ ላማ ለጉዞዋቸው መሰረዝ እንደምክንያት የቀረበው ዶክተሮቻቸው ረጅም ጉዞ እንዳያደርጉና እረፍት እንደሚያስፈልጋቸው ስለነገሩዋቸው ነው ተብሏል፡፡ እርሳቸውም ከዶክተሮቻቸው ምክር በኃላ "የሰማንያ ሁለት አመት የእድሜ ባለፀጋ ስለሆንኩ ሰውነቴ እረፍት ያስፈልገዋል" በሚል ጉዞዋቸውን እንደሰረዙት እወቁት ብለዋል፡፡
ዳላይ ላማ በቦትስዋና ዋና መዲና ጋቦሮኒ በሚካኤደው የሰብአዊ መብት ኮንፍረንስ ላይ ለመሳተፍና እግረ መንገዳቸውንም የቦትስዋናውን ፕሬዝደንት አያን ካሃማን ለማግኘት አልመው ነበር፡፡
የቦትስዋናው ፕሬዝደንት አገራቸው በቲቤታውያን መንፈሳዊው መሪ እንደምትጎበኝ አሳውቀው በነበረበት ወቅት ቻይና ይህንን መሰል የአገሯን መሠረታዊ ጥቅም የሚጎዳ ነገር በፍፁም እንደማትቀበለው ማስጠንቀቋ ይታወሳል፡፡
ቻይና ቦትስዋናን ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት ጋር ያላት ግንኙነት ጠንካራ ነው፡፡ በዚህም መንፈሳዊው መሪ እ.ኤ.አ ከ2009 ጀምሮ ለሶስት ጊዜያት ያህል የቦትስዋና ጎረቤት አገር ወደ ሆነችው ደቡብ አፍሪካ እንዳይገቡ የመግቢያ ፈቃድ ተከልክለዋል፡፡
የቻይና መንግስት ቲቤትን ከአስተዳደሬ ነጥለው ራስ ገዝ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ነው የሚላቸው የቲቤት መንፈሳዊው መሪ ዳላይ ላማ በስድስት አህጉራት የሚገኙ ስልሳ ሰባት አገራትን ጎብኝተዋል፤ የኖቤል የሠላም ሽልማትን ጨምሮ አንድ መቶ ሃምሳ ሽልማቶችን ተቀብለዋል ሲል ሚካኤል ጌታሠጠኝ አፍሪካ ኒውስን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ሁለተኛ ምድብ ችሎት በትላንት ውሎው በሙስና ወንጀል በተጠረጠሩ የ 54 ሰዎች ላይ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቀደ ፡፡
ፍርድ ቤቱ በቅርቡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉት የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ባለሃብቶችና ደላሎች መካከል በትላንትናው ዕለት የሃያ ሁለቱን ጉዳይ ሲመለከት ማምሸቱ ይታወሳል ፡፡
ፍርድ ቤቱ በትላንት ውሎው ከእሮብ ችሎት ለትላንት በይደር የተላለፉ የ 32 ተጠርሪዎችን እና በዛሬው እለት ከገንዘብና ኢኮኖሚክ ትብብር ሚኒስቴር ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን የአቶ ሲጀን አባ ጎጃም ጉዳይ መርምሯል፡፡
ፖሊስ ፍርድ ቤቱ በርካታ የሰነድ ማስረጃዎች መመርመር ይቀረኛል ፤ የሰው ምስክሮች አልሰማውም ፤ አብዛኞቹ ተጠርጣሪዎች ከፍተኛ ባለ ስልጣናት በመሆናቸው መረጃ ይሸሽጉብኛል፣ ምስክሮቼንም ያባብላሉ በሚል የዋስትና መብታቸው እንዳይከበርና ተጨማሪ የአስራ አራት ቀን የምርመራ ጊዜ ጠይቋ፡፡
የተጠርጣሪዎች ጠበቃ በበኩላቸው አብዛኞቹ ተጠርጣሪዎች ከተጠረጠሩበት መስሪያ ቤት ከለቀቁ የቆዩ በመሆናቸው ሰነዶችን መደበቅ አይችሉም ቀደም ሲል ለፖሊስ የተሰጠው የምርመራ ጊዜ በቂ በመሆኑ ፖሊስ ተጨማሪ የተጠየቀው 14 የምርመራ ቀን አላስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
ግራ ቀኙን የመረመረው የልደታ ምድብ ችሎት ፖሊስ ጉዳዩን እንዲያጣራ ተጨማሪ 14 ቀን ፈቅዷል፡፡
በዚህም መሰረት በነ አቶ ፀጋዬ ፣በነአቶ ዘነበ ፣በነ አቶ አበበ ፣በአ አቶ ኤፍሬም፣ ስር ያሉ የክስ መዝገቦች ለነሀሴ 17 ሲቀጠሩ
በነ አቶ አብዶ መሀመድ ፣ በነ አቶ ሙሳ ፣ በነ ኢንጂነር ፍቃደ እና ወይዘሮ ሳባ የክስ መዝገቦች ነሀሴ 15 2009 እንዲታዩ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ፍርድ ቤቱ አክሎም በአዲስ አበባ መንገዶች ባለ ስልጣን እና በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮቸክት ላይ ፖሊስ ገና ያልመረመራቸውና ያላደራጃቸው 99 ሰነዶች መኖራቸውን ገልፆ ፖሊስ በአፋጣኝ ምርመራውን እንዲያካሄድ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡፡
ለተጠርጣሪዎች የጤናና የአስተዳደር መብቶች እንዲከበሩ በሳምንት ሁለት ቀን ከጠበቃቸውና ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ ፈቅደዋል፡፡

Friday, 11 August 2017 09:47

የቬንዙዌላን ቀውስ ለማረጋጋት እና የምርጫ ውጤቱን ግልጽ ለማድረግ አጣሪ የእውነት ኮሚቴ ተመሰረተ፡፡

የቬንዙዌላን ቀውስ ለማረጋጋት እና የምርጫ ውጤቱን ግልጽ ለማድረግ አጣሪ የእውነት ኮሚቴ ተመሰረተ፡፡
የአዲሱ የእውነት ኮሚቴ መሪ የሆኑት ዴልሲ ሮድሪጊየዝ እንደገለጹት አዲሱ ኮሚቴ በአሁን ሰአት ያለውን የፖለቲካ ብጥብጥ፣አለመረጋጋት እና ጥላቻን ለማስቆም የሚረዳ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ካሳለፍነው ሚያዚያ ወር ጀምሮ በሀገሪቷ በተፈጠረው የፖለቲካ አለመረጋጋት ከመቶ ሀያ የሚበልጡ ሰዎች ሞተዋል፡፡
ህገ መንግስቱ አሸባሪ ተቋሞችን የተቃወመ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት ግን አሸባሪዎቹ በጦር ሰራዊቱ እንዲገደሉ ሀሳብ ሰጥቷል፡፡
የኮሚቴው ምስረታ የጸደቀው በስብሰባው በተካፈሉት የመንግስት ባለስልጣናት ድምጽ ሲሆን ስብሰባውን በአፈ ጉባሄነት ይመሩ የነበሩትም ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ናቸው፡፡
ፕሬዝዳንት ማዱሮ እንደገለጹት አዲስ የተቋቋመው የእውነት ኮሚቴ በህገ መንግስቱ እና በህብረተሰቡ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት እንዲቀንሰ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ነገር ግን አምስት መቶ አርባ አምስት የሚሆኑት የካቢኔ አባላቶች አሁን ያለው የፖለቲካ ብጥብጥ ይህን የእውነት ኮሚቴ ለማቋቋም ያስቸግራል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የአዲሱ የእውነት ኮሚቴ መሪ ሆነው የተሾሙት ዴልሲ ሮድሪጊየስ እንደገለጹት ይህ ኮሚቴ እየተካሄደ ያለውን የፖለቲካ ረብሻ በደንብ ማጣራት አለበት ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ዘገባው የቢቢሲ ነው

Friday, 11 August 2017 09:31

ካናዳ ስደተኞች ወደ ሀገራ እስኪገቡ ድረስ እንዳይንገላቱ በሚል ጊዜያዊ የመጠለያ ካምፕ ሰራች፡፡

ካናዳ ስደተኞች ወደ ሀገራ እስኪገቡ ድረስ እንዳይንገላቱ በሚል ጊዜያዊ የመጠለያ ካምፕ ሰራች፡፡
የካናዳ ወታደራዊ ሀይል ከአሜሪካ ለሚመጡ የጥገኝነት ስፍራ ፈላጊዎች የሚሆን ካምፕ ለአሜሪካ ወሰን ቅርብ በሆነ ሴንት በርናርድ ዲላኮሊ በተባለ ከተማ አቋቋመ፡፡
የጦር ሰራዊቱ እንደገለፀው ከ አምስት መቶ ለሚበልጡ የጥገኝነት ስፍራ ፈላጊዎች የሚሆነው ይህ ካምፕ ስደተኞቹን የሚያገለግል በቂ መብራት እና የማሞቂያ መሳሪያዎች አሉት፡፡
በ2017 መጀመሪያ አካባቢም ከ አራት ሺህ ሦስት መቶ የሚበልጡ ስደተኞች የአሜሪካን ጠረፍ አቋርጠው ወደ ካናዳ ሄደው ነበር፡፡
ስደተኞቹ በቅድሚያ ያረፉት በሞንትሪል ኦሎምፒክ እስታዲየም ሲሆን በአሁን ሰአትም ለስደተኞቹ ለወደፊት የሚያገለግል ሆስፒታል በድጋሚ ተከፍቷል፡፡
ስደተኞቹ በአሜሪካ ለብዙ አመታት የኖሩ ቢሆንም እ.ኤ.አ በ2010 በደረሰው አስደንጋጭ የመሬት መንቀጥቀጥ የተሰደዱ ስልሳ ሺህ ስደተኞችን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማባረሩ ወደ ካናዳ እንዲሰደዱ አድርጓቸዋል፡፡
የካናዳ መንግስት ይህ ስደተኞችን የመቀበል ስራ እንደሚቀጥል አሳውቋል፡፡
ምንጫችን ቢቢሲ ነው

Friday, 11 August 2017 09:23

30 ንጹሀን ዜጎች በማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በተፈጸመ ጥቃት ህይወታቸው አለፈ፡፡

30 ንጹሀን ዜጎች በማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በተፈጸመ ጥቃት ህይወታቸው አለፈ፡፡
ግጭቱ የተፈጠረው በማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በሚገኙት የታጠቁ ቡድኖች እና በራስ መከላከል ቡድን መካከል ሲሆን ህይወታቸው ካለፉ ንጹሃን መከከል በጋመቦ ከተማ የሚገኘው በቀጣይ ረቡእ እለት ለሚካሄደው የጤና ድርጅት ስብሰባ ለመታደም የመጡ 6የቀይ መስቀል በጎአደራጊዎች ይገኙበታል፡፡
በደም መፋሰስ ምስቅልቅሉ የወጣው ከባንጋሱ 75 ኪሎ ሜትር የምትርቀው የጋምቦ ከተማ ሁከቱ የተጀመረው ባሳለፍነው ሳምንት ነው፡፡ የምስራቅ አፍሪካ የ ቀይ መስቀል ፕሬዝዳንት የሆኑት አንቶኒ የአጋሮቻችንን ሞት መስማታችን ለኛ አስደንጋጭ ዜና ነው ሲሉ አያይዘውም ሁሉንም ፓርቲዮች ንጹሃን ዜጎችን እንዲተዉ እና የበጎ አድራጎት ሰራተኞችን እንዲያከብሩ ነግረናቸው ነበር ብለው ተናግረዋል፡፡
በ ማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ አስራ ሁለት ሺህ የሰላም አስከባሪዎች ቢኖሩም በጋመቦ በተፈጠረው ግጭት ላይ አንዳቸውም ግጭቱን ለማብረድ አልተገኙም፡፡
የሃገሪቱ ቃለ አቀባይ እንዳሉት የሰላም አስከባሪዎቹ ሳይመጡ ስለቀሩ የራሳቸንን ወታደሮች አደራጅትን ልከናል ብለዋል፡፡
የአለም አቀፍ ጥበቃ ደርጅት በህጉ ላይ እንዳስቀመጠው ማንኛውም የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በማንኛውም ቦታ ሲንቀሳቀሱ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ይላል ነገር ግን በዚህ አመት በቻ በቀይ መስቀል ላይ እነደዚህ አይነት አደጋ ሲደርስ 3ኛ ጊዜ ነው፡፡ የተባበሩት መንግሰታት የእርዳታ ድርጅት ዋና መሪ ይሄ ግጭት የ ጅምላ ጭፍጨፋ ምልክት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡