አገር አቀፍ ዜናዎች

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የልማት ድርጅቶቹን የ2009 ዓ.ም የ11 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት የስኳር ፕሮጀክቶቹ በመርሃ ግብሩ መሰረት ካልተጠናቀቁ የሚመለከታቸው አካላት ከተጠያቂነት አይድኑም ማለቱን ተከትሎ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር አንድ በከፊል የስኳር ምርት ማምረት መጀመሩ ተነግሯል፡፡ ፋብሪካው ምርቱን መጀመሩ ለምክር ቤቱ ማሳሰቢያ ምሳሽ ለመስጠት የታሰበ ነው ወይ ለሚለው ጥያቄ የስኳር ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ጋሻው አይችሉም እውነት ነው ሲሉ ምላሽ ሰተዋል፡፤
የአዋጭነት ጥናት አንስቶ ዝርዝር ዲዛይንን ጨምሮ የግንባታ ምርትና አቅርቦት፣ የሲቪል ስራዎች እንዲሁም የኢሬክሽን አና የዝርጋታ ስራዎች በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች ተሰርተዋል የሚሉት የብረታብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ጠና ቁሩንዲ ናቸው እንደ ጀነራሉ ገለፃ ከሆነ የሙከራ ስራውን የጀመረው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር አንድ ስኳር ፋብሪካ በቀን 12 ሺ ቶን አገዳ መፍጨት እንደሚችል ተናግረዋል፡፡
ከኦሞ ኩራዝ ቁጥር አንድ ባሻገር የጣና በለስ ቁጥር አንድና ሁለት ስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ ለሜቴክ የተሰጡ መሆናቸውም የሚታወስ ነው፡፡የጣና በለስ ቁጥር ሁለት ፕሮጀክት አፈጻጻም 25 በመቶ ብቻ በመሆኑ ከብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋር የተደረገው ውል እንዲቋረጥ እርምጃ መውሰድ ጀምረናል ሲሉ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መናገራቸው ይታወሳል፡፡ኮርፖሬሽኑ በአሁኑ ወቅት የጣና በለስ ቁጥር አንድ ፕሮጀክት ግንባታን አጠናቆ ወደ ሙከራ ስራ መግባት የነበረበት ቢሆንም እስካሁን ያለውን አፈፃፀም በመቶኛ የሚያስቀምጥበት ጊዜ ላይ አለመድረሱን በተናገሩበት በዚህ ወቅት ነው የኩራዝ ፋብሪካ ወደ ምርት የገባው
የፋብሪካው ግንባታ በሚያዝያ ወር ተጠናቆ የክረምት ወቅት ከመግባቱ በፊት የስኳር ምርት ስራ መጀመር እንደነበረበት ነው ሚኒስቴሩ ባሳለፍነው ሳምንት ያመለከቱት።
ይህ በእንዲህ እያለ የስኳር ኮርፖሮሽን የኮርፖሬት ስራ አስፈፃሚው አቶ ጋሻው አይችሉም የኩራዝ ስኳር ፋብሪካ ስራ መጀመር ስኬት ነው ሲሉ ተናገረዋል፡፡
ከ3 ዓመታት በፊት ስራ ይጀምራል የተባለው ፕሮጀክቱ ዛረም ድረስ ወደ መደበኛ የማምረት ስራ መግባት አልቻለም፡፡ ፋብሪካው በ 3 ወራት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ምርት ማምርት እንደሚጀምር ብርጋዴር ጄኔራል ጠና ቁሩንዲ ተናግረዋል፡፡
የኦሞ ኩራዝ ቁጥር አንድ ስኳር ፋብሪካ በ235 ሚሊዩን ዶላር እንደተገነባ ከሜቴክ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡ የጣና በለስ ቁጥር አንድና ሁለት፣ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር አንድ ሙሉ በሙሉ ፕሮጀክቶችን በተከለሰው መርሃ ግብር መሰረት በ2010 ዓ.ም ለማጠናቀቅ መታቀዱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መነገሩ ሲታወስ ለፋብሪካዎቹ የተተከሉት አገዳዎች እየደረሱ በመሆናቸው የፕሮጀክቶቹ ግንባታ በፍጥነት እንዲካሔድ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ ክትትል ማድረግ አለበት በአፅንኦት የተነገረ ጉዳይ ነው፡፡

ዘገባው የነጋሽ በዳዳ ነው፡፡

የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ሳውዲ አረቢያ ውጡልኝ ያለቻቸውን ኢትዮጵያውያንን አስመልክቶና በሌሎች አገራዊ ጉዳዮች ላይ ሰኔ 22 ቀን 2009 ዓ.ም በመስሪያ ቤታቸው መሰብሰቢያ አዳራሽ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም መቶ አስራ አንድ ሺህ በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የጉዞ ሰነድ ወስደዋል፡፡ የጉዞ ሰነድ ከወሰዱት ውስጥም አርባ አምስት ሺህዎቹ አገራቸው ገብተዋል ብለዋል፡፡ የሳውዲ መንግስት መጋቢት 20 ቀን 2009 ዓ.ም ቀን ያወጣው የውጡልኝ አዋጅ ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም ቢጠናቀቅም እስካሁን ድረስ ግን ተጨማሪ ዜጎችም ወደ አገራቸው በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡
ቃል አቀባዩ 29ኛው የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ በአዲስ አበባ እንደሚካኤድ ገልፀው ለስብሰባውም ስኬት መንግስት አስፈላጊውን ዝግጅት እንዳደረገ ተናግረዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዚህ ስብሰባ ላይ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽነር ለመሆን ኢትዮጵያዊው አቶ ነዋይ ገብረአብ በእጩነት እንደቀረቡ ቃል አቀባዩ ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያና የሩሲያን ግንኙነት አስመልክቶ የሩሲያው ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ለኢትዮጵያ አቻቸው ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ባቀረቡት ግብዣ መሰረት ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ በሩሲያ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ በጉብኝታቸውም የሁለቱን አገራት ግንኙነት ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ከመግባባት ላይ መድረሳቸውን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡
ሚካኤል ጌታሠጠኝ

ኢትዮጵያ በአመት ሁለት ቢሊዮን ገንዘብ በህገ ወጥ በሆነ መልኩ ወደ ሀገሯ ይገባል ሲል ክፍያ ፋይናንሺያል የአለም ባንክ ሪፖርትን ጠቅሶ ተናገረ፡፡
እኤአ በ2015 በወጣ የወርልድ ባንክ ሪፖርት መሰረት ከሰሀራ በታች ወደሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት በአመት ወደ 36 ቢሊዮን ዶላር ይላካል፡፡ ከአፍሪካ ሀገራት መካከል ከናይጄሪያ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ የምትገኘው ኢትዮጵያ ስትሆን በአመት ከሀዋላ ከ 2 እስከ 3 ቢሊዮን ዶላር እንደምታስገባ ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡ከዚህ ገቢ ላይ 2 ቢሊዮን የሚሆነው ገንዘብ ህጋዊ ባልሆኑ መንገዶች የሚገባ ነው፡፡ ክፍያ ፋይናንሺያል በአሜሪካ ሀገር ባደረገው ጥናት መሰረት በዙዎቹ አፍሪካውያን ዲያስፖራዎች ሀገር ቤት ካሉ ወዳጆቻቸው እና ዘመዶቻቸው የቤትና የማህበራዊ ወጪዎችን ጨምሮ መጋራት እንደሚፈልጉ ጥናቱ ይጠቁማል፡፡
ይህንኑ መሰረት በማድረግ ክፍያ ፋይናንሺያል ከአለም አቀፉ ማስተር ካርድ ጋር በመሆን ከአንድ ወር በኋላ በውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያን በሀገር ውስጥ ለሚገኙ ወዳጅ ዘመዶቻቸው የስልክ፣የመብራትና የውሀ ወጪዎችን ለመክፈል የሚያስችላቸውን አገልግሎት እንደሚጀምር ተነግሯል፡፡የጥሬ ገንዘብ ዝውውርን ለማስቀረት በሚደረገው ጥረት ጥሬ ገንዘብ ይዘው አገልግሎቶች እና ግብይቶችን ለመፈፀም ከቦታ ቦታ የሚደረጉ አላስፈላጊ የገንዘብ ዝውውሮችን በማስቀረት እና በመቀነስ በእለት ተዕለት ኑሮአቸው ላይ እንዲያተኩሩ የሚያደርጋቸው አዲስ እና ቀልጣፋ መንገድ ነው ሲሉ የክፍያ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አመራር ሀላፊ የሆኑት አቶ ሙኒር ዱሪ ተናግረዋል፡፡
በቀጣይ ማስተር ካርድ እና ክፍያ አገልግሎቱን በውጪ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለዘመድ ወዳጆቻቸው የመድህን ኢንሹራንስ፣የትምህርት እና የሆስፒታል ወጪዎችን ለመክፈል ብሎም የአለም አቀፍ ጥሪ መክፈያ አገልግሎቶችን ለመክፈት በእቅድ መያዙንም ሰምተናል፡፡ማስተር ካርድ በዓለም አቀፍ ክፍያዎች ውስጥ የሚገኝ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ነው፡፡ በዓለም ላይ ፈጣን ክፍያ የማስፈፀም ሂደትን ከተለያዩ ሸማቾች፣የገንዘብ ተቋማት፣ነጋዴዎች፣መንግስታዊ ድርጅቶች እና የንግድ ድርጅቶች እንዲሁም ከ 210 በላይ ሀገራት ጋር የሚሰራ በመሆኑ ምርጫዬ አድርጌዋለሁ ሲል ክፍያ ፋይናንሺያል አሳውቆል፡፡
ዘገባው የነጋሽ በዳዳ ነው፡፡

የንግድ ሚንስቴር ከኤክስፖርት ዘርፍ 4.3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ቢጠብቅም ከ2.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ መሰብሰብ አልቻለም፡፡
የውጪ ምንዛሬን በከፍተኛ ደረጃ ያስገኛል የተባለው የኤክስፖርት ዕቅድ ግቡን መምታት አለመቻሉን ነው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንግድ ሚኒስቴር ሪፖርት የሚያመላክተው፡፡ከሁሉም ዘርፎች ለውጪ ገበያ በማቅረብ 4.3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት የታሰበ ቢሆንም የእቅዱ 59 ከመቶ 2.53 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ብቻ እንደተገኘ ተነግሯል፡፡ ከገቢ ድርሻ አንፃር 77.5 በመቶ ከግብርና ምርቶች፣14.3 በመቶ ከኢንዱስትሪ ውጤቶች፣7.1 በመቶ ከማዕድን ቀሪው 1.1 በመቶ የሌሎች ዘርፎች እንደሆነ መረጃው ያመላክታል፡፡ የሀገሪቱን የቀጣይ የኢኮኖሚ ሸክም ይሸከማል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የኢንዱስትሪው ውጤቶች በአገልግሎት ካረጀው ግብርና ጋር ሲነፃፀር ከግማሽ በታች ውጤት አስመዝግቧል፡፡
የግብርና ምርቶችን በተመለከተ በዓለም ገበያ ላይ ያለው የግብርና ምርቶች ዋጋ መቀዛቀዝና ተወዳዳሪ መሆን አለመቻል ለጉድለቱ ቀዳሚ ምክንያት ተብሎ በሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ተቀምጧል፡፡የግብርና ምርቶችን አቅርቦት በጥራትና በመጠን ያለማሳደግ፣በአምራች ኢንዱስትሪው የግብአት አቅርቦትና የጥራት ችግር መኖር ተከታይ ችግሮች ተብለው ተለይተው ተነግረዋል፡፡በዚህ ችግር ብቻ ያልተገታው ኤክስፖርቱ የሀገር ውስጥ ዋጋ ሳቢ በመሆኑ ፋብሪካዎች ለሀገር ውስጥ ገበያ ማቅረብ መምረጣቸው፣በአንዳንድ ክልሎች የኮንትሮባንድ ንግድ መስፋፋት እና የግብይት ስርዓቱ ውስጥ የሚሰተዋሉ ክፍተቶች ተደማምረው ለሀገሪቱ የውጪ ምንዛሬ እንዳይገባ አድርገዋል ሲል የንግድ ሚንስቴር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ11 ወራት ሪፖርቱን ሲያስደምጥ አብራርቷል፡፡
ዘገባው የነጋሽ በዳዳ ነው፡፡

አቶ ንዋይ ክርስቶስ ገብረአብ ለ24 አመታት ከ1987 ጀም በተለያዩ የመንስት የሀላፊነት ቦታች አገልግለዋል፡፡
የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከቀድሞው የቀዳማዊ ሀይለስላሴ ከአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኢኮሞሚክ የትምህርት ዘርፍ የሰሩ ሲሆን በኢኮኖሚክስ ዘርፍ ስፔሻላይዝ በማድረግ ከኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በተመሳሳይ ዘርፍ ሰርተዋል፡፡
ንዋይ በ1960ዎቹ እና ሰባዎቹ በኢትጲያ ልማት ባንክ እና ከአቶ በእቅድ ኮሚሽን ውስጥ ሰርተዋል፡፡ በመቀጠልም በእንግሊዝ ሀገር እና በተለያዩ የተባበሩት ሀገራት ድርጅቶች ውስጥ በአማካሪነት ሰርተዋል፡፡
አቶ ንዋይ ክርስቶስ ከ1984 – 87 አ.ም በሽግግሩ ዘመን ለፕሬዚዳንቱ ከ1987-2008 ለጠቅላይ ሚኒስቴሩ ልዩ የኢኮኖሚ አማካሪ በመሆን አገልግለዋል፡፡
ከ1992 ጀም በኢትዩጲያ የልማት ጥናት ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነትም ሰርተዋል፡፡
አቶ ንዋይ ክርስቶስ ገብረአብ ሀምሌ 5 2008 ላይ በኢትዩጲያ የጃፓን አምባሳደር ከሆኑት ካዙሂሮ ሱዙኪ በጃፓኑ ንጉሰ ነገስት በኩል ለኢትዩ ጃፓን ግንኙነት በሰሩት ስራ በጃፓን ከውትድርና ውጪ ለሆኑ ሰዋች የሚጠው ትልቁ የማእረግ ሽልማት ራይዚንግ ሰን ጎልድ እና የብር ኮከብ ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡
በወቅቱ አምባሳደሩ ለአቶ ንዋይ ሽልማቱ የተበረከተላቸው በጃፓን እና በኢትዩጲያ መካከል ስለ ኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲዎች ውይይት እንዲካሄድ መስራች እና የውይይቱ ዋና ሰብሳቢ ስለሆኑ እና እንዲሁም ኢትዩጲያውያን መሪዎችም በፎረሙ እንዲሳተፉ በማድረጋቸው እንደሆነ ገልጸው ነበር፡፡
ባለፍነው ወር ለአለም አቀፍ ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖምን ላስመረጠችው ኢትዩጲያ አቶ ንዋይ ክስቶስ ገብረአብ በአፍሪካ ህብረት ኢኮኖሚ ኮሚሽን ኮሚሽነርነት የሚመረጡ ከሆነ ለአለም አቀፍ ተጽእኖ ፈጣሪነቷ ሌላ ታላቅ እርምጃ ይሆናል፡፡
ናርዶ ዩሴፍ

ረቂቅ አዋጁ ሌሎች ከትራንስፖርት ዘርፉ ጋር በተያያዘ ለሚፈጸሙ ወንጀሎችም ቅጣት ወስኗል፡፡
በህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት ለበጀት እና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ የቀረበ የባቡር ትራንስፖርት ረቂቅ አዋጅ ሳይመዘገቡ እና አገልግሎት ላይ ለመዋል የጸና የደህንነት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖራቸው የመሰረተ ልማት አስተዳዳሪነት ወይም አገልግሎት ሰጪነት ተግባርን እያከናወኑ የሰው ህይወት መጥፋትን ወይም የአካል መጉደልን አልያም ደግሞ ከአንድ ሚሊዩን ብር በላይ የሆነ የንብረት ጉዳትን ካስከተለ ከ20 አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እና ከሁለት መቶ ሺህ ብር በማያንስ እንዲሁም ከ500 ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጣ ተወስኗል፡፡
ወንጀሉ የሰው ሕይወት መጥፋን ወይም አካል መጉደልን የንብረት ጥፋቱም ከ1ሚሊየን ብር በታች ከሆነ ቅጣቱ ከ10 አመት የማይበልጥ ጽኑ እስራት እና ከ20ሺህ ብር የማይበልጥ መቀጮ ነው፡፡
ከኦዲት እና ኢንስፔክሽን መኮንን በረቂቅ አዋጁ ላይ እና በሌሎች ተያይዘው በሚወጡ ደንቦች እና መመሪያዎች በተሰጡት ስልጣን እና ተግባት ለማከናወን ወደ ሎኮሞቲቭ ፣ ፉርጎ፣ የባቡር መሰረተ ልማት ወይም እውቅና ወደ ተሰጠዉ ተቋም እንዳይገባ የከለከለ ከሆነ ወይም የኦዲት እነ ኢንስፔክሽን መኮንን ጥያቄ ማንኛውም ሰው ተገቢውን እነ እውነተኛ ምላሽ ያልሰጠወይም አግባብነት ያለው መረጃ ለማሳየት ፈቃደኛ ካልሆነ ከአንድ አመት በማይበልጥ ቀላል እስራ እና ከ20ሺህ ብር የማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል፡፡
የባቡር የደህነት ስጋ ክስተትን እና የባቡር አደጋን በህግ ስልጣን ለተሰጠው አካል አለማሳወቅ ከአንድ አመት የማይበልጥ ቀላል እስራት እና ከ20 ሺህ ብር የማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል፡፡
የደህንነት ስጋት ክስተቱን ወይም የባር አደጋ ሪፖርት ያልተደረገው የባቡር መሰረተ ልማት አስተዳዳሪውን ወይም የአገልግሎት ሰጪውን ወይም የሌላ ማናቸውንም ሰው ጥፋት ወይም ጉድለት እዳይታወቅ ለመደበቅ በማሰብ ከሆነ ከአምስት አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራ እና ከ100ሺህ ብር በማይበልጥ ገንዘብ ይቀጣል፡፡
ረቂቅ አዋጁ የኢትዩጲያ ምድር ባቡር ኮርሬሽን በተለያዩ የባቡር ትራንስፖር ፕሮጀክቶች ከ120 ቢሊየን ብር በላይ የገንዘብ እዳ ሪፖርት በተደረገበት በዚህ ወቅት ነው የወጣው፡፡ በአጠቃላይም የባቡር ትራንስፖርቱን ዘርፍ ለማተዳደር የተቀረጸ ነው፡፡
የባቡር ትራንስፖርት ዘርፍ ለማስተዳደር ህግ አውጥተው ተቋም አቋቁመው ህግ ካወጡ ሀገራት አንዷ አሜሪካ ናት፡፡ የትራንስፖርት ዘርፉን ለማስተድደር በ1879 አ.ም ኢንተርስቴት ኮሜርስ አክት በሚል አርእስት ያጣች ሲሆን የህጉን ማእቀፍ በ1898 አሻሽላዋለች፡፡
ናርዶስ ዩሴፍ

የኢትዮጲያ ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ለቀይ መስቀል ማህበር ለአንቡላንስ ግዚ የሚውል ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሺ ብር ከዚህ ቀደም ሰጥቶል፡፡ ታዲያ በዛሬው እለት የአንቡላንስ የቁልፍ ርክክብ ሲደረግ ቆይቶ ለቀይ መስቀል ተሰጥቷል ታዲያ በዛሬው እለት የአንቡላንስ የቁልፍ ርክክብ ሲደረግ ቆይቶ ለቀይ መስቀል ተሰጥቷል፡፡
የአንቡላንሱ ዋጋ 3.5 ሚሊዮን የሚገመት ሲሆን የቀይ መስቀል ማህበሩ ግን ከቀረጥነፃ ስለሚያስገባ ዘጠኝ መቶ ሰማኝያ ሺ ብር ተለግሷል ፡፡ በዛሬው እለት የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳድር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቁልፉን ለቀይመስቀል ማህበር በይፋ አስረክበዋል፡፡
እ.ኤ.አ. ከህዳር 2015 እስከ መጋቢት 2017 ድረስ ማህበሩ 435 አንቡላንስ አሉት እነዚህም አንቡላንስ ከ 288 ጣቢያዎች በሀገሪቱ የሚገኙና አገልግሎቶችንም ይሰጣሉ ፡፡ በተጨማሪም ለ5667 የነፃ አንቡላንስ አገልግሎትም ሰቷል ፡፡
የቀይ መስቀል ማህበሩ ከተለያዩ አጋሮች ፣ የንግድ ማህበረሰብ ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሲቪል ሰርቪስ ማህበራት የቀይ መስቀል አጋር በማድረግ እንደዚህ አይነት ድጋፎችን ማግኘት እንደሚቻል ተገልጧል ፡፡

ዘገባው የፍሬህይወት ታደሰ ነው

ኤህአዴግ ለድርድር አልቀመጥባቸውም ያላቸው ሶስት አጀንዳዎች የህገ መንግስቱ ይሻሻል ጥያቄ ቀዳሚው ነው፡፡የአለም አቀፍ የድንበር እና ወሰን እንዲሁም የአምስቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥያቄ ለድርድር የማይቀርቡት ተብለው ተለይተዋል፡፡የአምስቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥያቄ ከዚህ ቀደም ሰላማዊ የፖለቲካ መንገድን ያልተከተሉ ግለሰቦችን በሰላማዊ መንገድ እንዲመለሱ የሚያስችል አሰራርን መፍጠር የሚል ሲሆን ኤህአዲግ ይህ በድርድር ሳይሆን በሀገሪቱ ህግ የሚፈታ ነው በማለቱ ያልተመረጠ አጀንዳ ሆኖአል፡፡
ለመደበኛው የድርድር ጊዜ አጀንዳ ይሁኑ በማለት ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ አጀንዳዎቻቸውን ሲያስይዙ ቆይተው ከመጡት አጀንዳዎች መካከል 13 ያህሉ ተመርጠዋል፡፡ ከነዚህ ውስጥ ኢህአዴግ ለመደራደር ፈቃደኛ የሚሆንባቸውን አጀንዳዎች ሲያነሳ እና ሲጥል በስተመጨረሻም በአብዛኛዎቹ ላይ ለመደራደር ፈቃደኝነቱን አሳይቷል፡፡በዚህም መሰረት በአጀንዳ 1 የምርጫ ህግና ተያያዥ ጉዳዩችን በተመለከተ፡፡ የምርጫ ህግ አዋጅ ቁጥር 532/99፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የስነ-ምግባር አዋጅ 662/2002፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2000 በቀዳሚነት ጠቀምጠዋል፡፡
በአጀንዳ 2 የተላያዩ አዋጆችን በተመለከተ የፀረ ሽብር አዋጅ ፣ የብዙሀን መገናኛ አዋጅ፣ የታክስ ስርዓት ህግ ፣ የፍትህ አካላት አደረጃጀት አዋጅ እና አፈፃፀም ፣ የበጎ አድራጎት ማህበራት ህግ እንዲሁም የሊዝ አዋጅ እና የተፈናቃዮችን በተመለከተ በሁለተኛ አጀንዳ ስር ተይዘዋል፡፡ የመሬት ፖሊሲ ለድርድር የሚቀርብ አለመሆኑ እና በአፈጻጸም ዙርያ ግን መደራደርና መወያየት እንደሚቻልም የኤህአዴግ ተወካይ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ጠቅሰዋል፡፡
ኤህአዴግ ለድርድር ከተስማማባቸው ቀሪ ጉዳዮች መካከል የብሔራዊ መግባባት በአራተኝነት ሲመረጥ የዲሞክራሲና ሠብአዊ መብቶች ተቋማት አደረጃጀት እና አፈፃፀምን በተመለከተ እንዲሁም ዜጎች በየትኛውም የሀገሪቱ ክልሎች የመዘዋወር ፣ የመኖር ፣ ንብረት የማፍራፋት ፣ የፖለቲካና የሲቪል ህገ መንግስታዊ መብቶችን በክልል መንግስታት አደረጃጀት የሚተገበሩበትን የህግ ማዕቀፍ የተመለከተ የሚሉት ጉዳዮች ናቸው፡፡ የድርድሩ መሪዎች የድርድር አጀንዳዎች ቅደም ተከተልና የድርድሩ አጠቃላይ ማዕቀፍ የጊዜ ሰሌዳ አዘጋጅቶ እናዲያቀርብ እና በፍጥነት ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በመስማማት ተበትነዋል፡፡ ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር የሚል ስያሜን የያዘው መድረኩ ወደ ዋነኛው አጀንዳቸው ሳይገቡ ኤህአዲግን ጨምሮ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ከአምስት ወራት በላይ ጊዜን ወሰደዋል፡፡
ዘገባው የነጋሽ በዳዳ ነው

በቦሌ ኤርፖርት እና ሆቴሎች ቋሚ የቱሪስት ታክሲ አገልግሎት ሰጪ ባለንብረቶች እና በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን መካከል የስምሪት አሰራርን መሰረት በማድረግ የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ፍርድ ማምራቱ የሚታወስ ነው፡፡ በዚህም መሰረት የቱሪስት ታክሲ ማህበራቱ መጋቢት 25 ቀን 2009 ዓ/ም ተግባራዊ ሊደረግ የነበረውን ስምሪት በመቃወም በ18/07/09 ዓ/ም በቁጥር አ/አ/ት/ባ779/2009 ዓ/ም በተፃፈ ደብዳቤ የወጣው አዲሱ የሜትር ተጋክሲዎች ስምሪት እንዲሰረዝላቸው በማሰብ በስምቱ ላይ በስር ፍርድ ቤት እግድ አውጥተዋል፡፡
ፍርድ ቤቱም በ22/07/09 ዓ/ም በዋለው ችሎት የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ከዚህ ፍርድ ቤት ተለዋጭ ትዕዛዛ እስከሚሰጥ ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ባለስልጣን መስሪያ ቤት በ18/07/09 ዓ/ም በተፃፈ ደብዳቤ የሜትር ታክሲዎች የስምሪት ምድብ ድልድልን ተፈፃሚ ሳያደርግ ለጊዜው ታግዷል በማለት ትዕዛዝ ሰቷል፡፡
በዚህም መሰረት ይግባኝ ባይ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን በ04/08/09 ዓ/ም በተፃፈ አቤቶታ እግዱ እንዲነሳ ይግባኝ በማለት ጉዳዩን ወደ ቦሌ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት 2ኛ ፍትሀ ብሔር ችሎት ወስዶታል፡፡
ፍርድ ቤቱ ሁለቱን ወገኖች ሲያከራክር በቦሌ ኤርፖርት ቱሪስት ታክሲዎች በኩል እግዱ ቢነሳ ቀድሞ በቦታው ላይ የምንሰራ ሰዎች ገቢያችንን እናጣለን ማህበራቱና ቤተሰብም ይበተናል በሌላ በኩል ታክሲዎቹን ለማዘመን የባንክ ብድር ለመክፈል ይሳነናል ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን በጠበቃው በኩል ባሰማው ክርክር ያቀረቡት ማመልከቻና ይግባኝ ሙሉ በሙሉ ስልጣን አለን ከማለት በስተቀር በስልጣናቸው የተሰጠው እግድ ይነሳልን ከማለት በስተቀር በቂ ምክንያት አላቀረቡም ይላል በቀን 29/09/09 ተፅፎ በቀን 12/10/09 የተነበበው የውሳኔ መዝገብ፡፡
በአጠቃላይ የስር ፍርድ ቤቱ እግዱ እንዲነሳ በይግባኝ ባይ ወይንም በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን ላቀረቡት አቤቶታ እግዱ የተሰጠው በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ነጥብ ለይቶ የቀረበውን ክርክር አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች አናፃር መመርመር ሲገባው ሳይመረምር የደረሰበት ድምዳሜ የሰጠው ትዕዛዝ በአግባቡ ባለመሆኑ በፍትሀ ብሔር ስነ-ስርዓት ህግ ቀጥር 348‹1›መሠረት ተሸሯል ሲል መዝገቡን ዘግቷል፡፡
ዘገባው የነጋሽ በዳዳ ነው

በ3.4 ቢሊዮን ብር ተገንብቶ መስከረም ወር የተመረቀው የኢትዮ ጅቡቲ የምድር ባቡር ከምረቃው በኋላ ባሉት ከ 3 እስከ 6 ወራት ውስጥ መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚጀምር መነገሩ የሚታወስ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ባቡሩ በተያዘለት የጊዜ ገደብ ዛሬም ድረስ መደበኛ አገልግሎቱን አልጀመረም፡፡ ለምን ስንል ለኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደረጄ ተፈራን ባነጋገርንበት ወቅት ባቡሩ የሙከራ ስራውን በወቅቱ ባለመጀመሩ የመደበኛ ስራው መዘግየቱን ለዛሚ 90.7 ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
እስከ አሁን መደበኛ የሚባል ስራውን ያልጀመረው ባቡሩ ስራውን መች ይጀምራል ለሚለው ጥያቄ አቶ ደረጄ ተፈራ በምላሻቸው ጊዜውን በትክክል ማስቀመጥ ያስቸግራል ሲሉ ምላሽ ሰተዋል፡፡
መቀመጫውን አዲስ አበባ ያደረገው የኢትዩ ጅቡቲ የምድር ባቡር አስተዳደር 75 ከመቶ ከኢትዮጵያ ቀሪ 25 ከመቶ የሚሆነውን የንግድ ፈቃድ ከጅቡቲ ማግኘት ችሎአል፡፡
ጅቡቲ ላይ ቆመው የሚገኙት የባቡሩ ዋገኖች አገሪቱን ለኪራይ ኪሳራ እየዳረጉ በሀገር ውስጥ የገቡት ሎኮሞቲቮችም ቢሆኑ ለብልሽት መጋለጣቸው ኪሳራው በማን ይታሰባል ለሚለው ጥያቄ አቶ ደረጄ ተፈራ ጅቡቲን በተመለከተ የጋራ ንብረት ስለሆነ ኪራይ አታስከፍልም በሀገር ውስጥ ያሉትም በዚህ ጊዜ ውስጥ ለብልሽት ስለማይዳረጉ ስጋት የለብንም ሲሉ ምላሽ ሰተዋል፡፡
752 ኪሎ ሜትርን የሚሸፍነው ባቡሩ በሰዓት 120 ኪሎ ሜትሮችን በመጓዝ ቀናትን ይፈጅ የነበረውን ርቀት ወደ 10 ሰዓታት ዝቅ ያደርገዋል የሚል እምነት ተጥሎበታል፡፡
ለሚቀጥሉት 6 ዓመታት ቻይናውያን የሚያስተዳድሩትን ባቡር ለመመረቅ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሀ/ማርያም ደሳለኝ፣የጅቡቲው ፕሬዘዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌህ፣የቶጎ ሪፐብሊክ ፕሬዘዳንት ፋዩሪ ኦሲዙማ እና የቻይና ልዩ ልዑክ ተወካይ ዙሻኦሺ በለቡ ባቡር ጣቢያ መገኘታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ዘገባው የነጋሽ በዳዳ ነው

የኢትዮጵያ ምግብ፣ መድኃኒት እና ጤና እንክብካቤ ባለሥልጣን የህክምና አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ከሚመለከት ክፍል የሚመጡ የተለያዩ ጉዳዮችንና መረጃዎችን በማሰባሰብ እና ዶክተሮች ስራቸውን በሚከውኑበት ወቅት ሊያጋጥም የሚችል ስጋትን ከግምት ውስጥ በማስገባት የዶችተሮችና የህክምና ባለሙያዎች ኢንሹራንስ መክፈቱን ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንሽ አስታውቋል፡፡
ከዚህ ቀደም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባስተላለፈው የመጨረሻ ውሳኔ መሰረት በህክምና ወቅት ለተፈፀመ ስዕተት 4 ሚሊዮን ብር በካሳ መልክ ተጠይቆ ከ አንድ ሚሊዮን ብር በላይ እንዲከፈል ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡
የኢትዮጵያ ፍትሃ ብሄር ህግ በህክምና ወቅት ለሚደርስ ስዕተት የህክምና ተቋሙን እና ሠራተኞቹን ተጠያቂ በማድረግ ካሳ እንዲከፈል ያደርጋል፡፡ የተለያዩ አገራትም በህክምና ወቅት ለሚደርስ ስዕተት ካሳ እንዲከፈል እና አስፈላጊ ወጪዎችም እንዲሸፈኑ ያስገድዳሉ፡፡
የኢትዮጵያ ሜዲካል አሶሴሽን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር የኔነህ ጌታቸው እንዳሉት በኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንሽ የተጀመረው የኢንሹራንስ አይነት ለረጅም ግዜ ይጠብቁት የነበረ እና በሙያ ውስጥ ያሉ የህክምና ባለሙያዎችን የሚጠቅም እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በእንግሊዝ ሜዲካል ኢንደሚኒቲ ኢንሹራንስ የሌላቸው የህክምና ባለሙያዎች የንግድ ፍቃድ አይሰጣቸውም፡፡

ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስድስት የብድር ስምምነት አዋጆችን መርምሮ ማጽደቁን ባልደረባችን ናርዶስ ዮሴፍ ዘግባለች።
ምክር ቤቱ በሁለተኛ ዓመት የስራ ዘመን በ42ኛ መደበኛ ጉባኤው ከቀረቡለት 15 የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች በብድር ስምምነት ላይ ያተኮሩ ስድስት ረቂቅ አዋጆችን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
የስምምነት አዋጆቹ ለሁለተኛው የከተሞች የመጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን 236 ሚሊዮን 400 ሺህ ኤስ.ዲ.አር እና 125 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የብድር ስምምነት አዋጅ ጸድቋል።
ኤስ ዲ አር ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ለአባል አገራት እንደ አማራጭ መገበያያ የፈጠረው የገንዘብ መለኪያ ሲሆን የአንድ ኤስ ዲ አር ዋጋ ምንዛሬ 1 ነጥብ 4 የአሜሪካ ዶላር አካባቢ ነው።
ለንግድና ሎጂስቲክስ 110 ሚሊዮን 400 ሺህ ኤስ.ዲ.አር፣ ለጥራት ማረጋገጫ መሰረተ ልማት ማሻሻያ 37 ሚሊዮን 200 ሺህ ኤስ.ዲ.አር፣ ለጤና መሰረተ ልማት ፕሮግራም ማስፈጸሚያ 110 ሚሊዮን 600 ሺህ ኤስ.ዲ.አር ከአለም አቀፉ የልማት ማህበር ጋር የተደረጉ ስምምነቶች ጸድቀዋል።
ከጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ድርጅት ጋር ለሴቶች ንግድ ስራ ፈጠራ ብቃት ማሻሻያ ማሳደጊያ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚሆን 5 ነጥብ 5 ቢሊዮን የጃፓን የን የብድር ስምምነት አዋጅ ጸድቋል።
ለኅብረተሰቡ ተደራሽ የሆኑ የጤና ተቋማት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የጸደቀው የአምስት ሚሊዮን ዩሮ የብድር ስምምነት አዋጅ በኢትዮጵያና በኢጣልያ መንግስት መካከል የተደረገ ነው።
የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ገነት ታደሰ እንዳሉት፤ የብድር ስምምነት አዋጆቹ አገሪቱ የጀመረችውን ልማት ለማስቀጠል የሚያግዙ ናቸው።
ከስምምነቱ የሚገኘው ገንዘብ የብድር ጫናው ያልበዛና ከአገሪቱ የብድር ስትራቴጂ ጋር የተጣጣመ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ምክር ቤቱ በተጨማሪም የባቡር ትራንስፖርት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።

ከጠዋቱ 12፡52 ደቂቃ በአዲስ አበባ ከተማ በወረዳ ሰባት በተለምዶ ሀብተ ጊዮርጊስ ድልድይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ አደጋ አምስት መቶ አርባ አንድ ሺ ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል፤
በቃጠሎው ስድስት ንግድ ቤቶች፣ ካፍቴሪያዎች፣የሸቀጣሸቀጥ ሱቆች የተለያዩ እቃዎች መጋዘን የተቃጠሎ ሲሆን አደጋውን ለመቆጣጠር አራት የእሳት አደጋ ሰራተኞች እንዲሁም ሃያ አንድ ሺ ሊትር ውሀ ጥቅም ላይ ውሏል፤
በሰው ህይወት ላይም ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም ሲሉ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግዋል፡፡
ዘገባው የፍሬህይወት ታደሰ ነው፡፡

የጊኒ እና የኮትዲቩዋር ዜግነት አላቸው የተባሉ ሁለት ዜጎች በርካታ የዱር እንስሳ ውጤቶችን ከሀገር ለማስወጣት ሲሞክሩ ነበር በቁጥጥር ስር የዋሉት በዚህም ለፍርድ ቀርበው እያንዳንዳቸው የ10 ሺ ብር ቅጣት ተጥሎባቸዋል፤

በአጠቃላይ በዚህ ዓመት ብቻ ከ40 በላይ ሰዎች የተያዙ ሲሆን ባሳለፍነው ዓመት ደግሞ 68 ሰዎች እርምጃ ተወስዶባቸዋል፤ ከአምናው ጋርም ሲነፃፀር በዘንድሮው ዓመት የዱር እንስሳት ህገ-ወጥ ዝውር የቀነሰ እንደሆነ የተናገሩት የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት መረጃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘሪሁን ዘውዴ የመቀጣጫ ህጉ እንዲሻሻል ጠይቀናል በፍትሀብሄር ህግ ውስጥ እንደሚካተት ወንጀለኞችም ተመጣጣኝ ቅጣት እንዲቀጡ አስረግጠው ተናግረዋል፤

በየአመቱ ከሚያዙ የእንስሳት ውጤቶች መካከል የዝሆንና የአውራሪስ ጥርስ፣የአንበሳ ጥፍር ከፍተኛውን ደረጃ ሲይዝ የጅብና የአቦ ሸማኔ ግልገሎች፣ የሰጎን እንቁላል፣ የተለያዩ የእባብ ዝርያዎች ከፖሊስ፣ ከቦሌ አለም አቀፍ አየር መንገድ እንዲሁም ከሌሎች ሀገራት ድንበር ከሚያዋስኑ ክልሎች ጋር በመተባበር እንደተያዙ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያና ኬንያ በህገ-ወጥ መንገድ የሚያዙ የዱር እንስሳት ውጤቶችን ማቃጠል ብቸኛ መፍትሄ እንደሆነ የሚያስቀምጡ ሀገራት ናቸው፡፡

ፍሬህይወት ታደሰ ዘግባዋለች

የሲዳማ ፍቼ ጨምበላላ የዘመን መለወጫ በዓል በሀዋሳ ከተማ በሲዳማ ባህል አዳራሽ 500ሺህ ሰዎች በተገኙበት ዛሬ እየተከበረ ነው፡፡
አከባበሩ የጀመረው ዛሬ ከሰአት በኋላ ሲሆን በአሉ ለቀጣይ ሁለት ቀናት መከበሩን ይቀጥላል፡፡
የብሔሩ ተወላጆች የዘመን መለወጫ በዓላቸውን ከ1983 አመተምህረት ጀምሮ በደማቅ ሁኔታ በሀዋሳ በመሰብሰብ ባህሉን መሰረት ባደረገ ሁኔታ በማክበር ላይ ይገኛሉ፡፡
ፍቼ ጨምበላላ ባለፈው አመት ህዳር ወር ላይ በተደረገው የዩኔስኮ አመታዊ ስብሰባ ላይ በአለም አቀፍ ደረጃ በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ፣ የትምህርትና የባህል ማእከል (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ቅርስነት ተመዝግቧል፡፡

እነዚህ ሁለት የጭነት አውሮፕላኖች የሚገዙት በየአመቱ በፈረንጆቹ ከሰኔ 15 እስከ 21 ድረስ ከሚካሄደው ከፓሪስ የአውሮፕላኖች ሾው ላይ ነው፡፡
የፓሪስ የአውሮፕላን ሾው የተጀመረው በ1949 ሲሆን የዘንድሮው 53ኛው ነው፡፡ በዝግጅቱ የተለያዩ አውርፕላን አምራች ድረውጅቶች እና የአየር መንገድ ሀላፊዎች ይሳተፋሉ፡፡
የኢትዩጲያ አየር መንገድ የሚያስመጣቸው የቦይንግ ቢ777 200 ኤል አር የጭነት አውሮፕላኖች በአለም በስፋት እና በርዝመት አንደኛ ነው፡፡ 4 900 ኪሎ ሜትር ሲኖረው 112 ቶን መሸከም ይችላል፡፡
የሁለቱ የጭነት አውሮፕላኖች ግዢ ከዚህ በፊት በቦይንግ የግዢ እና ማድረስ አገልግሎት ድረ ገጽ ላይ ማንነቱ ያልታወቀ ገዢ በሚል ተጠቅሶ ነበር፡፡
የኢትዩጲያ አየርመንገድ ዋና ሀላፊ ዶክተር ተወልደ ገብረማሪያም አውሮፕላኖቹ የኢትዩጲያን ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ለማሻሻል እንደሚገዙ ተናግረዋል፡፡
የጭነት ማጓጓዣ አውሮፕላኖች ከማስገባት ጎንለጎን አየርመንገዱ የካርጎ አገልግሎቱን ለማሻሻል እና ዘመናዊ ለማድረግ 150 ሚሊዩን ዶላር ኢንቨስት አድርጓል፡፡
በዚህ ወር መጨረሻ ላይ በሚያዘጋጀው በአይ ሲ ኤኮ አለም አቀፍ የአየርካርጎልማትፎረምላይም 15ሺህ ካሬሜትርላይያረፈካርጎተርሚናሉንያስመርቃል፡፡
የካርጎተርሚናሉሁለተኛክፍልሲጠናቀቅአየርመንገዱበአመት 600ሺህ ቶንማጓጓዛይችላል፡፡
ከጭነት አውሮፕላኖቹ በተጨማሪም አየርመንገዱ 10 የ7373 ማክስ 8 አውሮፕላኖቸን ለማስገባት አዟል፡፡ የእነዚህ አውሮፕላኖች ስምምነት የተጠናቀቀው በዚህአመት መስከረም ወር ላይ ነበር፡፡
ከአፍሪካ ሰላሳ የ737 ማክስ 8ኤስ አውሮፕላን ሞዴል አውሮፕላኖችን በብዛት ለማስገባት በማዘዝ ከአፍሪካ ተቀዳሚ አድርጎታል፡፡
የኢትዩጲያ አየር መንገድ በትላንትናው እለትም ለተጎዦች የሚውል 10 ኤ 350-900 ኤርክራፍት አውሮፕላኖች ለማስገባት አዟል፡፡
ባሳለፍነው በዚህ ወር 12 የዕዚህ ሞዴል አውሮፕላኖችን በማዘዝ ከአፍሪካ የመጀመሪያው አየር መንገድ ሆኖ ነበር፡፡ከእነዚህ ውስጥም በአሁን ወቅት አራቱ አገልግሎት እየሰጡ ነው፡፡

ከኢትዩጲያ አየር መንገድ ለተገኘው መረጃ ናርዶስ ዩሴፍ

40 የመንግስት መስሪያ ቤቶች በ32 ሚሊዩን ዶላር በሚገነባ የአንድ መስኮት አገልግሎት ግንባታ ኩፒክ ከተባለ የድርጅት ሊገነባ ነው፡፡ በሁለት ምእራፍ እንዲጠናቀቅ የአራት አመት የግንባታ ጊዜ ተቀምጦለታል፡፡
ይህ ግንባታ በመጀመሪያው ምእራፍ የሚያካትታቸዉ የመንግስት መስሪያቤቶች ገቢዎች እና ጉምሩክ፣ባንኮች የኢንሹራንስድርጅቶች፣የገንዘብእናኢኮኖሚትብብርሚኒስቴር፣የግብርናሚኒስቴር፣ኢንዱስትሪሚስቴር፣ንግድሚኒስቴር እና ሌሎች ለህዝቡ በተቀዳሚነት አስፈላጊ ናቸው ተብለው የተለዩ ድርጅቶች ናቸው፡፡
በሁለተኛው ምእራፍ ደግሞ ቀሪዎቹ 20 የመንግስት ድርጅቶች ይጠቃለላሉ፡፡ በዚህ መሰረት አንድ ተጠቃሚ የ20 መንግስት መስሪያቤቶችን አገልግሎት በአንድ መስኮት ያገኛል፡፡
በአሁን ወቅት ይህ ፕሮጀክት ጨረታው ተጠናቋል፣ አጠቃላይ የሆነ እቅድም ተሰርቶለታል፡፡ በአሁን ወቅት መስሪያ ቤቶቹ የነበራቸው የአሰራር አይነት እና ወደፊትም መሆን ያለበት የግልጋሎቱ አይነት ጥናት ተደርጓል፡፡
በአጠቃላይ ደግሞ ይሀ የአንድ መስኮት አገልግሎት ሊይዛቸው የሚገቡ የጋራ ስራዎች፣ የንግድ እቅድ ተጠናቆ መዋቅሩም ተቀርጾ የትግበራ እቅድ ላይ ደርሷል፡፡

ከ አዲስ አበባ ወደ ደቡብ ምእራብና ጅማ መስመር የሚደረጉ የሀገር አቋራጭ አዉቶብስ ጉዞዎች ከ ሀሙስ ጀምሮ ቀድሞ የነበራቸዉ  የአዉቶብስ ተራ የመነሻ መስመር ወደ አየርጤና ተዛዉሯል።

41 ያህል የጉዞ መስመሮች የተዘጋጁ ሲሆን የተጓዦች ምዝገባም በዛዉ በአየርጤና መናኻሪያ ይከናወናል

መናኻሪያዉ የተገልጋዮችን ጊዜና እንግልት ይቆጥባል ተብሎለታል።

ከዚህ ቀደም በሀገር አቋራጭ አዉቶብሶች አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በተሰራ ጥናት መሰረት 74 በመቶ ያህል ተገልጋዮች በቂ አገልግሎት መስጫ ቦታ አለመኖሩን የጠቆሙ ሲሆን 55 በመቶ  ያህሎቹ ደግሞ መናኻሪያዎቹ ምቹ አይደሉም ብለዋል።

ዘገባው የያልፋል አሻግር