አገር አቀፍ ዜናዎች

ጥር 25/2008 ዓ.ም

ከስዋዚላንድ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የልምድ ልውውጥ ተሞክሮ ለማድረግ ለመጡት የልዑካን ቡኑ አባላት የፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ከበደ ወርቁ በኢትዮጵያ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም አፈጻጸም ዙሪያ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ገልጸው በሽታዎችን በመከላከል፤ በመቆጣጠርና በመቀነስ ረገድ ለውጦች ተመዝግበዋል ብለዋል፡፡

በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም አፈጻጸሙ በየደረጀው የተለያዩ አደረጃጀቶች መኖራቸውን የገለጹት ዶ/ር ከበደ በተለይ የሴቶች የልማት ቡድንና የጤና ልማት ሠራዊት አደረጃጀት ለእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎት መሻሻል የጎላ ድርሻ ማበርከቱን ገልጸዋል፡፡

የስዋዚላንድ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሲለቦነሌ ዲሌሌ (Slbonglle Ndlela) እንደተናገሩት ከዚህ በፊት ለእንደዚህ አይነት ተግባር ወደ አሜሪካና ሌሎች የአውሮፓ አገራት ያቀኑ እንደነበር አስታውሰው አሁን ግን በአህጉራችን አፍሪካ ጥሩ አፈጻጸም መገኘቱ የሚያነቃቃ ነው ብለዋል፡፡

በዋናነትም ኢትዮጵያ ተላላፊ በሽታዎችን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ ያስመዘገበችውን ውጤት ያደነቁት ሚኒስትሯ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም አፈጻጸሙን ለማየት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ግምቢቹ ወረዳ ያከናወኑት ጉብኘት የተሳከ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

-    ምንጭ- የፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስቴር

ጥር 25/2008 ዓ.ም

 

ይሄን ያሉት የፌዴራል ኤች.አይ.ቪ መከላከያ ጽህፈት ቤት ምክትል ዳይሬክተር አቶ አለሙ አኑ ናቸው፡፡ ጽህፈት ቤቱ በ2030 ሃገራችን ኢትዮጲያ የኤች.አይ.ቪ ስርጭትን ለመግታት የሚዲያዎች ሚና ምን መሆን አለበት በሚል ለሚዲያ ባለሙያዎች በአዳማ ከተማ ባዘጋጀው ስልጠና ላይ ሚዲያዎች በቫይረሱ ስርጭት ላይ የሚሰሯቸው የመማሪያ ፕሮግራሞች መቀዛቀዛቸውን አሳውቀዋል፡፡ የሚዲያዎች ሚና ላይ ትኩረቱን ያደረገውን ስልጠና የፌዴራል ኤች አይ ቪ መከላከያ ቢሮ በአለም አቀፍ ደረጃ በቤተሰብ ጤና ላይ ከሚሰራው FHI360 ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር ያዘጋጀው መሆኑ ታውቋል፡፡ ግብረ ሰናይ ድርጅቱ ከ37 አመታት በላይ በቤተሰብ ጤና ላይ የሰራ ሲሆን መሰረቱ ከወደ አሜሪካ ነው ተብሏል፡፡ በሃገራችን ኢትዮጲያ ከ15 አመታት በፊት በተለያዩ ክልሎች ላይ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ሲሰራ መቆየቱን የ FHI360 የኢትዮጲያ ቅርንጫፍ አስተባባሪ ዶክተር ማሞ ገብረጻዲቅ ለዛሚ ተናግረዋል፡፡ (እንየው ቢሆነኝ)

ጥር 25/2008 ዓ.ም

ይሄን ያሉት የፌዴራል ኤች.አይ.ቪ መከላከያ ጽህፈት ቤት ምክትል ዳይሬክተር አቶ አለሙ አኑ ናቸው፡፡ ጽህፈት ቤቱ 2030 ሃገራችን ኢትዮጲያ የኤች.አይ.ቪ ስርጭትን ለመግታት የሚዲያዎች ሚና ምን መሆን አለበት በሚል ለሚዲያ ባለሙያዎች በአዳማ ከተማ ባዘጋጀው ስልጠና ላይ ሚዲያዎች በቫይረሱ ስርጭት ላይ የሚሰሯቸው የመማሪያ ፕሮግራሞች መቀዛቀዛቸውን አሳውቀዋል፡፡ የሚዲያዎች ሚና ላይ ትኩረቱን ያደረገውን ስልጠና የፌዴራል ኤች አይ መከላከያ ቢሮ በአለም አቀፍ ደረጃ በቤተሰብ ጤና ላይ ከሚሰራው FHI360 ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር ያዘጋጀው መሆኑ ታውቋል፡፡ ግብረ ሰናይ ድርጅቱ 37 አመታት በላይ በቤተሰብ ጤና ላይ የሰራ ሲሆን መሰረቱ ከወደ አሜሪካ ነው ተብሏል፡፡ በሃገራችን ኢትዮጲያ 15 አመታት በፊት በተለያዩ ክልሎች ላይ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ሲሰራ መቆየቱን FHI360 የኢትዮጲያ ቅርንጫፍ አስተባባሪ ዶክተር ማሞ ገብረጻዲቅ ለዛሚ ተናግረዋል፡፡ (እንየው ቢሆነኝ)

ጥር 24/2008 ዓ.ም

እንስሳቶቹ የተገኙት በኢትዮጲያና ሱዳን ድንበር አቅራቢያ በአማራ ክልል በሚገኘው የአልጣሽ ብሄራዊ ፓርክ ነው፡፡ እንስሳቶቹ ከዚህ በፊት በዚህ ቦታ ይኖሩ እንደነበር ምንም የታወቀ መረጃ የለም፡፡ አናብስቶቹም ምናልባት አመቱን ሙሉ በፓርኩ የሚቆዩ ወይንም ቦታውን ለቀው የሚሄዱ ስለመሆናቸው ባለሙያዎች ጥናት እያደረጉ ነው፡፡ የአልጣሽ ብሄራዊ ፓርክ 10,000 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን ከዚህ በፊት ቁጥራቸው ከ27-54 የሚሆኑ አናብስት መኖሪያ ሆኖ ቆይቷል፡፡ አሁን ላይ በአፍሪካ የሚገኙት አናብስት ከ20,000 እንደማይበልጡ ይነገራል፡፡ (እንየው ቢሆነኝ)

ጥር 23/2008 ዓ.ም

እንደ ፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር በ1990 የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት የነበሩትን ሄስኒ ሃብሬን ከስልጣን አስወግደው መንበረ መንግስቱን የተቆጣጠሩት ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ የህብረቱ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡

የሊቢያ፣ የሩዋንዳ፣ የቤኒን፣ የቻድ እና የዙምባቡዌ መሪዎች በእጩነት ቀርበው ነበር፡፡ የ2015 የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሆነው ያገለገሉት የዙምባቡዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ስልጣናቸውን ለኢድሪስ ዴቢ አስረክበዋል፡፡ በህብረቱ ጉባኤ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ሮበርት ሙጋቤ የአለም መንግስታት ድርጅት ለአፍሪካ መሪዎች ተገቢውን ክብር ሊሰጥ እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡ አፍሪካውያን በህብረቱ ቋሚ የጸጥታው ምክር ቤት አባልነት ይገባቸዋል ብለዋል፡፡ 54 የአፍሪካ ሀገራት ቋሚ መቀመጫ በሌላቸው ሁለት ሃገራት ብቻ ሊወከሉ አይገባም ነው ያሉት ሮበርት ሙጋቤ፡፡ ሙጋቤ አክለውም ከ3.5 ቢሊዮን ህዝብ በላይ ላላቸው አፍሪካና የእስያ ሀገራት ተገቢ ክብር ሊሰጥ ይገባልም ብለዋል፡፡ አዲሱ የህብረቱ ሊቀመንበር ኢድሪስ ዴቢ የ2063 አጀንዳን ለማሳካት፤ አፍሪካን በአንድ መሰረተ ልማት ለማስተሳሰር፤ ሰብአዊ መብቶችን ለማስክበርና የአፍሪካ ሰላምና መረጋጋት እውን እንዲሆን እሰራለሁ ብለዋል፡፡ (እንየው ቢሆነኝ)

ጥር 18/2008 ዓ.ም

በኦሮሞያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ሊባኖስ ወረዳ ሰሌ አሮጌ ቀበሌ የተያዘው ቶዮታ ፒክአፕ ተሽከርካሪ ኮድ 3 95075 ታርጋ ያለው ተሽከርካሪ የፍተሸ ጣቢያ ሰራተኞችን ለማለፍ በከፍተኛ ፍጥነት ሲያሽከረክር ከመንገድ ወጥቶ ተገልብጧል፡፡

መሳሪያዎቹ ለፍተሻ ሰራተኞች እይታ በመደበቅ በተመሳሳይ መልኩ በመጫኛው ላይ በተዘጋጀ ማስቀመጫ ተሸሽገው ተቀምጠው የነበረ ሲሆን ተሸከርካሪው ሲገለበጥ ብይዱ በመልቀቁና መሳሪያቹ በመውደቃቸው ሊያዝ ችሏል፡፡

አሽከርካሪው ከአደጋው በኋላ ከስፍራው አምልጦ መሰወሩን የገለፁት የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ የኮሙኒኬሽን ዲቪዥን ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር አስፋው ዳባ ናቸው፡፡

በተሸርካሪው ውስጥ ሌላ አብሮ የተሳፈረ ታዳጊ ወጣት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ወጣቱ ወደ ጎንደር ለመጓዝ ድል በር አካባቢ አሽከርካሪውን ለምኖ እንደተሳፈረ ገልጧል፡፡ በፖሊስ ቁጥጥር ስርም ውሎ ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል፡፡

ከ45ቱ መሳሪያዎች ውስጥ 28ቱ ታጣፊ ባለ ክላሽ እና 17ቱ ባለ ሰደፍ ሲሆኑ ካርታ ሲኖራቸው ጥይት ግን እንደሌላቸው ታውቋል፡፡

በተሸከርካሪው ውስጥ በተደረገ ምርመራም በ16/05/2008 ዓ.ም መቱ በደሌ አካባቢ አሸከርካሪው ነዳጅ መቅዳቱን የሚያሳይ ደረሰኝ ተገኝቷል፡፡ (ሱራፌል ዘላለም)

ጥር 12/2008 ዓ.ም

የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ ኃላፊ አቶ ወርቅነህ ጣፋ እንደገለጹት፥ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች 13 የንግድ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎችን ለግል ለመስጠት እቅድ ተይዟል። ነገር ግን ከተመዘገቡት ተወዳዳሪዎች መካከል የተቀመጠውን መስፈርት የሚያሟላ ተመዝጋቢ እስካሁን አለመገኘቱን ሃላፊው ገልፀዋል። ፈቃዱ ሊሰጥ የታሰበው ስድስቱ በአዲስ አበባና ቀሪዎቹ በዋና ዋና የክልል ከተሞች ቢሆንም በወጣው ማስታወቂያ መሰረት መስፈርቱን አሟልተው የሚመዘገቡ ግን አልተገኙም።

እንደ አቶ ወርቅነህ ገለፃ ጨረታው ለ60 ቀናት አየር ላይ በቆየበት ወቅት 39 የሚሆኑ አመልካቾች ሰነዱን ወስደው ለውድድር ቢቀርቡም የንግድ ሬዲዮ መመሪያ ቁጥር 1/2000ን አሟልተው አልተገኙም። ከተወዳዳሪዎቹ መካከል በብዛት ሊያሟሉት ያልቻሉት የገንዘብ አቅማቸው የሚፈለገውን ያህል አለመሆንና የአቅም ውስንነቶች መሆናቸውን አቶ ወርቅነህ ገልፀዋል።

ይኸው ጨረታ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በድጋሚ የሚወጣ በመሆኑ በአዲስ አበባም ሆነ በክልል የሚገኙ ተወዳዳሪዎች አቅማቸውን አጠናክረው እንዲቀርቡም ጥሪ አቅርበዋል። በእቅድ ዘመኑ መንግስት የመገናኛ ብዙሃን ዘርፉን በብዛትም ይሁን በአይነት ለማሳደግ የሚያስችል እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑንም አቶ ወርቅነህ አስረድተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት አገልግሎት በመስጠት ላይ ያለውን የአናሎግ ቴሌቨዥን ወደ ዲጂታል ለመቀየር የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን በሳተላይት የቴሌቪዥን ስርጭት ለማድረግ የሚችሉ የግል ባለሃብቶችን በጨረታ አወዳድሮ ፈቃድ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉንም ጠቁመዋል። በአሁኑ ወቅት በመላ አገሪቱ ሰባት የንግድ ኤፍ ኤም ሬዲዩ ጣቢዎች ፈቃድ ወስደው ስራ ላይ ይገኛሉ።

ምንጭ- Federal Government Communication Affairs Office of Ethiopia

ጥር 12/2008 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የተመሰረተበትን 50ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ዝግጅቶች ከጥር 24-29 ቀን 2008 ዓ.ም ድረስ ሊያከብር መሆኑን ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫው አስታውቋል፡፡

ኤግዚቢሽን፣ የፓናል ውይይት፣ የጥያቄና መልስ ውድድር እና የኢቢሲ ማህበረሰብን የሚያሳትፍ የሰብአዊ አገልግሎት (ለ6 ተቋማት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ) 50ኛ ዓመቱን አስመልክቶ የሚካሄዱ ስነ-ስርዓቶች ናቸው፡፡ (ሱራፈል ዘላለም)

ጥር 04/2008 ዓ.ም

ባለፈው ታህሳስ 26 ቀን 2008 ዓ.ም በሳዑዲ ዓረቢያ ጂዛን ከተማ በአንድ መኖሪያ ቤት በተዘጋጀው የሰርግ ስነ-ስርዓት ላይ ሙሽሮችን ጨምሮ ከ 120 በላይ ዜጎቻችን የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸውና በሀገሪቱ ህግ የተከለከለውን መጠጥ ይዞ በመገኘታቸው በሳዑዲ የፀጥታ ሀይሎች ተይዘው መታሰራቸው የሚታወስ ነው፡፡ በጂዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤት ከጂዛን ኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ጋር በመሆን ከሳዑዲ መንግስት ጋር ባደረገው ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እና ድርድር ኢቃማ (መኖሪያ ፈቃድ ) ያላቸውና ከጉዳዩ ጋር ቀጥታ ግንኙነት የሌላቸውን ዜጎች ከእስር ማስለቀቅ የተቻለ ሲሆን የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሰርግ ስነ ስርዓቱ ላይ የተያዙ ዜጎቻችን በተደረገው መግባባት በወንጀል ሳይጠየቁ ወደ ኢትዮጵያ እንዲሸኙ ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ስለሆነም ዜጎቻችን ለወደፊት በሚያደርጉት የማህበራዊ ግንኙነት ላይ የሀገሪቱን ህግና ስርዓት እንዲያከብሩ እናሳስባለን፡፡

ምንጭ- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ጥር 03/2008 ዓ.ም

የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ምስረታ ጉባኤ ዛሬ በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮምሽን አዳራሽ የተካሄደ ሲሆን የምክር ቤቱ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎችም አባል ሆነው ተመርጠዋል፡፡

  1. አቶ አማረ አረጋዊ - ፕሬዝዳንት
  2. ወ/ሮ መአዛ ብሩ - ም/ፕሬዝዳንት
  3. አቶ አብርሀም ገ/መድህን - ዋና ፀሐፊ
  4. አቶ መሰረት አታላይ - አባል
  5. አቶ ታምራት ሃይሌ - አባል

(ሱራፌል ዘላለም)

ጥር 03/2008 ዓ.ም

የማህበሩ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ወይዘሮ አዳነች አበበ እንዳስታወቁት በድርቁ ምክንያት ጉዳት እየደረሰባቸው ያሉ ሰዎችንና እንስሳቶችን ለመታደግ የኦሮሚያ ልማት ማህበር የራሱን ድርሻ ለመወጣት በማስብ 10 ሚሊዮን ብር ለግሷል፡፡

ማህበሩ ከአባላቱ መዋጮ ያገኘውን ገንዘብ ተጠቅሞ እርዳታ ማድረጉንና ችግሩ የመቀጥል አዝማሚያ ስላለው በተለይ ታች ድረስ ያሉ ዜጎችን ለመታደግ ያለመ ድጋፍ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

በድርቁ ምክንያት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተቸገሩ ተማሪዎችን ለማገዝ ኦልማ ከሌሎች መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ተማሪዎች የትምህርት ቤት የምግብ ፕሮግራም እንዲኖራቸው መደረጉን በተለይ በሀረርጌ ያለውን ምሳሌ በማንሳት ወይዘሮ አዳነች አብራርተዋል፡፡

የኦሮሚያ ልማት ማህበር ላለፉት 15 አመታት በክልሉ በተለያዩ የልማት እንቅስቃሴዎች በመሳተፍ ከ3 ሚሊየን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረገ ስራ የሰራ ሲሆን ለዚህም ከ115 ሚሊየን ብር የሚበልጥ ገንዘብ አውጥቷል፡፡ (እንደገና ደሳለኝ)

ታህሳስ 27/2008 ዓ.ም

ተነሺዎቹ የተገባላቸው ቃል አለመሟላቱንና የተሰሩ መሰረተ ልማቶች ደረጃቸውን የጠበቁ አይደሉም በሚል ነው ቅሬቸውን ያቀረቡት፡፡

የኢትዮጵያ ቱሪዝም ዘላቂ ልማት ፕሮጀክት እያከናወነ በነበረው የልማት እንቅስቃሴ ላይ ቅሬታቸውን ያቀረቡ ነዋሪዎችን ጉዳይ በተመለከተ ያነጋገርናቸው የፌዴራል ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ደስታና የፌዴራል ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ በዛሬው ዕለት በስፍራው ተገኝተው ውይይት በማድረግ መፍትሄ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡ (መስታወት ተፈራ)

ታህሳስ 26/2008 ዓ.ም

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሽ በሚከናወነው ስነ-ስርዓት ላይ  ምስረታው እንደሚካሄድ የምክር ቤቱ አደራጅ ኮሚቴ ገልጧል፡፡ በሀገሪቱ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሀን በታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ የስነ-ምግባር ደንብ ለመገዛት፣ ለሚያገለግሉት ህዝብ ተጠያቂ ለመሆን ቃል የሚገቡበት እንደሆነ የኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ ሚሚ ስብሀቱ ተናግረዋል፡፡

አቶ አማረ አረጋዊ የምክር ቤቱ አደራጅ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ በበኩላቸው የምክር ቤቱ መመስረት በሚዲያና በህዝቡ መካከል ጠንካራ ግንኙነት መፍጠር ከማስቻሉ በተጨማሪ አቤቱታና ቅሬታ በማስተናገድ ወደ ፍርድ ቤት የሚደረገውን አካሄድ እና እንግልት እንደሚቀንሰው አስረድተዋል፡፡ (ሱራፌል ዘላለም)

ታህሳስ 20/2008 ዓ.ም

የፌዴራል የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በደረሰው ጥቆማ መሰረት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሰራተኛ የሆኑት ግለሰብ የስራ ሃላፊነታቸውን በመጠቀም ታህሳስ 19 ቀን 2008 ዓ.ም ከአንድ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ መያዙን ገልጧል፡፡

ተጠርጣሪው በአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋሙ ብልሹ አሰራር ላይ ያተኮረ ዶክመንተሪ ፕሮግራም ሰርቻለሁ፤ ለህዝብ እንዳይተላለፍ ከፈለጋችሁ 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) ክፈሉኝ ብለው በማግባባት እና በቅድሚያ 2,000.00 (ሁለት ሺ) ብር ሲቀበሉ ኮሚሽኑ በደረሰው ጥቆማ መሰረት እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተገልጧል፡፡

በአሁኑ ወቅት ኮሚሽኑ በተጠርጣሪው ላይ ተጨማሪ ምርመራዎችን አካሂዶ ክስ ለመመስረት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ በላከው መግለጫ አሳውቋል፡፡

ዛሚ 90.7 ኤፍ ኤምም ጉዳዩን አጣርቶ የደረሰበትን የሚያሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ታህሳስ 11/2008 ዓ.ም

በላስታ ላሊበላ ከተማ ገጠርጌ መንደር ውስጥ ታህሳስ 9 ከሌሊቱ 7፡30 ሰዓት ላይ እድሜያቸው በግምት ከ40 ዓመት በላይ የሆናቸው እናት እና አባት፣ የ11 ዓመት ልጃቸው፣ 15 ዓመት እድሜ ያላት የዘመድ ልጅ እና እድሜው ያልተገለፀ አንድ ወጣት እንቅልፍ ላይ እንዳሉ በድንገተኛ አደጋ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል፡፡ የአደጋው መንስኤ ከመኖሪያ ቤቱ በላይ ያለው የአንድ ሆቴል የድንጋይ ካብ በመፍረሱና መሬቱ ተደርምሶ በቤቱ ላይ በመጫኑ እንደሆነ የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ፅ/ቤት ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አወቀ ፋንታው ለዛሚ 90.7 ኤፍ ኤም ገልፀዋል፡፡

በወቅቱ ከሟቾች መኖሪያ ቤት ጋር ተያይዞ በተሰራው የሳር ቤት ውስጥ ተከራይተው ይኖሩ የነበሩ ሁለት ተማሪዎች በመትረፋቸው ባሰሙት ጩኸት ፖሊስና የአካባቢው ነዋሪ በስፍራው መድረስ ችለዋል፡፡

ከአደጋው ስፍራ አስከሬኖቹን ለማውጣት ከሌሊቱ 7፡50 ላይ የተጀመረው ቁፋሮ ማለዳ 1፡30 የተጠናቀቀ ሲሆን አምስቱንም አስከሬን ማውጣት መቻሉን ዋና ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል፡፡ (ነጋሽ በዳዳ)

ህዳር 30/2008 ዓ.ም

ኢትዮ ቴሌኮም በላከው መግለጫ መሰረት በሞሪሽየስ በተካሄደው 5ኛው የአፍሪካ ቴሌኮም ሊደርሺፕ ሽልማት ሥነ-ስርዓት ላይ በአራት ዘርፎች አሸናፊ በመሆን ተሸላሚ ሆኗል፡፡ ሽልማቱን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አንዷለም አድማሴ በትናንትናው ዕለት በሞሪሽየስ በተካሄደው ጉባኤ ላይ ተገኝተው ተቀብለዋል፡፡

ድርጅቱ ተሸላሚ የሆነባቸው አራት ዘርፎች፡ የዓመቱ ምርጥ የቴሌኮም ኦፕሬተር፣ የዓመቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ የዓመቱ ምርጥ የሰው ሃይል ተኮር ዋና ስራ አስፈጻሚ እና ዓለም አቀፍ ቀጣይነት ያለው ስራ አመራር የተገበረ ተቋም በሚሉት መሆኑን ገልጿል፡፡

ህዳር 23/2008 ዓ.ም

ማንኛውም የማህበራዊ ጤና መድህን ስርዓት ተጠቃሚ ከጤና መድህን ኤጀንሲ ጋር ውል ገብቶ ውስን መዋጮ እየከፈለ ጤና ላይ እክል ሲገጥም በአቅራቢያው የጤና ተቋም ሂዶ ተገቢውን የጤና መድህን ሽፋን አግኝቶ ህክምናውን ማከናወን እንዲችል በአዋጅ የተደነገገለት ሲሆን ለቅንጦት እና ውበትን ለማሻሻል ታስቦ ለሚደረጉ የጤና አገልግሎቶች ግን ምንም አይነት የጤና መድህን ሽፋን እንደማይሰጥ ታውቋል፡፡

የተመላላሽ ህክምና፣ የተኝቶ ህክምና፣ የወሊድ አገልግሎትና የቀዶ ጥገና ህክምና፤ ብሎም በህክምና ባለሞያዎች የታዘዙ የምርመራ አገልግሎቶች በአዋጅ የተደነገጉና በኤጀንሲው የመድህን ጥላ ስር የተካተቱ የጤና አገልግሎቶች ሲሆኑ ማንኛውም ዜጋ ከኤጀንሲው ጋር በገባው ውል አማካኝነት አገልግሎቱን ማግኘት የሚችል መሆኑ በአዋጅ ተደንግጓል፡፡

የማህበራዊ ጤና መድህን ስርዓት ተጠቃሚው ከነቤተሰቡ በጤና ተቋማት አገልግሎት በሚፈልግበት ወቅት ከኪሱ የሚከፍለውን የበዛ ወጭ በመቀነስ ጥራት ያለውና ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋን ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲያገኝ የሚያስችል ዋነኛ ዓላማ ይዞ ተመስርቷል፡፡ (ያልፋል አሻግር)

ህዳር 22/2008 ዓ.ም

በአንዲት ሀገር ዜጎች ላይ በዋነኛነት የልደት፣ የጋብቻ፣ የፍቺ እና የሞት ክስተቶችን በቀጣይነት በቋሚነት እና በአስገዳጅነት የመመዝገብና የማከማቸት ተግባራት በውስጡ የሚገኘው የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስርዓት ለሀገሪቱ ከሚሰጠው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች አንዱ በተሟላ መረጃ ላይ የተመሰረተ የጤና አገልግሎትን ለመስጠት አመላካች መሆኑ ይጠቀሳል ተብሏል፡፡

ህፃናት ከወሊድ ጀምሮ እድገታቸውን የተከተለ የክትባትና እና ሌሎች የጤና ክትትሎችን ለማድረግ፣ ለህፃናት የበሽታ መከላከልና የጤና እንክብካቤ አገልግሎት ለመስጠት ከማስቻሉ ባለፈ ከወሊድ በኋላ ለእናትየው እና ለህፃኑ የተቀናጀ የጤና አገልግሎት በአግባቡ ለመስጠትም  አጋዥ ነው ተብሏል፡፡

ህብረተሰቡ በአግባቡ የወሳኝ ኩነቶች አመዘጋገብ ሂደት ውስጥ ከገባ ጠቀሜታው ከዚህም በላይ ይሆናል የተባለ ሲሆን በተለይም በሀገሪቱ አሁን ላይ የተስፋፋው እና ብዙሃኑን ሰው ለሞት የዳረገው በሽታ የቱ ነው የሚለውን ለመለየት በቀጣይም የሚከሰተውን የሞት መጠን እና በበሽታ የመጠቃት እድል ለመቀነስ የመፍትሄ አማራጭም ጭምር ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

በጤናው ዘርፍ ከታችኛው የገጠር ክፍል እስከ ዋና ዋና ከተሞች ድረስ የተሻለ እና ለውጥ አምጭ ስራዎችንም ለመከወን ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ሚና የላቀ ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡ (ያልፋል አሻግር)

ህዳር 22/2008 ዓ.ም

በመላው የሀገሪቱ ክልሎች ቅርንጫፍና ቢሮዎችን በመክፈት የጤና መድህን ስርዓትን ለመዘርጋት እየተሰራ ቢሆንም በአንዳንድ ክልሎች እና የክልል ከተሞች ግን ባጋጠሙ ውስን ችግሮች ምክንያት ቢሮዎች አልተደራጁም ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ጤና መድህን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አታክልቲ አብርሃ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክልሎች ቢሮዎቻችንን ከፍተን አደራጅተናል፤ ወደ ስራም ተገብቶባቸዋል ያሉ ሲሆን በአራት ክልሎችና የክልል ከተሞች ላይ ግን መጠነኛ ችግር ስለገጠመን ቢሮዎቹን ማደራጀት እና መክፈት አልተቻለንም ብለዋል፡፡ አፋር፣ ጋምቤላ፣ ጅግጅጋ እንዲሁም ቀብሪድሃር ቢሮዎችን ለማደራጀት ያልተቻለባቸው ክልሎችና ከተሞች ሲሆኑ ይህ የሆነበት ዋነኛ ምክንያትም የሰው ሃይል እጥረት ነው ሲሉ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

በጅግጅጋ አሁን ላይ 50 በመቶ በላይ ችግሩን ሊፈታ የሚችል የሰው ሃይል አግኝተናል ያሉት አቶ አታክልቲ ለሌሎች ቅርንጫፎቻችን የሰው ሃይል ፍለጋ ላይ ነን፡፡ በቶሎ መፍትሄውን በማምጣት ቢሮዎቹ በተገቢው መልኩ እንዲደራጅና ለህዝቡ አገልግሎቱን እንዲሰጡ እናደርጋለንም ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ጤና መድህን ኤጀንሲ የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ መስተዳድሮቻችንን ጨምሮ በጥቅሉ 20 ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በክልሎች ከፍቷል፡፡ (ያልፋል አሻግር)