Super User

Super User

Email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

መስከረም 22/2007 ዓ.ም

የከተማው ህዝብ ባለፈው እሁድ የጀመረውን የተቃውሞ ሰልፍ እንዲያበቃ የከተማው አስተዳደርና የቻይና ማዕከላዊ መንግሥት ቢጠይቁም ሰልፉ አለመቋረጡን ተናግረዋል፡፡ የፀጥታ አስከባሪዎች አስለቃሽ ጋዝ በመጠቀም ሰልፈኛውን ለመበተን ያደረጉት ጥረት እንዳልተሳካም መረጃዎች አመላክተዋል፡፡ የሰልፈኞቹ መልዕክት በሀገሪቱ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን የሆንግ ኮንግ  ዋና አስተዳዳሪ በነፃነት መምረጥ በሚችሉበት ዙሪያ እንደሆነም ታውቋል፡፡ ምንም እንኳን ሰልፈኞችን ለመበተን የተለያዩ ጥረቶች ቢደረጉም የተቃውሞ ሰልፍ አስተባባሪዎች እንዳሉት የሆንግ ኮንግ ዝናባማና ነፋሻማ አየርን በመቋቋም በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች የከተማይቱ አደባባይ ላይ ተገኝተዋል፡፡ ሰልፉ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ስልጣን ከያዘበት 65 ዓመት ክብረ በዓል ጋር መገጣጠሙን ሮይተርስ ነው የዘገበው፡፡

መስከረም 22/2007 ዓ.ም

ሰሞኑን ሲካሄድ በነበረው የአፍሪካ ሆቴሎች ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ መግለጫውን የሰጠው የማሪዮት አለም አቀፍ ሆቴሎች ኩባንያ የመካካለኛው ምስራቅ ዋና ሀላፊ አሌክስ ካሪኪድስ እንደገለጹት አፍሪካ በፍጥነት እያደገች ያለች አህጉር እንደመሆኗ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፡፡

በአፍሪካ እ.ኤ.አ አስከ 2050 ድረስ 18 ሆቴሎች እንደሚኖሯቸውም ገልፀዋል፡፡ (እንደገና ደሳለኝ)

መስከረም 22/2007 ዓ.ም

ከ100 በላይ የሚሆኑና ቀድመው በውጊያ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ወታደሮች በዚሁ በገጠማቸው ረሀብ ምክንያት ህይወታቸውን እያጡ ነው፤ ቤተሰቦቻቸውም ተመሳሳዩ እጣ ደርሷቸዋል፡፡

የሂውማን ራይትስ ዎች ሪፖርት እንዳመላከተው ባለፈው ዓመት በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሰሜን ምዕራብ ክፍል በሚገኘው ብዙ ትኩረት በማይሰጠው ካምፕ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርገዋል፡፡ ይህም የተደረገው እጅ መስጠታቸውን ተከትሎ ነው፡፡

የሚላክላቸው ምግብ ሊዳረስ የሚችል አይደለም የተባለ ሲሆን የጤና አገልግሎቱንም በበቂ ሁኔታ ማግኘት አልቻሉም፡፡ አንዳንዶቹም በአካባቢው ካሉ ገበሬዎች እህል መስረቅ ጀምረዋል፡፡ የሀገሪቱ ወታደራዊ ሃይል ጉዳዩን አጣራዋለሁ ያለ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ ተጠይቋል፡፡ ዜናው የቢቢሲ ነው፡፡

መስከረም 21/2007 ዓ.ም

በደሴ ከተማ በጢጣ አካባቢ የተከናወነው የ47 ሺ ሔክታር መሬት የካርታ ርክክብ በመከላከያ ሚኒስቴርና በክልሉ መንግሥት ሲሆን ቦታው ቀደም ሲል ለመካለከያ ሰራዊት በካምፕነት ያገለግል የነበረ ቦታ ነው፡፡ 700 አልጋዎችን የሚይዝ የሆስፒታል ህንፃ የሚገነባ ሲሆን ከህክምናውም ባሻገር በሆስፒታሉ የህክምና ትምህርት እንደሚሰጥበትም ታውቋል፡፡ ሆስፒታሉ ለድንገተኛ ህሙማን አገልግሎት የሚሰጡ የሄሊኮፕተር ማሳረፊያ ግንባታም ይካሄዳል ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል ሂሌኮፕተርን እንደሚሰራ የመከላከያ ሚኒስቴር ቃል መግባቱን በርክክቡ ታውቋል፡፡ (ቴድሮስ ብርሀኑ)

መስከረም 21/2007 ዓ.ም

በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ በተለይም አርሶ አደሮች የደረሱ ሰብሎች ቀድመው በመሰብሰብ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

በመጪው የበጋ ወቅት የዝናብ ተጠቃሚ የደቡብና የደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች የተሻለ ዝናብ ሊኖራቸው እንደሚችል የብሔራዊ የሜትሮሎጂ ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡ ያለፈው ክረምት ወቅት ዝናብ በመላው ሀገሪቱ ላይ ለግብርናው ስራ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ እንዲሁም ለውሃ ነክ አገልግሎቶች ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደነበረውም ተነግሯል፡፡ ይሁን እንጂ የክረምቱ ዝናብ አጀማመሩ መልካም ቢሆንም በለይም በስምጥ ሸለቆ በምስራቅ ሸዋ አርሲና ሀረርጌ በሰኔና ሐምሌ ወር ከባድ ዝናብና ጎርፍ መከሰቱን የገለፁት የብሔራዊ ሚትዮሮሎጂ ትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ድሪባ ቆርቾ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል በአሁኑ ወቅት በስፍራው የሚጠበቀው ዝናብ መጣል መቻሉ ቀድሞ ይከሰት የነበረውን ድርቅ እንዳይከሰት ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

የበጋው ወራት በደረቅነቱ የሚታወቅ ቢሆንም በመጪው የበጋ ወቅት ያለወቅቱ ሊከሰት የሚችል የዝናብ ሁኔታ ሊከሰት እንደሚችል ተገልጧል፡፡ በተለይም በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ አርሶ አደሮች የደረሱ ሰብሎችን ቀድሞ በመሰብሰብ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ዶ/ር ድሪባ ቆርቾ ተናግረዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በቆላማ አካባቢዎች በሰሜን ምስራቅ፣ በስምጥ ሸለቆ፣ በደቡብና ደቡብ ምስራቅ፣ በኦሮሚያና በሶማሊያ አጋማሽ ክልሎችና ቦታዎች ላይ ሰብሎች ቀድመው የሚሰበሰብ መሆናቸውን ለሁለተኛ ጊዜ የዝናብን መምጣት የሚጠባበቁ በመሆናቸው በበጋው ወቅት ይከሰታል ተብሎ የሚጠበቀው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ለግጦሽ ሳር፣ ለውሃ መከማቸት እና ለከብቶ መኖነትን ጨምሮ በረሃማ ለሆኑ አካባቢዎች የአየር ንብረቱን በማስተካከል ጠቃሚ እንደሚሆን ተገልጧል፡፡ (ነጋሽ በዳዳ)

መስከረም 20/2007 ዓ.ም

የአዲስ አበባ እግርኳስ ማህበር በየአመቱ የሚያካሂደው የከተማ ዋንጫ ዘንድሮ ካስትል ካፕ ተብሎ ነው የሚካሄደው፡፡

6 የአዲስ አበባ ክለቦች፣ 2 ተጋባዥ የክልል ክለቦችን አካቶ በሁለት ምድብ ይካሄዳል፡፡ ተጋባዦቹ አዳማ ከነማ እና ዳሽን ቢራ ናቸው፡፡

ዛሬ በተከናወነው የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ቅ/ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና የምድብ አባት ሲሆኑ

በምድብ ሀ፡-

-ኢትዮጵያ ቡና

-አዳማ ከነማ

-ደደቢት እና

-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲደለደሉ

በምድብ ለ፡-

-ቅ/ጊዮርጊስ

-ዳሽን ቢራ

-መከላከያና መብራት ሀይል ተቀምጠዋል፡፡

ጫወታው መስከረም 25 እሁድ ሲጀመርም በ9፡00 ሰዓት አዳማ ከነማ ከ ደደቢት

11፡00 ሰዓት ላይ ደግሞ ኢትዮጵያ ቡና ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይጫወታሉ፡፡

ሰኞ የምድብ ሁለት ጫወታዎች ቀጥለው ሲደረጉ፡-

- 9፡00 ሰዓት ላይ ዳሽን ቢራ ከ መከላከያ

- ቅ/ጊዮርጊስ ከ መብራት ሀይል ጫወታቸውን ያደርጋሉ፡፡

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌደሬሽን በመግለጫው የስታዲየም መግቢያ ዋጋዎችንም ይፋ አድርጓል፡፡

- ክቡር ትሪቡን- 70 ብር

- ጥላ ፎቅ- 50 ብር

- ከማን አንሼ ባለወንበር- 30 ብር

- ከማን አንሼ ወንበር የሌለው- 20 ብር

- ካታንጋ- 10 ብር

-ሚስማር ተራ- 5 ብር ሆኗል፡፡ (አርያት ራያ)

መስከረም 20/2007 ዓ.ም

የወሎ ተሪሼሪ ኬር እና ማስተባበሪያ ሆስፒታል በሀገራችን ታክመን በሀገራች እንዳን በሚል መርህ በአይነቱ ልዩና የመጀመሪያው የሆነ አለም አቀፍ ሆስፒታል በደሴ ጢጣ በሚባል አካባቢ ሊገነባ በዝግጅት ላይ መሆኑ ከዚህ ቀድ የተገለፀ ሲሆን በዚህም መሰረት በትናንትናው እለት በደሴ ከተማ የሚዲያና የኪነጥበብ ባለሙያዎችን እና የክልሉ ተወላጆችን ያቀፈ የገቢ ማሰባሰቢያ ቅስቀሳ ተካሂዷል፡፡

ይህ 1.5 ቢሊዮን ብር የሚፈጀው ሆስፒታልን እውን ለማድረግ ነው የገቢ ማሰባሰቢያ ቅስቀሳ የተጀመረው፡፡ በተጨማሪም በትናንትናው እለት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የፓናል ውይይት ተደርጓል፡፡ በፓናል ውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሆስፒታሉ የግንባታ ፕሮጀክት ሀላፊ አቶ እሸቱ አየለ ናቸው፡፡ የግንባታው አላማም ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ ታክሞ ለመዳን  ገንዘብ ለማሰባሰብ በየጎዳናው የወጡ ወገኖችን ለመርዳትና የሚያጋጥመውን ውጣውረድ ለማስቀረት ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ጋር በጋራ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የደሴ ከተማ ከንቲባ የሆኑት አቶ አለባቸው የሱፍ በበኩላቸው የተጀመረውን የልማት እንቅስቃሴ ለማጠናከር የጤና ዘርፉ ላይ ማተኮር መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ (ቴድሮሰ ብርሀኑ)

መስከረም 20/2007 ዓ.ም

በትናንትናው እለት በአዳማ ከተማ በራስ ሆቴል አዳራሽ የአ/አ እና የመቀሌ ዩንቨርስቲ ምሁራን እና  የኢትዮጲያ እንባ ጠባቂ ተቋም የተሳተፉበት ግምገማ ተካሂዷል፡፡ ግምገማውም ምቹ የሆነ ለአንደኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስተማሪያነት በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ሲሆን ሰነዱ ላይም ማሻሻያ ሀሳቦች ከተሳታፊዎች ቀርበዋል ፡፡

የግምገማውን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስተር ዴታ አቶ ፉአድ ኢብራሂም ናቸው፡፡ ይህ ግምገማ ዛሬም እንደሚቀጥል ለዛሚ 90.7 ኤፍ ኤም የገለጹት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የሕጻናትና የሴቶች ጉዳይ ኮሚሽን ኮሚሽነር ወይዘሮ አስማሩ በሪሁን ናቸው፡፡ (ታሪክ አዱኛ)

መስከረም 20/2007 ዓ.ም

ባለፈው ሳምንት በሀገር ውስጥ ታጣቂዎች በፈረንሳዩ ቱሪስት ላይ የተደረገው አፈና እና ግድያ ከአይ ኤስ ጋር የተያያዘ ነው ተብሏል፡፡

ይህም የሰሜን አፍሪካ ሀገራትን ያሰጋ ሲሆን የቱሪዝም ኢንዱስትሪውም ተቀዛቅዟል፡፡

በአልጄሪያ ደቡብ ክፍል ያሉት በርካታ የቱሪዝም ኤጀንሲዎች ባቀረቡት ሪፖርት መሰረት በርካታ ጎብኚዎች ወደ ሰሀራ በረሀ ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞ ሰርዘዋል፡፡ ኤጀንሲዎቹ ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ለውጥ ማምጣት የሚችለውን ቱሪዝምን ለማጠናከር ሀገሪቱ ምቹና ሰላማዊ መሆኗ በስፋት ሊቀሰቀስ ይገባል እያሉ ነው፡፡

የ55 ዓመቱ ፈረንሳያዊ ጎብኚ ጉዳይ ግን በእቅዱ ላይ ከፍተኛ የሆነ እንቅፋት ሆኗል፡፡

አልጄሪያ መሰል ተግባራትን ለመከላከል ተጨማሪ ወታደራዊ ሀይል ያሰማራች ሲሆን ቱሪስቶችም መረጃዎችን አሟልተው የሚገኙበትና እነርሱም በግልፅ ያሉበትን ሁኔታ የሚናሩበት መንገድ ምቹ ሆኗል፡፡ ዜናው የኦል አፍሪካ ነው፡፡

መስከረም 20/2007 ዓ.ም

ይህንን ያሉት የትግራይ ባህልና ቱሪዝም ዋና  ስራ አስኪያጅ አቶ ከበደ አማረ  ሲሆኑ በተለይም የክልሉ ባህላዊ እሴት ተጠብቆ ለትውልድ አንዲተላለፍና ለጎበኚ ምቹ አንዲሆን የተለያዩ አማራጮችን ተጠቅመን አየሰራን ነው ብለዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የመቀሌ ቤተመንግስት ለቱሪስት ምቹ እንድሆን ለማስቻል በቅርብ ጊዜ ውስጥ ስራ ለመጀመር እቅድ ይዘናል ማለታቸውን ባልደረባችን ያልፋል አሻግር ዘግቧል፡፡ (ያልፋል አሻግር)