Super User

Super User

Email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

መስከረም 04/2007 ዓ.ም

በ2006 ዓ.ም አገር አቀፍ ፈተና ወስደው አስረኛ ክፍልን ያጠናቀቁ ተማሪዎች 60 በመቶ ወደ መንግሥት 40 በመቶ ደግሞ ወደግል ተቋማት እንደሚገቡ ተገልጧል፡፡

ወደ ቴክኒክና ሙያ የመግቢያ ነጥብ ያመጡ እንደየ ደረጃቸው ለወንድ 1.8 እና ከዚያ በታች፣ ለሴት 1.57 እና ከዚያ በታች፣ ለአካል ጉዳተኞች 1.29 እና ከዚያ በታች፣ በደረጃ 2 ለወንድ ከ2.0-2.14፣ ለሴት 1.71፣ ለአካል ጉዳተኞች 1.29፣ በደረጃ ሶስት ለወንድ 2.29፣ ለሴት 1.86፣ ለአካል ጉዳተኞች 1.57፣ በደረጃ አራት ለወንድ 2.43፣ ለሴት 2.0፣ ለአካል ጉዳተኞች 1.5 እና ከዚያ በላይ መሆኑ ታውቋል፡፡ የመግቢያ ነጥብ የሴቶችን ተሳትፎ 50 በመቶ ለማድረስ የታቀደ ሲሆን ለአካል ጉዳተኞችና ሰልጣኞች ልዩ ትኩረት መሰጠቱንና  ገበያውን መሰረት ያደረገና ምርታማነትን ለመጠበቅ እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ የስራ ሂደት መሪ አቶ ሚካኤል ተስፋዬ ለዛሚ 90.7 ገልፀዋል፡፡ 

IMG 0668

ጥቅምት 03/2007 ዓ.ም

በኦሮሚያ ክልል ቢቢኤቾ ወረዳ በ6 ሚሊዮን ሄክታር በተዘራው የስንዴ እና የጤፍ ምርት ላይ የፀረ አረም መድኃኒት በመጠቀም አረሙን ማስወገድ መቻላቸውን አርሶ አደሮች ገለፀዋል፡፡

በ2006 ዓ.ም በወርሃ ሃምሌ የተዘራ የጤፍና የስንዴ ምርት ላይ ፓላስ ፀረ አረም መድኃኒት በመጠቀማቸው በምርታቸው ላይ ይበቅል የነበረው አረም መጥፋቱን ለዛሚ 90.7 ኤፍ ፍም የገለፁት የቢኤቾ ወረዳ አርሶ አደር ወ/ሮ ጆርጌ ናኒሳ ናቸው፡፡

በክልሉ በእያንዳንዱ ቀበሌ ከ3 በላይ የግብርና ኤክስቴንሽን ባለሞያዎች ተመድበው አርሶ አደሩ ማዳበሪያ እንዲጠቀምና በመስመር እንዲዘራ መደረጉን የገለፁት የኦሮሚያ ክልል በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ዘላለም ጀማነህ ናቸው፡፡

በአቅም ማነስ ምክንያት ማዳበሪያ መጠቀም ላልቻሉ 700ሺ በክልሉ ለሚገኙ አርሶ አደሮች ከያካባቢያቸው ማይክሮ ፋይናንስ ብድር እንዲያገኙ እና ማዳበሪያ እንዲጠቀሙ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ (ታሪክ አዱኛ)

ጥቅምት 03/2007 ዓ.ም

በደቡባዊ ቱርክ ያለውን ቦታ ቱርክ መፍቀዷን ሱዛን ራይዝ አድንቀዋል፡፡ ቱርክ IS የሚገኝባቸው የሶሪያ እና የኢራቅ ድንበሮችን ታጋራለች፡፡

በቱርክ ድንበር አቅራቢያ በIS እና በኩርድ ሃይሎች እየተደረገ ያለው ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን ዘገባዎች አመላክተዋል፡፡

በኮባኒ እየተደረገ ባለው ጦርነት 200,000 የሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ድንበር አቋርጠው ወደ ቱርክ ተሰደዋል፡፡ ዜናው የቢቢሲ ነው፡፡

ጥቅምት 03/2007 ዓ.ም

በበዓሉ ላይ የኤፌዴሪ ፕሬዝዳን ዶ/ር ሙላቱ ተሾመን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ከአስሩም ክ/ከተማ የመጡ ተማሪዎችና ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፤ የመከላከያ ሰራዊትና የፖሊስ አባላት በበዓሉ ስፍራ በመገኘት በወታደራዊ ስርዓት ተሳትፈዋል፤ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትር የሰለጠኑ ከ400 በላይ ወጣቶች ለታዳሚው ትርዒት አቅርበዋል፡፡ በመጨሻም የቃል-ኪዳን ስነ-ስርዓትበማካሄድ  የሰንደቅ ዓላማ መስቀል ስነ-ስርዓት በማድረግ የበዓሉ ፍፃሜ ሆኗል፡፡ (ሱራፌል ዘላለም)

መስከረም 30/2007 ዓ.ም

ሀገራችን ኢትዮጵያ የተለያየ ባህል፣ ወግና ታሪክ ያላቸው በርካታ ብሔረሰቦች በሺዎች የሚቆጠሩ ዓመታትን በአንድነት የኖሩባትና እየኖሩባት የምትገኝ ሀገር ናት፡፡ ታዲያ እነዚህ ብሄረሰቦች ለዘመናት የየራሳቸው ባህላዊ አልባሳት፣ የመመገቢያ ቁሳቁስ፣ የሙዚቃ መሳሪያ፣ ጌጣጌጥና መሰል ባህላዊ ቁሶች ነበሯቸው፡፡ የዘርፉ ሙያተኞች እነዚህ የባህል መገለጫ የሆኑ ቁሳቁሶችን ‹‹ኢትኖግራፊክ ቅርሶች›› ብለው ይጠሯቸዋል፡፡

አሁን አሁን ዘመናዊነት እየፈጠረው ባለው ለውጥ ምክንያት እነዚህን ቅርሶች ማግኘት አዳጋች እየሆነ መምጣቱን በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን የኢትኖግራፊክ ቅርሶች ከፍተኛ ባለሞያ ወ/ሮ እንዳሻሽ አባተ ይገልፃሉ፡፡

እንደ ባለሞያዋ ገለፃ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን በ5 ዓመት ውስጥ የሀገሪቱን ኢትኖግራፊክ ቅርሶች ለመሰብሰብ አቅዶ የነበረ ቢሆንም ባለፉት 4 ዓመት ውስጥ ያከናወነው 40 በመቶ ብቻ ነው፡፡ ለዚህ እንደዋነኛ ምክንያት የተጠቀሰው ደግሞ በሀገሪቱ ያለው የኢትኖግራፊክ ቅርስ ከተገመተው በላይ ሰፊ ሆኖ በመገኘቱና ባለስልጣኑም በቂ የሰው ሃይልና አቅም ስላልነበረው መሆኑን ወ/ሮ እንዳሻሽ አብራርተዋል፡፡ በቀሪው አንድ ዓመትም ባለስልጣኑ ቅርሶቹን በስፋት መሰብሰብ እንዲችል ከክልሎች ጋር ተባብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

ቅርሶቹ ከመጥፋታቸው በፊት ከያሉበት አሰባስቦ በማዕከል በማስቀመጥ ለታሪክና ለባህል ጥናት፣ ለጎብኝዎችና ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ አስፈላጊ መሆኑም ተገልጧል፡፡ (እንደገና ደሳለኝ)

መስከረም 30/2007 ዓ.ም

42 የሚጠጉት ስደተኞች በአምስት የቤተሰብ አባላት የተከፈሉ እንደሆነም ታውቋል፡፡ ከሊባኖስ የመጡትን ስደተኞች የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጆሴ ሙኪካኦ ተቀብለውም አነጋግረዋል፡፡ ስደተኞቹ ለሁለት ወራት ያህል በሚኖራቸው ቆይታ ሙሉ ወጪዎቻቸው ተችሎ ከኡራጓይ ዋና ከተማ በቅርበት በምትገኘው ሞንቴቪዲዮ የስፓኒሽ ቋንቋ እና የሀገሪቱን ባህል እንደሚማሩም ተነግሯል፡፡ ኡራጓይ የተቀበለቻቸውን ስደተኖች ለስራ ብቁ የሆኑትን ወደ ስራ ለማስገባት እና ህፃናቱን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ ማቀዷ የታወቀ ሲሆን ለዚህም የሁለት ዓመት ወጪው ሶስት ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንደምታወጣ ተገልጧል፡፡ ከሶሪያ የሚመጡ ስደተኞችን የደቡብ አሜሪካ ሀገራት እየተቀበሉ ቢገኙም ኡራጓይ ግን የስደተኞቹን ወጪ በመሸፈን በቀበሏ የመጀመሪያ ሀገር አድርጓታል፡፡ ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡

መስከረም 30/2007 ዓ.ም

በ2007 ዓ.ም የሚካሄደውን አጠቃላይ ምርጫ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመሆን ለተወዳዳሪ ፓርቲዎች ፕሮግራሞቻቸውንና ዓላማቸውን ለህብረተሰቡ የሚያስተዋውቁበት ነፃ የአየር ጊዜና የጋዜጣ አምድ እንደሚደለደል ገልጧል፡፡ በተጨማሪም የአፈፃፀም መመሪያዎችን ተግባራዊ እንደሚያደረግ ለዛሚ 90.7 ኤፍ ኤም የገለፁት የባለስልጣን መ/ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ ሃላፊ አቶ ወርቅነህ ጣፋ ናቸው፡፡

ምርጫው ሰላማዊና ፍትሃዊ እንዲሆን የበኩላቸውን ሚና እንደሚጫወቱ ተናግረዋል፡፡ በመገናኛ ብዙሃን የሚዘገቡ የምርጫ አዘጋገቦችን እንደሚቆጣጠሩም ገልፀዋል፡፡ (ታሪክ አዱኛ)

መስከረም 29/2007 ዓ.ም

ይህ የተገለፀው 140ኛ የዓለም የፖስታ ቀን በዛሬው ዕለት በተከበረበት ወቅት ነው፡፡ በዓሉም በ150 የህብረቱ አባል ሀገራት እየተከበረ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ግደይ ገ/ዮሃንስ በተወካያቸው በአቶ በዛብህ አስፋው በኩል ባስተላለፉት መልዕክት፤ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዓመታት ‹‹ፖስታ ቤት ቀይ መብራት የበራበት›› ከተባለበት አስጊ ሁኔታ በአጭር ጊዜ ውስጥ በመውጣት በሰራተኛው ብርቱ ትጋትና በባለድርሻ አካላት የነቃ ተሳትፎ አስተማማኝ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

ድርጅቱ በአሁኑ ወቅትም 746 ቋሚ ፖስታ ቤቶች እና ወኪል መደበኛ ፖስታ ቤቶችን ጭምሮ በአጠቃላይ በ1,240 አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ስራውን እያከናወነ ይገኛል፡፡

(ሱራፌል ዘላለም)

መስከረም 29/2007 ዓ.ም

ከሚያዝያ አጋማሽ እስከ ማክሰኞ በነበረው ጊዜ ህይወታቸውን ካጡት 3,660 በተጨማሪ 8,756 የሚሆኑት ሰዎች በምስራቅ ዩክሬን ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ቢሮ በትላንትናው ዕለት ባወጣው ወርሃዊ ሪፖርት ነው ጉዳዩን ያስታወቀው፡፡

በአማፂያኑ እና በዩክሬን መንግሥት መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረገ በኋላም ቢሆን ቀውሱ የተረጋጋ ቢመስልም ግጭቶች ነበሩ ያለው ሪፖርቱ ሰዎች በዚሁ ቀውስ ሂወታቸውን እንዳጡ አትቷል፡፡ ዘገባው የYahoo News ነው፡፡ 

መስከረም 29/2007 ዓ.ም

የማሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብሉላዬ ዲዮብ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት በቅርቡ በተ.መ.ድ ሰላም አስከባሪዎች ላይ የተፈፀመውን ግድያ ተከትሎ አፋጣኝ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ተወስኗል፡፡

በታጣቂዎቹ ቀደም ባለው ጊዜ ከኒጀር የመጡ 9 ሰላም አስከባሪዎች ተገድለው የነበረ ሲሆን ማክሰኞ እለት ደግሞ አንድ ሴኔጋላዊ ሰላም አስከባሪ ህይወቱን አጥቷል፡፡

የተ.መ.ድ ሰላም ማስከበር ቡድን ሃላፊ እንዳሉት በማሊ ያለው ወታደራዊ ሃይል የፈረንሳይ ወታደሮች በመልቀቃቸው የተፈጠረውን ክፍተት መሸፈን አልቻለም፡፡

ምንጮች እንዳመለከቱት እስካሁን እ.ኤ.አ በ2013 ተልዕኮውን ለማስፈፀም ወታደሮች ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ 31 ሰላም አስከባሪዎች ሞተዋል፤ 91 የሚሆኑት ቆስለዋል፡፡ ዘገባው የBBC ነው፡፡