Super User

Super User

Email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

የሲዳማ ፍቼ ጨምበላላ የዘመን መለወጫ በዓል በሀዋሳ ከተማ በሲዳማ ባህል አዳራሽ 500ሺህ ሰዎች በተገኙበት ዛሬ እየተከበረ ነው፡፡
አከባበሩ የጀመረው ዛሬ ከሰአት በኋላ ሲሆን በአሉ ለቀጣይ ሁለት ቀናት መከበሩን ይቀጥላል፡፡
የብሔሩ ተወላጆች የዘመን መለወጫ በዓላቸውን ከ1983 አመተምህረት ጀምሮ በደማቅ ሁኔታ በሀዋሳ በመሰብሰብ ባህሉን መሰረት ባደረገ ሁኔታ በማክበር ላይ ይገኛሉ፡፡
ፍቼ ጨምበላላ ባለፈው አመት ህዳር ወር ላይ በተደረገው የዩኔስኮ አመታዊ ስብሰባ ላይ በአለም አቀፍ ደረጃ በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ፣ የትምህርትና የባህል ማእከል (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ቅርስነት ተመዝግቧል፡፡

እነዚህ ሁለት የጭነት አውሮፕላኖች የሚገዙት በየአመቱ በፈረንጆቹ ከሰኔ 15 እስከ 21 ድረስ ከሚካሄደው ከፓሪስ የአውሮፕላኖች ሾው ላይ ነው፡፡
የፓሪስ የአውሮፕላን ሾው የተጀመረው በ1949 ሲሆን የዘንድሮው 53ኛው ነው፡፡ በዝግጅቱ የተለያዩ አውርፕላን አምራች ድረውጅቶች እና የአየር መንገድ ሀላፊዎች ይሳተፋሉ፡፡
የኢትዩጲያ አየር መንገድ የሚያስመጣቸው የቦይንግ ቢ777 200 ኤል አር የጭነት አውሮፕላኖች በአለም በስፋት እና በርዝመት አንደኛ ነው፡፡ 4 900 ኪሎ ሜትር ሲኖረው 112 ቶን መሸከም ይችላል፡፡
የሁለቱ የጭነት አውሮፕላኖች ግዢ ከዚህ በፊት በቦይንግ የግዢ እና ማድረስ አገልግሎት ድረ ገጽ ላይ ማንነቱ ያልታወቀ ገዢ በሚል ተጠቅሶ ነበር፡፡
የኢትዩጲያ አየርመንገድ ዋና ሀላፊ ዶክተር ተወልደ ገብረማሪያም አውሮፕላኖቹ የኢትዩጲያን ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ለማሻሻል እንደሚገዙ ተናግረዋል፡፡
የጭነት ማጓጓዣ አውሮፕላኖች ከማስገባት ጎንለጎን አየርመንገዱ የካርጎ አገልግሎቱን ለማሻሻል እና ዘመናዊ ለማድረግ 150 ሚሊዩን ዶላር ኢንቨስት አድርጓል፡፡
በዚህ ወር መጨረሻ ላይ በሚያዘጋጀው በአይ ሲ ኤኮ አለም አቀፍ የአየርካርጎልማትፎረምላይም 15ሺህ ካሬሜትርላይያረፈካርጎተርሚናሉንያስመርቃል፡፡
የካርጎተርሚናሉሁለተኛክፍልሲጠናቀቅአየርመንገዱበአመት 600ሺህ ቶንማጓጓዛይችላል፡፡
ከጭነት አውሮፕላኖቹ በተጨማሪም አየርመንገዱ 10 የ7373 ማክስ 8 አውሮፕላኖቸን ለማስገባት አዟል፡፡ የእነዚህ አውሮፕላኖች ስምምነት የተጠናቀቀው በዚህአመት መስከረም ወር ላይ ነበር፡፡
ከአፍሪካ ሰላሳ የ737 ማክስ 8ኤስ አውሮፕላን ሞዴል አውሮፕላኖችን በብዛት ለማስገባት በማዘዝ ከአፍሪካ ተቀዳሚ አድርጎታል፡፡
የኢትዩጲያ አየር መንገድ በትላንትናው እለትም ለተጎዦች የሚውል 10 ኤ 350-900 ኤርክራፍት አውሮፕላኖች ለማስገባት አዟል፡፡
ባሳለፍነው በዚህ ወር 12 የዕዚህ ሞዴል አውሮፕላኖችን በማዘዝ ከአፍሪካ የመጀመሪያው አየር መንገድ ሆኖ ነበር፡፡ከእነዚህ ውስጥም በአሁን ወቅት አራቱ አገልግሎት እየሰጡ ነው፡፡

ከኢትዩጲያ አየር መንገድ ለተገኘው መረጃ ናርዶስ ዩሴፍ

ሳኡዲ አረቢያ ባለቤትነታቸዉ የ ኳታር የሆኑ ሰባት ሺህ ግመሎችና አምስት ሺኅ ያህል በጎችን ከሀገሯ አባራለች
እንስሳቶቹ በጊዜያዊ መጠለያ ምግብ እና ዉሀ እየተሰጣቸዉ እንዲቆዩ መደረጋቸዉን የኳታር ጋዜጣ የሆነዉ peninsula በትናንትናዉ እለት ገልጾ የነበረ ሲሆን al raya የተሰኘዉ ድረ ገጽ ግን የእንሰሳቶቹ ቁጥር ሃያ አምስት ሺህ መሆኑን አስነብቧል
በ ኳታር 22ሺኅ ያህል ግመሎች የሚገኙ ሲሆን ለዉድድር እንዲሁም ለምግብነት ይቀርባሉ ይሁን እንጂ እረኞቹ የግጦሽ መሬት የሚከራዩት ከ ጎረቤት ሀገር ሳኡዲ አረብያ ነዉ
ከዚህም ጋር ተያይዞ ከሪያድ በተላለፈዉ ዉሳኔ የኳታር ገበሬዎችን አበሳጭቷል
የምንፈልገዉ ግመሎቻችንን በሰላም ወደ ሀገራችን መልሰን ቤተሰባችንን መንከባከብ ነዉ በተፈጠረዉ የ ፖለቲካ ቀዉስ ዉስጥ መግባት አንፈልግም ሲሉም ገበሬዎቹ ተናግረዋል
በሳኡዲ የሚመራዉ ቡድንና በኳታር መካከል በተፈጠረዉ በዚህ አለመግባባት እነዚህ ገበሬዎች ግንባር ቀደም ተጠቂዎች ሆነዋል ።
በተጨማሪም እነዚህ ሀገራት ከኳታር ጋር የነበራቸዉን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በማቋረጥ አንባሳደሮቻቸዉን የጠሩ ሲሆን አገራቸዉ የሚገኙ የኳታር ዜጎችንም በሁለት ሳምንታት ጊዜ ዉስጥ ለቀዉ እንዲወጡ አዘዋል።

40 የመንግስት መስሪያ ቤቶች በ32 ሚሊዩን ዶላር በሚገነባ የአንድ መስኮት አገልግሎት ግንባታ ኩፒክ ከተባለ የድርጅት ሊገነባ ነው፡፡ በሁለት ምእራፍ እንዲጠናቀቅ የአራት አመት የግንባታ ጊዜ ተቀምጦለታል፡፡
ይህ ግንባታ በመጀመሪያው ምእራፍ የሚያካትታቸዉ የመንግስት መስሪያቤቶች ገቢዎች እና ጉምሩክ፣ባንኮች የኢንሹራንስድርጅቶች፣የገንዘብእናኢኮኖሚትብብርሚኒስቴር፣የግብርናሚኒስቴር፣ኢንዱስትሪሚስቴር፣ንግድሚኒስቴር እና ሌሎች ለህዝቡ በተቀዳሚነት አስፈላጊ ናቸው ተብለው የተለዩ ድርጅቶች ናቸው፡፡
በሁለተኛው ምእራፍ ደግሞ ቀሪዎቹ 20 የመንግስት ድርጅቶች ይጠቃለላሉ፡፡ በዚህ መሰረት አንድ ተጠቃሚ የ20 መንግስት መስሪያቤቶችን አገልግሎት በአንድ መስኮት ያገኛል፡፡
በአሁን ወቅት ይህ ፕሮጀክት ጨረታው ተጠናቋል፣ አጠቃላይ የሆነ እቅድም ተሰርቶለታል፡፡ በአሁን ወቅት መስሪያ ቤቶቹ የነበራቸው የአሰራር አይነት እና ወደፊትም መሆን ያለበት የግልጋሎቱ አይነት ጥናት ተደርጓል፡፡
በአጠቃላይ ደግሞ ይሀ የአንድ መስኮት አገልግሎት ሊይዛቸው የሚገቡ የጋራ ስራዎች፣ የንግድ እቅድ ተጠናቆ መዋቅሩም ተቀርጾ የትግበራ እቅድ ላይ ደርሷል፡፡

ዋርሚበር ለ 17 ወራት በሰሜን ኮሪያ ቁጥጥር ስር ውሎ ከባድ ስራ እንዲሰራ በመደረጉ ምክንያት ወደ አገሩ አሜሪካ ሲመለስ አደገኛ ሁኔታ ላይ እንደነበር ተገልፆዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ለሞት እንደተዳረገ ነው የተገለፀው፡፡

በዚህ ወጣት ሞት ምክንያት ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራፕ የተሰማቸውን ሐዘን ገልፀው ለዋርሚበር ሞት ምክንያት የሆነውን የሰሜን ኮሪያ አስተዳደር ገደብ ለማስያዝ የሚያደርጉን ጥረት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡

ከ አዲስ አበባ ወደ ደቡብ ምእራብና ጅማ መስመር የሚደረጉ የሀገር አቋራጭ አዉቶብስ ጉዞዎች ከ ሀሙስ ጀምሮ ቀድሞ የነበራቸዉ  የአዉቶብስ ተራ የመነሻ መስመር ወደ አየርጤና ተዛዉሯል።

41 ያህል የጉዞ መስመሮች የተዘጋጁ ሲሆን የተጓዦች ምዝገባም በዛዉ በአየርጤና መናኻሪያ ይከናወናል

መናኻሪያዉ የተገልጋዮችን ጊዜና እንግልት ይቆጥባል ተብሎለታል።

ከዚህ ቀደም በሀገር አቋራጭ አዉቶብሶች አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በተሰራ ጥናት መሰረት 74 በመቶ ያህል ተገልጋዮች በቂ አገልግሎት መስጫ ቦታ አለመኖሩን የጠቆሙ ሲሆን 55 በመቶ  ያህሎቹ ደግሞ መናኻሪያዎቹ ምቹ አይደሉም ብለዋል።

ዘገባው የያልፋል አሻግር

በድርጅቱ ጥገና የተሰጠባቸዉ አዉቶብሶች ከ 6 አመታት በፊት ከቢሾፍቱ አዉቶሞቲቭ ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ ከተገዙት 500 ዎቹ መካከል ናቸዉ ።

እነዚህ 370 ያህል መኪኖች ለጥገና ሲቀርቡ አገልግሎት አሰጣጡ ላይ ችግሮች አልተፈጠሩም ወይ ብለን ላነሳነዉ ጥያቄ

የድርጅቱ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ደጋፊ የስራ ሂደት መሪ አቶ ተሾመ ንጋቱ ለ ዛሚ ሲናገሩ ጥገና የተደረገላቸዉ አዉቶብሶች በብልሽት ቆመዉ ሳይሆን አገልግሎት በመስጠት ላይ እንዳሉ በወረፋ ነዉ ብለዋል።

 ሀላፊዉ አክለዉም ምንም እንኳን ድርጅቱ ባለዉ የ አዉቶብስ ቁጥር ህብረተሰቡን እያገለገልን ቢሆንም ይህ በቂ አይደለም በሚቀጥለዉ አመት ከ 700 በላይ አዉቶብሶች በከተማ አስተዳደሩ እንደሚገዙ ተወስኗል በተሻለ መልኩ አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችሉም ይጠበቃል ብለዋል።

 

 

ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ዉለዋል በጤናዉ ዘርፍ ደግሞ ከ አንድ መቶ ሀያ ስድስት ቶን በላይ እንዲሁም 8.5 ሚሊየን ብር የሚገመት መድሀኒት አገልግሎት ላይ እንዳይዉል ተደርጓል

 

በኮንትሮባንድ መድሀኒት ለሚያስገቡ ድርጅቶችም ሆነ ግለሰቦች በወንጀለኛ መቅጫ ህግ መሰረት ቅጣት ይጠብቃቸዋል

 

የቁጥጥር ዘርፉ እንደዋና ችግር ያስቀመጠዉ ከተለያዩ ጎረቤት ሀገሮች በህገወጥ መንገድ የሚገቡ መድሀኒቶች ሲሆኑ መፍትሄዉ ደግሞ ህብረተሰቡ ለራሱ ደህንነት ሲባል  በህገወጥ መንገድ የሚመጡ መድሀኒቶች መግዛት እንደሌለበት እንዲሁም መስሪያ ቤቱ ከዚህ ቀደም ከነበረዉ በተጨማሪ ቁጥጥሩን ሰፋ አድርጎ እንደሚሰራ የኢትዮጲያ የምግብ የመድሀኒት እና የጤና እንክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን መስሪያ ቤት የመድሀኒት ተቋማት ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ኢንስፔክተር እንዲሁም  ኬዝ ቲም አስተባባሪ አቶ ሳሙኤል ማሬ ለዛሚ ተናግረዋል።

 

ፍሬህይወት ታደሰ

 

 

ሰዎቹ በህይወት መትረፍ የቻሉት በአካባቢው ውሀ በመቋረጡ ምክንያት ባዶ የነበረ የውሀ ታንከር ውስጥ በመግባት ነዉ ለስድስት ሰአት ያህልም በውሀ ማጠራቀሚያው ውስጥ ቆይተዋል።በህይወት ከተረፉት ውስጥ የ95 አመት አካል ጉዳተኛ ሴት ይገኙበታል።

በውሀ ማጠራቀሚያው ውስጥ ህይወትን የማዳኑ ሀሳብ የመጣው ማሪያ ደቹ ሲልቫ የተባለች ወጣት አካል ጉዳተኛ የሆኑት እናቷን ከሞት ለመታደግ ባደረገችው ጥረት ነው አሁን ታዲያ ማሪያ በፖርቹጋል እንደ ጀግና እየታየች ትገኛለች።

የተነሳው ሰደድ እሳት አሁን በቁጥጥር ስር ዉሏል

ከማእከላዊ ፖርቹጋል በተከሰተው ሰደድ እሳት ከሞቱት ሰዎች መካከል አብዛኛዎቹ በመኪና ውስጥ እያሉ ነው ህይወታቸው ያለፈው  በአደጋዉ ምክንያት የ64 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 130 ያህል ሰዎች ለጉዳት ተዳርገዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

የኢትዮጲያ  ከሀያ አንድ ሀገራት የተውጣጡ  850000 ስደተኞች በስድስት ክልሎቿ ባስገነባቻቸው  በሀያ ሰባት ካምፖች  ከደቡብ ሱዳን  ከሶማሊያ እና  ሱዳን  የተውጣጡ ስደተኞችን ታስተናግዳለች ፡፡

ሆኖም  የስደተኞችና ከስደት ተመላሽ አስተዳደር ኢትዮጲያ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኛ መርጃ ኮሚሽን ለስደተኞች የሚሰጠው ድጋፍ  በመቀነሱ ስደተኞች በደራሽ ድጋፍ ላይ ብቻ እንዳይወሰኑ የአካባቢውን ማህበረሰብ ባማከለ መልኩ ስደተኞችን በልማት ለማስተሳሰር እየሰራች መሆኑ ተገለፀ

ስደተኞችና ከስደት ተመላሽ አስተዳደር ምክትል ዳይሬክተር አቶ ዘይኑ ጀማል ስደተኞቹን በልማት ማሰማራት የጋርዮሽ ጥቅም አለው ይላሉ፡፡

ዘይኑ ጀማል

የኢትዮጲያ ከሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ስደተኛን የማስተናገድ ልምድ ስላላት የዘንድሮ አመቱንም ዓለማቀፍ የስደተኞችቀንን እንድታከብር ተመርጣለች የሚሉት አቶ ዘይኑ  ዛሚ ኢትዮጲያ በዓሉን እንድታዘጋጅ በምን ተመረጠች ምንስ ትጠቀማለች ብሏቸዋል፡፡

ዘይኑ ጀማል

አጋርነት ለስደተኞች ወገኖቻችን በሚል መሪ ቃል በጉኝል የስደተኞች ካምፕ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ሚስተር ፍሊፕ ግራንዴ በተገኙበት ዓለማቀፉ የስደተኞች ቀን ነገ በጋምቤላ  ክልል ይከበራል፡፡