Super User

Super User

Email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ሁለተኛ ምድብ ችሎት በትላንት ውሎው በሙስና ወንጀል በተጠረጠሩ የ 54 ሰዎች ላይ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቀደ ፡፡
ፍርድ ቤቱ በቅርቡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉት የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ባለሃብቶችና ደላሎች መካከል በትላንትናው ዕለት የሃያ ሁለቱን ጉዳይ ሲመለከት ማምሸቱ ይታወሳል ፡፡
ፍርድ ቤቱ በትላንት ውሎው ከእሮብ ችሎት ለትላንት በይደር የተላለፉ የ 32 ተጠርሪዎችን እና በዛሬው እለት ከገንዘብና ኢኮኖሚክ ትብብር ሚኒስቴር ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን የአቶ ሲጀን አባ ጎጃም ጉዳይ መርምሯል፡፡
ፖሊስ ፍርድ ቤቱ በርካታ የሰነድ ማስረጃዎች መመርመር ይቀረኛል ፤ የሰው ምስክሮች አልሰማውም ፤ አብዛኞቹ ተጠርጣሪዎች ከፍተኛ ባለ ስልጣናት በመሆናቸው መረጃ ይሸሽጉብኛል፣ ምስክሮቼንም ያባብላሉ በሚል የዋስትና መብታቸው እንዳይከበርና ተጨማሪ የአስራ አራት ቀን የምርመራ ጊዜ ጠይቋ፡፡
የተጠርጣሪዎች ጠበቃ በበኩላቸው አብዛኞቹ ተጠርጣሪዎች ከተጠረጠሩበት መስሪያ ቤት ከለቀቁ የቆዩ በመሆናቸው ሰነዶችን መደበቅ አይችሉም ቀደም ሲል ለፖሊስ የተሰጠው የምርመራ ጊዜ በቂ በመሆኑ ፖሊስ ተጨማሪ የተጠየቀው 14 የምርመራ ቀን አላስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
ግራ ቀኙን የመረመረው የልደታ ምድብ ችሎት ፖሊስ ጉዳዩን እንዲያጣራ ተጨማሪ 14 ቀን ፈቅዷል፡፡
በዚህም መሰረት በነ አቶ ፀጋዬ ፣በነአቶ ዘነበ ፣በነ አቶ አበበ ፣በአ አቶ ኤፍሬም፣ ስር ያሉ የክስ መዝገቦች ለነሀሴ 17 ሲቀጠሩ
በነ አቶ አብዶ መሀመድ ፣ በነ አቶ ሙሳ ፣ በነ ኢንጂነር ፍቃደ እና ወይዘሮ ሳባ የክስ መዝገቦች ነሀሴ 15 2009 እንዲታዩ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ፍርድ ቤቱ አክሎም በአዲስ አበባ መንገዶች ባለ ስልጣን እና በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮቸክት ላይ ፖሊስ ገና ያልመረመራቸውና ያላደራጃቸው 99 ሰነዶች መኖራቸውን ገልፆ ፖሊስ በአፋጣኝ ምርመራውን እንዲያካሄድ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡፡
ለተጠርጣሪዎች የጤናና የአስተዳደር መብቶች እንዲከበሩ በሳምንት ሁለት ቀን ከጠበቃቸውና ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ ፈቅደዋል፡፡

የቬንዙዌላን ቀውስ ለማረጋጋት እና የምርጫ ውጤቱን ግልጽ ለማድረግ አጣሪ የእውነት ኮሚቴ ተመሰረተ፡፡
የአዲሱ የእውነት ኮሚቴ መሪ የሆኑት ዴልሲ ሮድሪጊየዝ እንደገለጹት አዲሱ ኮሚቴ በአሁን ሰአት ያለውን የፖለቲካ ብጥብጥ፣አለመረጋጋት እና ጥላቻን ለማስቆም የሚረዳ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ካሳለፍነው ሚያዚያ ወር ጀምሮ በሀገሪቷ በተፈጠረው የፖለቲካ አለመረጋጋት ከመቶ ሀያ የሚበልጡ ሰዎች ሞተዋል፡፡
ህገ መንግስቱ አሸባሪ ተቋሞችን የተቃወመ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት ግን አሸባሪዎቹ በጦር ሰራዊቱ እንዲገደሉ ሀሳብ ሰጥቷል፡፡
የኮሚቴው ምስረታ የጸደቀው በስብሰባው በተካፈሉት የመንግስት ባለስልጣናት ድምጽ ሲሆን ስብሰባውን በአፈ ጉባሄነት ይመሩ የነበሩትም ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ናቸው፡፡
ፕሬዝዳንት ማዱሮ እንደገለጹት አዲስ የተቋቋመው የእውነት ኮሚቴ በህገ መንግስቱ እና በህብረተሰቡ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት እንዲቀንሰ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ነገር ግን አምስት መቶ አርባ አምስት የሚሆኑት የካቢኔ አባላቶች አሁን ያለው የፖለቲካ ብጥብጥ ይህን የእውነት ኮሚቴ ለማቋቋም ያስቸግራል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የአዲሱ የእውነት ኮሚቴ መሪ ሆነው የተሾሙት ዴልሲ ሮድሪጊየስ እንደገለጹት ይህ ኮሚቴ እየተካሄደ ያለውን የፖለቲካ ረብሻ በደንብ ማጣራት አለበት ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ዘገባው የቢቢሲ ነው

ካናዳ ስደተኞች ወደ ሀገራ እስኪገቡ ድረስ እንዳይንገላቱ በሚል ጊዜያዊ የመጠለያ ካምፕ ሰራች፡፡
የካናዳ ወታደራዊ ሀይል ከአሜሪካ ለሚመጡ የጥገኝነት ስፍራ ፈላጊዎች የሚሆን ካምፕ ለአሜሪካ ወሰን ቅርብ በሆነ ሴንት በርናርድ ዲላኮሊ በተባለ ከተማ አቋቋመ፡፡
የጦር ሰራዊቱ እንደገለፀው ከ አምስት መቶ ለሚበልጡ የጥገኝነት ስፍራ ፈላጊዎች የሚሆነው ይህ ካምፕ ስደተኞቹን የሚያገለግል በቂ መብራት እና የማሞቂያ መሳሪያዎች አሉት፡፡
በ2017 መጀመሪያ አካባቢም ከ አራት ሺህ ሦስት መቶ የሚበልጡ ስደተኞች የአሜሪካን ጠረፍ አቋርጠው ወደ ካናዳ ሄደው ነበር፡፡
ስደተኞቹ በቅድሚያ ያረፉት በሞንትሪል ኦሎምፒክ እስታዲየም ሲሆን በአሁን ሰአትም ለስደተኞቹ ለወደፊት የሚያገለግል ሆስፒታል በድጋሚ ተከፍቷል፡፡
ስደተኞቹ በአሜሪካ ለብዙ አመታት የኖሩ ቢሆንም እ.ኤ.አ በ2010 በደረሰው አስደንጋጭ የመሬት መንቀጥቀጥ የተሰደዱ ስልሳ ሺህ ስደተኞችን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማባረሩ ወደ ካናዳ እንዲሰደዱ አድርጓቸዋል፡፡
የካናዳ መንግስት ይህ ስደተኞችን የመቀበል ስራ እንደሚቀጥል አሳውቋል፡፡
ምንጫችን ቢቢሲ ነው

ካናዳ ስደተኞች ወደ ሀገራ እስኪገቡ ድረስ እንዳይንገላቱ በሚል ጊዜያዊ የመጠለያ ካምፕ ሰራች፡፡
የካናዳ ወታደራዊ ሀይል ከአሜሪካ ለሚመጡ የጥገኝነት ስፍራ ፈላጊዎች የሚሆን ካምፕ ለአሜሪካ ወሰን ቅርብ በሆነ ሴንት በርናርድ ዲላኮሊ በተባለ ከተማ አቋቋመ፡፡
የጦር ሰራዊቱ እንደገለፀው ከ አምስት መቶ ለሚበልጡ የጥገኝነት ስፍራ ፈላጊዎች የሚሆነው ይህ ካምፕ ስደተኞቹን የሚያገለግል በቂ መብራት እና የማሞቂያ መሳሪያዎች አሉት፡፡
በ2017 መጀመሪያ አካባቢም ከ አራት ሺህ ሦስት መቶ የሚበልጡ ስደተኞች የአሜሪካን ጠረፍ አቋርጠው ወደ ካናዳ ሄደው ነበር፡፡
ስደተኞቹ በቅድሚያ ያረፉት በሞንትሪል ኦሎምፒክ እስታዲየም ሲሆን በአሁን ሰአትም ለስደተኞቹ ለወደፊት የሚያገለግል ሆስፒታል በድጋሚ ተከፍቷል፡፡
ስደተኞቹ በአሜሪካ ለብዙ አመታት የኖሩ ቢሆንም እ.ኤ.አ በ2010 በደረሰው አስደንጋጭ የመሬት መንቀጥቀጥ የተሰደዱ ስልሳ ሺህ ስደተኞችን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማባረሩ ወደ ካናዳ እንዲሰደዱ አድርጓቸዋል፡፡
የካናዳ መንግስት ይህ ስደተኞችን የመቀበል ስራ እንደሚቀጥል አሳውቋል፡፡
ምንጫችን ቢቢሲ ነው

30 ንጹሀን ዜጎች በማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በተፈጸመ ጥቃት ህይወታቸው አለፈ፡፡
ግጭቱ የተፈጠረው በማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በሚገኙት የታጠቁ ቡድኖች እና በራስ መከላከል ቡድን መካከል ሲሆን ህይወታቸው ካለፉ ንጹሃን መከከል በጋመቦ ከተማ የሚገኘው በቀጣይ ረቡእ እለት ለሚካሄደው የጤና ድርጅት ስብሰባ ለመታደም የመጡ 6የቀይ መስቀል በጎአደራጊዎች ይገኙበታል፡፡
በደም መፋሰስ ምስቅልቅሉ የወጣው ከባንጋሱ 75 ኪሎ ሜትር የምትርቀው የጋምቦ ከተማ ሁከቱ የተጀመረው ባሳለፍነው ሳምንት ነው፡፡ የምስራቅ አፍሪካ የ ቀይ መስቀል ፕሬዝዳንት የሆኑት አንቶኒ የአጋሮቻችንን ሞት መስማታችን ለኛ አስደንጋጭ ዜና ነው ሲሉ አያይዘውም ሁሉንም ፓርቲዮች ንጹሃን ዜጎችን እንዲተዉ እና የበጎ አድራጎት ሰራተኞችን እንዲያከብሩ ነግረናቸው ነበር ብለው ተናግረዋል፡፡
በ ማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ አስራ ሁለት ሺህ የሰላም አስከባሪዎች ቢኖሩም በጋመቦ በተፈጠረው ግጭት ላይ አንዳቸውም ግጭቱን ለማብረድ አልተገኙም፡፡
የሃገሪቱ ቃለ አቀባይ እንዳሉት የሰላም አስከባሪዎቹ ሳይመጡ ስለቀሩ የራሳቸንን ወታደሮች አደራጅትን ልከናል ብለዋል፡፡
የአለም አቀፍ ጥበቃ ደርጅት በህጉ ላይ እንዳስቀመጠው ማንኛውም የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በማንኛውም ቦታ ሲንቀሳቀሱ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ይላል ነገር ግን በዚህ አመት በቻ በቀይ መስቀል ላይ እነደዚህ አይነት አደጋ ሲደርስ 3ኛ ጊዜ ነው፡፡ የተባበሩት መንግሰታት የእርዳታ ድርጅት ዋና መሪ ይሄ ግጭት የ ጅምላ ጭፍጨፋ ምልክት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡

በኬንያ በአንድ የምርጫ ጣቢያ በተነሳ ብጥብጥ የ አራት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
አንድ የአይን እማኝ እንደተናገረው ፖሊስ 3ሰዎች ተኩሶ ገድለ አራተኛው ደግሞ በተቃዋሚዎች የተገደለ ነው፡፤ቢሆንም ግን ሁከት እና ብጥብጡ እስካሁን እንዳቀጠለ ነው፡፡ኬንያውያኖች የ2007 የፕሬዝዳንት ምርጫ አስከትሎ በመጣው ክርክር ምክንያት አንድ ሺህ ሰዎች የሞቱበት የዘር እልቂት ተመልሶ እንዳይመጣ በፍርሃት እና በጭንቀት ላይ ናቸው::
የኤሌክትሮኒክስ ድምጽ መስጫ ተጭበርብሯል በሚል የተቃዋሚ መሪው ራይሊ ኡዲንጋ ሲሰነዝሩ የነበረውን ትችት የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን መሰረተ ቢስ እንዲሁም የፈጠራ ወሬ ነው ሲል ጉዳዩን አጣጥሎታል፡፡በነሳይሮቢ እና በ ኪሰሙ ከማክሰኞ ጀምሮ የ ድምጽ ቆጠራው ቀጥሏል የምርጫ ኮሚሽኑም ምርጫው ነጻ እና ፍትሃዊ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡
የኤሌክተሮኒክሱን የድምጽ መስጫ የሰበሩት ሰዎች ባለፈው ጊዜ በጭካኔ ተገድሎ የነበረውን የምርጫ ቢሮ ሰራተኛውን መታወቂያ ሊጠቀም እንደሚችል ተቃዋሚው መሪ ኡዲነጋ ጥርጣሪያቸውን ገልጸዋል፡፡ በሚወጣው የኬንያ ውጤት ላይ የተቃዋሚ መሪው ንግግር ሽብር ሊያስነሳ እነደሚችል የኬንያ ስጋት ነው፡፡
በናይሮቢ የተቃውሞ ሰለፍ ከወጡት ሰዎች ፖሊስ አነድ ስው ገደለ እንዲሁም ሰላመዊ ሰልፍ የወጡ 100 ሰዎችን በትኗል በተመሳሳይም በ ኮስታል ታና ወንዝ ዳርቻ በምተገኝ መንደር በተከሰተው ጥቃት የተመለከቱ የአይን እማኝ እንደተናገሩት የታጠቁ ወንበዴዎች 1 ሰው ገድለው ብዙ ሰዎች ማቁሰላቸውን ተናግረዋል፡፡ ፖሊስም 2ጥቂዎችን ተኩሶ ገድሏል፡፡የውጭ ታዛቢዎች የተፈጠረው ነገር ማስረጃ ስለሌለው አስተያየት ከመስጠተት ተቆጥበዋል ነገር ግን ሁሉም ፓረቲዎች እንዲረጋጉ አሰገንዝበዋል
የምርጫ ቦረዱ መሪ እዛራ ቺሎባ እንዳሉት ከምርጫው በፊትም ሆነ ከምርጫው በኋላ ምንም አይነት የውጭ ጣልቃ ገብንት አልተፈጠረም የኛ የምርጫ አስተዳደር ስርአት ደህንነቱ የተጠበቀ ነው ሲል አያይዞም የኤሌክትሮኒክስ ድምጽ መስጫው ተሰብሯል እንዲሁም ተጭበርብሯል በሚል የተነሳውን ቅሬታ እነደሚያጣራ ለሀገሪቱ የዜና አሰራጮች ገልጸዋል፡፤
የምርጫ ቦርድ በድህረ ገጹ እነዳስቀመጠውፕሬዝዳንት ኬንያታ በ 54.3 በመቶ የመራጮች ድምጽ ለ 44.8በመቶ ተቃዋሚያቸውን ኦዲንጋን 97 በመቶ በሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች 1.4 ሚሊዮን በሚሆን የመራጭ ድምጽ በማግኘት በሰፊ ድምጽ እየመሩ እንደሆነ ዘግቧል ፡፡
ዘገባው all Africa .com

ኳታር ከ 80 ሀገራት የሚመጡ ዜጎች ያለ ቪዛ እንዲገቡ ፈቀደች ከአፍሪካ ሁለት ሀገራት ብቻ ተካተዋል፡፡
ሀገሪቱ በትናንትናዉ እለት ይፋ እንዳደረገችዉ እየደከመ የመጣዉን የአየር ትራንስፖርቷን ለመደገፍ ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡ ዜጎችን ያለ ቪዛ እንዲገቡ ፈቅዳለች
ህንድን ጨምሮ ሊባኖን ኔዘርላንድ ደቡብ አፍሪካ አሜሪካ እንዲሁም ከ አዉሮፓ ሀገራት የሚመጡ ዜጎች በነዳጅ ሀብቷ ወደበለጸገችዉ ሀገር ኳታር ለመግባት ፓስፖርት ብቻ እንደሚያስፈልጋቸዉ የተገለጸ ሲሆን
ቪዛ ከተፈቀደላቸዉ 80 ሀገራት መካከል 33 ቱ 180 ቀናት እንዲሁም ቀሪዎቹ 47 ሀገራት ለ 30 ቀናት ያህል ነዉ እንዲቆዩ የሚፈቀድላቸዉ
ይህ ዉሳኔም የኳታር ከፍተኛ የገቢ ምንጭ የሆነዉን ቱሪዝም ለማሳደግ እንደሚረዳ ታምኗል
የጎብኚዎቿን ቁጥር በግማሽ የሚይዙት የ ባህረሰላጤዉ ሀገራት ዜጎች ወደ ኳታር እንዳይገቡ የተከለከሉ በመሆኑ ሀገሪቱ አሁን የወሰነችዉ ዉሳኔ የተሻሉ ጉብኚዎችን እንድታገኝ ያስችላታል ተብሏል፡፡
በሳዑዲ አረቢያ የሚመራዉ የባህረሰላጤዉ ሀገራት ከኳታር ጋር ያላቸዉን ግንኙነት ካቋረጡ ሁለት ወራት አልፏል፡፡
የትራንስፖርት ክልላቸዉንም ለኳታር ዝግ አድርገዉ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ዘገባዉ የሮይተርስ ነዉ፡፡

የአፍሪካን ልማት ባንክ ለደቡብ ሱዳን ድርቅን እንከላከል በሚባለዉ የአጭር ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ መፍትሄ ሰጭ በሆነዉ ፕሮጀክት በኩል ለደቡብ ሱዳን አርባሶስት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ዶላር ሰጠ፡፡
የአፍሪካ ልማት ባንክ ከደቡብ ሱዳን እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) ጋር ድርቅን እንከላከል በተባለዉ ፕሮጀክት ስር ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ይህም ዉል ድርቅን እንከላከል በተባለዉ ፕሮጀክት ስር በአፍሪካ ልማት ባንክ ቦርድ ዳይሬክተሮች አማካኝነት እ.ኤ.አ ጁላይ 21 2017 የፀደቀ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት ድርጅትም በደቡብ ሱዳን በወኪሉ አማካኝነት ይህን በተግባር ላይ ለማዋል የሚከናወኑ ነገሮችን እየተከታተለ ሪፖርት እንደሚያደርግ ተናግሯል፡፡ወኪሉም ከመንግስታት ጋር በመተባበር እንደሚሰሩም ገልጸዋል፡፡
የባንኩ አላማም ሶስት መቶ ሺ ለሚደርሱ የደበብ ሱዳን ግለሰቦች ድርቁን በአስቸኳይ ለመቋቋም የሚያስችሏቸዉን መሰረታዊ ፍላጎቶችን ማለትም ምግብ ፣ ዉሀ እንዲሁም የህክምና አገልግሎቶች ማቅረብ እንደሆነ ተናግሯል፡፡በተጨማሪም በምግብ ለተጎዱ ሌሎች አካላትም እንደሚረዱ ጨምረዉ ገልፀዋል፡፡
የእርዳታዉም ስምምነት በዋነኝነት በሶማሊያ እና በደቡብ ሱዳን እጅጉን ለተጎዱ ህዝቦች የምግብ እና የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ነዉ፡፡
ይህ ባንክ በድርቅ ለተጎዱ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ሀገራት 1.1 ቢሊዮን ብር ለመስጠት አቅዷል፡፡
በፊርማዉ ሰአትም የቦርዱ አባላት እና የተለያዩ ባለስልጣናት እየሆነ ባለዉ ነገር ደስተኛ መሆናቸዉን ገልፀዋል በተጨማሪም ይህ ድጋፍ የደን የግብርና እና ተመሳሳይ የሆኑ የሚኒስተር መስሪያ ቤቶችን እንዲጠነክሩ ያደርጋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ምንጭ ሱዳን ትሪቡን

በ6ክልልሎች የሚገኙ 8.5 ሚሊየን ህዝቦች የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸዉ ሲሆን የኦሮሚያ ክልል 3.67 ሚሊየን ተጎጂዎችን በመያዝ ከፍተገኛዉን ቁጥር ይዟል፡፡ ለአጠቃላ ተጎጅዎችም እርዳታ 487.7 ሚሊየን ዶላር ያስፈልጋል፡፡
በበልግ አብቃይና በአርብቶ አደር አከባቢዎች በተደረገ የምግብ ዋስትና የዳሰሳ ጥናት ለቀጣይ አምስት ወራት ስምንት ነጥብ አምስት ሚሊየን ህዝብ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልገዉ የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገልጻዋል፡፡
የተረጂዎች ቁጥርም ባለፈዉ አመት ከነበረዉ ሰባት ነጥብ ስምንት ሚሊየን ወደ ስምንት ነጥብ አምስት ሚሊየን የጨመረ ሲሆን ለዚህም ምክንያት ናቸዉ የተባሉት
የበልግ ዝናብ መዛባት፤ የመኖና ግጦሽ ማነስ፤ የምርት መቀነስና የዉሀ እጥረት ተጠቅሰዋል፡፡ የኦሮሚያ ክልል በ ሶስት ነጥብ ስድስት ሚለየን ተጎጂ በመያዝ በተጎጂ ቁጥር ቀዳሚ ሆናለች፡፡
ለተጎጂዎች እርዳታ አራት መቶ ሰማንያ ሰባት ሚሊየን ሚሊየን ነጥብ ሰባት የአሜርካን ዶላር እንደሚያስፈልግ የገለፀዉ ኮሚሽኑ የኢትዮጲያ መንግስት ለዚህ እርዳታ ከስድስት መቶ ሰባ ሁለት ሚሊየን ብር በላይ በመመደብ የእህል ግዥ በመፈጸም ላይ እንደሚገኝ የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቴር የሆኑት አቶ ደበበ ዘዉዴ ለዛሚ ተናግረዋል፡፡
ትብለጽ ተስፋዬ ዘግባዋለች፡፡

የአለም የጤና ድርጅት ባወጣው መረጃ መሰረት በናይጄሪያ ወባ በከፍተኛ መጠን ገደይ ከሚባሉ በሽታዎች ውስጥ ቀዳሚነቱን ይዞል፡፡
በሰሜን ምስራቅ የናይጄሪያ ግዛት በሆነቸው ቦርኖ በስምንት አመት ውስጥ 3.7 ሚሊየን የሚደርሱ ዜጎች እርዳታ የሚፈልጉ ሲሆን በየሳምነቱ ስምንት ሺ ህ ያህል ደግሞ በበሽታው ይጠቃሉ፡፡ እንደ ጤና ድርጅቱ መረጃ ከሆነ ይሄ በሽታ በወርሃ ጥቅምት በይበልጥ እየተስፋፋ እንደሚመጣም ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም በሀገሪቱ የወባ በሽታ ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ እንደሚመጣ አስታውቀዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ከሚከሰው ሞት ከግማሽ በላይ የሚሆነው በወባ ሲሆን ኮሌራ እና ኢ የሚባለው የጉበት በሽታ ተከታዩን ስፍራ ይይዛሉ፡፡ 58.8 በመቶ ያህሉ በህጻናት ላይ እንደሚከሰቱም መረጃው ያሳያል፡፡
60 በመቶ የሚሆኑት የሀገሪቱ የጤና ማእከል አገልግሎት የሚሰጡት ለሌሎች ጤና ሽፋኖች በመሆኑ የወባ በሽታ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራበት እነደሚገባም በጥናቱ አስቀምጦል፡፡
በአንድ ሀገር ውስጥ የወባ በሽታ መስፋፋት ለሀገሪቱ ሰብአዊ ቀወስ ችግር ምክንያት እንደሚሆን የአለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተር የአለም አቀፍ የወባ በ መከላከል ዝግጅት ክፍል የሆኑት ዶክተር ፔድሮ አሎንሶ ገልጸዋል፡፡
10 ሺህ የሚደርሱ የናይጄሪያ ዜጎችን ከበሽታው ለመታደግ አለም የጤና ድርጅት ገንዘብ መመደቡን አስታውቋል፡፡
የወባ በሽታ የሚከሰተው ጥገኛ በሆኑ የሴት ወባ ትንኞች ማለትም በአናፎሊስ ነው፡፡ በአፍሪካ 200 ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች በወባ የተያዙ ሲሆን አራት መቶ ሰላሳ ሰባት ሺህ በዚሁ በሽታ ህይወታቸው አልፎል፡፡ በአጠቃላይ በአፍሪካ ከሚከሰቱ የሞት አደጋዎች 90 በመቶ የሚሆኑት በወባ እንደሆነ አለም የጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል፡፡