የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ሁለተኛ ምድብ ችሎት በነ ኢንጂነር ፍቃደ ሃይሌ መዝገብ የቀረበው የፅሁፍና የቃል ምርመራ ውጤት ተመሳሳይ አለመሆኑን ገለፀ፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ሁለተኛ ምድብ ችሎት በነ ኢንጂነር ፍቃደ ሃይሌ መዝገብ የቀረበው የፅሁፍና የቃል ምርመራ ውጤት ተመሳሳይ አለመሆኑን ገለፀ፡፡
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ሁለተኛ መደበኛ ችሎት በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ከፍተኛ የመንግስት ባለ ስልጣናት፣ ነጋዴዎችና .የደላሎችን መዝገብ ሲያይ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
ፍርድ ቤቱ በትላንት ውሎው በነ ኢንጂነር ፈቃደ ሀይሌ መዝገብ ፖሊስ ነሀሴ ሶስት 2009 ለፍርድ ቤት በበተፃፈ ደብዳቤ ላይ የተጠርጣሪዎችን የተከሳሽነት ቃል ሰምተናል የሚለው ፅፎ ሳለ በነሀሴ 17 2009 በተፃፈ ሌላ ደብዳቤ የተጠርጣሪዎችን የተከሳሽነት ቃል መስማት ይቀረናል የሚለውን ሀረግ መጠቀሙና መርማሪ ፖሊሶች በችሎት ፊት ቀርበው የተጠርጣሪዎችን ቃል ሙሉ በሙሉ አለመስማታቸውን መናገራቸው እርስ በራሱ የሚጣረስ በመሆኑ መርማሪ ቡዱኑ በቀጣይ ችሎት ሲመጣ በቃልና በሰነድ የሚያቀርበውን መረጃ እርግጠኛነት እንዲያረጋግጥ እና ተስተካክሎ ይቅረብ የሚል ጥብቅ ማሳሰሚያ አስተላልፏል፡፡
ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ የኦዲት ስራዎችን ለመስራት ፣በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተፃፉ ሰነዶችን ለማስተርጎም ፣ ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለ ስልጣንና በሌሎች የመንግስትና የግል ድርጅቶች ያሉ ሰነዶች መመርመር ይቀሩኛል ፣ ተጠርጣሪዎች መረጃ ሊያሸሹና ሊያበላሹ ስለሚችሉ የዋስትና መብታቸው አይከበር ለኔም ቀሪ ምርመራዎችን መፈፀም እንዲያስችለኝ ተጨማሪ 14 ቀናት ይጨመርልኝ ሲል ፍርድ ቤትን ጠይቋል፡፡
የተጠርጣሪ ጠበቃዎች በበኩላቸው ከአስራ አራት ቀን በፊት በዋለው ችሎት መርማሪ ፖሊሶቹ ተጨማሪ 14 ቀን ጊዜ ይፈቀድልን ባሉት መሰረት ቀኑ ቢፈቀድም እንሰራለን ያሉትን ስራ በትጋት አልሰሩም ፣አሁን ላይ እንሰራለን ያሉት ስራ በባለፈው ችሎት ተጥይቋል በዚህ ምክንያት የተጠርጣሪዎች የዋስትና መብት ይከበር ተጨማሪ የቀን ይጨመር ጉዳይ አግባብ አይደለም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡
የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው ፍርድ ቤትም ምርመራው በትጋት ይሰራ ከሚል ትዕዛዝ ጋር ተጨማሪ 10 ቀን ፈቅዷል፡፡
ፍርድ ቤቱ ከዚህም በተጨማሪ በነ አቶ መስፍን መዝገብ የነ አበበ ተስፋዬ የክስ መዝገብ ላይ የግራ ቀኙን ክርክር አይቶ ለነሀሴ 29 ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን
የነ አቶ ዘነበ ይማም መዝገብ ነሀሴ 25 እንዲታይ ወስኗል፡፡

Leave a comment

Make sure you enter the (*) required information where indicated. HTML code is not allowed.