ብሄራዊ የደም ባንክ አገልግሎት በተጠናቀቀው የበጀት አመት በአገር አቀፍ ደረጃ 173 ሺህ 923 ዩኒት ደም በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ 24 የደም ባንኮች አማካኝነት ሰብስቧል፡፡

ብሄራዊ የደም ባንክ አገልግሎት በተጠናቀቀው የበጀት አመት በአገር አቀፍ ደረጃ 173 ሺህ 923 ዩኒት ደም በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ 24 የደም ባንኮች አማካኝነት ሰብስቧል፡፡
በዘንድሮው አመት የተሰበሰበው ደም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ33 ሺህ 862 ዩኒት ደም ብልጫ እንዳለውም የብራዊ ደምባንክ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ብርሀኑ ስዩም ተናግረዋል፡፡
የሚሰበሰበውን ደም ሙሉ ለሙሉ ከበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች የተሰበሰበ ሲሆን ቀሪው 1.3 በመቶ ከቤተሰብ ምትክ የተለገሰ እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡
ከቤተሰብ ምትክ የደም ልገሳ ሙሉ ለሙሉ ባልተላቀቁት የጂግጂጋ፤ሀረርና ድሬ ዳዋ ደም ባንኮች የቅስቀሳ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶችን ለህብረተሰቡ ሰጥተዋል፡፡
በ2010 አ.ም 241 ሺህ ዩኒት ደም ከበጎ ፈቃደኞች ደም ለጋሾች ለማሰባሰብም ታቅዷል፡፡
ናርዶስ ዩሴፍ

Leave a comment

Make sure you enter the (*) required information where indicated. HTML code is not allowed.