ለ38 አመትአንጎላን የመሩት የ74 አመቱ ፕሬዚዳንት ጆዜ ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶስ ስልጣን በቃኝ ብለዋል ።

ለ38 አመትአንጎላን የመሩት የ74 አመቱ ፕሬዚዳንት ጆዜ ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶስ ስልጣን በቃኝ ብለዋል ።
በነገው እለት ምርጫ የሚያደርጉት አንጎላውያን አዲሱ መሪያቸውን ለመምረጥ በዝግጅት ላይ ናቸዉ
በምርጫውም የዶስ ሳንቶስ ፓርቲ ተወካይ እና ሌሎች ፓርቲዎች የሚሳተፉ ይሆናል።
የዶስ ሳንቶስ ፓርቲ የሆነው የአንጎላ ነጻ አውጪ ንቅናቄ በፕሬዚዳንቱ የሚደገፉትንና የመከላከያ ሚኒስትሩን ጃኦ ሎሬንዞን ለምርጫ የሚያቀርብ ሲሆን ያሸንፋሉ የሚል ግምትም ተሰጥቶአቸዋል።
በአፍሪካ ትልቋ የነዳጅ ላኪ ሀገር የሆነችው አንጎላ ሙስና በከፍተኛ ደረጃ ከሚታይባቸው ሀገራት ተርታ የምትመደብ ሲሆን
ኢዛቤላ የተባለችው የፕሬዚዳንት ዶስ ሳንቶስ ልጅም በሳቸው የአመራር ጊዜ ከአፍሪካ ሀብታም ሴቶች አንዷ መሆን ችላለች።
ተቃዋሚ ፓርቲዎች የአንጎላ ዜጎችን ለዘመናት በችግር ያለምግብ፣ ስራና ኤሌክትሪክ ኖራችኋል አሁን ይህ እንዲያበቃ እኛን ምረጡ እያሉ ይገኛሉ።
የአንጎላው ነጻ አውጪ ንቅናቄ የፖለቲካ ፓርቲ እ.ኤ.አ በ1975 አንጎላ ከፖርቹጋል ነፃ ከወጣች ጀምሮ ሀገሪቷን እየመራ ይገኛል።

Leave a comment

Make sure you enter the (*) required information where indicated. HTML code is not allowed.