በመንገድ ትራፊክ አደጋ በኢትዮጲያ በአምስት አመት ውስጥ 18 ሺ 24 ሰዎች ሂወታቸው ሲያልፍ አርባ ስምንት ነጥብ አንድ በመቶ የሚሆኑት ተሳፋሪዎች ፣አርባ ሶስት ነጥብ ሁለት በመቶ እግረኞች ስምንት ነጥብ ሰባት በመቶ የሚሆኑት ደግሞ አሽከርካሪዎች ናቸው፡፡

በመንገድ ትራፊክ አደጋ በኢትዮጲያ በአምስት አመት ውስጥ 18 ሺ 24 ሰዎች ሂወታቸው ሲያልፍ አርባ ስምንት ነጥብ አንድ በመቶ የሚሆኑት ተሳፋሪዎች ፣አርባ ሶስት ነጥብ ሁለት በመቶ እግረኞች ስምንት ነጥብ ሰባት በመቶ የሚሆኑት ደግሞ አሽከርካሪዎች ናቸው፡፡
በ መንገድ ትራፊክ አደጋ በቁጥርም ሆነ በአስከፊነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት እያስከተለ መጥቷል፡፡እንደ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ በ2008 በአገር አቀፍ ደረጃ የ4 ሺህ352 ዜጎች ሕይወት ጠፍቷል:: በአምስት አመት ውስጥ 18 ሺህ 24 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ከነዚህም መካከል48.1 በመቶ ተሳፋሪዎች 43.2 በመቶ እግረኞች 8.7በመቶ የሚሆኑት ደግሞ አሽከርካሪዎች ናቸው:: ከዚህም በተጨማሪ በዚህ አመት በ12ሺህ ዜጎች ላይ ከባድና ቀላል አደጋ ደርሷል::
በክልል ደረጃ አምስቱ ክልሎች በአጠቃላይ ከ90 በመቶ በላይ የሞት አደጋ ያስተናግዳሉ፣ኦሮሚያ ከ35 በመቶ በላይ ሞት በመያዝ ከፍተኛውን ቁጥር ሲይዝ አማራ ከ22 በመቶ በላይ ሞት በመያዝ ሁለተኛ ደረጃ ይዞል በአገር አቀፍ ደረጃ የሞት ጉዳቱ በጾታ ሲሰላ ከ75 በመቶ በላይ የሞት ተጋላጭ የሆኑት ወንዶች ናቸው፡፡
በአለማችን ከሚደርሱ አራት ሞቶች ውስጥ ሶስቱ በመኪና አደጋ ነው ፡፡ አንድ ነጥብ ሀያ አራት ሚሊየን ዜጎች በመኪና አደጋ ህይወታቸውን ያጣሉ እነዚህም እድሜያቸውም 15-29 የሚሆኑት ከፍተኛውን ደረጃ ይይዛሉ፡፡
የመንገድ ትራፊክ አደጋ በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ገዳይ ከሚባሉ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ በሽታዎች መካከል በ9ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን የተቀናጀና የተደራጀ ርምጃ ካልተወሰደበት በ2030 1.9 ሚሊዮን ሰዎችን ህይወት በማጥፋት ወደ ሶሰተኛ ደረጃ ከፍ እንደሚል ይገመታል፡፡ ዘገባው የፍሬህይወት ታደሰ ነው

Leave a comment

Make sure you enter the (*) required information where indicated. HTML code is not allowed.