በትግራይ ክልል አራት ቦታዎች ላይ በተደረገ የቅርስ ፍለጋና ምርምር የአሸንዳን ጥንታዊነት የሚገልጹ አልባሳት እና ቁሳቁሶች ተገኙ፡፡

በትግራይ ክልል አራት ቦታዎች ላይ በተደረገ የቅርስ ፍለጋና ምርምር የአሸንዳን ጥንታዊነት የሚገልጹ አልባሳት እና ቁሳቁሶች ተገኙ፡፡
የጀርመን እና የኢትዩጲያ የቅርስ ፍለጋና ምርምር ባለሙያዎች ከ3 አመታት በፊት አንስቶ ሲያከናውኑት በነበረው የቅርስ ፍለጋና ምርምር ተግባር ከ50 ያላነሱ የአሸንዳ ታሪካዊነትን የሚያመላክቱ ቅርሶችን አግኝተዋል፡፡
የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ ለዛሚ ብቻ እንደተናገሩት በሀውዜን፤ በውቅሮ፤ በበጋሀሙስ እና በአክሱም የሀ አካባቢዎች ሲከናወኑ የነበሩ የምርምር ስራዎች የአሸንዳ ባህል በክልሉ ከጥንት ጀምሮ ሲከበር እንደነበር አመላካች የሆኑ ቁሳቁሶችና ጌጣጌጦች ተገኝተዋል ብለውናል፡፡
ሴቶች ይጠቀሙበት የነበረ የአንገት ተንጠልጣይ ጨሌዎች፤ ጥንታዊ የሽቶ መያዣ እንዲሁም ከሸማ የተሰሩ ባህላዊ የሴቶች ልብሶች ከተገኙት መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡
እነዚህ ቅርሶች በአሁን ሰአት በከተማው ሙዚየም ለህዝቡ እይታ ቀርበዋል፡፡
ሲል ያልፋል አሻግር የአሸንዳ በአል ከሚከበርበት ከመቀሌ ሆኖ ዘግቦታል፡፡

Leave a comment

Make sure you enter the (*) required information where indicated. HTML code is not allowed.