የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ለ 2010 የበጀት አመት ላስቀመጣቸው ግቦችና ተግባራት በሚሰጣቸው ክብደት መለኪያ ከ 10 ሚሊየን ብር በላይ የተመደበለትን የፋይናንስ ጉዳይ ከአጠቃላይ ጉዳዩች 10 በመቶ ክብደት ብቻ ሰጥቶታል፡፡

የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ለ 2010 የበጀት አመት ላስቀመጣቸው ግቦችና
ተግባራት በሚሰጣቸው ክብደት መለኪያ ከ 10 ሚሊየን ብር በላይ የተመደበለትን የፋይናንስ
ጉዳይ ከአጠቃላይ ጉዳዩች 10 በመቶ ክብደት ብቻ ሰጥቶታል፡፡
ኤጀንሲው ለፋይናንስ ጉዳዩች ለዘመናዊ እና ፍትሀዊ የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር
ፕሮግራም ማስፈጸሚያ 2 ሚሊዩን 7ሺህ 702 ብር፤ ዘላቂ የመፈጸም እና የማስፈጸም
አቅም መገንባት ፕሮግራም 2 ሚሊዩን 706 ሺህ 333 ብር እንዲሁም ለአመራር እና ድጋፍ
አገልግሎት ፕሮግራም6 ሚሊየን 107 ሺህ 172 ብር የተመደበለት ሲሆን በተጨማሪም
የኤጀንሲውን ግዢ አፈጻጸም በተዘጋጀው ቅድ መሰረት ስራ ላይ ለማዋልና ለፋይናንስ ግዢ
እና ንብረት አስተዳደር ውጤታማነትን ለማሻሻል በአጠቃላይ በበጀት አመቱ አፈጻጸም
የሚኖረው ድርሻ 10 በመቶ ሆኗል፡፡
በእቅዱ ላይ ለተገልጋይ ማለትም የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እና የኤጀንሲው ሰራኞችን
እርካታ ለማሻሻል ለመሳሰሉት ነገሮች 30 በመቶ፤ ለውስጥ አሰራር ማሻሻያ 45 በመቶ
እንዲሁም ለመማማር እና እድገት ከፋይናንስ በተሸለ 15 በመቶ የትኩረት አቅጣጫ
አስቀምጧል፡፡
በተዘጋጀው የግዢ አፈጻጸም መከታተያ ማንዋል መሰረት በማድረግ የክልል ግዢ ተቆጣጣሪ
አካላት በኦሮሚያ፤ አማራ፤ ትግራይ እና ደቡብ ህዝቦች ብሄር ብሄረሰቦች በክልላቸው
ተጨባጭ ሁኔታ የማጣጣም ስራ ማከናወናቸውን መከታተልን ከ 1 በመቶ በታች የሆነ
ትኩረት እንደሚሰጠውም አስፍሯል፡፡

Leave a comment

Make sure you enter the (*) required information where indicated. HTML code is not allowed.