ግምታዊ ዋጋቸው ከ 4 ሚሊየን ብር በላይ ሊያወጡ የሚችሉ የኮንትሮባንድ እቃዎች የኢትዩጲያ ገቢዎች እና ጉምሩክ የጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ያዘ፡፡

ግምታዊ ዋጋቸው ከ 4 ሚሊየን ብር በላይ ሊያወጡ የሚችሉ የኮንትሮባንድ እቃዎች
የኢትዩጲያ ገቢዎች እና ጉምሩክ የጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ያዘ፡፡
በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ሊገቡና ሊወጡ ሲሉ የተያዙት እቃዎች ውስጥ ኤሌክትሮኒክስ፣
ምግብ ነክ ሸቀጦች፣ አዳዲስና ልባሽ ጨርቆች፣ ጫማዎች፣ ሲጋራ፣ መድሃኒት፣ የህንፃ
መሳሪያዎችና የቤት መገልገያ እቃዎች ሲሆኑ በወጭ ኮንትሮባንድ በኩል 73 የቀንድ ከብቶች፣
77 በጎች፣ 20 ፍየሎች፣ 5700 ኪ.ግ ጤፍ፣ 26 ኩንታል ቀይ ሽንኩርት፣ 3 ኩንታል ነጭ
ሽንኩርት፣ የተፈጨ ቡና እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት የመገበያያ ገንዘብ ይገኙበታል፡፡
እቃዎቹ የተያዙት ከሰኔ አንድ እስከ ሰኔ 30/2009 ዓ.ም. ሲሆን ጅግጅጋ ዙሪያ ቶጎ ጫሌ፣
ተፈሪ በር፣ ሐርሸን እና ለፈኢላ እቃዎቹ አካባቢ ነው የተያዙት፡፡

Leave a comment

Make sure you enter the (*) required information where indicated. HTML code is not allowed.