የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በዚህ ዓመት ብቻ ከሁለት መቶ በላይ ሀሰተኛ የመንጃ ፍቅድ ይዘው ሲያሽከረክሩ የነበሩ አሽከርካሪዎችን መያዙን ተናገረ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በዚህ ዓመት ብቻ ከሁለት መቶ በላይ ሀሰተኛ የመንጃ ፍቅድ ይዘው ሲያሽከረክሩ የነበሩ አሽከርካሪዎችን መያዙን ተናገረ፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በዚህ አመት በድንገተኛና መደበኛ ፍተሻ ሁለት መቶ ስድስት አሽከርካሪዎች ሀሰተኛ የመንጃ ፍቃድ ይዘው ሲገኙ ይህ ቁጥር አምና ከተመዘገበው በአስራ ስድስት ብልጫ አሳይቷል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ግርማ ተሰማ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በዘመናዊ መሳሪያ እና በቴክኖሎጂ ታግዞ ቁጥጥሩን ቢያደርግ ሀሰተኛ መረጃ የያዙት አሽከርካሪዎች ቁጥር ይጨምር ነበር ብለዋል፡፡
በከተማዋ ሀሰተኛ የመንጃ ፍቅድ ይዘው የተገኙት 75 እጅ የሚሆኑት የህዝብ ማመላለሻ መኪናዎችን የሚያሽከረክሩ ሲሆን የታክሲ እንዲሁም የከባድ ጭነት መኪና አሽከርካሪዎች ተከታዩን ስፍራ ይይዛሉ፡፡
ሀሰተኛ የመንጃ ፍቃድን በመያዝ ወጣቶችን የሚስተካከል አልተገኘም የተባለ ሲሆን በተለያዩ የጤና ችግሮች ዕጋዊ መንጃ ፍቃድ ማውጣት ያቃታቸው አምስት ግለሰቦችም ሀሰተኛ የመንጃ ፍቃድ ይዘው ተገኝተዋል፡፡
ሀሰተኛ መንጃ ፍቃድ የያዙ አስከርካሪዎች የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በመደበኛና በድንገተኛ ፍተሸዎች ከሚለያቸው ጎን ለጎን ጥፋት ያጠፉ አሽከርካሪዎች ቅጣታቸውን ሊከፍሉ ወደ የሁሉም ማህከላት በሚያመሩበት ወቅት ቅጣቱን ብቻ ከመቀበል የመንጃ ፍቃዱን ትክክለኝነት እንዲያረጋግጡ የአሽርካሪዎች መረጃ በዳታ ቤዝ የመያዝ ስራ እየተሰራ ነው ፡፡
በየሁሉም ማህከላት ሊሰራ ከታቀደው ውጪ ሀሰተኛ የመንጃ ፍቅድ የያዝትን ከህጋዊዎቹ በዘላቂነት ለመለየት ፖሊስ ኮሚሽኑ ምን እየሰራ ነው ብሎ ዛሚ ኮማንደር ግርማን ጠይቆ ከተሸከርካሪ አሽከርካሪ ባለስልጣን ጋር በመሆን በቀጣይ ዓመት በኮምፒዩተር የታገዘ ቁጥጥር ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ነግረውናል፡፡
በዚህ አመት 1600 አሽከርሪዎች ለትራፊክ ፖሊሶች ጉቦ ሲሰጡ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ሶስቱ አሽከርካሪዎች ሀሰተኛ የመንጃ ፍቃድ ይዘው ተገኝተዋል፡፡
ምትኬ ቶሌራ

Leave a comment

Make sure you enter the (*) required information where indicated. HTML code is not allowed.