የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ሳውዲ አረቢያ ውጡልኝ ያለቻቸውን ኢትዮጵያውያንን አስመልክቶና በሌሎች አገራዊ ጉዳዮች ላይ ሰኔ 22 ቀን 2009 ዓ.ም በመስሪያ ቤታቸው መሰብሰቢያ አዳራሽ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ሳውዲ አረቢያ ውጡልኝ ያለቻቸውን ኢትዮጵያውያንን አስመልክቶና በሌሎች አገራዊ ጉዳዮች ላይ ሰኔ 22 ቀን 2009 ዓ.ም በመስሪያ ቤታቸው መሰብሰቢያ አዳራሽ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም መቶ አስራ አንድ ሺህ በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የጉዞ ሰነድ ወስደዋል፡፡ የጉዞ ሰነድ ከወሰዱት ውስጥም አርባ አምስት ሺህዎቹ አገራቸው ገብተዋል ብለዋል፡፡ የሳውዲ መንግስት መጋቢት 20 ቀን 2009 ዓ.ም ቀን ያወጣው የውጡልኝ አዋጅ ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም ቢጠናቀቅም እስካሁን ድረስ ግን ተጨማሪ ዜጎችም ወደ አገራቸው በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡
ቃል አቀባዩ 29ኛው የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ በአዲስ አበባ እንደሚካኤድ ገልፀው ለስብሰባውም ስኬት መንግስት አስፈላጊውን ዝግጅት እንዳደረገ ተናግረዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዚህ ስብሰባ ላይ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽነር ለመሆን ኢትዮጵያዊው አቶ ነዋይ ገብረአብ በእጩነት እንደቀረቡ ቃል አቀባዩ ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያና የሩሲያን ግንኙነት አስመልክቶ የሩሲያው ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ለኢትዮጵያ አቻቸው ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ባቀረቡት ግብዣ መሰረት ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ በሩሲያ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ በጉብኝታቸውም የሁለቱን አገራት ግንኙነት ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ከመግባባት ላይ መድረሳቸውን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡
ሚካኤል ጌታሠጠኝ

Leave a comment

Make sure you enter the (*) required information where indicated. HTML code is not allowed.