ኢትዮጵያ በአመት ሁለት ቢሊዮን ገንዘብ በህገ ወጥ በሆነ መልኩ ወደ ሀገሯ ይገባል ሲል ክፍያ ፋይናንሺያል የአለም ባንክ ሪፖርትን ጠቅሶ ተናገረ፡፡

ኢትዮጵያ በአመት ሁለት ቢሊዮን ገንዘብ በህገ ወጥ በሆነ መልኩ ወደ ሀገሯ ይገባል ሲል ክፍያ ፋይናንሺያል የአለም ባንክ ሪፖርትን ጠቅሶ ተናገረ፡፡
እኤአ በ2015 በወጣ የወርልድ ባንክ ሪፖርት መሰረት ከሰሀራ በታች ወደሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት በአመት ወደ 36 ቢሊዮን ዶላር ይላካል፡፡ ከአፍሪካ ሀገራት መካከል ከናይጄሪያ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ የምትገኘው ኢትዮጵያ ስትሆን በአመት ከሀዋላ ከ 2 እስከ 3 ቢሊዮን ዶላር እንደምታስገባ ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡ከዚህ ገቢ ላይ 2 ቢሊዮን የሚሆነው ገንዘብ ህጋዊ ባልሆኑ መንገዶች የሚገባ ነው፡፡ ክፍያ ፋይናንሺያል በአሜሪካ ሀገር ባደረገው ጥናት መሰረት በዙዎቹ አፍሪካውያን ዲያስፖራዎች ሀገር ቤት ካሉ ወዳጆቻቸው እና ዘመዶቻቸው የቤትና የማህበራዊ ወጪዎችን ጨምሮ መጋራት እንደሚፈልጉ ጥናቱ ይጠቁማል፡፡
ይህንኑ መሰረት በማድረግ ክፍያ ፋይናንሺያል ከአለም አቀፉ ማስተር ካርድ ጋር በመሆን ከአንድ ወር በኋላ በውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያን በሀገር ውስጥ ለሚገኙ ወዳጅ ዘመዶቻቸው የስልክ፣የመብራትና የውሀ ወጪዎችን ለመክፈል የሚያስችላቸውን አገልግሎት እንደሚጀምር ተነግሯል፡፡የጥሬ ገንዘብ ዝውውርን ለማስቀረት በሚደረገው ጥረት ጥሬ ገንዘብ ይዘው አገልግሎቶች እና ግብይቶችን ለመፈፀም ከቦታ ቦታ የሚደረጉ አላስፈላጊ የገንዘብ ዝውውሮችን በማስቀረት እና በመቀነስ በእለት ተዕለት ኑሮአቸው ላይ እንዲያተኩሩ የሚያደርጋቸው አዲስ እና ቀልጣፋ መንገድ ነው ሲሉ የክፍያ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አመራር ሀላፊ የሆኑት አቶ ሙኒር ዱሪ ተናግረዋል፡፡
በቀጣይ ማስተር ካርድ እና ክፍያ አገልግሎቱን በውጪ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለዘመድ ወዳጆቻቸው የመድህን ኢንሹራንስ፣የትምህርት እና የሆስፒታል ወጪዎችን ለመክፈል ብሎም የአለም አቀፍ ጥሪ መክፈያ አገልግሎቶችን ለመክፈት በእቅድ መያዙንም ሰምተናል፡፡ማስተር ካርድ በዓለም አቀፍ ክፍያዎች ውስጥ የሚገኝ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ነው፡፡ በዓለም ላይ ፈጣን ክፍያ የማስፈፀም ሂደትን ከተለያዩ ሸማቾች፣የገንዘብ ተቋማት፣ነጋዴዎች፣መንግስታዊ ድርጅቶች እና የንግድ ድርጅቶች እንዲሁም ከ 210 በላይ ሀገራት ጋር የሚሰራ በመሆኑ ምርጫዬ አድርጌዋለሁ ሲል ክፍያ ፋይናንሺያል አሳውቆል፡፡
ዘገባው የነጋሽ በዳዳ ነው፡፡

Leave a comment

Make sure you enter the (*) required information where indicated. HTML code is not allowed.