የባቡር ትራንስፖርት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ከባቡር ትራንስፖርት ጋር በተያያዘ የሰው ህይወት መጥፋት ወንጀል እስከ 20 አመት የሚደርስ እስራት እና ከ500ሺህ ብር የማይበልጥ ገንዘብ ቅጣት ወስኗል፡፡

ረቂቅ አዋጁ ሌሎች ከትራንስፖርት ዘርፉ ጋር በተያያዘ ለሚፈጸሙ ወንጀሎችም ቅጣት ወስኗል፡፡
በህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት ለበጀት እና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ የቀረበ የባቡር ትራንስፖርት ረቂቅ አዋጅ ሳይመዘገቡ እና አገልግሎት ላይ ለመዋል የጸና የደህንነት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖራቸው የመሰረተ ልማት አስተዳዳሪነት ወይም አገልግሎት ሰጪነት ተግባርን እያከናወኑ የሰው ህይወት መጥፋትን ወይም የአካል መጉደልን አልያም ደግሞ ከአንድ ሚሊዩን ብር በላይ የሆነ የንብረት ጉዳትን ካስከተለ ከ20 አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እና ከሁለት መቶ ሺህ ብር በማያንስ እንዲሁም ከ500 ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጣ ተወስኗል፡፡
ወንጀሉ የሰው ሕይወት መጥፋን ወይም አካል መጉደልን የንብረት ጥፋቱም ከ1ሚሊየን ብር በታች ከሆነ ቅጣቱ ከ10 አመት የማይበልጥ ጽኑ እስራት እና ከ20ሺህ ብር የማይበልጥ መቀጮ ነው፡፡
ከኦዲት እና ኢንስፔክሽን መኮንን በረቂቅ አዋጁ ላይ እና በሌሎች ተያይዘው በሚወጡ ደንቦች እና መመሪያዎች በተሰጡት ስልጣን እና ተግባት ለማከናወን ወደ ሎኮሞቲቭ ፣ ፉርጎ፣ የባቡር መሰረተ ልማት ወይም እውቅና ወደ ተሰጠዉ ተቋም እንዳይገባ የከለከለ ከሆነ ወይም የኦዲት እነ ኢንስፔክሽን መኮንን ጥያቄ ማንኛውም ሰው ተገቢውን እነ እውነተኛ ምላሽ ያልሰጠወይም አግባብነት ያለው መረጃ ለማሳየት ፈቃደኛ ካልሆነ ከአንድ አመት በማይበልጥ ቀላል እስራ እና ከ20ሺህ ብር የማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል፡፡
የባቡር የደህነት ስጋ ክስተትን እና የባቡር አደጋን በህግ ስልጣን ለተሰጠው አካል አለማሳወቅ ከአንድ አመት የማይበልጥ ቀላል እስራት እና ከ20 ሺህ ብር የማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል፡፡
የደህንነት ስጋት ክስተቱን ወይም የባር አደጋ ሪፖርት ያልተደረገው የባቡር መሰረተ ልማት አስተዳዳሪውን ወይም የአገልግሎት ሰጪውን ወይም የሌላ ማናቸውንም ሰው ጥፋት ወይም ጉድለት እዳይታወቅ ለመደበቅ በማሰብ ከሆነ ከአምስት አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራ እና ከ100ሺህ ብር በማይበልጥ ገንዘብ ይቀጣል፡፡
ረቂቅ አዋጁ የኢትዩጲያ ምድር ባቡር ኮርሬሽን በተለያዩ የባቡር ትራንስፖር ፕሮጀክቶች ከ120 ቢሊየን ብር በላይ የገንዘብ እዳ ሪፖርት በተደረገበት በዚህ ወቅት ነው የወጣው፡፡ በአጠቃላይም የባቡር ትራንስፖርቱን ዘርፍ ለማተዳደር የተቀረጸ ነው፡፡
የባቡር ትራንስፖርት ዘርፍ ለማስተዳደር ህግ አውጥተው ተቋም አቋቁመው ህግ ካወጡ ሀገራት አንዷ አሜሪካ ናት፡፡ የትራንስፖርት ዘርፉን ለማስተድደር በ1879 አ.ም ኢንተርስቴት ኮሜርስ አክት በሚል አርእስት ያጣች ሲሆን የህጉን ማእቀፍ በ1898 አሻሽላዋለች፡፡
ናርዶስ ዩሴፍ

Leave a comment

Make sure you enter the (*) required information where indicated. HTML code is not allowed.