የኢትዮጲያ የምግብ የመድሃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ከወሰዱት ፍቃድ ውጭ የምግብ ዝግጅት ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች መኖራቸውን አሳወቀ፡፡

ሰኔ 16/2008 ዓ.ም

ከዋናው ቢሮ በተጨማሪ በስድስት የክልል ከተሞች ቅርንጫፎችን በመክፈት የቁጥጥር ስራ ላይ የተሰማራው ባለስልጣኑ በድህረ ምልከታ ወቅት ቀድሞ ከተፈቀደላቸው የምግብ ምርትና ዝግጅት ውጭ ፍቃድ ባልወሰዱበት ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ድርጅቶች ጉዳይ እንዳሳሰበው ተናግሯል፡፡ በአሁኑ ወቅት 30 የወተት አምራች ኩባንያዎች ከባለስልጣኑ ፈቃድ ወስደው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

ከንግድ ቢሮ ጋር በመተባበር እየሰራሁ ነው የሚለው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እስከ ስድስት ወር ድረስ የምርት ማምረት እገዳ በመጣል የማስተካከያ እርምጃ የተወሰደባቸው ድርጅቶችም መኖራቸውን አሳውቋል፡፡ በቅርቡ በለስላሳ መጠጦች ምክንያት የሰዎች ህይወት አልፏል መባሉን ተከትሎ የምርመራና ቁጥጥር ስራ የሰራው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑን ማረጋገጥ እንደቻለ የኢትዮጲያ የምግብ የመድሃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን የምግብ ምዝገባና ፈቃድ ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ግርማ ለዛሚ ተናግረዋል፡፡ (እንየው ቢሆነኝ)

Leave a comment

Make sure you enter the (*) required information where indicated. HTML code is not allowed.