አለም አቀፍ ዜናዎች (169)

Friday, 19 September 2014 12:25

ለጋዛ መልሶ ግንባታ ሳዒዱ አረቢያ ግማሽ ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለመስጠት ቃል ገባች፡፡

መስከረም 9/2006

በፍልስጤም እና በእስራኤል መሃከል ተከስቶ በነበረው ደም አፋሳሽ እልቂት ብዙዎች ህይወታቸውን ሲያጡ፤ በርካታ መኖሪያ ቤቶች ወደ ፍርስራሽነት ተቀይረዋል፤ የመሰረተ ልማት አውታሮችም በጋዛ ተናግረው ይገኛሉ፡፡ በጋዛ ሰርጥ የደረሰውን መፈራረስ መልሶ ለመገንባት በቀጣይ ሶስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ 4 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንደሚያስፈልግ የፍልስጤም ጠቅላይ ሚኒስትር ራሚ አል አምደላህ ተናግረዋል፡፡ በግብፅ ሸምጋይነት በካይሮ በሚደረገው የጋዛ መልሶ ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ አሜሪካ፣ አውሮፓ ህብረት አባል ሀገራትን ጨምሮ ኳታር እና ቱርክ እንደሚገኙ እና ድጋፍ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡ ሳኡዲ ቀደም ካለ ድጋፉን ለማድረግ ቃል መግባቷ ለፍልስጤም ያላትን አጋርነት ያሳየ ነው ተብሏል፡፡

እስራኤል በበኩሏ ለጋዛ ዳግም ግንባታ የሚውል ቁሳቁሶች እንዲገቡ መፍቀዷ ይታወሳል፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ተቆጣጣሪነት በሁለት ሳምንት ውስጥ ወደ ጋዛ ሰርጥ ለሚገቡ የግንባታ እቃዎች እስራኤል ይሁንታ ሰጥታለች፡፡ ዘገባው የሮይተርስ ነው፡፡

Friday, 19 September 2014 12:23

የሊቢያ የቀድሞው የአየር ሃይል መሪ በቤንጋዚ መገደላቸው ተሰማ፡፡

መስከረም 9/2006

አህመድ ሀቢብ አል ማስማሪ ምሽት ላይ ባልታወቁ ታጣቂዎች ጥይት በተደጋጋሚ የተተኮሰባቸው ሲሆን የቤንጋዚ የህክምና ማዕከልም ህይወታቸው ወዲያው ማለፉንና በበርካታ ጥይቶች መደብደባቸውን አመላክቷል፡፡የዜናው ምንጭ ዢንዋ ነው፡፡

Friday, 19 September 2014 12:22

ጊኒ በኢቦላ በሽታ /ቫይረስ/ ዙሪያ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለመስጠት በሚል በተለያዩ መንደሮች ውስጥ ገብተው የጠፉትን የጤና ባለሞያዎች የሚፈልግ ቡድን አሰማርታለች፡፡

መስከረም 9/2006

ከሁለት ቀናት በፊት በየመንደሩ ሲዞሩ ጥቃት የደረሰባቸውና አሁንም ያሉበት ያልታወቁት ባለሞያዎች ጉዳይ አሳሳቢ ሆኗል፡፡

ያልተረጋገጡ ሪፖርቶች ግን ታግተው ወይም ተገድለው እንደሆነ እያመላከቱ ነው፡፡

እማኞች እንደሚሉት በጤና ቡድኑ ላይ ከአካባቢው ነዋሪ ድንጋይ ሲወረወር ነበር፡፤

በቅርቡ እየወጡ ያሉ መረጃዎች በሚያመላክቱት መሰረት ደግሞ ግንዛቤውን ለመስጠት በጊኒ የሚንቀሳቀሱት ልዑካን መልካም አቀባበር እያገኙ አይደለም ከዚህ ቀደምም ይፋ ያልሆኑ ጥቃቶች መኖራቸው ተጠቁሟል፡፡

ከጠቱት ሰዎች ውስጥ ጋዜጠኞችና የሀገር ውስጥ ከፍተኛ ባለስልጣናት እንደሚገኙም ምንጮች እየተናገሩ ነው፡፡ ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡

Friday, 19 September 2014 12:21

በግብፅ ለእዕምሮ ህመም የሚያጋልጥ ነው የተባለ ህገ-ወጥ መድሀኒትን ይዞ ለመግባት የሞከረ ግለሰብ በቁጥጥ ስር ዋለ፡፡

መስከረም 9/2006

ግለሰቡ በግብፅ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ 420 ያህል ለአዕምሮ ህመም የሚያጋልጡ የተባሉና በግለሰብ ደረጃም ያለ ሀኪም ትዕዛዝ ይዞ መገኘት የማይፈቀዱ መድሀኒቶችን በህገ-ወጥ መንገድ ይዞ ለመግት ሲሞክር ነው በደህንነት ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋለው፡፡

በፍተሸ ወቅት በቦርሳው የያዛቸው እቃዎች በ x-ray ሲፈተሸ መድሀኒቶቹ እንደተገኙ ተነግሯል፡፡

የግብፅ መንግስት የግለሰቡን ስም መግለፅ ሳይፈልግ ቀርቷል ነገር ግን ከባድ ቅጣት እንደሚጠብቀው ተነግሯል፡፡

ዜናውን ኦል አፍሪካን ድረገፅ ዘግቦታል፡፡

Thursday, 18 September 2014 14:42

ስኮትላንዳውያን ከእንግሊዝ ለመገንጠል ህዝበ ውሳኔ ሰጥተዋል፡፡

መስከረም 8/2006

የስኮትላንድን መገንጠል በሚደግፉና የሀገሪቱን መገንጠል በሚቃወሙ ሁለት ወገኖች መካከል በሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ፣ የስኮትላንድን መገንጠል በሚቃወሙ ወገኖች ድምፅ የበላይነት እንደቀጠለ ነው፡፡

የስኮትላንድ ተቀዳሚ ሚኒስትር አሌክስ ሳልሞንድ ለመራጮች እንዳሉት ሀገሪቱ እንድትገነጠል ይሁኝታቸውን በድምፃቸው እንዲሰጡ ጠይቀዋል፡፡ የሀገሪቱን መገንጠል የሚቃወሙ በበኩላቸው ድምፅ ሰጪዎች ለስኮትላንድ መገንጠል አሉታዊ ድምፃቸውን እንዲሰጡ ቅስቀሳ እያደረጉ ይገኛል፡፡ ዛሬ በሚደረገው የህዝብ ውሳኔ ድምፅ የ307 ዓመት ጥምረታቸው ያበቃለታል ወይስ ይቀጥላል የሚለው ይታወቃል፡፡ ከ4 ሚሊዮን በላይ መራጮች የተመዘገቡ ሲሆን ከ2006 በላይ ድምፅ መስጫ ቦታዎች ተዘጋጅተዋል፡፡ ዘገባው የሮይተርስ ነው፡፡

Thursday, 18 September 2014 14:42

የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ጉደላክ ጆናታን በሀገሪቱ አሁን ላይ ምንም አይነት የተመዘገበ የ ኢቦላ የቫይረስ ተጠቂ እንደሌለ አስታወቁ፡፡

መስከረም 8/2006

በበሽታው ተይዘው ከነበሩ 19 ሰዎች መካከል 7ቱ ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ድነዋል ተብሏል፡፡

አሁንም እየተመለከትናቸውና ተከልለው የተቀመጡ ሰዎች አሉ ነገር ግን ሀገሪቱ ከቫይሰሩ ነፃ መሆኗን አረጋግጠናል ሲሉ በአቡጃ ተገኝተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም በሀገሪቱ ት/ቤቶች እንዲዘጉ መወሰናችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ሌላ ትርጉም ተሰጥቶታል፡፡ ነገር ግን እርምጃው የተወሰነው ወጥነት ያለውን የመከላከል ስራ ተግባራዊ ለማድረግ ነው ብለዋል፡፡ በሌሎች ሀገራት የሚገኙ በርካታ ናይጄሪያውያን በሽታውን ይዘው ይመጣሉ በሚል ግምት ከፍተኛ የሆነ መገለል እየደረሰባቸው እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ገፅታውን መቀየር አስፈላጊ እንደሆነም ጆናታን አሳስበዋል፡፡

ዘገባው የዥንዋ ነው፡፡ 

Wednesday, 17 September 2014 12:16

በካቡል በደረሰው የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት 3 የኔቶ (NATO) ወታደሮች ተገደሉ፡፡

መስከረም 07/2007

ጥቃቱ የደረሰው በታሊባኑ ታጣቂዎች መሆኑ ታውቋል፡፡ ከሞቱት ወታደሮች በተጨማሪ 16 ንፁሃን ዜጎች መጎዳታቸውን መንግሥት አስታውቋል፡፡ 4ቱ የኔቶ ወታደሮች ሲሆኑ ጉዳታቸው የከፋ ነው፡፡ አደጋው የተከሰተው የትራፊክ መጨናን በበዛበት መንገድ ላይ በመኪና በተጠመደ ቦንብ ነው፡፡ መንገዱ ለአሜሪከ ኤምባሲ ቅርብ ነው ተብሏል፡፡

ፍንዳታው የአካባቢው ያሉትን ህንፃዎች አናግቷል፡፡ በጥቃቱ የሞቱት የኔቶ ወታደሮ ዜግነት አልተነገረም፡፡ በአፍጋኒስታን የተደረገውን ምርጫ ተከትሎ በሁለቱ ተፎካካሪዎች መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር፤ ይህም ለታሊባን ተመችቷታል ሲል AFP ገልጧል፡፡

ሁለቱ ተፎካካሪዎች ስልጣን ለመጋራት ወደ ስምምነት እየመጡ ነው እየተባለ ይገኛል፡፡ ዘገባው የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ነው፡፡

 

Tuesday, 16 September 2014 13:32

አሜሪካ የኢቦላ ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ወደ ላይቤሪያ 3000 ወታደሮችን እንደምትልክ ተነገረ፡፡

መስከረም 06/2007

የኢቦላ ቫይረስ ስርጭትና ስጋቱ ለምእራብ አፍሪካ ሀገራት ብቻ ሊሆን አይገባውም በሚል የተለያዩ ባለድርሻ አካላትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ርብርብ እያደረጉ ነው፡፡ ምንጮች እዳመላከቱት ከሆነ ግን አሁንም በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተደረገ ያለው እገዛ አመርቂ አይደለም፡፡

በህክምና ጓንት አምራችነት የምትታወቀው ማሌዥያ ለጤና ባለሞያዎች የሚሆን 20 ሚሊዮን ጓንት ለአምስት ሀገራት እንደምትለግስ መነገሩን ተከትሎ ከወደ አሜሪካም አዲስ ነገር ተነስቷል፡፡ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ዛሬ እቅዳቸውን ሙሉ ለሙሉ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በተለይም ስርጭቱ በከፋባት በላይቤሪያ 3000 ያህል ወታደሮች /ደጋፊ አካላት/ እንደሚላኩ ታውቋል፡፡ በተለይም የከፋ ስጋት ውስጥ ባሉት ላይቤሪያ፣ ሴራሊዮንና ጊኒ ከ2400 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ ብዙሃኑ በላይቤሪያ የሚኖሩ ነበሩ፡፡ የተ.መ.ድ ባለስልጣናት በጉዳዩ ላይ በጄኔቫ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከአሜሪካ የሚላኩት ደጋፊ ቡድኖች በሳምንት 500 የጤና አጋዥ ባለሞያዎችን ለማፍራት ስልጠና መስጠትን በዋናነት ያካሂዳሉ ከዚህም ባሻገር ወደ 17 የሚጠጉ የጤና ተቋማትን በውስጣቸው 100 መኝታ በማሟላት ይገነባሉ፡፡ በተጨማሪ በቤት ውስጥ በሽታውን ለመከላከል የሚያስችሉ መሳሪያዎችን እንደሚሰጡና ቤት ለቤትም ስልጠና መስጠት እንደሚጠበቅባቸው ዘገባው አመላክቷል፡፡

Monday, 15 September 2014 09:27

አውስትራሊያ 600 የጦር ሃይል ወደ ዩናይትድ አረብ ኤምሬት ላከች፡፡ ወታደሮች የተላኩት IS የተሰኘውን ፅንፈኛ ቡድን ለመውጋት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ መሆኑ ተገልጧል፡፡

መስከረም 05/2006

ጠቅላይ ሚንስትሩ ቶኒ አቦት እንደተናገሩት ጦሩ የተላከው አሜሪካ ባቀረበችው ጥያቄ መሰረት ነው፡፡

በኢራቅ ያለውን ፅንፈኛ ቡድን ለመውጋት 40 ሀገራት ተባባሪነታቸውን አሳይተዋል፤ ከነዚህ መካከል አስሩ የአረብ ሀገራት ናቸው፡፡

ከአውስትራሊያ ጦር ጋር የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች እንደሚጓዙም ተነግሯል፡፡

በIS የፅንፈኛ ቡድን ላይ ሊወሰዱ ስለሚገቡ እርምጃዎች በፈረንሳይ ምክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Monday, 15 September 2014 09:25

የተ.መ.ድ ዋና ፀሃፊ ባንኩሙን በማሊ የተላኩ ሰላም አስከባሪዎች ላይ በደረሰው ጥቃት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል፡፡

መስከረም 05/2006

በተ.መ.ድ ሰላም አስከባሪዎች ተሽከርካሪ ላይ በደረሰው ጥቃት አንድ ካናዳዊ ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል፤ በዚሁ ጥቃት ሌሎች 4 ሰላም አስከባሪዎች መቁሰላቸውንም ዢንዋ ዘግቧል፡፡

ዋና ፀሃፊው በኪዳልl ግዛት በፈረንጆቹ መስከረም 2 ላይ ደርሶ የነበረውን ጥቃትና 4 የሰላም አስከባሪዎች ላይ የደረሰውን ተመሳሳይ አስከፊ እጣም አንስተዋል፡፡

Wednesday, 10 September 2014 08:40

በሰሜን ምዕራብ ጀርመን በደረሰ ፍንዳታ በርካታ ሰዎች ተጎዱ ፡፡

ጳጉሜ 05/2006

በአደጋውየተነሳ  አንድ  ሰው  ቆስሎ  ሌሎችምተጎድተዋል፡፡የሀገሪቱ  ፖሊስ  እንዳለውበስፍራው  የነበሩቤቶች  ከስፍራው  እንዲሪቁ  ተደርጎል፡፡

አብዛኛውቹ  ተቃጥለዋል፡፡እስካሁን  ፍንዳታውመንሰኤ  በውል  አልተለየም  የማጣራት  ሂደቱም  ቀጥላልተብሏል፡፡ፖሊስ  እንዳለው  ከሆነ   ተጎጂወቹ   ሄሊኮፍተር  ወደ  ሆስፒታል  ተወስዶል፡፡

ዘገባው  ቢቢሲ  ነው፡፡

Monday, 08 September 2014 09:07

የሱዳን የጭነት በረራ አውሮፕላን በርካታ የጦር መሳሪያዎችን እንደያዘ በሊቢያ መያዙ ተነገረ፡፡

በ ኩፍራ ከተማ የተያዘው ይኸው ጭነት ሊቢያ በሱዳን ላይ ጥርጣሬ እንድታነሳ የሚያደርግ እንደሆነም እየተነገረ ነው፡፡ የሀገሪቱ ዜና አገልግሎት ትናንት እንዳስታወቀው የተያዙት የጦር መሳሪያዎች ሱዳን በሊቢያ ራስምታት የሆኑትን እስላማዊ ተዋጊዎችን እንደምትደግፍ የሚያመላክት ወይም ማስረጃ የሚሆን ነው፡፡ የተያዙት የጦር መሳሪያዎች በሙሉም የመግቢያ ፍቃድ ያልያዙ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡

ነገር ግን የሱዳን መንግሥት ለጉዳዩ ማስተባበያ ሰጥቶበታል፤ በጉዳዩ ላይ የተሳሳተ ምልከታ ተደርጓል፡፡ የተላኩት የጦር መሳሪያዎች ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ሸቀጥ ማስገባትንና ህገ-ወጥ ዝውውርን ለመከላከል የታሰቡ ናቸው ብለዋል፡፡

ከሱዳንም በተጨማሪ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ግብፅ እንዲሁም ኳታር እስላማዊ ቡድኑን ይረዳሉ የሚል ጥርጣሬ እየተነሳ ነው፡፡ በተለይም ግብፅና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጥቃት ማድረሳቸው እየተነገረ ቢሆንም ግብፅ ግን ጉዳዩ መሰረተ ቢስ ውንጀላ ስትል አጣጥላዋለች፡፡

ዘገባው የዥንዋ ነው፡፡

Wednesday, 03 September 2014 09:38

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኢቦላ ቫይረስ ስጋት ውስጥ ባሉ ሀገራት የምግብ ዋጋ ሊጨምር እንደሚችል አሳሰበ፡፡

ነሐሴ 28/2006- ለዚህ ምክንያቱ በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩት ምርታቸውን በሚሰበስቡበት ጊዜ ላይ ምቹ ሁኔታን ባለማግኘታቸው ነው፡፡ በተለይም የሩዝና የበቆሎ ምርት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እንደሚደርስ ተገምቷል፡፡

በምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ስርጭቱ እየጨመረ ያለው የኢቦላ ቫይረስ ከ1,500 የሚበልጡ ሰዎች ህይወታቸውን እንዲያጡ ምክንያት ሆኗል፡፡ ይህም ስርጭቱ በታየባቸው ቦታዎች ከፍተኛ ጥበቃ እንዲደረግና ተከልለው እንዲቆዩም አድርጓል፡፡ የተለያዩ ሀገራትም ድንበራቸውን ከመዝጋት ባሻገር በረራዎችን ሰርዘዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብና ግብርና ተቋም /FAO/ በትናንትናው እለት እንዳስታወቀው እነዚህ ስርጭቱን ለመግታት በሚል የተወሰዱ እርምጃዎች በምግብ ግብይት ላይ ለውጥን የሚፈጥሩ ናቸው፡፡ 150 በመቶ ያህል ጭማሪ እንደሚኖርም ግምት ተቀምጧል፡፡ ሪፖርቱ እንዳመላከተው በላይቤሪያ፣ ጊኒ እና ሴራሊዮን 1.3 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች የምግብ እርዳታን ይፈልጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ዘገባው የአሶሼትድ ፕሬስ ነው፡፡

Friday, 29 August 2014 11:35

የጀርመን መንግሥት የኢራቅ ኩርዶችን ለማስታጠቅ መወሰኑ በሀገሪቱ በስፋት እያነጋገረ ይገኛል፡፡

ነሐሴ 23/2006

ፈረንሳይን የመሳሰሉ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ታጣቂ ቡድኑን አይ ኤስ አይ ኤስ ለመፋለም ያስችላቸው ዘንድ ለኩርድ ሃይሎች የጦር መሳሪያ እናቀርባለን በሚሉበት ወቅት ጀርመን ወደ ኢራቅ የጦር መሳሪያዎችን እንደማትልክ አስታውቃ ነበር፡፡ ጀርመን ሰብዓዊ እርዳታን ብቻ ለኢራቅ እንደምትሰጥ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየርም ተናግረው ነበር፡፡ ምንም እንኳን የመንግሥት ባለስልጣናት ይህንን አቋማቸውን ሲያንፀባርቁ ቢቆዩም አሁን ግን ታጣቂ ሃይሉን ለሚዋጉ የኢራቅ ኩርድ ፔሽሜርጋ ተዋጊዎች ጀርመን በልዩ አስተያየት ለማስታጠቅ መወሰኗን አስታውቃለች፡፡ ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረግ መንገድ ላይ ነን፤ የትጥቅ እርዳታም ያስፈልጋል፤ የኩርድ ሃይሎች ከአሜሪካ እና ከሌሎች ጋር ሆነው ጥቃቱን እየመከቱ ነው እኛም የድርሻችንን መወጣት አለብን ሲሉ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ተናግረዋል፡፡ ይህም ደግሞ ለጀርመናዊያኑ የመነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ የሆነ ሲሆን በእርዳታ የሚሰጡ የጦር መሳሪያዎች ከታሰበላቸው ቦታና ኢላማ ውጭ መዋል አለመዋላቸው አሳሳቢ ጉዳይ ነው እየተባለ ይገኛል፡፡ ዘገባው የዩሮ ኒውስ ነው፡፡    

Wednesday, 30 July 2014 18:48

ከ11,000 በላይ የሚሆኑ ሶሪያውያን ህፃናት በእርስ በርስ ጦርነት ም/ክ ህይወታቸው ማለፉ ተነገረ፤

ሶሪያ ለዓመታት ባስቆጠረው የእርስ በርስ ጦርነት ሳቢያ ከ100,000 በላይ ዜጎቿን አጥታለች፤ የሶሪያ መንግስት በስር ኦላሳድ ስልጣኔን አለቅም የተቃዋሚዎች የትለቃለህ ጥያቄ ከተራ ተቃውሞ አንስቶ ዜጎች እልቂት ምክንያት ሆኗል፡፡ እስካሁን ያልረገበው ይኸው አመፅ ታዲያ ለበርካታ ህፃናት በአነጣጣሪ ተኳሶች በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው ማለፉ ነው፤ እንደ ኦክስፎርድ ጥናታዊ ቡድን ዘገባ ከሆነ ከ11,420 ህፃናትም ውስጥ በርካቶች በፍንዳታ ምክንያት ሲሞቱ ሌሎችም በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል፡፡ (ቤተልሔም ለገሰ)