Super User

Super User

Email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ኢትዮጵያ በአመት ሁለት ቢሊዮን ገንዘብ በህገ ወጥ በሆነ መልኩ ወደ ሀገሯ ይገባል ሲል ክፍያ ፋይናንሺያል የአለም ባንክ ሪፖርትን ጠቅሶ ተናገረ፡፡
እኤአ በ2015 በወጣ የወርልድ ባንክ ሪፖርት መሰረት ከሰሀራ በታች ወደሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት በአመት ወደ 36 ቢሊዮን ዶላር ይላካል፡፡ ከአፍሪካ ሀገራት መካከል ከናይጄሪያ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ የምትገኘው ኢትዮጵያ ስትሆን በአመት ከሀዋላ ከ 2 እስከ 3 ቢሊዮን ዶላር እንደምታስገባ ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡ከዚህ ገቢ ላይ 2 ቢሊዮን የሚሆነው ገንዘብ ህጋዊ ባልሆኑ መንገዶች የሚገባ ነው፡፡ ክፍያ ፋይናንሺያል በአሜሪካ ሀገር ባደረገው ጥናት መሰረት በዙዎቹ አፍሪካውያን ዲያስፖራዎች ሀገር ቤት ካሉ ወዳጆቻቸው እና ዘመዶቻቸው የቤትና የማህበራዊ ወጪዎችን ጨምሮ መጋራት እንደሚፈልጉ ጥናቱ ይጠቁማል፡፡
ይህንኑ መሰረት በማድረግ ክፍያ ፋይናንሺያል ከአለም አቀፉ ማስተር ካርድ ጋር በመሆን ከአንድ ወር በኋላ በውጪ ያሉ ኢትዮጵያውያን በሀገር ውስጥ ለሚገኙ ወዳጅ ዘመዶቻቸው የስልክ፣የመብራትና የውሀ ወጪዎችን ለመክፈል የሚያስችላቸውን አገልግሎት እንደሚጀምር ተነግሯል፡፡የጥሬ ገንዘብ ዝውውርን ለማስቀረት በሚደረገው ጥረት ጥሬ ገንዘብ ይዘው አገልግሎቶች እና ግብይቶችን ለመፈፀም ከቦታ ቦታ የሚደረጉ አላስፈላጊ የገንዘብ ዝውውሮችን በማስቀረት እና በመቀነስ በእለት ተዕለት ኑሮአቸው ላይ እንዲያተኩሩ የሚያደርጋቸው አዲስ እና ቀልጣፋ መንገድ ነው ሲሉ የክፍያ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አመራር ሀላፊ የሆኑት አቶ ሙኒር ዱሪ ተናግረዋል፡፡
በቀጣይ ማስተር ካርድ እና ክፍያ አገልግሎቱን በውጪ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለዘመድ ወዳጆቻቸው የመድህን ኢንሹራንስ፣የትምህርት እና የሆስፒታል ወጪዎችን ለመክፈል ብሎም የአለም አቀፍ ጥሪ መክፈያ አገልግሎቶችን ለመክፈት በእቅድ መያዙንም ሰምተናል፡፡ማስተር ካርድ በዓለም አቀፍ ክፍያዎች ውስጥ የሚገኝ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ነው፡፡ በዓለም ላይ ፈጣን ክፍያ የማስፈፀም ሂደትን ከተለያዩ ሸማቾች፣የገንዘብ ተቋማት፣ነጋዴዎች፣መንግስታዊ ድርጅቶች እና የንግድ ድርጅቶች እንዲሁም ከ 210 በላይ ሀገራት ጋር የሚሰራ በመሆኑ ምርጫዬ አድርጌዋለሁ ሲል ክፍያ ፋይናንሺያል አሳውቆል፡፡
ዘገባው የነጋሽ በዳዳ ነው፡፡

የንግድ ሚንስቴር ከኤክስፖርት ዘርፍ 4.3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ቢጠብቅም ከ2.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ መሰብሰብ አልቻለም፡፡
የውጪ ምንዛሬን በከፍተኛ ደረጃ ያስገኛል የተባለው የኤክስፖርት ዕቅድ ግቡን መምታት አለመቻሉን ነው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንግድ ሚኒስቴር ሪፖርት የሚያመላክተው፡፡ከሁሉም ዘርፎች ለውጪ ገበያ በማቅረብ 4.3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት የታሰበ ቢሆንም የእቅዱ 59 ከመቶ 2.53 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ብቻ እንደተገኘ ተነግሯል፡፡ ከገቢ ድርሻ አንፃር 77.5 በመቶ ከግብርና ምርቶች፣14.3 በመቶ ከኢንዱስትሪ ውጤቶች፣7.1 በመቶ ከማዕድን ቀሪው 1.1 በመቶ የሌሎች ዘርፎች እንደሆነ መረጃው ያመላክታል፡፡ የሀገሪቱን የቀጣይ የኢኮኖሚ ሸክም ይሸከማል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የኢንዱስትሪው ውጤቶች በአገልግሎት ካረጀው ግብርና ጋር ሲነፃፀር ከግማሽ በታች ውጤት አስመዝግቧል፡፡
የግብርና ምርቶችን በተመለከተ በዓለም ገበያ ላይ ያለው የግብርና ምርቶች ዋጋ መቀዛቀዝና ተወዳዳሪ መሆን አለመቻል ለጉድለቱ ቀዳሚ ምክንያት ተብሎ በሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ተቀምጧል፡፡የግብርና ምርቶችን አቅርቦት በጥራትና በመጠን ያለማሳደግ፣በአምራች ኢንዱስትሪው የግብአት አቅርቦትና የጥራት ችግር መኖር ተከታይ ችግሮች ተብለው ተለይተው ተነግረዋል፡፡በዚህ ችግር ብቻ ያልተገታው ኤክስፖርቱ የሀገር ውስጥ ዋጋ ሳቢ በመሆኑ ፋብሪካዎች ለሀገር ውስጥ ገበያ ማቅረብ መምረጣቸው፣በአንዳንድ ክልሎች የኮንትሮባንድ ንግድ መስፋፋት እና የግብይት ስርዓቱ ውስጥ የሚሰተዋሉ ክፍተቶች ተደማምረው ለሀገሪቱ የውጪ ምንዛሬ እንዳይገባ አድርገዋል ሲል የንግድ ሚንስቴር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ11 ወራት ሪፖርቱን ሲያስደምጥ አብራርቷል፡፡
ዘገባው የነጋሽ በዳዳ ነው፡፡

ሞዛምቢክ 500 ሚሊየን ዶላር ብድር ምን ላይ እንደዋለ አላውቅም አለች ፡፡ አለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ ድርጅት ምርመራ ላይ ነው፡፡

አለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ አዲስ የእርዳታ ፕግራም የእርዳታ ፕግራም ድርድር ከመጀመሩ በፊት የሞዛምቢክ መንግስት ድርጅቶች ከዚህ ቀደም ከተለቀቀ 2 ቢሊዩን ዶላር ላይ 500 ሚሊዩኑ ኦዲት ያልተደረገ እና ለምን እንደዋለ ያልተገለጸ ገንዘብ መኖሩን ክሮል ኤልኤልሲ የተባለ ድርጅት ሪፖርት አድርጓል ስለዚህም ከመቀጠሌ በፊት ምርመራ ማድረግ አለብኝ ብሏል፡፡

የክሮል ሪፖርት ባሳለፍነው አመት ለሞዛምቢክ አቶርኒ ጄነራል የተሰጠ በጣም አስፈላጊ ለሆኑ ጉዳዩች እንዲውል የታቀደበት የ500 ሚሊዩን ዶላር ወጪ ኦዲት እንዳልተደረገ እና ለምን እንደወጣ እንዳልተብራራ ያሳያል፡፡

አቶርኒ ጄነራሉ ሪፖርቱ የደረሰው ባፈው ወር ቢሆንም ግኝቱን ለማሳወቅ ግምገማ ለማድረግ በሚል ሳይናገር ቆይቷል፡፡

ለብድሩ ሁለት ድርጅቶች ብድሩን ለማመቻቸት ወደ 200 ሚሊዩን ዶላር የሚጠጋ ክፍያ እንደተከፈላቸው መሰረቱን ኒው ዩርክ ያደረገ መርማሪ ለ ብሉምበርግ የዜና ምንጭ ተናግሯል፡፡ ድርጅቶቹ የገንዘብ ክፍያውን በተመለከተ ምንም አይነት አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

አለምአቀፍ የገንዘብ ፈንድ ድርጅት ሀገሪቷን ፈንድ ማድረጌን መቀጠል ካብኝ ምርመራ አስፈላጊ ነው ብሏል፡፡ የገንዘቡን ወጪ በተመለከተ የመረጃ ክፍተት ካለ ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ካልሆነ ግን ኦዲት ማድረግ እንዳለበት ተናግሯል፡፡
ብድርን በተመለከተ የተሻለ ግልጽነት እንዲኖር እነዚህ ዶክመንቶች ወሳኝ ናቸው ሲል ቅዳሜ እለት መግለጫ ሰጥቷል፡፡
በ ሶስት የመንግስት ድርጅቶች ላይ አሁን የሚደረገው ኦዲት ቀጣይ ከተበዳሪዋ ሞዛምቢክ ጋር ቀጣይ ብድሮችን ለመደራደር እና ከአለምአቀፉ ድርጅት ጋርም ያላትን ግንኙነት ለመጠገን መንገድ መጥረጊያ መንገድ ነው፡፡
ባሳለፍነው ሚያዚያ የሞዛምቢክ መንግስት ንብረትነታው የመንግስት ለሆነ ሁለት ድርጅቶች ከዚህ በፊት ተደራድሮ የጨረሳቸው ሁለት ድምራቸው አንድ ቢሊየን ዶላር ድብቅ የብድር ስምምነቶች መለቀቅ እንዳረጋገጠ ከተናገረ በኋላ ነው የገንዘብ ፈንድ ድርጅቱ በአለም 9ኛ ደሀ ሀገር ለሆነችው ሞዛምቢክ ሊለቅ የነበረውን ክፍያ የሰረዘው፡፡
በክሮል ኤል ኤል ሲ የተዘጋጀው ይህ የ67 ገጽ ሪፖርት ለሁለት የመንግስት ድርጅቶች ፕሮጀክት የተፈቀደው ይህ ብድር ለፕሮጀክታቸው ዋና ኮንትራክተር የተከፈለ ገንዘብ ላይም ጥያቄ አንስቷል፡፡ ክሮል ቀጥሮ ባስመረመራቸው ባሙያዎች ግምት 505 ሚሊዩን ዶላር እንደሆኑ በፕሮጀክቱ ለተገመቱ መርከቦች እና አውሮፕላኖች ከዋና ኮንትራክተሩ ውጪ በሌሎች ሁለት ኮንትራክተሮች በኩል በ1.2 ቢለየን ዶላር እንደተገዙ ያሳያል፡፡
ዋና ኮንትራክተሩ የኦዲት ሪፖርቱን ለምርመራው እንደተባበርን ያሳያል ሲል ተቀብሎታ፡፡ ክሮል በግዢዎቹ ላይ ያቀረበው ዋጋ ግን ሁለቱ የሞዛምቢኮቹ ድርጅቶች የከፈሉት ከሌሎች ደንበኞች ጋር በማነጻጸር የቀረበ ዋጋ እንደሆነ ተናግሮ ክሱን ውድቅ አድርጓል፡፡
የአለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ ድርጅት ቡድን የምርመራውን ግኝት ለመወያየት እና የሀገሪቷን ማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ ለመወያየት እንዲሁም የቀጣይ አመት በጀት ላይ ለመነጋገር ከሀምሌ ሁለት ጀም የ9 ቀን ቆይታ ያደርጋል፡፡
ኤስ ኤንድ ግሎባል ሬቲንግ የተባ ድርጅት የሞዛምቢክን የብድር መጠን በዚህ አመት ጥር ወር ላይ አስልቶ የነበረ ሲሆን የሀገሪቷ የተጣራ ብድር ከአመታዊ የምርት እድገቷ 90 ፐርሰንቱን እንደሚወስድ ዘግቧል፡፡
ዘገባው የብሉምበርግ ነው፡፡

ጉባኤው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ህብረተሰቡ የሚከተሉትን አማራጮች እንዲጠቀምም ኮሚሽኑ አስታውቋል።
ከፓርላማ መብራት- በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ መስቀል አደባባይ፣ ፍላሚንጎ፣ ኦሎምፒያ፣ ወሎ ሰፈር፣ ጃፓን ኤምባሲ፣ ፍሬንድ ሺፕ፣ ቦሌ ቀለበት መንገድ፣ ኤርፖርት እንዲሁም ከፓርላማ መብራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በብሄራዊ ቤተመንግስት፣ በፍልውሃ፣ በብሄራዊ ቴአትር፣ ሜክሲኮ አደባባይና አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዙሪያ ያሉ መንገዶች ዝግ ናቸው።
በተጨማሪም ከፓርላማ መብራት፣ በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን፣ ፍልውሃና አምባሳደር ቴአትር ዙሪያውንና ከንግድ ምክር ቤት ጀምሮ በሱዳን ኤምባሲ እስከ አፍሪካ ህብረት ዋናው በር ድረስ በሁለቱም አቅጣጫዎች ከሰኔ 20 ቀን 2009 ዓም ጀምሮ እንግዶች እስኪመለሱ ድረስ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የማይቻል መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል።
በተመሳሳይ ከጦር ኃይሎች ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች በኮካኮላ ድልድይ፣ በአብነት ተክለኃይማኖት ወይም በሞላ ማሩ ጌጃ ሰፈር፣ ጎማ ቁጠባ እንዲሁም ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡት ደግሞ ሳር ቤት፣ ካርል አደባባይ፣ በልደታ አድርገው መርካቶና ጎማ ቁጠባ፣ በሳር ቤት ወደ ቄራ፣ ጎተራ ያለውን መንገድ እንዲጠቀሙ አሳስቧል።
ለቦሌ መንገድ ተጠቃሚዎች ደግሞ በአትላስ፣ ዘሪሁን ህንጻ፣ ሲግናል፣ ቀለበት መንገድ፣ ቦሌ ሚካኤል፣ ሃኪም ማሞ፣ ወደ ጎተራ፣ ቀለበት መንገድ፣ መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ፣ እንግሊዝ ኤምባሲ፣ ቀለበት መንገድ፣ መገናኛ፣ አድዋ ጎዳና፣ አዋሬ፣ ቤሊየርና በፍላሚንጎ ደንበል ጀርባ መስቀል ፍላወርን መጠቀም እንደሚቻል ጠቁሟል።
መረጃ የኢዜአ

ፅንፈኛው አይ ኤስ ከኢራቅ 7 ንፁኀንን በግፍ ገድሏል
የኢራቅ የደህንነት ምንጭ ባግዳድ እንደገለፀው በትላንትናው እለት የኢድ-አልፈጥርን የሶላት
ስነ -ስረአት እንዳበቃ ሰባት ንፁአን ዜጎችን በሰቃቂ ሁኔታ ሁለት መቶ አምሳ ኪሎ ሜትር
በሰሜን ባግዳድ ርቀት በኪርኩክ አውራጃ ነው ተጥለው የተገኙት፡፡
ምንጩ እንደገለፀው ሰውነታቸውን ቆራርጦ በፕላስቲክ በተሰራ ቦርሳ ውስጥ በመክተት ከከተማው ወጣ ያለ ስፍራ ወደ ደቡባዊት ሀውጃ አውራጃ ወርውሮ ጥሏቸዋል፡፡
ባሁኑ ሰዓት ፅንፈኛው አይኤስ ሀውጃ የአልረ ሺድ፣ አል ባባሲ፣ አልዛብ ፣አልርያድ አካቢዎችን የአይ ኤስ ጠንካራ አሸባሪ ቡድን የተቆጣጠራቸው ስፍራዎች ናቸው፡፡
በተጨማሪም በሳላውዳን አውራጃ ላይና በኪርኩክአውራጃ ላይም ጥቃት ጀምሯል፡፡
የሳላውዲን ደህንነት አላፊ እንደገለፀው አራት ንፁሀን ዜጎች ተገድለዋል፡፡ሶስት ያህሉ ደግሞ በከፍተኛ ጉዳት ላይ እንደነበሩ ገልፀዋል፡፡
የጀርመን የዜና ምንጭ እንደገለፀው ብዙሀኑ በበዓሉ ወቅት ምንን ባለመፈፀሙ ደስታቸውን ሲገልፁ ቆይተው ነበረ ይሄ መፈፀሙን የሰሙት፡፡
አይ ኤስ ሰሜንና ምስራቅ ኢራቅን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን የሞክሆላ ተራራን ጨምሮ በረሀውን ከሳላውዳ እስከ አንባር መቆጣጠሩንም ተገልፃል፡፡

ዘገባው የአሽራቅ አል አውሳት ነው

አቶ ንዋይ ክርስቶስ ገብረአብ ለ24 አመታት ከ1987 ጀም በተለያዩ የመንስት የሀላፊነት ቦታች አገልግለዋል፡፡
የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከቀድሞው የቀዳማዊ ሀይለስላሴ ከአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኢኮሞሚክ የትምህርት ዘርፍ የሰሩ ሲሆን በኢኮኖሚክስ ዘርፍ ስፔሻላይዝ በማድረግ ከኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በተመሳሳይ ዘርፍ ሰርተዋል፡፡
ንዋይ በ1960ዎቹ እና ሰባዎቹ በኢትጲያ ልማት ባንክ እና ከአቶ በእቅድ ኮሚሽን ውስጥ ሰርተዋል፡፡ በመቀጠልም በእንግሊዝ ሀገር እና በተለያዩ የተባበሩት ሀገራት ድርጅቶች ውስጥ በአማካሪነት ሰርተዋል፡፡
አቶ ንዋይ ክርስቶስ ከ1984 – 87 አ.ም በሽግግሩ ዘመን ለፕሬዚዳንቱ ከ1987-2008 ለጠቅላይ ሚኒስቴሩ ልዩ የኢኮኖሚ አማካሪ በመሆን አገልግለዋል፡፡
ከ1992 ጀም በኢትዩጲያ የልማት ጥናት ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነትም ሰርተዋል፡፡
አቶ ንዋይ ክርስቶስ ገብረአብ ሀምሌ 5 2008 ላይ በኢትዩጲያ የጃፓን አምባሳደር ከሆኑት ካዙሂሮ ሱዙኪ በጃፓኑ ንጉሰ ነገስት በኩል ለኢትዩ ጃፓን ግንኙነት በሰሩት ስራ በጃፓን ከውትድርና ውጪ ለሆኑ ሰዋች የሚጠው ትልቁ የማእረግ ሽልማት ራይዚንግ ሰን ጎልድ እና የብር ኮከብ ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡
በወቅቱ አምባሳደሩ ለአቶ ንዋይ ሽልማቱ የተበረከተላቸው በጃፓን እና በኢትዩጲያ መካከል ስለ ኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲዎች ውይይት እንዲካሄድ መስራች እና የውይይቱ ዋና ሰብሳቢ ስለሆኑ እና እንዲሁም ኢትዩጲያውያን መሪዎችም በፎረሙ እንዲሳተፉ በማድረጋቸው እንደሆነ ገልጸው ነበር፡፡
ባለፍነው ወር ለአለም አቀፍ ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖምን ላስመረጠችው ኢትዩጲያ አቶ ንዋይ ክስቶስ ገብረአብ በአፍሪካ ህብረት ኢኮኖሚ ኮሚሽን ኮሚሽነርነት የሚመረጡ ከሆነ ለአለም አቀፍ ተጽእኖ ፈጣሪነቷ ሌላ ታላቅ እርምጃ ይሆናል፡፡
ናርዶ ዩሴፍ

ረቂቅ አዋጁ ሌሎች ከትራንስፖርት ዘርፉ ጋር በተያያዘ ለሚፈጸሙ ወንጀሎችም ቅጣት ወስኗል፡፡
በህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት ለበጀት እና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ የቀረበ የባቡር ትራንስፖርት ረቂቅ አዋጅ ሳይመዘገቡ እና አገልግሎት ላይ ለመዋል የጸና የደህንነት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖራቸው የመሰረተ ልማት አስተዳዳሪነት ወይም አገልግሎት ሰጪነት ተግባርን እያከናወኑ የሰው ህይወት መጥፋትን ወይም የአካል መጉደልን አልያም ደግሞ ከአንድ ሚሊዩን ብር በላይ የሆነ የንብረት ጉዳትን ካስከተለ ከ20 አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እና ከሁለት መቶ ሺህ ብር በማያንስ እንዲሁም ከ500 ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጣ ተወስኗል፡፡
ወንጀሉ የሰው ሕይወት መጥፋን ወይም አካል መጉደልን የንብረት ጥፋቱም ከ1ሚሊየን ብር በታች ከሆነ ቅጣቱ ከ10 አመት የማይበልጥ ጽኑ እስራት እና ከ20ሺህ ብር የማይበልጥ መቀጮ ነው፡፡
ከኦዲት እና ኢንስፔክሽን መኮንን በረቂቅ አዋጁ ላይ እና በሌሎች ተያይዘው በሚወጡ ደንቦች እና መመሪያዎች በተሰጡት ስልጣን እና ተግባት ለማከናወን ወደ ሎኮሞቲቭ ፣ ፉርጎ፣ የባቡር መሰረተ ልማት ወይም እውቅና ወደ ተሰጠዉ ተቋም እንዳይገባ የከለከለ ከሆነ ወይም የኦዲት እነ ኢንስፔክሽን መኮንን ጥያቄ ማንኛውም ሰው ተገቢውን እነ እውነተኛ ምላሽ ያልሰጠወይም አግባብነት ያለው መረጃ ለማሳየት ፈቃደኛ ካልሆነ ከአንድ አመት በማይበልጥ ቀላል እስራ እና ከ20ሺህ ብር የማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል፡፡
የባቡር የደህነት ስጋ ክስተትን እና የባቡር አደጋን በህግ ስልጣን ለተሰጠው አካል አለማሳወቅ ከአንድ አመት የማይበልጥ ቀላል እስራት እና ከ20 ሺህ ብር የማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል፡፡
የደህንነት ስጋት ክስተቱን ወይም የባር አደጋ ሪፖርት ያልተደረገው የባቡር መሰረተ ልማት አስተዳዳሪውን ወይም የአገልግሎት ሰጪውን ወይም የሌላ ማናቸውንም ሰው ጥፋት ወይም ጉድለት እዳይታወቅ ለመደበቅ በማሰብ ከሆነ ከአምስት አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራ እና ከ100ሺህ ብር በማይበልጥ ገንዘብ ይቀጣል፡፡
ረቂቅ አዋጁ የኢትዩጲያ ምድር ባቡር ኮርሬሽን በተለያዩ የባቡር ትራንስፖር ፕሮጀክቶች ከ120 ቢሊየን ብር በላይ የገንዘብ እዳ ሪፖርት በተደረገበት በዚህ ወቅት ነው የወጣው፡፡ በአጠቃላይም የባቡር ትራንስፖርቱን ዘርፍ ለማተዳደር የተቀረጸ ነው፡፡
የባቡር ትራንስፖርት ዘርፍ ለማስተዳደር ህግ አውጥተው ተቋም አቋቁመው ህግ ካወጡ ሀገራት አንዷ አሜሪካ ናት፡፡ የትራንስፖርት ዘርፉን ለማስተድደር በ1879 አ.ም ኢንተርስቴት ኮሜርስ አክት በሚል አርእስት ያጣች ሲሆን የህጉን ማእቀፍ በ1898 አሻሽላዋለች፡፡
ናርዶስ ዩሴፍ

የኢትዮጲያ ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ለቀይ መስቀል ማህበር ለአንቡላንስ ግዚ የሚውል ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሺ ብር ከዚህ ቀደም ሰጥቶል፡፡ ታዲያ በዛሬው እለት የአንቡላንስ የቁልፍ ርክክብ ሲደረግ ቆይቶ ለቀይ መስቀል ተሰጥቷል ታዲያ በዛሬው እለት የአንቡላንስ የቁልፍ ርክክብ ሲደረግ ቆይቶ ለቀይ መስቀል ተሰጥቷል፡፡
የአንቡላንሱ ዋጋ 3.5 ሚሊዮን የሚገመት ሲሆን የቀይ መስቀል ማህበሩ ግን ከቀረጥነፃ ስለሚያስገባ ዘጠኝ መቶ ሰማኝያ ሺ ብር ተለግሷል ፡፡ በዛሬው እለት የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳድር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቁልፉን ለቀይመስቀል ማህበር በይፋ አስረክበዋል፡፡
እ.ኤ.አ. ከህዳር 2015 እስከ መጋቢት 2017 ድረስ ማህበሩ 435 አንቡላንስ አሉት እነዚህም አንቡላንስ ከ 288 ጣቢያዎች በሀገሪቱ የሚገኙና አገልግሎቶችንም ይሰጣሉ ፡፡ በተጨማሪም ለ5667 የነፃ አንቡላንስ አገልግሎትም ሰቷል ፡፡
የቀይ መስቀል ማህበሩ ከተለያዩ አጋሮች ፣ የንግድ ማህበረሰብ ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሲቪል ሰርቪስ ማህበራት የቀይ መስቀል አጋር በማድረግ እንደዚህ አይነት ድጋፎችን ማግኘት እንደሚቻል ተገልጧል ፡፡

ዘገባው የፍሬህይወት ታደሰ ነው

ታንዛኒያውያን ሴቶች ወላድ ሴቶች ወደ ትምህርት ቤት እንዳይመለሱ የሚከለክለውን ህግ ከወጣ ከ15 አመት በኋላ ተቃወሙ፡፡ ህጉን የደገፉት የሀገሪቱ ፕዚዳንት ተማሪ ሴት ያስረገዘ ወንድ ለ30 አመት መታሰር አለበት ብለዋል፡፡

የታንዛኒያ የሴቶች መብት ተከራካሪዎች የወለዱ ሴቶች ወደ ትምህርት ቤት እንዳይመለሱ የሚደነግገውን በ2002 የወጣ ህግ ተቃወሙ፡፡

ከ15 አመታት በፊት የወጣው ህግ ሴቶች ከወለዱ ከትምህርት ቤት እንደሚባረሩ እና ወደ ትምህርት ቤቱም እዳይመለሱ ሞራልን ይሰብራል እንዲሁም የጋብቻ ውልንም ይጣረሳል በሚል ህግ የመጣስ ወንጀል ተካቶ ነበር የተደነገገው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ነው የታንዛኒያው ፕዚዳንት ጆን ማግፉሊ የወለዱ ሴቶች ወደ ትምህርት ቤቶች መመለስ የለባቸውም በማለት ለውግዘት የዳረጋቸውን አስተያየት የሰጡት፡፡

ፕሬዚዳንቱ ይህን የተናገሩት ሻሊኒዝ በተባለች ከዋና ከተማበ 100 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኝ ከተማ ለህዝብ ያደርጉት በነበረ ንግግር ወቅት ነው፡፡

በንግግራቸውም የወለዱ ወጣት ሴቶች ወደ ትምህርት ቤት ቢመለሱ ትኩረታቸውን ሰብስበው መማር አይችሉም፤ ክፍል ውስጥ አስተማሪው ትንሽ የሂሳብ ስሌት እንዳስተማራት ልሂድ እና የሚያለቅስ ልጄን ላጥባ ትላለች ብለዋል፡፡

ተማሪ ሴት ያስረገዘ ወንድ ለ30 አመት መታሰር አለበት እስር ቤት ሆኖ እያረሰም ሀገሪቷን መጥቀም አለበት ሲሉ አክለዋል፡፡

ወላድ ሴቶች ትምህርት ቤት እንዳይገቡ የሚከለክውን ህግ የሚቃወሙ የሴቶች መብት ተከራካሪ ድርጅቶችንም ፕሬዚዳንት ማግፉሊ በንግግራቸው አውግዘዋል፡፡ እነዚህ የእርዳታ ድርጅቶች ከፈለጉ ሄደው ትምህርት ቤት ሊከፍቱላቸው ይችላሉ መንግስት ህጉን እንዲቀይር ማገደድ አይችሉም ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ይቅርታ እንዲጠይቁ ለማድረግ ፓን አፍሪካ የሴቶች ድርጅት በኢንተርኔት በቀጥታ ድምጽ እያሰባሰበ ነው፡፡

የአፍሪካ የሴቶች ልማት እና ኮሚኒኬሽን ኔትዎርክ ፌምትኔት ህ መቀየር አለበት ሲል ድምጹን አሰምቷል፡፡

አፍሪካውያን ልጅአገረዶችን እና ሴቶችን ከመገለል እና ከጥቃት ነጻ ለማውጣት ብዙ ስራዎችን እየሰራን ባለንበት ወቅት ፕዚዳንቱ ተመልሶ ተጠቂዎች ሲያደርጋቸው እና መጠበቅ ያለባቸውን ሴቶች እንደ ተላላፊ በሽታ ሲያርቃቸው ማየት ትልቁ ክህደት ነው ብለዋል፡፡
በታንዛኒያ በየአመቱ እድሜያቸው ምንም ያህል ቢሆን በትንሹ 8ሺህ ሴቶች በወሊድ ምክንያት ከትምህርት እንደሚገለሉ የሂውማን ራይትስ ዎች ሪፖርት ያሳያል፡፡

ከ7 አመት በፊት በሀገሪቷ የጠደረገ ጥናትም ከ20-24 የእድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ሴቶች ከ20 ፐርሰንት በታች የሆኑት ናቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት፡፡ በሌላ በኩል ወንዶቹ ከ32 ፐርሰንት በላይ ናቸው፡፡

ሊንክ ኢትዩጲያ የተባለ ድረ ገጽ በኢትዩጲያ 17 ፐርሰንት ብቻ የተማሩ ሴቶች ሲኖሩ 42 ፐርሰንት ወንዶች ደግሞ መጻፍ እና ማንበብ የሚችሉ እና የተማሩ ወንዶች እንዳሉ ያሳያል፡፡

ከሲኤንኤን የተገኘውን ዘገባ ናርዶስ ዩሴፍ አጠናቅራዋለች፡፡

ኤህአዴግ ለድርድር አልቀመጥባቸውም ያላቸው ሶስት አጀንዳዎች የህገ መንግስቱ ይሻሻል ጥያቄ ቀዳሚው ነው፡፡የአለም አቀፍ የድንበር እና ወሰን እንዲሁም የአምስቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥያቄ ለድርድር የማይቀርቡት ተብለው ተለይተዋል፡፡የአምስቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥያቄ ከዚህ ቀደም ሰላማዊ የፖለቲካ መንገድን ያልተከተሉ ግለሰቦችን በሰላማዊ መንገድ እንዲመለሱ የሚያስችል አሰራርን መፍጠር የሚል ሲሆን ኤህአዲግ ይህ በድርድር ሳይሆን በሀገሪቱ ህግ የሚፈታ ነው በማለቱ ያልተመረጠ አጀንዳ ሆኖአል፡፡
ለመደበኛው የድርድር ጊዜ አጀንዳ ይሁኑ በማለት ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ አጀንዳዎቻቸውን ሲያስይዙ ቆይተው ከመጡት አጀንዳዎች መካከል 13 ያህሉ ተመርጠዋል፡፡ ከነዚህ ውስጥ ኢህአዴግ ለመደራደር ፈቃደኛ የሚሆንባቸውን አጀንዳዎች ሲያነሳ እና ሲጥል በስተመጨረሻም በአብዛኛዎቹ ላይ ለመደራደር ፈቃደኝነቱን አሳይቷል፡፡በዚህም መሰረት በአጀንዳ 1 የምርጫ ህግና ተያያዥ ጉዳዩችን በተመለከተ፡፡ የምርጫ ህግ አዋጅ ቁጥር 532/99፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የስነ-ምግባር አዋጅ 662/2002፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2000 በቀዳሚነት ጠቀምጠዋል፡፡
በአጀንዳ 2 የተላያዩ አዋጆችን በተመለከተ የፀረ ሽብር አዋጅ ፣ የብዙሀን መገናኛ አዋጅ፣ የታክስ ስርዓት ህግ ፣ የፍትህ አካላት አደረጃጀት አዋጅ እና አፈፃፀም ፣ የበጎ አድራጎት ማህበራት ህግ እንዲሁም የሊዝ አዋጅ እና የተፈናቃዮችን በተመለከተ በሁለተኛ አጀንዳ ስር ተይዘዋል፡፡ የመሬት ፖሊሲ ለድርድር የሚቀርብ አለመሆኑ እና በአፈጻጸም ዙርያ ግን መደራደርና መወያየት እንደሚቻልም የኤህአዴግ ተወካይ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ጠቅሰዋል፡፡
ኤህአዴግ ለድርድር ከተስማማባቸው ቀሪ ጉዳዮች መካከል የብሔራዊ መግባባት በአራተኝነት ሲመረጥ የዲሞክራሲና ሠብአዊ መብቶች ተቋማት አደረጃጀት እና አፈፃፀምን በተመለከተ እንዲሁም ዜጎች በየትኛውም የሀገሪቱ ክልሎች የመዘዋወር ፣ የመኖር ፣ ንብረት የማፍራፋት ፣ የፖለቲካና የሲቪል ህገ መንግስታዊ መብቶችን በክልል መንግስታት አደረጃጀት የሚተገበሩበትን የህግ ማዕቀፍ የተመለከተ የሚሉት ጉዳዮች ናቸው፡፡ የድርድሩ መሪዎች የድርድር አጀንዳዎች ቅደም ተከተልና የድርድሩ አጠቃላይ ማዕቀፍ የጊዜ ሰሌዳ አዘጋጅቶ እናዲያቀርብ እና በፍጥነት ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በመስማማት ተበትነዋል፡፡ ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር የሚል ስያሜን የያዘው መድረኩ ወደ ዋነኛው አጀንዳቸው ሳይገቡ ኤህአዲግን ጨምሮ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ከአምስት ወራት በላይ ጊዜን ወሰደዋል፡፡
ዘገባው የነጋሽ በዳዳ ነው