Super User

Super User

Email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ግምታዊ ዋጋቸው ከ 4 ሚሊየን ብር በላይ ሊያወጡ የሚችሉ የኮንትሮባንድ እቃዎች
የኢትዩጲያ ገቢዎች እና ጉምሩክ የጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ያዘ፡፡
በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ሊገቡና ሊወጡ ሲሉ የተያዙት እቃዎች ውስጥ ኤሌክትሮኒክስ፣
ምግብ ነክ ሸቀጦች፣ አዳዲስና ልባሽ ጨርቆች፣ ጫማዎች፣ ሲጋራ፣ መድሃኒት፣ የህንፃ
መሳሪያዎችና የቤት መገልገያ እቃዎች ሲሆኑ በወጭ ኮንትሮባንድ በኩል 73 የቀንድ ከብቶች፣
77 በጎች፣ 20 ፍየሎች፣ 5700 ኪ.ግ ጤፍ፣ 26 ኩንታል ቀይ ሽንኩርት፣ 3 ኩንታል ነጭ
ሽንኩርት፣ የተፈጨ ቡና እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት የመገበያያ ገንዘብ ይገኙበታል፡፡
እቃዎቹ የተያዙት ከሰኔ አንድ እስከ ሰኔ 30/2009 ዓ.ም. ሲሆን ጅግጅጋ ዙሪያ ቶጎ ጫሌ፣
ተፈሪ በር፣ ሐርሸን እና ለፈኢላ እቃዎቹ አካባቢ ነው የተያዙት፡፡

ሳውዲ አረብያ ህገ-ወጥ ስደተኞችን ከሀገሬ ይው ጡ ልኝ ያለችበት የጊዜ ገደብ ባቃበት እለት በግድያ ወንጀል ጥፋተኛ የተባ ሁለት ኢትዩጲያውያን በሞት ተቀጥተዋል፡፡
በሪያድ ሁለት ኢትዩጲያውያን አንድ የፓኪስታን ዜግነት ያለው የታክሲ አሽከርካሪን በመዝረፍ እና በአስለት ወግተው በመግደል ከአንድ አመት በፊት ክስ ተመስርቶባቸው የነበረ ሲሆን ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው የሞት ቅጣት ውሳኔው እንደተላለፈባቸው የሳውዲ አረቢያ የውስጥ ጉዳዩች ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡
በሀገሪቱ ያለውን የፍህ ስርአት ለማስጠበቅና የንጉሳዊ ስርአቱንም ደህንነት ለመጠበቅ እንዲሁም የሽሪያውን ህግ በጣሰ በማንኛውም ግለሰብ ላይ ለመፈጸም ሲባልም ይህ የፍርድ ውሳኔ መተግበሩን መግለጫው ጨምሮ ገልጾል፡፡
ሳውዲ አረቢያ የሰጠችው የ120 ቀናት የእፎይታ ጊዜ ሀምሌ 17 ቀን 2009 አ.ም መጠናቀቁ የሚታወስ ነው፡፡
እጹብድንቅ ሀይሉ፡፡

የማላዊ የቀድሞ ሚኒስትር በሙስና ቅሌት ወንጀል በቁጥጥር ስር ውለዋል::
የማላዊ የጸረ ሙስና ኮሚሽን በቆሎን ወደ ሀገረ ውስጥ ያለአግባብ በማሰገባት እና በመሸጥ የቀድሞ የግብረና ሚኒስትርን ጨምሮ የሀገሪቱ ነጋዴ እና የስራ ፈጣሪ በአጠቃላይ ሶስት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎዋል፡፡
ማላዊ የሀገሪቱን የምግብ እጥረት ችግር ለመቅረፍ እንዲሁም በባለፈው አመት በተከሰተው ጎርፍ ሳቢያ በደረሰው ድረቅ ምክንያት ወደ ሀገሪቱ በቆሎ በስፋት ታስገባለች ታዲያ በዚህ ወቅት ነው እነዚህ ሶስት ሰዎች ለግል ጥቅማቸው እንዳዋሉት የተገለጸው፡፡
በህገወጥ መንገድ አንድ መቶ ሺ ቶን በቆሎ ከዛንቢያ ወደ ማላዊ በማስገባት ለገበያ አቅርበዋል ሲል የማላዊ የግብርና እና የንግድ ህብረት አሳውቋል፡፡
የእስር ትእዛዙን ጨምሮ ሌሎችም በእንደዚህ አይነት የወንጀል ተግባሮች ፕሬዝዳንት ፒተር ሙታሀሪካ እና የፓርላማው አባላት መጣራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ሙታሀሪካ የግብርና ሚኒስትሩን ቻፖንዳ በወርሃ ጥቅምት ቤታቸው ውስጥ ወደ 2 መቶ ሺ ዶላር የሚጠጋ ጥሬ ገንዘብ ከተገኘ በኋላ ከስራ አባረዋቸዋል፡፡
ዘገባው የ All Africa news ነው

የሳኡዲ መንግስት የምህረት አዋጅ ሊጠናቀቅ ሶስት ቀን ቀረዉ መንግስት በበኩሉ ከምህረት አዋጁ ማብቂያ በኋላ ነገሮች ከቁጥጥሬ ዉጪ ይሆናሉ ሲል አስገንዝቧል፡፡
በሳኡዲ የሚኖሩ ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸዉ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ሀገሪቱን ለቀዉ እንዲወጡ የተሰጣቸዉ የ 30 ቀን የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ ሶስት ቀናት ብቻ የቀሩት ሲሆን እስከ አሁን ወደ ሀገር ለመመለስ ሰነዱን ከሞሉት 60 ሺህ ዜጎች ዉስጥ ከሚጠበቀዉ ቁጥር በታች የሆኑ ዜጎች ወደ ሀገራቸዉ ተመልሰዋል ፡፡
የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በትናንትናዉ እለት ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የሳዉዲ መንግስት የእፎይታዉ ጊዜ ሲጠናቀቅ በህገወጥ ስደተኞች ላይ የከፋ እርምጃ እንደሚወስድ ማስታወቁን የኢትዮጵያ መንግስትም አዋጁ ከተጠናቀቀ በኋላ ነገሮች ከቁጥጥር ዉጪ እንደሚሆንበት ተናግረዋል ፡፡
የሳኡዲ መንግስት ህጋዊ መኖሪያ ፍቃድ የሌላቸዉ ኢትዮጵያዉያን ዜጎች ከሀገሬ ይዉጡልኝ ማለቱን ተከትሎ የ90 ቀናት የእፎይታ ጊዜ ተሰጥቶ የነበረ ሲሆን በኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄ የተጨመረዉን 30 ቀን ጨምሮ የመመለሻ ሰነድ ከሞሉት 120 ሺህ ዜጎች መካከል ከ 58-60 ሺህ ያህል ዜጎች ብቻ ወደ ሀገራቸዉ ተመልሰዋል
ይህም ከሚጠበቀዉ ቁጥር በታች ነዉ
ዘገባዉ የ ፍሬህይወት ታደሰ ነዉ

የቃሊቲ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ በመጨው ዓመት ታህሳስ ወር ይጠናቀቃል፡፡
በአዲስ አባባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን እየተገነባ ያለው የቃሊቲ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ጣቢያ የግንባታ ሂደት በቀጣይ ዓመት ታህሳስ ወር መጨረሻ ላይ የግንባታ ሂደቱ ሲጠናቀቅ በስድስት ክፍለ ከተማ የሚገኙ 1.5 ሚሊዮን የአዲስ አባባ ከተማ ነዋሪዎችን ይጠቅማል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ደጋፊ የስራ ሂደት መሪ የሆኑት አቶ አቶ እስጢፋኖስ ብስራት ያማጣሪያ ጣቢያው ከአለም ባንክ በተገኘ አንድ ሚሊየን ዶላርና የኢትዮጲ መንግስት ወጪ ባደረገው ስምንት መቶ ሚሊየን ብር ወጪ የሚገነባ ነው፡፡
7500 የማጣራት አቅም የነበረው የቃሊቲ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ የግንባታ የማስፋፊያ ሂደቱ ሲጠናቀቅ 100 ሺህ ሜትር ኩብ ያክል ፈሳሽ ማጣራት ይችላል ፡፡
የቃሊቲ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ጣቢያ አሁን ላይ የግንባታ ሂደቱ 90 ፐርሰንት የደረሰ ሲሆን የግንባታ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በዋነኛነት ከሚሰጠው የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣራት ስራ የሚገኘው ውሃ ጥቅም ላይ ለማዋል ጥናት እየተካሄደ መሆኑን አቶ እስጢፋኖስ ለዛሚ ነግረዋል፡፡
አዲስ አበባ ከተማ ባሏት ሶስት የፍሳሽ ማጣሪያዎች በምስራቅ ቦሌና የካን ክፍለ ከተሞችን በአቃቂ የአቃቂን አካባቢን አሁን ደግሞ የማስፋፊያ ስራው የሚካሄድለትና ስድስት ክፍለ ከተሞችን የሚይዘው የቃሊቲ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎች ባለቤት ናት፡፡
ምትኬ ቶሌራ

የዕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በሶስት ክልሎችና በአንድ የከተማ አስተዳደር የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን አነስተኛ መሆኑን ተናገረ፡፡
የዕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የ2009 በጀት ዓመት የአስራ አንድ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ማጠቃለያ ሪፖርት ላይ እንደቀረበው በኦረሚያ በትግራይ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልሎች እንዲሁም በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የንፁህ ውሃ አቅርቦትን በተመለከተ በተደረገ ቁጥጥር የንፁህ ውሃ ሽፋናቸው አነስተኛ መሆኑን ገልፃል፡፡
ለአቅርቦቱ አነስተኛ መሆን በተለይም በገጠር አካባቢ የውሃ ተቋማት ግንባታ ጥራትና የግንባታ ጊዜ መጓተት እንደ ምክንያትነት የተጠቀሰ ሲሆን
ግንባታቸው የተጠናቀቁ የውኃ ተቋማት ባለባቸው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ አይል ማጣት የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግሩ በክልሎቹ ተከስቷል፡፡
በሪፖርቱ ችግሩን ለመፍታት ያልተቻለው የውሃ መስመር ስራዎች ከቴሌኮሚኒኬሽን ኮርፖሬሽንና ከኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ ሃይል ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር አነሰተኛ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
በተጨማሪም የውሃ መስመሮችን የሚያሳይ ካርታ ባለ መኖሩ ብልሽት ሲያጋጥም ለጥገና አስቸጋሪ መሆኑ ዋነኛ ምክንያት ነው ተብሏል፡፡
ምትኬ ቶሌራ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በዚህ ዓመት ብቻ ከሁለት መቶ በላይ ሀሰተኛ የመንጃ ፍቅድ ይዘው ሲያሽከረክሩ የነበሩ አሽከርካሪዎችን መያዙን ተናገረ፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በዚህ አመት በድንገተኛና መደበኛ ፍተሻ ሁለት መቶ ስድስት አሽከርካሪዎች ሀሰተኛ የመንጃ ፍቃድ ይዘው ሲገኙ ይህ ቁጥር አምና ከተመዘገበው በአስራ ስድስት ብልጫ አሳይቷል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ግርማ ተሰማ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በዘመናዊ መሳሪያ እና በቴክኖሎጂ ታግዞ ቁጥጥሩን ቢያደርግ ሀሰተኛ መረጃ የያዙት አሽከርካሪዎች ቁጥር ይጨምር ነበር ብለዋል፡፡
በከተማዋ ሀሰተኛ የመንጃ ፍቅድ ይዘው የተገኙት 75 እጅ የሚሆኑት የህዝብ ማመላለሻ መኪናዎችን የሚያሽከረክሩ ሲሆን የታክሲ እንዲሁም የከባድ ጭነት መኪና አሽከርካሪዎች ተከታዩን ስፍራ ይይዛሉ፡፡
ሀሰተኛ የመንጃ ፍቃድን በመያዝ ወጣቶችን የሚስተካከል አልተገኘም የተባለ ሲሆን በተለያዩ የጤና ችግሮች ዕጋዊ መንጃ ፍቃድ ማውጣት ያቃታቸው አምስት ግለሰቦችም ሀሰተኛ የመንጃ ፍቃድ ይዘው ተገኝተዋል፡፡
ሀሰተኛ መንጃ ፍቃድ የያዙ አስከርካሪዎች የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በመደበኛና በድንገተኛ ፍተሸዎች ከሚለያቸው ጎን ለጎን ጥፋት ያጠፉ አሽከርካሪዎች ቅጣታቸውን ሊከፍሉ ወደ የሁሉም ማህከላት በሚያመሩበት ወቅት ቅጣቱን ብቻ ከመቀበል የመንጃ ፍቃዱን ትክክለኝነት እንዲያረጋግጡ የአሽርካሪዎች መረጃ በዳታ ቤዝ የመያዝ ስራ እየተሰራ ነው ፡፡
በየሁሉም ማህከላት ሊሰራ ከታቀደው ውጪ ሀሰተኛ የመንጃ ፍቅድ የያዝትን ከህጋዊዎቹ በዘላቂነት ለመለየት ፖሊስ ኮሚሽኑ ምን እየሰራ ነው ብሎ ዛሚ ኮማንደር ግርማን ጠይቆ ከተሸከርካሪ አሽከርካሪ ባለስልጣን ጋር በመሆን በቀጣይ ዓመት በኮምፒዩተር የታገዘ ቁጥጥር ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ነግረውናል፡፡
በዚህ አመት 1600 አሽከርሪዎች ለትራፊክ ፖሊሶች ጉቦ ሲሰጡ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ሶስቱ አሽከርካሪዎች ሀሰተኛ የመንጃ ፍቃድ ይዘው ተገኝተዋል፡፡
ምትኬ ቶሌራ

የኢትዩጲያ ገቢዎች እና ጉምሩክ የቀን ገቢ ግምትንና ዓመታዊ ሽያጭን መሰረት በማድረግ ገቢ ግብር የሚሰላበትን መንገድ ነጋዴዎች እንዲረዱት አስታወቀ
የግብሩ ምጣኔ በሚጣወቅበት የስልት ዘዴ ለአብነት ያህል አንድ የበበርበሬ እና ቅመማ ቅመም ንግድ ላይ የተሰማራ ነጋዴ የቀን ገቢ ግምቱ መጠኑ 1ሺህ 500 ነው ከተባለ ከዚህ ላይ የዘርፉ ትርፍ መተመኛ 10 በመቶ ሲሆን የግብር ምጣኔውም 20 በመቶ ይሆናል
ይም ማለት በአመት 547ሺህ 500 ብር አመታዊ ጠቅላላ ገቢ የተተመነለት ነጋዴ የሚከፍለው ግብር 7 ሺህ 320 ብር ይሆናል፡፡
በጸጉር ቤት ዘርፍም የቀን ገቢ ግምቱ 2ሺህ 800 ብር የሆነ ነጋዴ አመታዊ ጠቅላላ ሽያጭ ገቢው 1 ሚሊየን 22ሺህ ሲገመት በ30 በመቶ የግብር ምጣኔ የሚከፍለው አመታ ግብር 19ሺህ 200 ብር ይሆናል፡፡
እነዚህ ለአብነት የጠቀስናቸው የግብ ከፋዩች በደረጃ ሀ እና ለ የሚመደቡ ናቸው፡፡
ገቢዎች እና ጉምሩክ የቀን ገቢ ግምቱን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ላይ ያስረዳው ያስረዳው በደሞዝተኛ እና በነጋዴ ግብር አከፋፈል መንገድ ሲሆን፤
አንድ የ10ሺ ብር ደመወዝተኛ የሆነ ሰው በወር 2ሺ 45 ብር፤ በዓመት ከሚከፈለው 120ሺ ብር ደግሞ 24ሺ 540 ብር ግብር ይከፍላል፡፡
120ሺ ብር ዓመታዊ ገቢ ያለው ነጋዴ ግን የትርፍ መተመኛ መቶኛው 10 በመቶ ላይ ካረፈ ግብር የሚጠየቅበት ገቢው 10 በመቶ ወይም 12ሺ ብር ይሆናል፡፡
ቀሪው 90 በመቶ ወይም 108ሺ ብር እንደ ወጪ ይታይለትና ከግብር ውጪ ይሆናል፡፡
12ሺውን ደግሞ በግብር ማስከፈያ መጣኔ ሲሰላለት 10 በመቶ ላይ ያርፍና 1ሺ 200 ብር ብቻ ዓመታዊ ግብር ይጠየቃል፡፡
ገቢዎች እና ጉምሩክ የነጋዴውን 1ሺ 200 ብር ከደመወዝተኛው 24ሺ 540 ጋር ማነጻጸር የቀን ገቢ ግምቱ ተገቢ እና የተጋነነ ለመሆኑ ማሳያ አድርጎ አቅርቧል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በ2009 በጀት ዓመት የደንበኞቹን ቁጥር ከ57 ሚሊዮን በላይ አደረሰ፤ በቀጣዩ የፈረንጆቹ ዓመት ኢትዮጲያ የሞባይል ተጠቃሚ ቁጥሯ ከፍ ይላል ተብሎ ተተንብዮላታል::
ከሰሀራ በታች የሚገኙ የሞባይል ተጠቃሚዎች በ2020 ከ500 ሚሊየን ሊበልጡ እንደሚችል አለም አቀፍ የሞባይል አገልግሎት ሰጪዎች ማህበር አስታውቋል፡፡ በ2016 መጨረሻ420 ሚሊየን የነበረው የሞባይል ስልክ በ2020 የተጠቃሚ ቁጥር 535 ሚሊየን ይደርሳል ተብሏል፡፡
አዲስ ከሚመጡ የሞባይል ተጠቃሚ ሀገራት ውስጥ 115 ሚሊየን የሚሆኑት ከኢትዮጲያ፣ከዲሞክራትክ ኮንጎ፣ ከናይጄሪያና ከታንዛኒያ እንደሚሆኑ በ2017 በወጣው ሪፖርት ተገልጾል፡፡
ኢትዮጲያ ከነዚህ ሀገራት መሀከል ተቀመጠች ሲሆን የሞባይል ስልክ አገልግሎት በሀገሪቱ ከ18 አመት በፊት በ36 ሺ ደንበኞች በአዲስ አበባ የተጀመረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ቁጥሩ ወደ 57 ሚሊየን አከባቢ እንደደረሰ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡በ2008 በጀት ዓመት የሞባይል ተጠቃሚዎችን ቁጥር 45 ነጥብ 96 ሚሊዮን እንደነበር ይታወቃል፡፡
ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር ደግሞ ሲነጻጸር ከፍተኛው የናይጄሪያ ሲሆን 216 ሚሊየን የሞባይል ተጠቃሚዎች አሉ፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም መረጃ እንደሚያሳው ከጥቂት አመታት በሆላ 103 ሚሊየን የሞባይል ተጠቃሚዎች እንደሚኖሩም አሳውቋል፡፡
የሞባይል ተጠቃሚ ቁጥር መጨመር ለአመታዊ ጥልቅ ምርት መጨመር፣ ለስራ እድል ፈጠራ እና ለማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳለው የማህበሩ የ2017 ሪፖርት ያመላክታል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም በያዝነው ዓመት አጠቃላይ የደንበኞችን ብዛት በሁሉም የአገልግሎት ዓይነቶች 57 ሚሊዮን ያደረሰ ሲሆን ካለፈው በጀት ዓመት መጨረሻ ጋር ሲነፃፀር የ16 በመቶ እድገት ያሳያል፡፡
የገቢውን ሁኔታ በተመለከተም በመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት15 ነጥብ 64 ቢሊዮን ብር ገቢ ያገኘ መሆኑን አመልክቷል። ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንፃር ሲተያይም የ16 በመቶ እድገት አሳይቷል ተብሏል። ያልተጣራ የትርፉ መጠንም በዚሁ 6 ወራት ጊዜ ውስጥ 11 ነጥብ 91 ቢሊዮን መሆኑን መግለጫው ጨምሮ አመልክቷል። ከዚህ አጠቃላይ ገቢውም ውስጥ ከሞባይል አገልግሎት የተገኘው የገቢ መጠን 74 ነጥብ 5 በመቶውን ይሸፍናል፡፡

በዘንድሮው ክረምት ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን ከባድ ጉዳት ለመቀነስ ከ1 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ የመጠባበቂያ ምግብ ተከማችቶ ተዘጋጅቷል::
የትሮፒካ ፓስፊክ ውቅያኖስ የባህር ወለል ሙቀት ከ5ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በላይ የሚሞቅ ከሆነ ኤልኒኖ ፤ ከ0.5 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በታች የሚቀዘቅዝ ከሆነ ደግሞ ላሊና ይባላል ሲሉ የዘርፏ ባለሙያዎች ስለ ተፈጥሮ ክስተቶቹ ኤልኒኖና ላሊና ይናገራሉ፡፡
በዘንድሮው የክረምት ወቅት አብዛኛው የላኒናን ክስተት ተከትሎ ከባድ ጎርፍ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል ሊከሰት እንደሚችልም የብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ የትንበያ ሪፖርት ያመለክታል። ይህም በሰዎች፣ በንብረትና በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያሰከተላል፡፡ ከመደበኛው መጠን በላይ ይዘንባል ተብሎ በሚጠበቀው ከባድ ዝናብ ምክንያት የሚከሰተው የጎርፍ አደጋ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚገመት ህዝብ ለችግር ሲል ብሄራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሰራው መረጃ ያሳያል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ 700 ወረዳዎች አሉ ከነዚህ መካከል ለአደጋ ተጋላጭ ተብለው 300 ወረዳዎች ላይ በተካሄደ ጥናት በኢትዮጵያ በአብዛኛው የሚከሰቱት አደጋዎች ጎርፍና ድርቅ መሆናቸው ተለይቷል፡፡
ታዲያ በዚህ ጉዳይ ላይ በሀገሪቱ በባለፈው አመት በአየር መዛባት (ኤልኒኖ) ምክንያት በአንዳንድ አካባቢዎች ድርቅ ተከስቶ ከ10 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተረጂ እንደሆኑ ይታወሳል፡፡ በኤልኒኖ ምክንያት በተፈጠረው ድርቅ 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን እህል ከኤጀንሲው ወጪ ተደርጓል። ለሴፍቲኔት ፕሮግራም 130 ሺ ሜትሪክ ቶን ፣ ለአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽንም ለአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ 270 ሺ ሜትሪክ ቶን ተሰጥቷል፡፡
በአሁኑ ወቅት የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት አስተዳደር ሊከሰት የሚችለውን ከባድ ጉዳት ለመቀነስ ወደ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ምግብ ክምችት ማዘጋጀቱን ገልïል፡፡
በ2008 በጀት ዓመት 20 ሺ ሜትሪክ ቶን ታዝዞ በጥራት ጉድለት 7 ሺ 500 ሜትሪክ ቶን ተመላሽ መደረጉን ይታወሳል፡፡ በኤጀንሲው መስፈርት መሠረት ከባዕድ ነገር ንጹሕ መሆኑን፣የእርጥበት መጠኑ፣ አቧራማነቱ፣ ጠጠራማነቱ፣ በተባይ አለመያዙና አለመበላቱ እንዲሁም የተሰባበረና የተጨማደደ አለመሆኑ ይረጋገጣል፡፡
ጥራቱን የጠበቀ እህል ማከማቸት ካልተቻለ ለረጅም ጊዜያት በተቀመጠ ቁጥር እህሉን ለማከም የሚወጣው ወጪ እየጨመረ፣ ንጥረ ነገሩን እያጣ ስለሚሄድ ለሰው ልጅ ምግብነት ወደማይውልበት ደረጃ በመድረስ ኪሳራ ሊያስከትል ስለሚችል በዓለም አቀፍ መስፈርት መሠረት ይመዘናል፡፡
ከ89 ነጥብ5 በላይ ንጹሕ ከሆነ በሁለተኛ ደረጃነት፣ ከ94 በመቶ በላይ አንደኛ ደረጃ ንጹሕ ሆኖ ገቢ እንደሚደረግም ኤጀንሲው በመስፈርትነት አስቀምጧል፡፡
የላኒናን ክስተት ተከትሎ በሚከሰት ከባድ ዝናብ ብቻ ሳይሆን የክረምት ዝናብ በጨመረ ቁጥር አብዛኞቹ የሀገሪቱ ክፍሎች በስጋት ላይ ያሉ መሆናቸው ይታወቃል።በክረምት ወቅት ይዘንባል ተብሎ በተተነበየው ከባድ ዝናብ 486ሺ 10 ሰዎች ለጎርፍ አደጋ ሊጋለጡ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል።