Super User

Super User

Email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

በአፍጋኒስታን ኢ-ሰብዓዊ በሆነ መንገድ በርካታ ሰዎች መገደላቸው ተሰማ፡፡
በሰሜናዊ አፍጋኒስታን ሳሬ ፑል ክፍለ አገር አማፂዎች ባደረሱት ጥቃት ከሃምሳ በላይ ሰዎች ጭካኔ በተሞላበት መንገድ መገደላቸው ታውቋል፡፡ የሳሬ ፑል ክፍለ አገር አስተዳደር ቃል አቀባይ ዛቢሁላህ አማኒ እንዳሉት በሚርዛ ኦላንግ አካባቢ ሳያድ አውራጃ የውጪ ታጣቂ ኃይሎች ጭምር ተሳትፈውበታል ባሉት ጥቃት ነው ሰዎቹ ለህልፈት የተዳረጉት፡፡
ቃል አቀባዩ አክለው የታሊባን እና አይ. ኤስ. ኃይሎች በጋራ ጥምረት የፈፀሙት ጥቃት ነው ቢሉም የታሊባን ኃይል ይህንን ጥቃት አልፈፀምኩም፤ ከጥቃቱ ጋር የተየያዘ ምንም አይነት ንክክኪም የለኝም ሲል አስተባብሏል፡፡ እንደውም እንደ ታሊባን ገለፃ የቀረበበት ክስ ፕሮፖጋንዳ ነው፡፡
የሺያ ሃዛራ ማህበረሰብ ናቸው የተባሉ ህፃናት፣ ሴቶች እና በእድሜ የገፉ አዛውንቶች የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን የመንደሩ ሽማግሌዎች ገልፀዋል፡፡ በጥቃቱም ሰባት የአፍጋኒስታን የደህንነት ኃይሎችን ጨምሮ የአማፂ ቡድኑ አባላቶች መገደላቸው ታውቋል፡፡
በዋና መዲናይቱ ካቡል ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣን የሆኑ አንድ ሰው እንዳሉት የአፍጋን አየር ኃይልን ጨምሮ ሌሎች የደህንነት ኃይሎች ጥቃቱ ወደ ደረሰበት ቦታ ተልከዋል፡፡
በአፍጋኒስታን ያለው ግጭት በዚህ አመት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን በደርዘን የሚቆጠር የደህንነት ችግር በየቀኑ ይከሰታል፡፡ እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለፃ ከሆነ ደግሞ በአመቱ አጋማሽ እንኳን አንድ ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ሁለት ንፁኃን የአገሪቱ ዜጎች ሲገደሉ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ሰማንያ አንድ ሰዎች የጉዳት ሰለባ ሆነዋል፡፡ ዘገባው የ ዘ ኢንዲፔንደንት ነው፡፡

የመብት ተሟጋች ቡድኖች እስራኤል በአልጀዚራ ላይ ለመጣል ያሰበችውን እገዳ አወገዙት፡፡
በእየሩስአሌም የሚገኘውን የአልጀዚራ ቢሮ እንዲዘጋ እስራኤል ውሳኔ ለማስተላለፍ ማቀዷን ተከትሎ የመብት ተሟጋች ቡድኖች፣ ጋዜጠኞች እና ታዛቢዎች ያላቸውን ቅሬታ አሰምተዋል፡፡
የእስራኤል መገናኛ ሚኒስትር የሆኑት አዩብ ካራ በአገራቸው የሚገኘው የአልጀዚራ የዜና አውታር በአረቢኛ እና እንግሊዝኛ የሚያስተላልፋቸው የተለያዩ ዘገባዎች ታአማኝነት የሌላቸው በመሆኑ እገዳው እንዲጣል ለአገሪቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክረ-ሃሳብ አቀርባለሁ ማለታቸውን ተከትሎ ነው ቅሬታውና ተቃውሞው መደመጥ የጀመረው፡፡
አልጀዚራ የዜና አውታር የተለያዩ ቡድኖች ሽብር መንዣ ሆኗል ሲሉ ሚነስትሩ አክለው ተናግረዋል፡፡ አዩብ ካራ ይህንን መግለጫ በሰጡበት ወቅት የአልጀዚራ ጋዜጠኞች ወደ ስብሰባ አዳራሽ እንዳይገቡ እገዳ ተጥሎባቸው ነበር፡፡
መሰረቱን ኳታር፥ ዶሃ ያደረገው አልጀዚራ በበኩሉ በመካከለኛው ምስራቅ 'ብቸኛ ዲሞክራሲያዊት አገር' የምትባለው እስራኤል እንዲህ አይነቱን ውሳኔ ማስተላለፏን ነቅፎ የውሳኔ ሃሳቡን እንደማይቀበለው አስታውቋል፡፡
CPJ በበኩሉ እስራኤል እንዲህ አይነት ውሳኔ ለማስተላለፍ ማቀዷን ሙሉ በሙሉ እንድታስቀረውና ጋዜጠኞች በአገሪቱና እና አገሪቱ በወረረቻቸው አካባቢዎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው እንዲዘግቡ መፍቀድ አለባት ብሏል፡፡
ጥቅምት 22 ቀን 1989 ዓ.ም በይፋ ስራውን የጀመረው አልጀዚራ የዜና አውታር ከኳታሩ ኤሚር ሼክ ሃማድ ቢን ከሊፋ በተገኘ አንድ መቶ ሠላሳ ሰባት ሚሊዮን ዶላር ብድር የተመሰረተ ነው፡፡ ዘገባው የሮይተርስ ነው፡፡

810 ግራም የኮኬይን እፅ በሆዱ ዉስጥ ይዞ የተያዘዉ ተከሳሽ በእስራት እና በገንዘብ ተቀጣ::
ተከሳሽ ሚስተር መላቼይ አኩቹኩዉ በፈፀመዉ የተከለከሉ ዕጾችን ማዘዋወር ወንጀል በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ የልደታ የወንጀል እና የፍትሐብሔር ፍትህ አስተዳደር ዘርፍ የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬከቶሬት ዐቃቢ ሕግ በመሰረተዉ ክስ በእስራት እና በገንዘብ መቀጮ መቀጣቱን አስታወቀ::
የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳዉ ተከሳሽ የወንጀል ህግ አንቀጽ 525 /1/ለ ስር የተመለከተዉን በመተላለፍ ግንቦት 18 ቀን 2009 አመት ምህረት ከምሽቱ በግምት 3 ሰዓት ሲሆን ከብራዚል ሳኦወፖሎ ወደ ናይጀሪያ ሌጎስ ለመሄድ ቦሌ አየር መንገደ ለትራዚተ ባረፈበት ወቅት እንዳይመረት እንዳይዘዋወርና ጥቅም ላይ እንዳይዉል የታገደ የኮኬይን ዕፅ በሆዱ ዉጦ ለማለፍ ሲሞክር በተደረገ ፍተሻ ሀያ ዘጠኝ ፍሬ እጽ ከሆዱ ዉስጥ የወጣ ሲሆን በፌዴራል ፖሊሲ ኮሚሽን ለምርመራ ከሄደ በኃላ 15 ፍሬ ከሆዱ ወጥቷል ተከሳሽ አጠቃላይ 810 ግራም የኮኬይን እፅ በሆዱ ዉስጥ ይዞ የተገኘ በመሆኑ በፈፀመዉ መርዛማ እፆችን ማዘዋወር ወንጀል ተከሷል።
ለተከሳሹ ክሱ ደርሶት እና በችሎት ተነቦለት በአስተርጋሚ እየታገዘ እንዲረዳዉ ከተደረገ በኃላ የእምነት ክህደት ቃሉን እንዲሰጥ የተጠየቀዉ ተከሳሽ ያለምንም መቃወሚያ ድርጊቱን ፈፅሜለሁ ጥፋተኛ ነኝ ብሏል::
የፌዴራል ዐቃቢ ሕግ ለጉዳዩ ያስረዱልኛል ያላቸዉን የሰነድ ማስረጃ ካቀረበ በኋላ ተከሳሹ የወንጀል ድርጊቱን ፈፅሜለሁ በማለቱ ሌላ ማስረጃ መሰማት ሳያስፈልግ የጥፋተኝነት ዉሳኔ እንዲሰጥ የጠየቀ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን በመመልከት ተከሳሹን በተከሰሰበት ክስ ጥፋተኛ ነህ ብሎታል::
የቅጣት አስተያያት የተጠየቀዉ የፌዴራል ዐቃቢ ህግም የወንጀሉ አፈፃፀምና ይዞ የተገኘዉን የኮኬን ዕፅ መጠኑ ሲታይ ደረጃዉ መካከለኛ ተይዞ ተከሳሹን ሊያስተምር ሌሎችንም ሊያስጠነቅቅ የሚችል ቅጣት እንዲወሰን በማለት ሲያመለክት ተከሳሽ በበኩሉ በተከላካይ ጠበቃዉ አማካኝነት የወንጀል ድርጊቱን ማመኑ የቤተሰብ አስተዳዳሪ እና የወንጀል ሪከርድ የሌለበት መሆኑን በመጥቀስ በማቅለያነት እንዲያዝለት በማለት አመልክተዋል።
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ደረጃዉ በመካከለኛ በማለት መነሻ ቅጣት 10 አመት በመያዝ ግንቦት 14 ቀን 2009 አመት ምህረት በዋለዉ ችሎት በ7 አመት ጽኑ እስራትና በ7000 ብር የገንዘብ መቀጮ አንዲቀጣ ሲል ወስኗል::
የመረጃ ምንጭ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነዉ።

በአሁኑ ሰአት በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ ጉዳት እያደረሰ የሚገኘዉን የአሜሪካ መጤ ተምች ለማጥፋት በዘርፉ ተመራማሪዎች የተለያዩ ሙከራዎች እየተደረጉ ባለበት ወቅት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የአሜሪካ መጤ ተምችን የሚያጠፋ ፀረ ተምች መድሀኒት ማግኘታቸዉን ይፋ አድርገዋል።
ተመራማሪዎቹ ይህ መጤ ተምች ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ ምርምር መጀመራቸዉን እና ያገኙትን ጸረ ተምች መድሀኒት በወላይታ ዞን በሚገኙ የተወሰኑ ወረዳዎች ላይ ሙከራ አድርገዉ ጥሩ ዉጤት መገኘቱን በዩኒቨርስቲዉ የምርምር እና ማህበረሰብ ምክትል ፕሬዝደንት የሆኑት ዶክተር ብርሃኑ ኩማ ለዛሚ ተናግረዋል።
በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ያገኙትን የጸረ ተምች መድሀኒት የባለቤትነት ማረጋገጫ እስካላገኙ ድረስ ለህብረተሰቡ ጥቅም ላይ እንደማያዉሉት እየተናገሩ እንደሆነ የሚገልጹ መልእክቶች እየተጻፉ ስለመሆኑ ከዛሚ ለተነሳላቸዉ ጥያቄም
ዶክትር ብርሀኑ መድሀኒቱ ስለተቀመመባቸዉ እጽዋቶች እንዲሁም ስለ ሂደቱ ለመናገር ተመራማሪዎቹ የፈጠራ ባለመብት መሆናቸዉ እንዲረጋገጥ እንደሚፈልጉ መናገራቸዉን እና ለዚህም እንቅስቃሴ መጀመራቸዉን ገልጸዉ
ከኢትዮጵያ አእምሮአዊ ንብረት ጽ/ቤት ጋር በመነጋገርም የባለቤትነት ማረጋገጫ ምዝገባዉን ካደረጉበት እለት ጀምሮ ስራቸዉን መቀጠል እንደሚችሉ ስምምነት ላይ መደረሱን ነግረዉናል።
የኢትዮጵያ አእምሮአዊ ንብረት ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ በበኩላቸዉ ምንም እንኳን የፈጠራ ባለመብትነት ሂደቱ ግዜ የሚወስድ ቢሆንም ከጉዳዩ አሳሳቢነት እና ሀገራዊ ፋይዳ አንጻር በልዩ ሁኔታ ታይቶ የምርመራዉ ጊዜ እንዲያጥር ሊደረግ እንደሚችል ለዛሚ ተናግረዋል።
ተመራማሪዎቹ ሀምሌ 24 ቀን ወደ ኢትዮጵያ አእምሮአዊ ንብረት ጽ/ቤት በማምራት የባለቤትነት ማረጋገጫ ጥያቄያቸዉን እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል።
እጹብድንቅ ሀይሉ

እራኤል በአላስቃ መስኪድ ላይ ያደረገችው የብረት መፈተሻ እዲነሳ ተደረገ፡፡
በእስራኤላውያኑ ቴምፕል ማውንት የሚባለውና ፍልስጤማውያኑ ሃራም አል ሸሪፍ የሚሉት የአል አቅሳ መስኪድ የሚገኝበት ቅዱሱ ስፍራ ከብዙ ውዝግብ በኋላ ለአምልኮ ተከፍቷል።
በምስራቃዊ ኢየሩሳሌም የሚገኘው የአል አቅሳ መስኪድ ባሳለፈው ሃምሌ ወር በደረሰው ጥቃት ምክንያት መዘጋቱ በርካታ ተቃውሞዎችን አስነስቶ ነበር።
በሰአቱ በቅዱሱ ስፍራ በተፈጠረው ግጭትም ስምንት ፍልስጤማውያን ሶስት እስራኤላዊያን መሞታቸው አይዘነጋም ፡
ከብዙ ውዝግብ ቡሃላ የአላቅሳ መስኪድ ለአምልኮ ክፍት ተደርጓል ይሁን እንጂ
በአካባቢው ያለውን የፀጥታ ስራ ለማጠናከር የጦር መሳሪያ መፈተሻዎች እና የደህንነት ካራሜራዎች በመግቢያ በሮቹ ላይ ተገጥመዋለታል።
እስራኤል የፀጥታ ስራ ስትል የወሰደቺው እርምጃ ፍልስጤማውያኑን በማስቆጣቱ ተደርጎ የነበረው የብረት መፈተሸ መሳሪያዎችን እንድታነሳ ተደርጋለች ።
ቢቢሲ

ኢትዮጲያ ለደቡብ ሱዳን ስደተኞች 1 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ወጪ በማዉጣት ተጨማሪ የመጠለያ ጣቢያ ከፈተች፡፡
አዲስ የተከፈተዉ የስደተኞች ጣቢያ በደቡብ ሱዳን በተከሰተዉ አስከፊ የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸዉ የተፈናቀሉ የሀገሪቱ ዜጎችን የሚያስተናግድ እንደሆነ ታዉቋል፡፡
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተገነባዉ ጣቢያ ስደተኞችን ለማስተናገድ ጤቀሜታዉ የጎላ እንደሆነና መጠለያ ጣቢያዉም በጋምቤላ ሸርቆሌ ያለዉን ዋነኛ የስደተኞች መቀበያ መጨናነቅ እና ጫናን እንደሚቀንስ ተገልፁል፡፡
እደተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ገለጻ ከሆነ በኢትዮጲያ ጋምቤላ የሚገኘዉ ጣቢያ ብቻዉን 285.809 የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን በማስተናገድ ላይ ይገኛል አጠቃላይ በክልሉ 7 የመጠለያ ጣቢያዎች ሲኖሩ 370.000 ስደተኞች አስጠልሏል ፡፡
እ.እ.አ 2011 ከሱዳን ነጻነቷን ያገኘችዉ ደቡብ ሱዳን ከ 2አመት ቆይታ በሃሏ እንደ እ.እ.አ 2013 በሀገሪቱ በተፈጠረዉ ቀዉስ ምክንያት ከ 2 ሚሊየን በላይ ዜጎች ለስደት ሲጋለጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ደግሞ ለሞት ተዳርገዋል፡፡
ትብለጽ ተስፋዬ ዘግባዋለች

የአደጋ ጊዜ መውጫ ህግ ለሰባት ተከታታይ አመታት ለአዲስአበባ ምክርቤት ቢቀርብም ውሳኔ ባለመስጠት የከተማዋ ነዋሪዎች አደጋ ላይ መሆናቸውን የእሳት እና ድንገተኛ አደጋዎች ባለስልጣን አረጋገጠ፡፡
የአደጋ ጊዜ መውጫ ደንቡ ከ2002 ጀምሮ የወጣ ቢሆንም እሰከአሁን ግን አልጸደቀም ምንም አስገዳጅ ህግ ባለመኖሩ የህንጻ ባለቤቶች ደግሞ ወጪ መቀነስ ላይ ትኩረት በመስጠት እንዲሁም የግንዛቤ እጥረት በመኖሩ በተጨማሪም በቸልተኝነት ይሄንን ችግር እየፈጠረ መሆኑ አሳሳቢ ጉዳይ ነው ሲሉ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋዎች ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት የሆኑት አቶ ንጋቱ ማሞ ለዛሚ ገልጸዋል፡፡
በከተማው የሚታዩ ትልልቅ ህንጻዎች ጨምሮ መጓጓዣዎች የአደጋ ጊዜ መውጫ አይሰራለቸውም ምንአልባትም ቢሰራላቸው እንኳን ማህበረሰቡ ስለአጠቃቀሙ ያለው ግንዛቤ ተጨባጭ አይደለም፡፡
የአደጋ ጊዜ መውጫ በር አከባቢ የተለያዩ ቁሳቁሶች መቀመጥ እንደሌለበት ባለሞያው አክለው ይናገራሉ፡፡ በተጨማሪም በዚህ ጉዳይ ላይ መንግስት አስገዳጅ ደንብ መውጣት እንዳለበት እንዲሁም የሚመለከተው መስሪያቤት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ቢሰሩ የህንጻ ባለቤቶች ለራሳቸውም ለህብረተሰቡም ደህንነት ሲባል ህንጻዎች ሲያሰሩ የአደጋ ጊዜ መውጫ አስፈላጊነት ተረድተው ቢያሰሩ የተሻለ ለውጥ እንደሚመጣ አቶ ንጋቱ ማሞ ይናገራሉ፡፡
ዘገባው የፍሬህይወት ታደሰ ነው

የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል በመዛኞች ጥራት ላይ ጉድለት እንዳለበት አመነ፡፡
በሀገሪቱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ስርአትን ዋነኛ ግቡ ያደረገዉና በዝቅተኛና መካከለኛ ደረጃ ሙያተኞች በሚፈልገዉ ብዛት ፤ብቃትና ጥራት በራሱ የሚተማመንና ብቁ የሰዉ ሀይል የመፍጠር አላማን ያነገበዉ የሙያ ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል በመዛኞች ጥራት ላይ ጉድለቶች እንዳሉና በ2010 ይህንን ችግር ሙሉ ለሙሉ ለመፍታት ማቀዱን በሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ወይንሸት ዘርይሁን ዛሬ ለጋዜጠኞ በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል፡፡
በ2000አ.ም ስራ የጀመረዉ የብቃትና ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል እስከ አሁን ድረስ ማለትም እስከ 2009 በጀት አመት ማጠቃለያ ድረስ 570.831 ተመዛኞች ወደ ተቋሙ በመምጣት 289.331 ብቃታቸዉን ማረጋገጣቸዉን ሪፖርቱ ዳሳል፡፡
በአዲስ አበባም 5 አከባቢዎች ተጨማሪ ቅርንጫፎችን በመገናኛ ፤ በጎና ሲኒማ፤ በሰፈረሰላም፤ በልደታና አራት ኪሎ መክፈቱን ገልፆ የቅርንጫፎቹ መከፈት ለተመዛኞች የተቀላጠፈ መስተንግዶ ትልቅ አስተዋፅዎ እዳለዉም ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡
ትብለጽ ተስፋዬ ዘግባዋለች፡፡

የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ለ 2010 የበጀት አመት ላስቀመጣቸው ግቦችና
ተግባራት በሚሰጣቸው ክብደት መለኪያ ከ 10 ሚሊየን ብር በላይ የተመደበለትን የፋይናንስ
ጉዳይ ከአጠቃላይ ጉዳዩች 10 በመቶ ክብደት ብቻ ሰጥቶታል፡፡
ኤጀንሲው ለፋይናንስ ጉዳዩች ለዘመናዊ እና ፍትሀዊ የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር
ፕሮግራም ማስፈጸሚያ 2 ሚሊዩን 7ሺህ 702 ብር፤ ዘላቂ የመፈጸም እና የማስፈጸም
አቅም መገንባት ፕሮግራም 2 ሚሊዩን 706 ሺህ 333 ብር እንዲሁም ለአመራር እና ድጋፍ
አገልግሎት ፕሮግራም6 ሚሊየን 107 ሺህ 172 ብር የተመደበለት ሲሆን በተጨማሪም
የኤጀንሲውን ግዢ አፈጻጸም በተዘጋጀው ቅድ መሰረት ስራ ላይ ለማዋልና ለፋይናንስ ግዢ
እና ንብረት አስተዳደር ውጤታማነትን ለማሻሻል በአጠቃላይ በበጀት አመቱ አፈጻጸም
የሚኖረው ድርሻ 10 በመቶ ሆኗል፡፡
በእቅዱ ላይ ለተገልጋይ ማለትም የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እና የኤጀንሲው ሰራኞችን
እርካታ ለማሻሻል ለመሳሰሉት ነገሮች 30 በመቶ፤ ለውስጥ አሰራር ማሻሻያ 45 በመቶ
እንዲሁም ለመማማር እና እድገት ከፋይናንስ በተሸለ 15 በመቶ የትኩረት አቅጣጫ
አስቀምጧል፡፡
በተዘጋጀው የግዢ አፈጻጸም መከታተያ ማንዋል መሰረት በማድረግ የክልል ግዢ ተቆጣጣሪ
አካላት በኦሮሚያ፤ አማራ፤ ትግራይ እና ደቡብ ህዝቦች ብሄር ብሄረሰቦች በክልላቸው
ተጨባጭ ሁኔታ የማጣጣም ስራ ማከናወናቸውን መከታተልን ከ 1 በመቶ በታች የሆነ
ትኩረት እንደሚሰጠውም አስፍሯል፡፡

በአሜሪካ ሚቺጋን አንድ የፌደራል ዳኛ ከሀገር እንዲወጡ የተወሰነባቸውን1ሺህ 400 የኢራቅ ዜጎች እንዲቆዩ አደረገ፡፡ የሚቺጋን አካባቢ ዳኛ የሆነው ማርክ ጎልድ ስሚዝ በአሜሪካ የሲቪል ነጻነት ህብረት ጠበቆች ኢራቃውያኑ ተመልሰው ወደ ሀገራቸው ከሄዱ በዘር እና በሀይማኖታቸው የተሇዩ እና በአካባቢቸውም በቁጥር ጥቂት እንደሆኑ ገልጸው ከተመሇሱ የሞት ፍርድ ይጠብቃቸዋል ሲለ ሇፍርድ ቤቱ አቅርበው ሰዎቹ እንዲቆዩ ያቀረቡትን ጥያቄ አጽድቋል፡፡ ዳኛው ከአሜሪካ ሉሸኙ የነበሩት 1ሺህ 400 ኢራቃውያን እንዲቆዩ ባዘዘበት 34 ገጽ ጽሁፍ ሊይ የጊዜው መራዘም በመመሇሳቸው አንዲትም ቀን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ወደ መቃብር ሉሸኙ የሚችለት ሰዎች ሇመሇየት ይረዳል ብሏል፡፡ ውሳኔው በአሁን ወቅት ግን የኢራቅ ዜጎች ከአሜሪካ እንዳይባረሩ አድርጓል፡፡ በአሜሪካ በአሁኑ ወቅት ወደ ሀገራቸው እንዲመሇሱ የተወሰነባቸው 1 444 ኢራቃውያን የነበሩ ሲሆን የአሜሪካ መንግስት 199 ብቻ በሰኔ ወር ከሀገሩ አስወጥቷል፡፤ ዘገባው የ the globe and the mail ነው፡፡