Super User

Super User

Email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

የአለም የጤና ድርጅት ባወጣው መረጃ መሰረት በናይጄሪያ ወባ በከፍተኛ መጠን ገደይ ከሚባሉ በሽታዎች ውስጥ ቀዳሚነቱን ይዞል፡፡
በሰሜን ምስራቅ የናይጄሪያ ግዛት በሆነቸው ቦርኖ በስምንት አመት ውስጥ 3.7 ሚሊየን የሚደርሱ ዜጎች እርዳታ የሚፈልጉ ሲሆን በየሳምነቱ ስምንት ሺ ህ ያህል ደግሞ በበሽታው ይጠቃሉ፡፡ እንደ ጤና ድርጅቱ መረጃ ከሆነ ይሄ በሽታ በወርሃ ጥቅምት በይበልጥ እየተስፋፋ እንደሚመጣም ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም በሀገሪቱ የወባ በሽታ ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ እንደሚመጣ አስታውቀዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ከሚከሰው ሞት ከግማሽ በላይ የሚሆነው በወባ ሲሆን ኮሌራ እና ኢ የሚባለው የጉበት በሽታ ተከታዩን ስፍራ ይይዛሉ፡፡ 58.8 በመቶ ያህሉ በህጻናት ላይ እንደሚከሰቱም መረጃው ያሳያል፡፡
60 በመቶ የሚሆኑት የሀገሪቱ የጤና ማእከል አገልግሎት የሚሰጡት ለሌሎች ጤና ሽፋኖች በመሆኑ የወባ በሽታ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራበት እነደሚገባም በጥናቱ አስቀምጦል፡፡
በአንድ ሀገር ውስጥ የወባ በሽታ መስፋፋት ለሀገሪቱ ሰብአዊ ቀወስ ችግር ምክንያት እንደሚሆን የአለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተር የአለም አቀፍ የወባ በ መከላከል ዝግጅት ክፍል የሆኑት ዶክተር ፔድሮ አሎንሶ ገልጸዋል፡፡
10 ሺህ የሚደርሱ የናይጄሪያ ዜጎችን ከበሽታው ለመታደግ አለም የጤና ድርጅት ገንዘብ መመደቡን አስታውቋል፡፡
የወባ በሽታ የሚከሰተው ጥገኛ በሆኑ የሴት ወባ ትንኞች ማለትም በአናፎሊስ ነው፡፡ በአፍሪካ 200 ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች በወባ የተያዙ ሲሆን አራት መቶ ሰላሳ ሰባት ሺህ በዚሁ በሽታ ህይወታቸው አልፎል፡፡ በአጠቃላይ በአፍሪካ ከሚከሰቱ የሞት አደጋዎች 90 በመቶ የሚሆኑት በወባ እንደሆነ አለም የጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል፡፡

ንፋስ የቀላቀለ ከፍተኛ ዝናብ ተከስቶ የወደቀ ዛፍ ሁለት መኪኖች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አስከትሏል፡፡
በአዲስ አበባ በተለምዶ ፍልውሃ እየተባለ በሚጠራው አከባቢ ከፍተኛ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ ምክንያት 96907 ታርጋ ቁጥር አ.አ የተመዘገበ ሀይሎክስ መኪና ላይ ዛፍ ወድቆበት ከጥቅም ውጪ ሆኖል፡፡
በተጨማሪም እዛው የቆመ የቤት መኪና ታርጋ ቁጥር 974220 የተመዘገበ የሆላ መስታወቱ ሙሉ በሙሉ ረግፎል ፡፡
አደጋው የተከሰተው ሀይለኛ ዝናብ በመዝነቡ ምክንያት እና ከፍተኛ ዝናብ በመኖሩ እንደሆነም በቦታው የነበሩ የአይን እማኞች ገልጸውልናል፡፡
ግዙፉ ዛፍ ከስሩ ተነቅሎ መኪናው ላይ በመውደቁ መኪናው ከአገልግሎት ውጪ እንደሆነም መመልከት ችለናል ፡፡
በቦታው የትራፊክ ፖሊሶች እንዲሁም የከተማው ፖሊሶች የነበሩ ቢሆንም አደጋውን መከላከል አልተቻለም ፡፡
ዛፉ የመኪና አሰፋልት ላይ በመውደቁ መንገዱ በጣም ተጨናንቆ የነበረ ሲሆን የአካባቢው ነዋሪዎች በመተባበር ዛፉን ከወደቀበት ለማንሳት ጥረት እያደረጉ እንደነበር በቦታው ተገኝታ ፍሬህይወት ታደሰ ዘግባዋለች፡፡

ከ59ሺህ በላይ የደረጃ ሐ ግብር ከፋዩች ውስጥ በቀን ገቢ ግምቱ ዙሪያ 24 በመቶው ብቻ ቅሬታ ቢያቀርቡም ባለስልጣኑ የክፍያው ሂደት በዚህ ምክንያት ተጓቷል ሲል የመክፈያ ቀነ ገደቡን ለ10 ቀናት አራዘመ፡፡
የኢትዮጲያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የቀን ገቢ ግምትን አስመልክቶ ከማህበረሰቡ ያሰባሰባቸዉን የህዝብ ቅሬታና አስተያየት መሰረት በማድረግ ሀምሌ 18 ቀን 2009 አ.ም በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች ቅሬታ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ እንደተፈታና ከ 59ሺ 275 የደረጃ ሐ የግብር ከፋዮች መካከል ቅሬታ ያቀረበዉ 24በመቶዉ የሚሆነዉ ብቻ መሆኑን የገለጸዉ ባለስልጣኑ ቅሬታቸዉንም 99.2በመቶ ፈትቻለሁሲል አሳውቆ ነበር፡፡
ታዲያ የ2009 ግብር ማሳወቂያ ከሐምሌ 1 ቀን እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2009 ዓ.ም. መጠናቀቅ ቢኖርበትም በቀን ገቢ ግምት መረጃ አሰባበሰቡ ዘግይቶ በመጀመሩ በርካታ ግብር ከፋዮች ጊዜው እንዲራዘም ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡ ባለስልጣኑም ግብርን አሳውቆ የመክፈያ ጊዜው እስከ ነሃሴ 10 ቀን 2009 ዓ.ም. ድረስ ለ 10 ቀናት አራዝሟል፡፡ በተለያየ ጊዜ ከህዝቡ የተነሱ ቅሬታዎችንና የባለስልጣኑን ምላሽ በምሽት የዛሚ 24 አቅርቦ እንደነበር የሚታወስ ነዉ፡፡
ትብለፅ ተስፋዬ ዘግባዋለች፡፡

ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ አዋጅ 573/2000 ላይ በሚያደርጉት ድርድር የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ሲሳተፉ የሚያስፈልጋቸው የድጋፍ ማሰባሰቢያ ፊርማ ብዛት ከፍ እንዲል ተስማሙ፡፡
በዛሬው እለት በአዋጁ ላይ መጨመር እና መቀነስ እንዲሁም መሻሻል ባለባቸው ጉዳዮች ላይ የተወያዩት የፓለቲካ ፓርቲዎች ለእለቱ ካነሷቸው ጉዳዩች መካከል የድጋፍ ማሰባሰቢያ ድምጽ ብዛት ላይ ከስምምነት ደርሰዋል፡፡
በዚህም መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ሲሳተፉ የሚያስፈልጋቸው የድጋፍ ማሰባሰቢያ ፊርማ ብዛት በሀገር አቀፍ ደረጃ መወዳደር የሚፈልግ ፓርቲ ያስፈልገው የነበረው የ1ሺህ500 ሰዎች ፊርማ ወደ 3000 እንዲሁም በክልል ደረጃ 750 የነበረው ወደ 1ሺህ500 እንዲያድግ ፓርቲዎቹ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የድርድሩ የሚዲያና ኮሚዩንኬሽን ኮሚቴ አስታውቋል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ባለፉት ሁለት መድረኮች ባደረጉት ድርድር ከአዋጁ ውስጥ የመጀመሪያዎቹን 31 አንቀፆች ተወያይተውባቸዋል፡፡
በአዋጁ ላይ የሚደረገው ውይይት ሲጠናቀቅ ስምምነት ላይ የተደረሰባቸውን ነጥቦች ለህዝብ ይፋ እንደሚደረጉ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡
የፓለቲካ ፓርቲዎቹ ለመደራደር የሚሆኑ ጉዳዩች እና ቅደምተከተላቸው ላይ ሲደራደሩ ከስድስት ወራት በላይ ከፈጀ በኋላ ይህ ድርድር በሰኔ ወር መጨረሻ ላይ መጀመሩ ይታወሳል፡፡
ናርዶስ ዩሴፍ

የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ከማስታወቂያ ጀምሮ ባሉ ከአንድ ሺህ በላይ ጉዳዩች ላይ የሚያወጡትን አላስፈላጊ ወጪ እንዲያቆሙ አስጠነቀቀ፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለ2010 የበጀት አመት 320.8 ቢሊዩን ብር ለኢፌድሪ የህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት አቅርቦ ያጸደቀ ሲሆን የተለያዩ የመንግስት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን ተቋማት ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ገንዘብ በማፍሰስ በማስታወቂያ መስሪያ ቤቶቻቸውን ለማስተዋወቅ፤ አላስፈላጊ የሆነ በሚል ያስቀመጠውን ለስብሰባ የሚወጣ ከፍተኛ አበል ፤ ለተለያዩ ጉዳዩች የሚፈጸሙ የአበል ክፍያዎች እጅግ ከፍተኛ መሆን እና ነዳጅ አጠቃቀሞችንም የሚጨምር ከአንድ ሺህ በላይ ጉዳዩች የተካተቱበት ዝርዝር በማዘጋጀት ለሚኒስትር መስሪያ ቤቶቹ የገንዘብ አጠቃቀማቸውን ወጪ ቆጣቢ እንዲያደርጉ አሳስቦ አሰራጭቷል፡፡
ከእነዚህ መስሪያ ቤቶች መካከል የፌደራል የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ለአመራር እና ድጋፍ አገልግሎት ፕሮግራም 6 ሚሊየን 107 ሺህ 172 ብር የተመደበለት ሲሆን ይህ ገንዘብ ለአበል እና ለስልጠና ወጪ የሚደረግ ነው፡፡
የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀጂ ኢብሳ ለዛሚ እንደተናገሩት መስሪያቤቶቹ እንዲሰሩ የተሰጣቸውን ገንዘብ አላፈላጊ በሆነ ሁኔታ እያባከኑት እንደሆነ እና ከአትራፊ ድርጅት እኩል እራሳቸውን ማስተዋወቅም አላስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
እንደ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መረጃ ከሆነ መስሪያ ቤቶቹ በሬድዩ እና በቴሌቪዥን የሚያሰራጯቸው ማስታወቂያዎች እና ስፖንሰር የሚያደርጓቸው ፕሮግራሞች በቀጥታ እነሱን የሚመለከቱ ሆነው አልተገኙም ውጤት ተኮርም አይደሉም፡፡
ውጤት ተኮር ናቸው ተብለው ከተጠቀሱት መስሪያ ቤቶች መካከል የኢትዩጲያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ስለ ግብር መክፈል የሚያስተላልፋቸው ዝግጅቶች ውጤት ተኮር የሆነ መስሪያ ቤቱ ገንዘብ አውጥቶ በሌላ መልኩ የሚያገኝበት ነገር ነው ሲሉ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬቱ ለዛሚ ተናግረዋል፡፡
በ2010 የበጀት አመት የኢትዩጲያ መንገዶች ባለስልጣን 50 ቢሊዩን ብር፤ በሁለተኛነት የትምህርት ሚኒስቴር እና በስሩ ያሉት ኤጀንሲዎች እንዲሁም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከ700 ሚሊዩን እስከ 1 ቢሊዩን ብር ድረስ ተመድቦላቸዋል፤ ግብርና እና መከላከያ እንዲሁም ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከ9 እስከ 12 ቢሊዩን ብር በሚደርስ በጀት ከፍተኛ ገንዘብ ከተመደበላቸው መካከል ናቸው፡፡
አቶ ሀጂ ታዲያ ሁሉንም መስሪያ ቤቶች ትልልቅ በጀት ከተመደበላቸው በተዋረድ እንደየጠቀሜታ ፈርጃቸው በጀት የጸደቀላቸውን መስሪያ ቤቶች የተመደበላቸው ገንዘብ ለስራ እንጂ አላፈላጊ በሆነ መልኩ መስሪያቤቱን ለማስተዋወቅ እና ገንዘብ ለማውጣት አይደለም ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ናርዶስ ዩሴፍ ዘግባዋለች

የዩጋንዳና የታንዛኒያ ፕሬዚዳንቶች ለአለም ረጅሙ የድፍድፍ ነዳጅ ማስተላለፊያ የትቦ መስመር ለመዘርጋት የግንባውን የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ፡፡
የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ጆን ማግፉሊ እና የዩጋንዳ አቻቸው ወሪ ሙሴቪኒ ቅዳሜ እለት ለድፍድፍ ነዳጅ ማተላለፊያ የሚሆን ከሆሚያ ዩጋንዳ እስከ ታንዛኒያ የህንድ ውቂያኖስ ወደብ ታንጋ የሚደርስ ማስተላለፊያ ትቦ ለመገንባት የመሰረት ድንጋዩን አስቀምጠዋል፡፡

መስመሩ 1ሺህ 443 ኪሎ ሜትር ሲረዝም 3.55ቢሊዩን ዶላር ይፈጃል፡፡ ሲጠናቀቅም በቀን 200ሺህ ሊትር ነዳጅ ያስተላልፋል፡፡ በዚህም በአለም ረጅሙ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ይሆናል፡፡

የሀገራቶቹ ባለስልጣናት ግንባታው እ.ኤ.አ በ2018 መጀመሪያ ላይ ይጀመራል ብለዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በ 36 ወራት እንደሚጠናቀቅ እና ከ6ሺህ እስከ 10ሺህ ለሚሆኑ ሰራተኞች የስራ እድል እንደሚፈጥርም ይጠበቃል፡፡

ዩጋንዳ በአሁኑ ወቅት 6.5 ቢሊዩን በርሜል የሚሆን የድፍድፍ ነዳጅ ክምችት አላት፡፡ በተጨማሪም 1.7 ቢሊየን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ደግሞ በመሬቷ ያለ እና ገና ተቆፍሮ ያልወጣ ነው፡፡

በታንዛኒያ በኩል በተጨማሪም እንደ ካሌሚኒ ገለጻ የማስተላለፊያ መስመሩ 8 ክልሎችን፤ 24 ወረዳዎችን እና 184 መንደሮችን ያልፋል፡፡
ፕሬዚዳንት ማግፉሊ በመሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ ስነ ስርአቱ ላይ በታንጋ አካባቢ ብቻ በቀጥተኛም ሆነ ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ከፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሚሆኑ 45ሺህ የሚሆኑ ወጣቶች አሉ ብለዋል፡፡
መረጃውን ያገኘነው ከዩጋንዳ ዴይሊ ኦይል ጆርናል ነው፡፡

የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመራጮች ስም ዝርዝር ለህዝብ ይፋ እንዲሆን አዘዘ፡፡
ፍርድ ቤቱ የኬንያ ነጻ የሆነ ምርጫ አስመራጭ እና የድንበር ኮሚሽን (IEBC) በ48 ሰአታት ውስጥ ለመምረጥ የተመዘገቡ ሰዎችን ዝርዝር አሳትሞ ለህዝቡ ይፋ እንዲያደርግ አዟል፡፡
ምንም እንኳን (IEBC) ዝርዝሩ ከፍርድ ቤቱ ትእዛዝ በፊትም ለህዝብ ክፍት እንደሆነ ቢናገርም ፍርድ ቤቱ ግን እንዲያሳትሙ አዟቸዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ በተጨማሪም ዝርዝሩ ይፋ ስለመደረጉ ለፍርድቤቱ የቀረበ ምንም አይነት የማረጋገጫ ማስረጃ የለም ብሏል፡፡
በመጨረሻም ዳኛ ኦቡንጋ ከዚህ በኋላ ኮሚሽኑ በየምርጫው ይህንን የማሳወቅ እና የማሳተም ግዴታ እንዳለበት አስፈላጊውን የህግ ድንጋጌ ጠቅሶ አስታውቋል፡፡
የኬንያ የምርጫ ድንጋጌ ኮሚሽኑ ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርጫ 90 ቀን አስቀድሞ ወይም ከ30 ቀን ባላነሰ ጊዜ ውስጥ የመራጮች ስም ዝርዝር ለህዝብ ይፋ ማድረግ እንደሚኖርበት ይደነግጋል፡፡
ዘገባው የኦል አፍሪካ ነው፡፡

የአሜሪካ ተምች 32 በመቶ የሚሆነውን የኢትዩጲያ የበቆሎ ማሳ በማጥቃቱ የሀገሪቷ የዋጋ ግሽበት እንዲያሻቅብ አደረገ፡፡
ትላንት ባጠናቀቅነው የሀምሌ ወር የሀገሪቷ ወርሀዊ የዋጋ ግሽበት ወደ 9.4 በመቶ ማደጉን የማእከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች የዋጋ ግሽበትን አጠቃላይ የሆነ የዋጋ መጨመር ወይም ደግሞ ብዙ ገንዘብ ትንሽ እቃ ሲፈልግ ማለት ነው ሲሉ ይተረጉሙታል፡፡
ባለፉት 10 ወራት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ የመጣው የዋጋ ግሽበት በጥቅምት ወር ከነበረበት 5.6 በመቶ አሁን ወደ ሁለት አሀዝ እድገት እጅጉን ተጠግቷል፡፡
የዋጋ ግሽበት ባለሁለት አሀዝ እድገት ማሳየት ያለውን ትርጉም የኢኮኖሚ ባለሙያ አቶ አክሊል ውበት የወጋ ግሽበት እድገት ኢኮኖሚው ሲያድግ ሊፈጠር የሚችል ነገር ቢሆንም ከነጠላ አሀዝ እድገት በአንዴ ወደ ባለሁለት አሀዝ እድገት ከተሸጋገረ በኢኮኖሚው የፍላጎት እና የአቅርቦት አቅም ላይ ክፍተት መኖሩን እንደሚያመላክት ለዛሚ ተናግረዋል፡፡
ግሽበቱ የተፈጠረው የእህል ዋጋ በተለይም የበቆሎ ዋጋ በመናሩ እንደሆነ ሲጠቀስ የምግብ ዋጋ ግሽበት በሰኔ ወር ከነበረበት 11.2 በመቶ ወደ 12.5 በመቶ አድጓል፡፡
በሀገሪቷ አብዛኛው ክፍሎች አዲስ አበባን ጨምሮ አንድ ኪሎ በቆሎ በ12 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡
ከጥቂት ወራት በፊት በኪሎ በ7 እና 8 ብር ሲሸጥ የነበረው ምርት አሁን ዋጋው እንዲያሻቅብ ሀገሪቷ ለመሰብሰብ ያቀደችው 30 ሚሊዩን ኩንታል በቆሎ በተከሰተው የአሜሪካ ተምች ምክንያት በበቆሎ ከተሸፈነው 71ሺህ 508 ሄክታር 32.2 በመቶው መውደሙ ግሽበቱ እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል፡፡
በሀገሪቱ የሰብል ምርት ማሽቆልቆል የጀመረው ከባለፈው አመት ጀምሮ ሲሆን በወቅቱ የተሰበሰበው ምርት ከዚያ ቀደም ከነበረው አመት ማለትም በ2007 ከነበረበት በ4.8 ሚሊዩን ኩንታል ዝቅ ብሏል፡፡
ናርዶስ ዩሴፍ ዘግባዋለች፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ለተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ከ200 በላይ የአሳንሰር ግዢ ጨረታ የተጫራቾች አቅም ከደረጃ በታች መሆን አዘገየ
በተለያዩ አካባቢዎች በከተማ አስተዳደሩ የአሳንሰር የይገዛልን ጥያቄ የቀረበባቸው ከሁለት መቶ በላይ አሳንሰሮች ወይም ሊፍቶች ግዢ ጨረታ ሲያካሂድ የነበረው የፌደራል ንብረት ግዢና ማስወገድ ኤጀንስ ጨረታው በወቅቱ ውድቅ የተደረገበትን ምክንያ ተጫራቾች በቴክኒክና በፋይናንስ ያሳዩት ብቃት ከደረጃ በታች በመሆኑ ነው ፡፡
ሜሪት እና ኮምፕሪናስ ቤዝድ የተጫቾቹ ቴክኒክ አቅም እና በፋይናንስ የተጫራቾቹ አቅም ቢፈተሸም በሁለቱም ዘርፍ ተጫራቾቹ ማሟላት ባለ መቻላቸው ጨረታው ውድቅ ተደርጓል፡፡
የንብረት ጊዢ አዋጅ ቁጥር 649 /2001 የፌደራል ንብረት ግዢና ማስወገድ ኤጀንሲ የፌደራል ባለ በጀት መስሪያቤቶች አቅም ይገነባል የመንግስት ንብረቶችን ያስተዳድራል በሻጭና በገዢ መካከል ያሉ አቤቱታዎችን ይፈታል ከክልሎች የሚመጡለትን የዕቃ ግዢዎች እንደሚያስተናግድ በግልፅ ተቀምጠዋል፡፡
አሁን ላይ የ202 አሳንሰሮችን የግዢ ጨረታ ከፌደራል ንብረት ግዢና ማስወገድ ኤጀንሲ ተረክቦ እየሰራ ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንብረት ግዢና ማስወገድ ኤጀንሲ ሲሆን አሳንሰሮቹ የጨረታ ግዢ ሂደት ላይ መሆኑንና በመስከረም አሊያም ጥቅምት ወር ላይ ግዢያቸው ይፈፃማል ተብሏል፡፡

በአፋር ክልል በደረሰ ከፍተኛ ጎርፍ ሳቢያ 63 ሺህ ሰዎች አደጋ ላይ ወድቀዋል፡፡
በአፋር ክልል መጋሌ ወረዳ ዞን ሁለት በደረሰው የጎርፍ አደጋ 204 የሚደርሱ ቤቶች፣ትምህርት ቤቶች እና የህክምና ጣቢያዎች ችግር ገጥሞቸዋል፡፡ በክልሉ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ነዋሪዎቹ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ፣ የምግብ እጥረትም አጋጥሞቸዋል በተጨማሪም በዚህ ክረምት ብቻ 44 ሺህ አንድ መቶ ዜጎች ከቤታቸው እንደሚፈናቀሉ ተተንብዮል፡፡ ይህንን ችግር ተመልክቶ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ለክልሉ በተለይም በወረዳዉ በድርቁ የከፍ ጉዳት በደረሰባቸው 15 ቀበሌዎች ለሚገኙ አንድ ሺ ያህል ነዋሪዎች 5ሺ ፍየሎች አከፋፍሎል፡፡ በባለፈው አመትም ከ2 ሺህ 3 መቶ በላይ የወረዳዉ ነዋሪዎች የምግብና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጎል፡፡ አፋር ክልል በከፍተኛ መጠን ጎርፍ ከሚያጠቃቸው ክልሎች ቀዳሚውን ስፍራ ስትይዝ እንደ ዋና ምክንያት ደግሞ የሚቀመጠው የአዋሽ ወንዝ በከፍተኛ መጠን መሙላት ነው፡፡ ሌላው ከፍተኛ ዝናብ ከከፍታማ የሀገሪቱ ክፍሎች ማለትም በአማራ እና በትግራይ ክልል መከሰት ለአፋር ክልል በጎርፍ መጥለቅለቅ ተጠቃሽ ምክንያት ናቸው ስትል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያወጣውን ሪፖርት ዋቢ በማድረግ
ፍሬህይወት ታደሰ ዘግባዋለች ፡፡