Super User

Super User

Email: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

በሴራሊዮን በደረሰዉ የጎርፍና አፈር ናዳ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ 400 በላይ ደርሷል
ባሳለፍነዉ ሰኞ በዋና ከተማዋ ፍሪታዉን በደረሰዉ የጎርፍና የአፈር ናዳ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ 400 ከፍ እንዳለ የተነገረ ሲሆን 600 ያህል ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አልታወቀም ይህም የሟቾች ቁጥር ከፍ እንዲል ሊያደርግ ይችላል ተብሏል
በሀገሪቱ ትልቁ የሆነዉ ኮኖት ሆስፒታል የተጎጂዎች ቁጥር ከ አቅም በላይ እንደሆነበትም እየገለጸ ይገኛል
በተራራና በባህር የተከበበችዉ ፍሪታዉን ከፍተኛ ዝናብን ከሚያስተናግዱ ከተሞች መሀል አንዷ ስትሆን መጠነኛ ጎርፍ በከተማዋ የተለመደ ቢሆንም የአሁኑ አይነት የጎርፍ አደጋ ግን አጋጥሟት አያዉቅም
ለአደጋዉ እንደመንስኤ የሚጠቀሰዉ የአየር ንብረት ለዉጥ ቢሆንም የህዝቡ አሰፋፈር. ከተማዋ በ ፕላን አለመገንባቷ እና የጎርፍ መከላከያዎችና ዛፎች አለመኖራቸዉም አደጋዉን ከባድ ሊያደርጉት መቻላቸዉ ተገልጻል
በአደጋዉ ከቤት ንብረታቸዉ የተፈናቀሉ ዜጎችም ማረፊያቸዉን በእምነት ተቋማት አድርገዋል
የሴራኒዮን መንግስትም ድጋፍ እንዲደረግለት የጠየቀ ሲሆን ብሪታንያ እና እስራኤል ንጹህ ዉሃን ጨምሮ መድሃኒትና ብርድ ልብስ እየላኩ ይገኛሉ
ሴራሊዩን በኢቦላ ምክንያት በአንድ ቀን 111 ዜጎቿን አጥታ እንደነበር ይታወሳል bbc

ቻይና ከሰሜን ኮሪያ የምታስገባቸው ምርቶች ላይ ተግባራዊ ያደረገችውን ማእቀብ ተከትሎ ሀገሪቱ በአሜሪካ የጦር ሰፈር ጉዋም ላይ አደርገዋለሁ ያለችውን ጥቃት መሰረዟን አስታወቀች፡፡

ቻይና ከሰሜን ኮሪያ የምታስገባቸውን የከሰል፤ብረት፤የብረት አፈር እና የባህር ምግቦች እንደምታቆም ባሳወቀች ማግስት የሰሜን ኮሪያ ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን ሚሳኤሎቹን ለመተኮስ ያለው እቅድ መሳካት ላይ በጄነራሎቹ ማብራሪያ ቢደረግለትም ለመቆየት እንደመረጠ በሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን በኩል አሳውቋል፡፡
ምንም እንኳን ጉዋምን ለመምታት አስፈላጊውን ዝግጅት ብናጠናቅቅም ውሳኔ ከማስተላለፋችን በፊት ሞኞቹ ያንኪዎች የሚያደርጉትን ማየት እንፈልጋለን ስትል ሰሜን ኮሪያ በሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ተናግራለች፡፡
የሰሜን ኮሪያን 90 በመቶ አለምአቀፍ ንግድ ድርሻ የምትወስደው ቻይና ምርቶቹን ከመላክ እንደምትቆጠብ ያሳወቀችው በተባበሩት መንግስታት ሀገሪቱ ባሳለፍነው ወር ያደረገችውን ተከታታይ የባሊስቲክ ሚሳኤል ተኩስ ሙከራ ተከትሎ የተጣለውን ማእቀብ ለመተግበር እንደሆነ ተናግራለች፡፡
ማእቀቡ ሰሜን ኮሪያ በየአመቱ ከምታገኘው ገቢ 1ቢሊየን ዶላር ለማጣት ታቅዶ የተደረገ ነው፡፡
ቻይና በ2009 አ.ም ብቻ ከሰሜን ኮሪያ 1.2 ቢሊዩን ዶላር የሚያወጣ ከሰል አስገብታ ነበር እንደ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ከሆነ የዚህ አመቱ ቁጥር በማእቀቡ ምክንያት እጅግ ዝቅተኛ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
አሁን ሀገሪቷ ጉዋም ላይ ያነጣጠረችውን ጥቃት ለጊዜው እንዳቆመች መግለጾን ተከትሎ የጎረቤቷ ደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ሙን ጄ ኢን አሜሪካን ሳታማክሪኝ በኮሪያ ቆንጽላ አካባቢ ጥቃት እንዳታደርስ ጠይቃለች፡፡
ቢቢሲ ዘግቦታል፡፡

ወደ አምሳ ሺ የሚጠጉ ረዳት አልባ የሆኑ ሰዎች በደቡብ ሶሪያ ጆርዳን ጠረፍ ላይ ይገኛሉ፡፡
ወደ ሀምሳ ሺ ከሚጠጉት እነኚህ ረዳት አልባ ከሆኑት ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ሴቶች እና ህጻናት ሲሆኑ ይህ ያረፉበት ጠረፍም ያልተስተካከለ ቦታ እና የአየር ንብረቱም አስቸጋሪ ነው ሲል የተባበሩት መንግስታት ተናግሯል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ምክትል ቃለ አቀባይ የሆኑት ፋርሀን ሀቅ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ስደተኞቹ ቦታውን ለቀው በሚሄዱበት ጊዜ የተለያዩ አደጋዎች ደርሶባቸዋል ብለዋል፡፡
ቃለ አቀባዩ በርም ተብላ በምትጠራው ቦታ ላይ የቀሩት እነኚህ ሰዎች የጤና ችግር እና የምግብ እጥረት አጋጥሟቸዋል ሲሉ በድጋሚ ተናግረዋል፡፡
የሶሪያ መንግስት እና አጋሮቹ በቦታው ላይ ያሉትን ስደተኞች በመቃወም ጆርዳን ጠረፍ ላይ ያለ ቁልፍ የሆነ ቦታ ተቆጣጥረዋል፡፡
የሶሪያ ብዙሃን መገናኛዎች እንደገለጹት የሀገሪቷ የመንግስት ወታደሮች የያዙት ቦታ አንድ ሺህ ሦስት መቶ ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሆን ነው ሲሉ ገልጸዋል ፡፡
ካለፉት አመታት በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጆርዳን ጠረፍ ላይ ለሚገኙ ስደተኞች የእርዳታ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ተስማምቷል፡፡
ፈርአን ሀቅ በትናንትናው ዕለት እንደተናገሩት የተባበሩት መንግስታት የጆርዳንን ግዛት መደገፋቸውን እንዲቀጥሉ እና ተጨማሪ ህይወት አድን እርዳታ እንደሚያስፈልግም ቃለ አቀባዩ ተናግረዋል፡፡
ምንጫችን አልጀዚራ ነው

የኢራን ፕሬዝዳንት የሆኑት ሀሰን ሮሀኒ በሠአታት ውስጥ የኒውክለር ማብላያችንን በድጋሚ ስራ ማስጀመር እንችላለን ሲሉ አሜሪካ በሀገሪቱ ላይ ማህቀብ ከመጣል እንድትቆጠብ አስጠነቀቁ፡፡
ዋሽንግተን ኢራንን በመቃወም በሀገሪቱ ላይ የጣለችው ማዕቀብ እና ማስፈራሪያ በሰዓት እና በቀናት ውስጥ መቆም አለባት ሲሉ ሀሰን ሮሀኒ ተናግረዋል፡፡
ሮሃኒ እንደተናገሩት በድጋሚ የተጀመረው የኒውክለር ማብላያ ስራ ሁለት ሺህ አምስት ላይ ከነበረው በበለጠ መሰራት አለበት በተጨማሪም ኢራን ከአለም አቀፍ ሀይላት ጋር የተፈራረመችው የኒውክለር ስምምነት የሀገሪቷን የዩራኒየም መበልጸግ አቅም ከፍ እንዲል እና አለም አቀፍ ማዕቀቡ እንዲነሳሳ በማሰብ ነው ብለዋል፡፡
ስለ ሮሃኒ የሃገሪቱ የህግ ባለሙያዎች በዛሬው ዕለት ባደረጉት ንግግር ስለ ኢራን አቅም ምንም አይነት ማስረጃ አላቀረቡም፡፡ ነገር ግን የትራምፕ አስተዳደር በኢራን ላይ ያለውን ግፊት እንዲያነሳ የሚገፋፋ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ሮሃኒ ካስተላለፈው ዛቻ በኋላ በሌላ በኩል ኢራን በስምምነቱ ላይ ታማኝ መሆን እንደምትፈልግ ተናግረዋል፡፡ ዩ ኤስ ኤ ቱ ዴይ ዘግቦታል

የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር በስሩ ለሚገኙ ሶስት ድርጅቶች ካፒታል ማስተካከያ ተደረገ፡፡

በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር ሥር የሚገኙ የኢትዮጵያ ማዕድን፣ነዳጅና ባዬፊዩል ኮርፖሬሽን ፣ የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፣የአሰላ ብቅል ፋብሪካ እና የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ካፒታል መጠንን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተጠቀሱትን የልማት ድርጅቶች ካፒታል ፈትሾ እንዲስተካከል የውሳኔ ሀሳብ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ያቀረበ ሲሆን፣ ምክር ቤቱ ነሐሴ 5 ቀን 2ዐዐ9ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የውሳኔ ሀሳቡን ተቀብሎ አጽድቋል፡፡

በዚሁ መሠረት የኢትዮጵያ ማዕድን፣ ነዳጅና ባዩፊዬል ኮርፖሬሽን በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 367/2ዐዐ8 ሲቋቋም የተፈቀደ ካፒታሉ ብር 15.26 ቢሊዬን እና የተከፊለ ካፒታሉ ብር 4 ቢሊዬን መሆኑ የተጠቀሰ ቢሆንም ኮርፖሬሽኑ ወደ ሥራ ሲገባ በተጨባጭ የተከፈለው ካፒታል ብር 419.6 ሚሊዮን ብቻ መሆኑ ተረጋግጧል ፡፡
ስለሆነም የዚሁ የተከፈለ ካፒታልን መነሻ በማድረግ በአዋጅ ቁጥር 25/84 አንቀጽ 2ዐ (1) መሠረት የተፈቀደ ካፒታሉ ወደ ብር 1ቢሊዩን 678ሚሊዩን 64ዐሺህ ዝቅ እንዲል ተደርጎ ተስተካክሏል፡፡

የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በሚኒስትሮች ቤት ደንብ ቁጥር 22/1985 ሲቋቋም የተከፈለ ካፒታሉ ብር 8.39 ሚሊየን ብር የነበረ ሲሆን፣ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ምንም ዓይነት ማሻሻያ ሳይደረግበት ቆይቷል፡፡
አሁን የድርጅቱ የተከፈለ ካፒታል ወደ ብር 382ሚሊዩን 177ሺህ እና የተፈቀደ ካፒታሉ ደግሞ ወደ ብር 1ቢሊዩን 528ሚሊዩን 700 ሺኅ ብር እንዲያድግ ተደርጓል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ ከሃያ ዓመት በፊት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 74/1985 እንደገና ተቋቁሞ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ የተከፈለ ካፒታል ብር ወደ ብር 220ቢሊዩን 985ሚሊዩን 434ሺህ 93 እንዲያድግ በሚኒስቴሩ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡
እነዚህ የካፒታል ማሻሻያዎች የልማት ድርጅቶቹ ማቋቋሚያ ደንቦች በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው እንዲወጡና ተግባራዊ እንዲደረጉ የሚኒስትሮች ምክር ቤት መወሰኑ ታውቋል፡፡
ናርዶስ ዩሴፍ

ሦስት አክስዮን ማኅበራት ከኬሚካል ኢንዱስትሪዎች ኮርፖሬሽን ጋር እንዲዋሀዱ ውሳኔተሰጠ፡፡
አዳሚ ቱሉ ፀረ ተባይ ማዘጋጃ አክሲዮን ማኅበር፣ አዋሽ መልካሳ አሉሚኒየም ሰልፌትና ሳልፈሪክ አሲድ አክሲዮን ማኅበር እና ኮስቲክ ሶዳ አክሲዮን ማኅበር ከኢትዮጵያ ኬሚካል ኢንዱስትሪዎች ኮርፖሬሽን ጋር እንዲዋሀዱ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ተቀብሎ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ነሐሴ 5 ቀን 2009 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
አክሲዮን ማኅበራቱና ኮርፖሬሽኑ እንዲዋሀዱ ያስፈለገው ተቋማቱ አሁን ባሉበት አቅም የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ለማሳደግ የሚጠበቅባቸውን ሚና በአግባቡ ሊጫወቱ ስለማይችሉ የአመራር፣ የኢንቨስትመንት፣ የሰው ኃይል፣ የግብይት እና የአሠራር አቅማቸውን አቀናጅቶ በአጭሩ ጊዜ በማጎልበት የተጠናከረ የተወዳዳሪነት ቁመና እንዲይዙ ለማድረግ ነው፡፡
አዳሚ ቱሉ ፀረ ተባይ ማዘጋጃ አክሲዮን ማኅበር በ2008 አ.ም የአሁኑ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የቀድሞ የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት የልማት ድርጅት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ከሚያስተዳድራቸውና ለሽያጭ አቅርቧቸው ከነበሩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡
ባሳለፍነው አመት ከአዲስ አበባ በ165 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ዝዋይ ከተማ ሀገሪቱ በአመት 5.2 ሚሊዩን ዶላር ታወጣበታለች የተባለውን 2.4. d የተባለ ጸረ አረም ኬሚካል ማምረቻ ፋብሪካውን ገንብቶ ስራ ጀምሮ ነበር፡፡
በወቅቱ አክሲዩን ማህበሩን ማስፋፊያ ፕሮጀክቶቹን ለመቀጠል የ5 አመት እቅድ መዘጋጀቱ እና በተጨማሪም ያሉትን የጸረ አረም ምርቶች ቁጥርም ከ 23 ወደ 37 ለማሳደግ እየሰራ መሆኑ ተገልጾ ነበር፡፡
የጸረ-ተባይ ማዘጋጃ ማኅበሩ በ1987 ዓ.ም. ወደ ሥራ የገባ ሲሆን፣ በ2000 ዓ.ም. በ40.5 ሚሊዮን ብር ካፒታል በአክሲዮን ኩባንያ ደረጃ እንዲዋቀር ተደርጓል፡፡ እስከ 2008 አ.ም ድረስም 435 ሠራተኞች የነበሩት ሲሆን፣ 343ቱ ቋሚ ናቸው፡፡
ማህበሩ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወደ ግል ለማዛወር ሁለት ጊዜ ጨረታ ወጥቶ በግዥ እጦት ሳይዛወር ቀርቷል፡
በአሁን በድርጅቶቹ እና በኮርፖሬሽኑ በተደረገው ውህደት በሚፈጠረው ኮርፓሬሽን አስተዳድራዊ ወጪ የመቀነስ ውጤት ሊኖረው የሚችል ሲሆን፣ በውህደቱ የተጣመሩ ተቋማት እንደየሥራ ባህሪያቸው የተመጣጠነ ውስጣዊ የአመራር ነጻነት ይኖራቸዋል፡፡ የተዋሀዱት ተቋማት ምርቶች ለግብርና፣ ለምግብ፣ ለኮንስትራክሽን፣ ለጤና፣ ለቆዳና ቆዳ ውጤቶች፣ ለጨርቃ ጨርቅ እና ለሌሎች በርካታ ኢንዱስትሪዎች ግብዓት የሚያገለግሉ ናቸው፡፡
የተጠቀሱት የኬሚካል ማምረቻ አክስዮን ማኅበራት ከኬሚካል ኮርፖሬሽን ጋር ሲዋሃዱ የኮርፓሬሽኑን ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 280/2005 ማሻሻል አስፈላጊ በመሆኑ የሦስቱ አክሲዮን ማኅበራት መብትና ግዴታዎች ወደ ኮርፓሬሽኑ ተዛውረው እንዲሻሻል ተደርገጓል፡፡
የኮርፓሬሽኑ የፈቀደ ካፒታልም ብር 21.7 ቢሊዮን የነበረው ወደ ብር 21ቢሊዩን 719 ሚሊዩን 751ሺህ 376 ብር እና የተከፈለ ካፒታል ብር 5.4 ቢሊዮን ብር 5ቢሊዩን 893ሚሊዩን 694ሺህ እንዲሆን ተወስኗል፡፡

በሚኒስትሮች ምክር ቤት በተቋቋመው አዲስ የአቪየሽን ቡድን አየር መንገድ በ4 ጉዳዩች ላይ የኤርፖርቶች ድርጅት አስተዳደር ውሳኔውን በቅድሚያ ለአየር መንገዱ ማሳወቅ አለበት አለ፡፡
ለቀድሞው የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በላከው የውስጥ ደብዳቤ ድርጅቱ በሰው ሀብት ልማት አስተዳደር፤ በጨረታ፤ በውል አፈጻጸም እና ህጋዊ ጉዳዩች ላይ አስተዳደሩ በቅድሚያ የአየር መንገዱን ይሁንታ ማግኘት እንዳለበት አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት የኤርፖርቶች ድርጅት ካለ አየር መንገዱ ፈቃድ ማንኛውንም ሰራተኛ እድገት መስጠት፤ ማዘዋወር እና ከደረጃ ዝቅ ማድረግ ወይም መሻር አይችልም፡፡
ጨረታ እና ገንዘብን በተመለከተ ሁሉም ከ150 ሺህ ብር በላይ የሆኑ ወጪዎች በቅድሚያ በአየር መንገዱ መጽደቅ ሲኖርበት ውሎችን እና በአሁን ወቅት ያለተጠናቀቁ ማናቸውንም ህጋዊ ጉዳዩች ለአየር መንገዱ በቅድሚያ እንዲያሳውቅ አዲስ የተመሰረተው የአቪዬሽን ቡድን ለድርጅቱ የላከው ደብዳቤ ይገልጻል፡፡
ሁለቱ የሀገሪቷ አንጋፋ ድርጅቶች የተዋሀዱት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለማዋሀድ የቀረበውን ረቂቅ ደንብ ዓርብ ሐምሌ 7 ቀን 2009 ዓ.ም. ካጸደቀ በኋላ ነው፡፡
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ቡድን ባሳለፍነው ወር በአዋጅ ሲቋቋም በሥሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድና የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅትን ያቀፈ ተደርጎ ነው፡፡ ፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድና የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት በአንድ ቦርድ የሚተዳደሩ ሲሆን፣ የጋራ መርሐ ግብር ይኖራቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ሁለቱ ድርጅቶች የየራሳቸው መለያ ብራንድና የንግድ ምልክት ይዘው ይቀጥላሉ፡፡ ሽግግሩ በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ እንደሚከናወን ሚኒስትር አህመድ ሺዴ በወቅቱ አስረድተዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 86 ዘመናዊ አውሮፕላኖች ባለቤትና 95 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች አሉት፡፡ የአየር መንገዱ ሠራተኞች ብዛት ከ12,000 በላይ ሆኗል፡፡
የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት በበኩሉ በርካታ የኤርፖርት ግንባታ ፕሮጀክቶችን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የመንገደኞች ማስተናገጃ ሕንፃ በ350 ሚሊዮን ዶላር ወጪ በማስፋፋት ላይ የሚገኝ ሲሆን በክልል በሰመራ፣ በሐዋሳ፣ በሽሬ፣ በባሌ ሮቤ፣ በደምቢዶሎና በነቀምቴ ከተሞች ኤርፖርቶች በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ወቅት ድርጅቱ 23 ኤርፖርቶች ሲያስተዳድር፣ አራቱ ዓለም አቀፍ ናቸው፡፡
ናርዶስ ዩሴፍ ዘግባዋለች

የብሄራዊ ትምባሆ ድርጅት የአርባ በመቶ ድርሻውን ለግል ድርጅት በአምስት መቶ አስር ሚሊዮን ዶላር በሸጠ ማግስት በግማሽ ዓመቱ ከውጭ በሚያስገባቸው የትምባሆ ምረቶች ማግኘት የነበረበትን 26 ሚሊዮን ብር አጣ፡፡
የብሄራዊ ትንባዎ ድርጅት በፈረንጆቹ 2017 አጋማሽ ወር ላይ ከውጭ አገራት በሚያስገባቸው የሮዝማንና ና የማልቦሮ የሲጋራ ምርቶቹ 29.8 ሚሊዮን ብር ለማግኘት አስቦ 3.1 ሚሊዮን ብር በማግኘት ከ26 ሚሊየን ብር በላይ አጥቷል፡፡
የድርጅቱ የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ የሆኑት አቶ ጌቱ አለማየሁ ለምርቶቹ ሽያጭ መቀነስ የውጪ ምንዛሬ መቀነስን እንደ ምክንያትነት አስቀምጠዋል፡፡
ድርጅቱ በተጨማሪም በሀገሪቱ ላሉ አጫሾች የሚሆኑ አምስት የሲጋራ አይነቶችን ማምረት ብችልም በአገሪቱ ውስጥ በተስፋፋው የኮንትሮባንድ ንግድ የሀገር ውስጥ የገበያ ድርሻዬ 65 ፐርሰንት ብቻ ሆኗል ብለዋል፡፡
የኢትዮጲያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለ ስልጣን የጅጅጋ ቅርንጫፍ ከሰኔ አንድ እስከ ሰኔ 30/2009 ድረስ ግምታቸው 4 ሚሊየን ብር በላይ ሊያወጡ የሚችሉ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን ሲጋራም ዋነኛ ምርት መሆኑን አስታውቋል ፡፡
ድርጅቱ በጃፓኑ ቶባኮ ኢንተርናሽናል 40 ፐርሰንት በመንግስት 31 እንዲሁም በሼባ ኩባንያ 29 ፐርሰንት ድርሻው የተያዘ ሲሆን
የድርጅቱን ከፍተኛ ድርሻ የያዘው የጃፓኑ ድርጅት ሱዳን ደቡብ አፍሪካ እና ናይጄሪያ ጨምሮ በሰባት የአፍሪካ አገራት ግዙፍ ኢኮኖሚን እያንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡
ምትኬ ቶሌራ

በኦሮሚያ ክልል በህገ ወጥ ማስረጃ ሲሰሩ የነበሩ ከ1ሺህ በላይ የመንግስት ሰራተኞች ተገኙ::
በኦሮሚያ ክልል በሀስተኛ የትምህርት ማስረጃ ሲሰሩ የነበሩ ከ1 ሺህ በላይ የመንግስት ሰራተኞች መገኘታቸውን የክልሉ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ገለጸ።
ሰራተኞቹ በክልሉ ከወረዳ እስከ ክልል ድረስ ባሉ የተለያዩ መስሪያ ቤቶች ውስጥ በሀስተኛ የትምህርት ማስረጃ እየሰሩ የሚገኙ ናቸው።
በዚህም ያለአግባብ የማይገባቸውን ጥቅም እያገኙና በማይመጥናቸው የስራ ደረጃ ላይ በመስራት ላይ ይገኛሉ በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ራሳቸውን የሚያጋልጡ ሰራተኞችን ይቅርታ ተደርጎላቸው ከዚህ በፊት ባላቸው ትክክለኛ የትምህርት ማስረጃና በሚመጥናቸው የስራ ቦታ የሚሰሩ ሲሆን
ከነሐሴ 16 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ቢሮው በሚያደርገው ማጣራት ህጋዊ ያልሆነ መረጃ ይዞ በማገልግል ላይ ያሉ ሰራተኞች ከስራው እስከ መጨረሻ ድረስ ይባረራሉ ፤ እስከ አሁን በሀሰተኛ መረጃ ያገኙትን ደመወዝና ጥቅማጥቅም ይመልሳሉ
ሰራተኞቹ የትምህርት ማስረጃ ያገኙባቸዉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ምርመራ በመደረግ ላይ እንደሚገኝም ተነግሯል
በክልሉ ከ470 ሺህ በላይ የመንግስት ሰራተኞች ያሉ ሲሆን በክልል ባሉት ተቋማት፣በከተማ አስተዳደሮች፣በዞኖች፣ በወረዳ እና በመንግስት የልማት ድርጅት የሚሰሩ ናቸው።
ከሐምሌ 15 እስከ ነሐሴ 15 ቀን 2009 ዓ.ም ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ይሰሩ የነበሩ የመንግስት ሰራተኞቹ እራሳቸውን እንዲያጋልጡ በተሰጣቸው ዕድል መሰረት ሰራተኞቹ ራሳቸውን እያጋጡ ነው ተብሏል።
እጹብ ድንቅ ሀይሉ

ጀርመን የስዊዘርላንድ ባለስልጣኖች የታክስ ባለስልጣን መስሪያ ቤቴ ውስጥ በስውር ሰርገው ለመግባት ሰላዮች ልካብኛለች ስትል ወነጀለች፡፡
ውንጀላውን ተከትሎ የጀርመን የመገናኛ ብዙሃን የፌዴራል ዐቃብያነ-ሕግ ምርመራውን እንደከፈቱ ዘግበዋል፡፡
የጀርመን ዓቃብያኖች ከስዊዘርላንድ የስለላ ድርጅት ሶስት ሰላዮች ላይ ምርመራ ማካሄድ በመጀመራቸው በጀርመን ባለሥልጣናት እንደታሰሩ ለሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡.ጉዳዩ ደግሞ የታክስ ስርዓቱን በህገ ወጥ መልኩ ለመሰለል በማሰባቸው እንደሆነ ተነግሯል፡፡
የስዊስ ባንኮች ላይ ያነጣጠረ የግብር አፇፃፀም በሚሰራው የጀርመን ታክስ ተመራማሪዎች ቡድንን ለመሰለል በመሞከር ወንጀል ተከስሰዋሌ.
የስለላ ሙከራ ተደርጎብኛል የምትለው ጀርመን አንድ በስዊስ ፌዴራላዊ አገልግሎት (NDB) ተቀጥሮ የሚሠራ "ዳንኤል ኤም 54" ሰው ብቻ ነው የስዊዘርላንድ ዜጋ በስዊዲን ህግ መሰረት የታወቀው.
የጀርመን ጋዜጣ ሱጁድቼ ፃይቱንግ እና የሁለቱን የሀገሪቱ አጠቃላይ ስርጭቶች እንዲሁም ሶስት አዳዲስ ግለሰቦች በስዊስ ናምቢ ሠራተኞች ተቀጣሪዎች እንደሆኑ ይናገራሉ.የጀርመን ፌዴራላዊ አቃቤ ህግ ጽ / ቤት በቅርብ ወቅታዊ የይገባኛል ጥያቄ ላይ አስተያየት አልሰጠም, እንዲሁም ሶስት ተጨማሪ ወንዶች ስማቸው አልተለቀቀም.
የ 2006 የጀርመን ባለስልጣናት ከስዊስ ባንኮቹ የተወረወሩ የግል መረጃዎችን የተሰረዙ ዲስኮች እና የዩኤስቢስ ዶከመንቶች የጀርመን ታክሶችን ማጭበርበሪያ ለመለየት ጥቅም ላይ ውለዋል.
ዘ ኢንዲፔንደንት