Tuesday, 22 August 2017 10:08

በሲንጋፖር በአሜሪካን የባህር ሃይል መርከብ እና በነዳጅ መጫኛ መርከብ መካከል በተፈጠረ ግጭት አስር ሰዎች መጥፋታቸው ተገለጸ፡፡

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በሲንጋፖር በአሜሪካን የባህር ሃይል መርከብ እና በነዳጅ መጫኛ መርከብ መካከል በተፈጠረ ግጭት አስር ሰዎች መጥፋታቸው ተገለጸ፡፡
ከወር በፊት በባህርሀይሉ እና የአቃ መጫኛ መርከብ ተጋጭተው የነበረ ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ በ ሲንጋፖር ባህርዳርቻ በተፈጠረው ግጭት አስር የባህርሀይል አባል ሲጠፉ አምሰቱ ደግሞ ቆስለዋል፡፡
አስሩ የባህር ሀይሉ አባላት የደረሱበት ያልታወቀ ሲሆን የተቀሩት አምስቱ ደግሞ ቆስለዋል፡፡የባህርሃይሉ መሪ አንደተናገሩት የሲንጋፖር የባህር ሀይል እና ሄሊኮፕትሮች ጥቃት ከደረሰበት መርከብ ላይ የተረፉትን በመፈለግ ላይ ናቸው፡፡ከቆሰሉት ውሰጥ አራቱ በ ሲንጋፖር የጦር ሀይል ሄልኮፕተር ወደ ሲንጋፖር የተወሰዱ ሲሆን በ ሲንጋፖር ሆሰፒታል በመረዳት ላይ ናቸው
በተመሳሳይ አደጋ ከ ሁለት ወር በፊት ስባት የባህር ሀይል አባላት ሰዎች የሞቱ ሲሆን ይህ በድጋሜ መፈጠሩ በአካባቢው ያለውን የደህንነነት ጉዳይ ጥያቄ ውሰጥ የሚከት ሆኗል፡፡
የባህር ሃይሉ በሰጠው መግለጫ ለይ አጥፊው በሲንጋፖር ቻንጊ ናቫል እንሆነ እና በአደጋው በደረሰው ጎርፍ በስፍራው የሰራተኞች የመኝታ ክፍሎች ማሽኖች ላይ እና የመልእክት ማሰተላለፊያ ክፍል ላይ ከፍተኛ ጉዳትን አድርሰዋል እንደ ሲንጋፖር ባለስልጣን ዘገባ ምንም አይነት የነዳጅ መፍስስ በአካባቢው እንዳልታየ ተገልጿል፡፡
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስለ ግጭቱ በዋይት ሃውስ ቃለ አቀባያቸው በኩል ተጠይቀው በጸሎታቸው እና በሃሳባቸው እንደማይለዋቸው ለመርከበኞቹ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ዘገባዉ የ ዘ ኒዎርክ ታይምስ ነዉ

Read 57 times

Leave a comment

Make sure you enter the (*) required information where indicated. HTML code is not allowed.