Tuesday, 27 June 2017 11:31

ታንዛኒያውያን ሴቶች ወላድ ሴቶች ወደ ትምህርት ቤት እንዳይመለሱ የሚከለክለውን ህግ ከወጣ ከ15 አመት በኋላ ተቃወሙ፡፡

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ታንዛኒያውያን ሴቶች ወላድ ሴቶች ወደ ትምህርት ቤት እንዳይመለሱ የሚከለክለውን ህግ ከወጣ ከ15 አመት በኋላ ተቃወሙ፡፡ ህጉን የደገፉት የሀገሪቱ ፕዚዳንት ተማሪ ሴት ያስረገዘ ወንድ ለ30 አመት መታሰር አለበት ብለዋል፡፡

የታንዛኒያ የሴቶች መብት ተከራካሪዎች የወለዱ ሴቶች ወደ ትምህርት ቤት እንዳይመለሱ የሚደነግገውን በ2002 የወጣ ህግ ተቃወሙ፡፡

ከ15 አመታት በፊት የወጣው ህግ ሴቶች ከወለዱ ከትምህርት ቤት እንደሚባረሩ እና ወደ ትምህርት ቤቱም እዳይመለሱ ሞራልን ይሰብራል እንዲሁም የጋብቻ ውልንም ይጣረሳል በሚል ህግ የመጣስ ወንጀል ተካቶ ነበር የተደነገገው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ነው የታንዛኒያው ፕዚዳንት ጆን ማግፉሊ የወለዱ ሴቶች ወደ ትምህርት ቤቶች መመለስ የለባቸውም በማለት ለውግዘት የዳረጋቸውን አስተያየት የሰጡት፡፡

ፕሬዚዳንቱ ይህን የተናገሩት ሻሊኒዝ በተባለች ከዋና ከተማበ 100 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኝ ከተማ ለህዝብ ያደርጉት በነበረ ንግግር ወቅት ነው፡፡

በንግግራቸውም የወለዱ ወጣት ሴቶች ወደ ትምህርት ቤት ቢመለሱ ትኩረታቸውን ሰብስበው መማር አይችሉም፤ ክፍል ውስጥ አስተማሪው ትንሽ የሂሳብ ስሌት እንዳስተማራት ልሂድ እና የሚያለቅስ ልጄን ላጥባ ትላለች ብለዋል፡፡

ተማሪ ሴት ያስረገዘ ወንድ ለ30 አመት መታሰር አለበት እስር ቤት ሆኖ እያረሰም ሀገሪቷን መጥቀም አለበት ሲሉ አክለዋል፡፡

ወላድ ሴቶች ትምህርት ቤት እንዳይገቡ የሚከለክውን ህግ የሚቃወሙ የሴቶች መብት ተከራካሪ ድርጅቶችንም ፕሬዚዳንት ማግፉሊ በንግግራቸው አውግዘዋል፡፡ እነዚህ የእርዳታ ድርጅቶች ከፈለጉ ሄደው ትምህርት ቤት ሊከፍቱላቸው ይችላሉ መንግስት ህጉን እንዲቀይር ማገደድ አይችሉም ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ይቅርታ እንዲጠይቁ ለማድረግ ፓን አፍሪካ የሴቶች ድርጅት በኢንተርኔት በቀጥታ ድምጽ እያሰባሰበ ነው፡፡

የአፍሪካ የሴቶች ልማት እና ኮሚኒኬሽን ኔትዎርክ ፌምትኔት ህ መቀየር አለበት ሲል ድምጹን አሰምቷል፡፡

አፍሪካውያን ልጅአገረዶችን እና ሴቶችን ከመገለል እና ከጥቃት ነጻ ለማውጣት ብዙ ስራዎችን እየሰራን ባለንበት ወቅት ፕዚዳንቱ ተመልሶ ተጠቂዎች ሲያደርጋቸው እና መጠበቅ ያለባቸውን ሴቶች እንደ ተላላፊ በሽታ ሲያርቃቸው ማየት ትልቁ ክህደት ነው ብለዋል፡፡
በታንዛኒያ በየአመቱ እድሜያቸው ምንም ያህል ቢሆን በትንሹ 8ሺህ ሴቶች በወሊድ ምክንያት ከትምህርት እንደሚገለሉ የሂውማን ራይትስ ዎች ሪፖርት ያሳያል፡፡

ከ7 አመት በፊት በሀገሪቷ የጠደረገ ጥናትም ከ20-24 የእድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ሴቶች ከ20 ፐርሰንት በታች የሆኑት ናቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት፡፡ በሌላ በኩል ወንዶቹ ከ32 ፐርሰንት በላይ ናቸው፡፡

ሊንክ ኢትዩጲያ የተባለ ድረ ገጽ በኢትዩጲያ 17 ፐርሰንት ብቻ የተማሩ ሴቶች ሲኖሩ 42 ፐርሰንት ወንዶች ደግሞ መጻፍ እና ማንበብ የሚችሉ እና የተማሩ ወንዶች እንዳሉ ያሳያል፡፡

ከሲኤንኤን የተገኘውን ዘገባ ናርዶስ ዩሴፍ አጠናቅራዋለች፡፡

Read 68 times

Leave a comment

Make sure you enter the (*) required information where indicated. HTML code is not allowed.