አለም አቀፍ ዜናዎች (154)

Friday, 18 August 2017 08:48

የዙምባቤ ቀዳማዊት እመቤት ግሬስ ሙጋቤ በደቡብ አፍሪካ አንዲት ሴት ላይ አካላዊ ጥቃት በማድረስ የቀረበባት ክስ በዲፕሎማቲክ ያለመከሰስ መብት እንድትታለፍ የሀገሪቱ መንግስት ጠይቆላታል፡፡

የዙምባቤ ቀዳማዊት እመቤት ግሬስ ሙጋቤ በደቡብ አፍሪካ አንዲት ሴት ላይ አካላዊ ጥቃት በማድረስ የቀረበባት ክስ በዲፕሎማቲክ ያለመከሰስ መብት እንድትታለፍ የሀገሪቱ መንግስት ጠይቆላታል፡፡

የ20 አመቷ ደቡብ አፍሪካዊት ሞዴል ቀዳማዊት እመቤቷን እሁድ እለት በጆሀንስበርግ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ አግኝታት አካላዊ ጥቃት እንዳደረሰችባት ተናግራለች፡፡
የ52 አመቷ የሙጋቤ ሚስት ማክሰኞ እለት ራሷ እጇን ለፖሊስ እንደምትሰጥ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም ፖሊስ ይህን አለማድረጓን አሳውቋል፡፡
የዙምባቤ መንግስት ለሙጋቤ ሚስት በዲፕሎማሲያዊ ያለመከሰስ መብቷ ይጠበቅላት ሲል መከላከሉን የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ተናግሯል፡፡

ነገር ግን ደቡብ አፍሪካ ግሬስ በግል ጉብኝት ስም ወደ ሀገሬ እሰከገባች ድረስ በህጋዊ ሂደቴ ውስጥ ማለፍ አለባት ብላለች ሲል የዙምባቤ መንግስት ተወካይ ሚኒስቴር ዲፕሎማሲያዊ ከለላውን መጠየቁን ባሳወቀበት መግለጫ ላይ ተናግሯል፡፡
በጉዳዩ ላይም የግሬስ ጠበቆችና የዙምባቤ ከፍተኛ ኮሚሽን እየተወያየበት ስለ መሆኑም አክሏል፡፡

ግሬስ ሙጋቤ አሁንም በደቡብ አፍሪካ እንደምትገኝ እና ወደ ሀገሯ ተመልሳለች የሚለው ወሬም ሀሰት እንደሆነም የተለያዩ የዜና ምንጮች አትተዋል፡፡

ከፓርላማዊ ፍርድ ቤት የቀረበው የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ዋና ሀላፊ ሌስትጃ ሞቲባ ግሬስ ሙጋቤ ፍርድ ቤት መቅረብ አለባቸው ብሏል፡፡
ቀዳማዊት እመቤቷ እስካሁን ድረስ በጉዳዩ ላይም ሆነ በፖሊስ ምርመራ ላይ ምንም አይነት አስተያየት አልሰጡም፡፡

የደቤብ አፍሪካ መንግስት ቀዳማዊት እመቤቷን ፍርድ ቤት ሳትቀርብ የሚለቃት ከሆነ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2015 ከአለም አቀፉ ፍርድ ቤት የፍርድ ማዘዣ ወጥቶበት ሳያስረው የቀረውን የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ወቅት የተነሳበት የህዝብ አመጽ ይነሳል ተብሎ ተሰግቷል፡፡
ግሬስ ሙጋቤ የዙምባቤው ፕሬዚዳንት ሙጋቤ ሁለተኛ ሚስት ስትሆን ጸሀፊው ሆና በምትሰራበት ወቅት ምንም እንኳን ፕሬዚዳንቱ በወቅቱ ባለትዳር የነበሩ ቢሆንም ውሽማቸው ሆና መቆየቷን እና የመጀመሪያ ሚስታቸው በህመም ምክንያት ህይወቷ ሲያልፍ እ.ኤ.አ በ1996 መጋባታቸው ይታወሳል ሲል ቢቢሲ ዘግቦታል፡፡

Friday, 18 August 2017 08:46

በኬንያ የተቃዋሚ ፓርቲ በመወከል ለፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የተወዳደሩት ራይላ ኦዲንጋ ውጤቱን በፍርድ ቤት ተካሰው አንደሚቃወሙ እና እንደሚጠይቁ አስታወቁ፡፡

በኬንያ የተቃዋሚ ፓርቲ በመወከል ለፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የተወዳደሩት ራይላ ኦዲንጋ ውጤቱን በፍርድ ቤት ተካሰው አንደሚቃወሙ እና እንደሚጠይቁ አስታወቁ፡፡
የኬንያ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የሆኑት ራይላ ኦዲንጋ በሳለፍነው ሳምንት በኬንያ በተካሄደዉ ምርጫ ዉጤት በህጋዊ መንገድ በፍርድ ቤት እንደሚቃወሙ እና እንደሚከሱ አስታወቁ፡፡
በኡሁሩ ኬንያታ የተሸነፉት ራይላ ኦዲንጋ የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን የፈፀመውን የድምፅ ማጭበርበር ምክንያት አድርጎ የኬንያታ መንግስት የጅምላ ጭፍጨፋ አድርጓል በሚል ከሷል፡፡
ሆኖም ግን የዉጪ ታዛቢዎች እንደተመለከቱት ምርጫዉ ነፃ እና ትክክለኛ እንደነበረ ገልፀዋል፡፡
የአለም አቀፍ ተቋም ይህ ክስ ብጥብጥን ሊያስነሳ እንደሚችል በመስጋት እንዲረጋጉ አጥብቀዉ አሰገንዝበዋል፡፡
ከምርጫ በኋላ በምርጫ ቦርዱ የተነገረው ውጤት እደሚያሳየዉ ፕሬዘዳንት ኬንያታ 54 በመቶዉ ድምፅ ያገኙ ሲሆን ኦዲንጋ ደግሞ 45 በመቶ የሚሆነዉን ድምፅ አጊኝተዋል፡፡
ኦዲንጋ ከዚህ ቀደም የቀረበውን ውጤትና የፍርድ ቤት ውሳኔ ውድቅ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፤ ለዚህም የሚረዳቸውን ተጨባጭ የሆነ ማስረጃ አቅርበው ነበር በዚህም ማስረጃቸው የምርጫ ድምፁን ለማስቀልበስ እየሞከሩ ነው፤
እንደ ኦዲንጋ ገለፃ በኮምፒውተር የተደረገው የድምፅ መስጠት ሂደት ሙሉ ለሙሉ የተጭበረበረ እና ተአማኒነት የሌለው ነው በዚህም ምክንያት ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለመሄድ ተገደናል ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡
የአውሮፓ ህብረት የውጪ ጉዳዩች ዋና ሀላፊ ፌድሪካ ሞግሄሪኒ እና የቀድሞ የተባበሩት መንግስታት ጄነራል ኮፊ አናን ኦዲንጋ ጥያቄያቸውን በፍርድ ቤ በኩል እንዲያደርጉ ከተናገሩት መካከል ቢሆኑም ፕሬዝዳንታዊ እቹወ ግን ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ መርጫለሁ ማለት ለእነሱ ሀሳብ እጄን ሰጥቻለሁ ማለት አይደለም ብለዋል፡፡
ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የመሄድ ውሳኔ ያስተላለፍነው ለፍርድ ቤቱ ሁለተኛ እድል ለመስጠት ነው፤ ፍርድ ቤቱ ራሱን ለማዳን አንድ እድል ያስፈልገዋል፤ ወይም እንደ 2013ቱ የደም መፋሰስ ነው የሚሆነው ሲሉም ተደምጠዋል፡፡
ዘገባዉ የቢቢሲ ነዉ

Friday, 18 August 2017 08:42

ስፔን በሀያ አራት ሰዐት ውስጥ ስድስት መቶ ስደተኞችን ህይወት ከአደጋ ታደገች፡፡

ስፔን በሀያ አራት ሰዐት ውስጥ ስድስት መቶ ስደተኞችን ህይወት ከአደጋ ታደገች፡፡
የስፔን የባህር በር ጠባቂዎች እንደገለጹት በሀያ አራት ሰአት ውስጥ ስድስት መቶ ስደተኞች ሞሮኮን በማቋረጥ በስፔን ይገኛሉ፡፡
ስደተኞቹን እና ሰላሣ አምስት የሚደርሱ ህጻናትን ጨምሮ አስራ አምስት መርከቦችን እና ጄት አውሮፕላኖችን በመጠቀም ስፔን ህይወታቸውን ታድጋለች፡፡
የተባበሩት መንግስታት እንደገለጸው ባሳለፍነው አመታት ከዘጠኝ ሺህ የሚበልጡ ስደተኞች በስፔን እንዳረፉ ይታወሳል፡፡ በዚህ ጊዜም ከመቶ ሀያ የሚበልጡ ሰዎች የመስመጥ አደጋ እንደደረሰባቸው ይታመናል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንትም ወደ ስፔን በስምንት ወራት ውስጥ የገቡ ስደተኞች ቁጥር ከ13ሺህ በላይ መሆኑን እና ከባለፈው አመት ሲነጻጸር በሶስት እጥፍ ማደጉን አስታውቆ ነበር፡፡
አያይዞም ስፔን የኢኮኖሚዋን እድገት መታደግ የምትፈልግ ከሆነ ወደ ሀገሪቷ ሚገቡትን ስደተኞች ቁጥር መቀነስ እንዳለባትም ተገልጾ ነበር፡፡
የአለም አቀፍ የስደተኞች ተቋም እንደተናገረው ከዚህ ቀደም ስደተኞች የሚበዙባት ሀገር ግሪክ ስትሆን በአሁን ሰአት ግን ስደተኞች በብዛት የሚሰፍሩባት ሀገር ስፔን ሆናለች ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ከዚህ አመት መጀመሪያ ጊዜ አንስቶ ወደ መቶ ሺህ የሚደርሱ ስደተኞች ከሊቢያ ወደ ጣሊያን ሲያቋርጡ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ አርባ ሁለት ሰዎች መንገድ ላይ እንደሞቱ የአለም አቀፍ ስደተኞች ተቋም ይናገራል፡፡
የጣሊያን የባህር በር ጠባቂዎች እንደተናገሩት ባሳለፍነው ሰኔ ወር ከሊቢያ የመጡ አምስት ሺህ የሚደርሱ ስደተኞችን ህይወት ታድገናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡

Friday, 18 August 2017 08:32

በቬንዙዌላ እስር ቤት በእስረኞች እና ጠባቂዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት የ37 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

በቬንዙዌላ እስር ቤት በእስረኞች እና ጠባቂዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት የ37 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
በደቡብ ቬንዙዌላ በሚገኝ አነስተኛ እስር ቤት በእስረኞች እና ታጣቂዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት 37 የሚደርሱ እስረኞች ህይወታቸው ማለፉን የክልሉ መንግስት አሳወቀ፡፡
እስር ቤቱ አስራ ስድስት ሺህ እስረኞችን እንዲይዝ ተደርጎ የተገነባ ቢሆንም በአሁን ሰአት ሀምሳ ሺህ የሚደረሱ እስረኞችን በውስጡ ይዟል፡፡
የሃገሪቱ መሪ ሊቦሪኦ ጉአሩላ እንደገለጹት የጥበቃ ሀይሉ በእስር ቤቱ የተካሄደውን የእስረኞች አመጽ ለመመለስ ሲል ባደረገው ትግል እስረኞቹ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል ብሏል ፡፡
አመጹ በተካሄደበት ምሽትም አሰደንጋጭ የጠመንጃ ተኩስ እና የፈንጂ ድምጽ ሰምተናል ሲሉ ጉአሩላ ለ አሶሼትድ ፕሬስ ተናግረዋል፡፡
በቬንዙዌላ ዋና አቃቤህግ በማህበራዊ ድረ ገጽ እንዳስነበቡት በረብሻው ላይ በተደረገው ምርመራ 11የእስር ጠባቂዎች ቆስለዋል ፡፡
በቬንዝዌላ 30 የሚድርሱ እስር ቤቶች ሲኖሩ በውስጡ ያሉት እስረኞችም የጦር መሳሪያ በማንቀሳቀስ እና በአደንዛዥ እጽ የታሰሩ ናቸው፡፡
ከዚህ ቀደም በ ሁለት ሺህ አስራ ሁለት በቬንዙዌላ በተፈጠረው የእስረኞች አመጽ የ61 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል ፡፡

ዘገባው የታይምስ ወርልድ ነው

Thursday, 17 August 2017 08:01

ፍሊፒንስ ሀገር በተፈጠረው በፖሊሶችና አደንዛዥ እጽ አዘዋዋሪዎች በተፈጠረው ግጭት ሰላሳ ሁለት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል::

ፍሊፒንስ ሀገር በተፈጠረው በፖሊሶችና አደንዛዥ እጽ አዘዋዋሪዎች በተፈጠረው ግጭት ሰላሳ ሁለት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል::
በፍሊፒንስ አደንዛዥ እጽ አዘዋዋሪዎች እጽ ሲያዘዋውሩና ሲነግዱ የተገኙት አንድ መቶና ከዛ በላይ የሆኑ ሰዎች እንደተያዙና ሰላሳ ሁለት የሚሆኑ ሰዎችም ከፖሊሶዎች ጋር ባደረጉት ግጭት ህይወታቸው ማለፉ ተገልጻል፡፡
የፍሊፒንስ ፖሊስ የተፈጠረውን ሲገልጽ የአደንዛዣ እጽ አዘዋዋሪዎች ህገወጥ ስራቸውን የሚጀምሩት ሌሊት እንደሆነ ባገኙት መረጃ መሰረት በቦታው በመሄድ መቶ የሚሆኑ ስዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውንና በተፈጠረው ግጭትም ሰላሳ ሁለት ሰዎች እንደሞቱ ገልጸው በቀጣይ የሰው ደም መጣጭ የሆነውን አደንዛዣ እጽ ለማጥፋት ያላቸውን ሀይል በሙሉ በመጠቀም እንደሚሰሩ ገልጸዋል ፡፡
የሀገሬቱ መሪ የሆኑትን ሮድሪጎ ዱትሬት እንደተናገሩት በሀገሪቱ የአደንዛዥ እጽ እጅጉን እየተስፋፋ እንዳአለን ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በሶስት እጥፍ መጨመሩን ገልጸው በቀጣይም ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስዱ ገልጸዋል፡፡
ዘገባው የቢቢሲ ነው

Thursday, 17 August 2017 07:33

የህንድ እና የቻይና ወታደሮች በሂማሊያ ድንበር ጠብመንጃ ተማዘዋል

የህንድ እና የቻይና ወታደሮች በሂማሊያ ድንበር ጠብመንጃ ተማዘዋል
ቻይና እና ህንድ ከዚህ ቀደም በዚሁ ቦታ ክርክር ገጥመው የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ነገሩን አባብሰውታል፡፡ የህንድ ባለስልጣናት እንደገለጹት ከሆነ በምእራብ ሂማሊያ ድንበር ችግር እንደነበር እና በህንድ እና በቻይና መካከል ያለው የድንበር ግጨት እንደነበር በትላንተናው እለት ተናግረዋል፡፡
የፒቲ አይ የዜና ምንጭ እንደገጸው የግጭቱ መነሻ በሁለቱም ሀገራት በኩል ድንጋይ መወርወር ሲሆን የቻይና ወታደር የህንድ ድንበር አጠገብ በሆነቸው ፓንጎሊካ ሀይቅ አከባቢ ጥሶ ለመግባት ሲሞክር እንደሆነም ተገልጾል፡፡
የሁለቱም ሀገራት ዜጎች ከሀገር ሀገር እንዳይሸጋገሩ እና ዶክላምን እንዳያልፉ ሌላው የቻይና የህንድ እና የበሁታን ድንበር እንዳያልፉ ስምምነት ነበራቸው፡፡
ፒቲ አይ ያናገራቸው የወታደር ባለስልጣናት እነደገለጹት ከሆነ ያልተስማሙበት ቻይና ድንብሩ የኔ ነው ስትል ህንድም በበኩሏ የኔ ነው እያለች የመብት ጥያቄ እያቀረበች ነው፡፡ የህንድ ባለስልጣናት በበኩላቸው ለቢቢሲ እንደገለጹት ይሄ ጉዳይ ምንም አዲስ ነገር የለውም ለመጀመሪያም ጊዜ የተፈጠረ ነገር አይደለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዳስጠነቀቁት ህንድ ያላትን ሰራተኛ ፣ መገልገያ እቃዎች ከሀገሬ እንድታስወጣ ከምድሬ ላይም እንድትወጣ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በሁለቱ ሀገራት መካከል ምንም አይነት የድንበር መስመር አለመኖሩ ለችግሩ ምክንያት እንደሆነ ተገልጾል፡፡
እ.እ.አ አቆጣጠር ከ1962 ጀምሮ የሁለቱ ሀገራት የድንብር ግጭት እስከ አሁንድረስቀጥሎል፡፡
ዘገባው የ ቢቢሲ ነው

Thursday, 17 August 2017 07:25

በሜድትራኒያን ባህር ላይ በነብስ አድን ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሁለት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ስራቸውን አቆሙ።

በሜድትራኒያን ባህር ላይ በነብስ አድን ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሁለት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ስራቸውን አቆሙ።
በሜድትራኒያን ባህር ላይ በነብስ አድን ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሁለት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ስራቸውን አቁ መዋል ፤ የሊቢያ መንግስት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በባህር ክልሉ ላይ እንዳይንቀሳቀሱ ማገዱ ለድርጅቶቹ ስራ ማቆም ምክንያት ሆኖል።
ድርጅቶቹ የጀርመኑ ሲ አይ እና ዶክተር ስዊዝ አውት ቦርደርስ ተብሎ የሚታወቁት ናችው።
የሊቢያ መንግስት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለህገወጥ አዘዋዋሪዎችን ከለላ እየሆኑ ነው በሚል ነው ድርጅቶቹ በባህር ክልሉ ላይ እንዳይንቀሳቀሱ ያገደው።
ከሊቢያ በባህር የሚጓዙ አፍሪካውያን ስደተኞች ዋነኛዋ ማረፊያቸው የሆነችው ጣሊያንም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ለህገወጥ አዘዋዋሪዎች ከለላ እንዳይሆኑ ልዩ ግዴታ እያስፈረመች ትገኛለች።
የጀርመኑ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲ አይ ግን ህጉም ሆነ የሊቢያ ገደብ የሜድትራኒያን የነብስ አድን ስራ ላይክፍተት ይፈጥራል ሲል አስታውቆል።
ድርጅቱ ከባለፈው የፈረንጆቹ አመት ጀምሮ ከ 12 ሺህ በላይ ስደተኞች ህይወት አድኛለው ብሏል።
ዘገባው የሲኤንኤን እና አልጀዚራ ነው

Thursday, 17 August 2017 07:23

በሴራሊዮን በደረሰዉ የጎርፍና አፈር ናዳ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ 400 በላይ ደርሷል

በሴራሊዮን በደረሰዉ የጎርፍና አፈር ናዳ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ 400 በላይ ደርሷል
ባሳለፍነዉ ሰኞ በዋና ከተማዋ ፍሪታዉን በደረሰዉ የጎርፍና የአፈር ናዳ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ 400 ከፍ እንዳለ የተነገረ ሲሆን 600 ያህል ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አልታወቀም ይህም የሟቾች ቁጥር ከፍ እንዲል ሊያደርግ ይችላል ተብሏል
በሀገሪቱ ትልቁ የሆነዉ ኮኖት ሆስፒታል የተጎጂዎች ቁጥር ከ አቅም በላይ እንደሆነበትም እየገለጸ ይገኛል
በተራራና በባህር የተከበበችዉ ፍሪታዉን ከፍተኛ ዝናብን ከሚያስተናግዱ ከተሞች መሀል አንዷ ስትሆን መጠነኛ ጎርፍ በከተማዋ የተለመደ ቢሆንም የአሁኑ አይነት የጎርፍ አደጋ ግን አጋጥሟት አያዉቅም
ለአደጋዉ እንደመንስኤ የሚጠቀሰዉ የአየር ንብረት ለዉጥ ቢሆንም የህዝቡ አሰፋፈር. ከተማዋ በ ፕላን አለመገንባቷ እና የጎርፍ መከላከያዎችና ዛፎች አለመኖራቸዉም አደጋዉን ከባድ ሊያደርጉት መቻላቸዉ ተገልጻል
በአደጋዉ ከቤት ንብረታቸዉ የተፈናቀሉ ዜጎችም ማረፊያቸዉን በእምነት ተቋማት አድርገዋል
የሴራኒዮን መንግስትም ድጋፍ እንዲደረግለት የጠየቀ ሲሆን ብሪታንያ እና እስራኤል ንጹህ ዉሃን ጨምሮ መድሃኒትና ብርድ ልብስ እየላኩ ይገኛሉ
ሴራሊዩን በኢቦላ ምክንያት በአንድ ቀን 111 ዜጎቿን አጥታ እንደነበር ይታወሳል bbc

Wednesday, 16 August 2017 07:56

ቻይና ከሰሜን ኮሪያ የምታስገባቸው ምርቶች ላይ ተግባራዊ ያደረገችውን ማእቀብ ተከትሎ ሀገሪቱ በአሜሪካ የጦር ሰፈር ጉዋም ላይ አደርገዋለሁ ያለችውን ጥቃት መሰረዟን አስታወቀች፡፡

ቻይና ከሰሜን ኮሪያ የምታስገባቸው ምርቶች ላይ ተግባራዊ ያደረገችውን ማእቀብ ተከትሎ ሀገሪቱ በአሜሪካ የጦር ሰፈር ጉዋም ላይ አደርገዋለሁ ያለችውን ጥቃት መሰረዟን አስታወቀች፡፡

ቻይና ከሰሜን ኮሪያ የምታስገባቸውን የከሰል፤ብረት፤የብረት አፈር እና የባህር ምግቦች እንደምታቆም ባሳወቀች ማግስት የሰሜን ኮሪያ ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን ሚሳኤሎቹን ለመተኮስ ያለው እቅድ መሳካት ላይ በጄነራሎቹ ማብራሪያ ቢደረግለትም ለመቆየት እንደመረጠ በሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን በኩል አሳውቋል፡፡
ምንም እንኳን ጉዋምን ለመምታት አስፈላጊውን ዝግጅት ብናጠናቅቅም ውሳኔ ከማስተላለፋችን በፊት ሞኞቹ ያንኪዎች የሚያደርጉትን ማየት እንፈልጋለን ስትል ሰሜን ኮሪያ በሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ተናግራለች፡፡
የሰሜን ኮሪያን 90 በመቶ አለምአቀፍ ንግድ ድርሻ የምትወስደው ቻይና ምርቶቹን ከመላክ እንደምትቆጠብ ያሳወቀችው በተባበሩት መንግስታት ሀገሪቱ ባሳለፍነው ወር ያደረገችውን ተከታታይ የባሊስቲክ ሚሳኤል ተኩስ ሙከራ ተከትሎ የተጣለውን ማእቀብ ለመተግበር እንደሆነ ተናግራለች፡፡
ማእቀቡ ሰሜን ኮሪያ በየአመቱ ከምታገኘው ገቢ 1ቢሊየን ዶላር ለማጣት ታቅዶ የተደረገ ነው፡፡
ቻይና በ2009 አ.ም ብቻ ከሰሜን ኮሪያ 1.2 ቢሊዩን ዶላር የሚያወጣ ከሰል አስገብታ ነበር እንደ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ከሆነ የዚህ አመቱ ቁጥር በማእቀቡ ምክንያት እጅግ ዝቅተኛ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
አሁን ሀገሪቷ ጉዋም ላይ ያነጣጠረችውን ጥቃት ለጊዜው እንዳቆመች መግለጾን ተከትሎ የጎረቤቷ ደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ሙን ጄ ኢን አሜሪካን ሳታማክሪኝ በኮሪያ ቆንጽላ አካባቢ ጥቃት እንዳታደርስ ጠይቃለች፡፡
ቢቢሲ ዘግቦታል፡፡

Wednesday, 16 August 2017 07:53

ወደ አምሳ ሺ የሚጠጉ ረዳት አልባ የሆኑ ሰዎች በደቡብ ሶሪያ ጆርዳን ጠረፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

ወደ አምሳ ሺ የሚጠጉ ረዳት አልባ የሆኑ ሰዎች በደቡብ ሶሪያ ጆርዳን ጠረፍ ላይ ይገኛሉ፡፡
ወደ ሀምሳ ሺ ከሚጠጉት እነኚህ ረዳት አልባ ከሆኑት ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ሴቶች እና ህጻናት ሲሆኑ ይህ ያረፉበት ጠረፍም ያልተስተካከለ ቦታ እና የአየር ንብረቱም አስቸጋሪ ነው ሲል የተባበሩት መንግስታት ተናግሯል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ምክትል ቃለ አቀባይ የሆኑት ፋርሀን ሀቅ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ስደተኞቹ ቦታውን ለቀው በሚሄዱበት ጊዜ የተለያዩ አደጋዎች ደርሶባቸዋል ብለዋል፡፡
ቃለ አቀባዩ በርም ተብላ በምትጠራው ቦታ ላይ የቀሩት እነኚህ ሰዎች የጤና ችግር እና የምግብ እጥረት አጋጥሟቸዋል ሲሉ በድጋሚ ተናግረዋል፡፡
የሶሪያ መንግስት እና አጋሮቹ በቦታው ላይ ያሉትን ስደተኞች በመቃወም ጆርዳን ጠረፍ ላይ ያለ ቁልፍ የሆነ ቦታ ተቆጣጥረዋል፡፡
የሶሪያ ብዙሃን መገናኛዎች እንደገለጹት የሀገሪቷ የመንግስት ወታደሮች የያዙት ቦታ አንድ ሺህ ሦስት መቶ ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሆን ነው ሲሉ ገልጸዋል ፡፡
ካለፉት አመታት በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጆርዳን ጠረፍ ላይ ለሚገኙ ስደተኞች የእርዳታ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ተስማምቷል፡፡
ፈርአን ሀቅ በትናንትናው ዕለት እንደተናገሩት የተባበሩት መንግስታት የጆርዳንን ግዛት መደገፋቸውን እንዲቀጥሉ እና ተጨማሪ ህይወት አድን እርዳታ እንደሚያስፈልግም ቃለ አቀባዩ ተናግረዋል፡፡
ምንጫችን አልጀዚራ ነው

Wednesday, 16 August 2017 07:33

የኢራን ፕሬዝዳንት የሆኑት ሀሰን ሮሀኒ በሠአታት ውስጥ የኒውክለር ማብላያችንን በድጋሚ ስራ ማስጀመር እንችላለን ሲሉ አሜሪካ በሀገሪቱ ላይ ማህቀብ ከመጣል እንድትቆጠብ አስጠነቀቁ፡፡

የኢራን ፕሬዝዳንት የሆኑት ሀሰን ሮሀኒ በሠአታት ውስጥ የኒውክለር ማብላያችንን በድጋሚ ስራ ማስጀመር እንችላለን ሲሉ አሜሪካ በሀገሪቱ ላይ ማህቀብ ከመጣል እንድትቆጠብ አስጠነቀቁ፡፡
ዋሽንግተን ኢራንን በመቃወም በሀገሪቱ ላይ የጣለችው ማዕቀብ እና ማስፈራሪያ በሰዓት እና በቀናት ውስጥ መቆም አለባት ሲሉ ሀሰን ሮሀኒ ተናግረዋል፡፡
ሮሃኒ እንደተናገሩት በድጋሚ የተጀመረው የኒውክለር ማብላያ ስራ ሁለት ሺህ አምስት ላይ ከነበረው በበለጠ መሰራት አለበት በተጨማሪም ኢራን ከአለም አቀፍ ሀይላት ጋር የተፈራረመችው የኒውክለር ስምምነት የሀገሪቷን የዩራኒየም መበልጸግ አቅም ከፍ እንዲል እና አለም አቀፍ ማዕቀቡ እንዲነሳሳ በማሰብ ነው ብለዋል፡፡
ስለ ሮሃኒ የሃገሪቱ የህግ ባለሙያዎች በዛሬው ዕለት ባደረጉት ንግግር ስለ ኢራን አቅም ምንም አይነት ማስረጃ አላቀረቡም፡፡ ነገር ግን የትራምፕ አስተዳደር በኢራን ላይ ያለውን ግፊት እንዲያነሳ የሚገፋፋ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ሮሃኒ ካስተላለፈው ዛቻ በኋላ በሌላ በኩል ኢራን በስምምነቱ ላይ ታማኝ መሆን እንደምትፈልግ ተናግረዋል፡፡ ዩ ኤስ ኤ ቱ ዴይ ዘግቦታል

Tuesday, 15 August 2017 10:45

ጀርመን የስዊዘርላንድ ባለስልጣኖች የታክስ ባለስልጣን መስሪያ ቤቴ ውስጥ በስውር ሰርገው ለመግባት ሰላዮች ልካብኛለች ስትል ወነጀለች፡፡

ጀርመን የስዊዘርላንድ ባለስልጣኖች የታክስ ባለስልጣን መስሪያ ቤቴ ውስጥ በስውር ሰርገው ለመግባት ሰላዮች ልካብኛለች ስትል ወነጀለች፡፡
ውንጀላውን ተከትሎ የጀርመን የመገናኛ ብዙሃን የፌዴራል ዐቃብያነ-ሕግ ምርመራውን እንደከፈቱ ዘግበዋል፡፡
የጀርመን ዓቃብያኖች ከስዊዘርላንድ የስለላ ድርጅት ሶስት ሰላዮች ላይ ምርመራ ማካሄድ በመጀመራቸው በጀርመን ባለሥልጣናት እንደታሰሩ ለሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡.ጉዳዩ ደግሞ የታክስ ስርዓቱን በህገ ወጥ መልኩ ለመሰለል በማሰባቸው እንደሆነ ተነግሯል፡፡
የስዊስ ባንኮች ላይ ያነጣጠረ የግብር አፇፃፀም በሚሰራው የጀርመን ታክስ ተመራማሪዎች ቡድንን ለመሰለል በመሞከር ወንጀል ተከስሰዋሌ.
የስለላ ሙከራ ተደርጎብኛል የምትለው ጀርመን አንድ በስዊስ ፌዴራላዊ አገልግሎት (NDB) ተቀጥሮ የሚሠራ "ዳንኤል ኤም 54" ሰው ብቻ ነው የስዊዘርላንድ ዜጋ በስዊዲን ህግ መሰረት የታወቀው.
የጀርመን ጋዜጣ ሱጁድቼ ፃይቱንግ እና የሁለቱን የሀገሪቱ አጠቃላይ ስርጭቶች እንዲሁም ሶስት አዳዲስ ግለሰቦች በስዊስ ናምቢ ሠራተኞች ተቀጣሪዎች እንደሆኑ ይናገራሉ.የጀርመን ፌዴራላዊ አቃቤ ህግ ጽ / ቤት በቅርብ ወቅታዊ የይገባኛል ጥያቄ ላይ አስተያየት አልሰጠም, እንዲሁም ሶስት ተጨማሪ ወንዶች ስማቸው አልተለቀቀም.
የ 2006 የጀርመን ባለስልጣናት ከስዊስ ባንኮቹ የተወረወሩ የግል መረጃዎችን የተሰረዙ ዲስኮች እና የዩኤስቢስ ዶከመንቶች የጀርመን ታክሶችን ማጭበርበሪያ ለመለየት ጥቅም ላይ ውለዋል.
ዘ ኢንዲፔንደንት

Monday, 14 August 2017 08:29

የቲቤት መንፈሳዊ መሪ ዳላይ ላማ ወደ አፍሪካዊቷ አገር ቦትስዋና ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞ ሰረዙ፡፡

የቲቤት መንፈሳዊ መሪ ዳላይ ላማ ወደ አፍሪካዊቷ አገር ቦትስዋና ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞ ሰረዙ፡፡
መንፈሳዊው መሪ ዳላይ ላማ ለጉዞዋቸው መሰረዝ እንደምክንያት የቀረበው ዶክተሮቻቸው ረጅም ጉዞ እንዳያደርጉና እረፍት እንደሚያስፈልጋቸው ስለነገሩዋቸው ነው ተብሏል፡፡ እርሳቸውም ከዶክተሮቻቸው ምክር በኃላ "የሰማንያ ሁለት አመት የእድሜ ባለፀጋ ስለሆንኩ ሰውነቴ እረፍት ያስፈልገዋል" በሚል ጉዞዋቸውን እንደሰረዙት እወቁት ብለዋል፡፡
ዳላይ ላማ በቦትስዋና ዋና መዲና ጋቦሮኒ በሚካኤደው የሰብአዊ መብት ኮንፍረንስ ላይ ለመሳተፍና እግረ መንገዳቸውንም የቦትስዋናውን ፕሬዝደንት አያን ካሃማን ለማግኘት አልመው ነበር፡፡
የቦትስዋናው ፕሬዝደንት አገራቸው በቲቤታውያን መንፈሳዊው መሪ እንደምትጎበኝ አሳውቀው በነበረበት ወቅት ቻይና ይህንን መሰል የአገሯን መሠረታዊ ጥቅም የሚጎዳ ነገር በፍፁም እንደማትቀበለው ማስጠንቀቋ ይታወሳል፡፡
ቻይና ቦትስዋናን ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት ጋር ያላት ግንኙነት ጠንካራ ነው፡፡ በዚህም መንፈሳዊው መሪ እ.ኤ.አ ከ2009 ጀምሮ ለሶስት ጊዜያት ያህል የቦትስዋና ጎረቤት አገር ወደ ሆነችው ደቡብ አፍሪካ እንዳይገቡ የመግቢያ ፈቃድ ተከልክለዋል፡፡
የቻይና መንግስት ቲቤትን ከአስተዳደሬ ነጥለው ራስ ገዝ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ነው የሚላቸው የቲቤት መንፈሳዊው መሪ ዳላይ ላማ በስድስት አህጉራት የሚገኙ ስልሳ ሰባት አገራትን ጎብኝተዋል፤ የኖቤል የሠላም ሽልማትን ጨምሮ አንድ መቶ ሃምሳ ሽልማቶችን ተቀብለዋል ሲል ሚካኤል ጌታሠጠኝ አፍሪካ ኒውስን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

Friday, 11 August 2017 09:47

የቬንዙዌላን ቀውስ ለማረጋጋት እና የምርጫ ውጤቱን ግልጽ ለማድረግ አጣሪ የእውነት ኮሚቴ ተመሰረተ፡፡

የቬንዙዌላን ቀውስ ለማረጋጋት እና የምርጫ ውጤቱን ግልጽ ለማድረግ አጣሪ የእውነት ኮሚቴ ተመሰረተ፡፡
የአዲሱ የእውነት ኮሚቴ መሪ የሆኑት ዴልሲ ሮድሪጊየዝ እንደገለጹት አዲሱ ኮሚቴ በአሁን ሰአት ያለውን የፖለቲካ ብጥብጥ፣አለመረጋጋት እና ጥላቻን ለማስቆም የሚረዳ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ካሳለፍነው ሚያዚያ ወር ጀምሮ በሀገሪቷ በተፈጠረው የፖለቲካ አለመረጋጋት ከመቶ ሀያ የሚበልጡ ሰዎች ሞተዋል፡፡
ህገ መንግስቱ አሸባሪ ተቋሞችን የተቃወመ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት ግን አሸባሪዎቹ በጦር ሰራዊቱ እንዲገደሉ ሀሳብ ሰጥቷል፡፡
የኮሚቴው ምስረታ የጸደቀው በስብሰባው በተካፈሉት የመንግስት ባለስልጣናት ድምጽ ሲሆን ስብሰባውን በአፈ ጉባሄነት ይመሩ የነበሩትም ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ናቸው፡፡
ፕሬዝዳንት ማዱሮ እንደገለጹት አዲስ የተቋቋመው የእውነት ኮሚቴ በህገ መንግስቱ እና በህብረተሰቡ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት እንዲቀንሰ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ነገር ግን አምስት መቶ አርባ አምስት የሚሆኑት የካቢኔ አባላቶች አሁን ያለው የፖለቲካ ብጥብጥ ይህን የእውነት ኮሚቴ ለማቋቋም ያስቸግራል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የአዲሱ የእውነት ኮሚቴ መሪ ሆነው የተሾሙት ዴልሲ ሮድሪጊየስ እንደገለጹት ይህ ኮሚቴ እየተካሄደ ያለውን የፖለቲካ ረብሻ በደንብ ማጣራት አለበት ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ዘገባው የቢቢሲ ነው

Friday, 11 August 2017 09:31

ካናዳ ስደተኞች ወደ ሀገራ እስኪገቡ ድረስ እንዳይንገላቱ በሚል ጊዜያዊ የመጠለያ ካምፕ ሰራች፡፡

ካናዳ ስደተኞች ወደ ሀገራ እስኪገቡ ድረስ እንዳይንገላቱ በሚል ጊዜያዊ የመጠለያ ካምፕ ሰራች፡፡
የካናዳ ወታደራዊ ሀይል ከአሜሪካ ለሚመጡ የጥገኝነት ስፍራ ፈላጊዎች የሚሆን ካምፕ ለአሜሪካ ወሰን ቅርብ በሆነ ሴንት በርናርድ ዲላኮሊ በተባለ ከተማ አቋቋመ፡፡
የጦር ሰራዊቱ እንደገለፀው ከ አምስት መቶ ለሚበልጡ የጥገኝነት ስፍራ ፈላጊዎች የሚሆነው ይህ ካምፕ ስደተኞቹን የሚያገለግል በቂ መብራት እና የማሞቂያ መሳሪያዎች አሉት፡፡
በ2017 መጀመሪያ አካባቢም ከ አራት ሺህ ሦስት መቶ የሚበልጡ ስደተኞች የአሜሪካን ጠረፍ አቋርጠው ወደ ካናዳ ሄደው ነበር፡፡
ስደተኞቹ በቅድሚያ ያረፉት በሞንትሪል ኦሎምፒክ እስታዲየም ሲሆን በአሁን ሰአትም ለስደተኞቹ ለወደፊት የሚያገለግል ሆስፒታል በድጋሚ ተከፍቷል፡፡
ስደተኞቹ በአሜሪካ ለብዙ አመታት የኖሩ ቢሆንም እ.ኤ.አ በ2010 በደረሰው አስደንጋጭ የመሬት መንቀጥቀጥ የተሰደዱ ስልሳ ሺህ ስደተኞችን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማባረሩ ወደ ካናዳ እንዲሰደዱ አድርጓቸዋል፡፡
የካናዳ መንግስት ይህ ስደተኞችን የመቀበል ስራ እንደሚቀጥል አሳውቋል፡፡
ምንጫችን ቢቢሲ ነው

Friday, 11 August 2017 09:31

ካናዳ ስደተኞች ወደ ሀገራ እስኪገቡ ድረስ እንዳይንገላቱ በሚል ጊዜያዊ የመጠለያ ካምፕ ሰራች፡፡

ካናዳ ስደተኞች ወደ ሀገራ እስኪገቡ ድረስ እንዳይንገላቱ በሚል ጊዜያዊ የመጠለያ ካምፕ ሰራች፡፡
የካናዳ ወታደራዊ ሀይል ከአሜሪካ ለሚመጡ የጥገኝነት ስፍራ ፈላጊዎች የሚሆን ካምፕ ለአሜሪካ ወሰን ቅርብ በሆነ ሴንት በርናርድ ዲላኮሊ በተባለ ከተማ አቋቋመ፡፡
የጦር ሰራዊቱ እንደገለፀው ከ አምስት መቶ ለሚበልጡ የጥገኝነት ስፍራ ፈላጊዎች የሚሆነው ይህ ካምፕ ስደተኞቹን የሚያገለግል በቂ መብራት እና የማሞቂያ መሳሪያዎች አሉት፡፡
በ2017 መጀመሪያ አካባቢም ከ አራት ሺህ ሦስት መቶ የሚበልጡ ስደተኞች የአሜሪካን ጠረፍ አቋርጠው ወደ ካናዳ ሄደው ነበር፡፡
ስደተኞቹ በቅድሚያ ያረፉት በሞንትሪል ኦሎምፒክ እስታዲየም ሲሆን በአሁን ሰአትም ለስደተኞቹ ለወደፊት የሚያገለግል ሆስፒታል በድጋሚ ተከፍቷል፡፡
ስደተኞቹ በአሜሪካ ለብዙ አመታት የኖሩ ቢሆንም እ.ኤ.አ በ2010 በደረሰው አስደንጋጭ የመሬት መንቀጥቀጥ የተሰደዱ ስልሳ ሺህ ስደተኞችን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማባረሩ ወደ ካናዳ እንዲሰደዱ አድርጓቸዋል፡፡
የካናዳ መንግስት ይህ ስደተኞችን የመቀበል ስራ እንደሚቀጥል አሳውቋል፡፡
ምንጫችን ቢቢሲ ነው

Friday, 11 August 2017 09:23

30 ንጹሀን ዜጎች በማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በተፈጸመ ጥቃት ህይወታቸው አለፈ፡፡

30 ንጹሀን ዜጎች በማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በተፈጸመ ጥቃት ህይወታቸው አለፈ፡፡
ግጭቱ የተፈጠረው በማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በሚገኙት የታጠቁ ቡድኖች እና በራስ መከላከል ቡድን መካከል ሲሆን ህይወታቸው ካለፉ ንጹሃን መከከል በጋመቦ ከተማ የሚገኘው በቀጣይ ረቡእ እለት ለሚካሄደው የጤና ድርጅት ስብሰባ ለመታደም የመጡ 6የቀይ መስቀል በጎአደራጊዎች ይገኙበታል፡፡
በደም መፋሰስ ምስቅልቅሉ የወጣው ከባንጋሱ 75 ኪሎ ሜትር የምትርቀው የጋምቦ ከተማ ሁከቱ የተጀመረው ባሳለፍነው ሳምንት ነው፡፡ የምስራቅ አፍሪካ የ ቀይ መስቀል ፕሬዝዳንት የሆኑት አንቶኒ የአጋሮቻችንን ሞት መስማታችን ለኛ አስደንጋጭ ዜና ነው ሲሉ አያይዘውም ሁሉንም ፓርቲዮች ንጹሃን ዜጎችን እንዲተዉ እና የበጎ አድራጎት ሰራተኞችን እንዲያከብሩ ነግረናቸው ነበር ብለው ተናግረዋል፡፡
በ ማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ አስራ ሁለት ሺህ የሰላም አስከባሪዎች ቢኖሩም በጋመቦ በተፈጠረው ግጭት ላይ አንዳቸውም ግጭቱን ለማብረድ አልተገኙም፡፡
የሃገሪቱ ቃለ አቀባይ እንዳሉት የሰላም አስከባሪዎቹ ሳይመጡ ስለቀሩ የራሳቸንን ወታደሮች አደራጅትን ልከናል ብለዋል፡፡
የአለም አቀፍ ጥበቃ ደርጅት በህጉ ላይ እንዳስቀመጠው ማንኛውም የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በማንኛውም ቦታ ሲንቀሳቀሱ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ይላል ነገር ግን በዚህ አመት በቻ በቀይ መስቀል ላይ እነደዚህ አይነት አደጋ ሲደርስ 3ኛ ጊዜ ነው፡፡ የተባበሩት መንግሰታት የእርዳታ ድርጅት ዋና መሪ ይሄ ግጭት የ ጅምላ ጭፍጨፋ ምልክት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡

Friday, 11 August 2017 09:11

በኬንያ በአንድ የምርጫ ጣቢያ በተነሳ ብጥብጥ የ አራት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

በኬንያ በአንድ የምርጫ ጣቢያ በተነሳ ብጥብጥ የ አራት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
አንድ የአይን እማኝ እንደተናገረው ፖሊስ 3ሰዎች ተኩሶ ገድለ አራተኛው ደግሞ በተቃዋሚዎች የተገደለ ነው፡፤ቢሆንም ግን ሁከት እና ብጥብጡ እስካሁን እንዳቀጠለ ነው፡፡ኬንያውያኖች የ2007 የፕሬዝዳንት ምርጫ አስከትሎ በመጣው ክርክር ምክንያት አንድ ሺህ ሰዎች የሞቱበት የዘር እልቂት ተመልሶ እንዳይመጣ በፍርሃት እና በጭንቀት ላይ ናቸው::
የኤሌክትሮኒክስ ድምጽ መስጫ ተጭበርብሯል በሚል የተቃዋሚ መሪው ራይሊ ኡዲንጋ ሲሰነዝሩ የነበረውን ትችት የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን መሰረተ ቢስ እንዲሁም የፈጠራ ወሬ ነው ሲል ጉዳዩን አጣጥሎታል፡፡በነሳይሮቢ እና በ ኪሰሙ ከማክሰኞ ጀምሮ የ ድምጽ ቆጠራው ቀጥሏል የምርጫ ኮሚሽኑም ምርጫው ነጻ እና ፍትሃዊ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡
የኤሌክተሮኒክሱን የድምጽ መስጫ የሰበሩት ሰዎች ባለፈው ጊዜ በጭካኔ ተገድሎ የነበረውን የምርጫ ቢሮ ሰራተኛውን መታወቂያ ሊጠቀም እንደሚችል ተቃዋሚው መሪ ኡዲነጋ ጥርጣሪያቸውን ገልጸዋል፡፡ በሚወጣው የኬንያ ውጤት ላይ የተቃዋሚ መሪው ንግግር ሽብር ሊያስነሳ እነደሚችል የኬንያ ስጋት ነው፡፡
በናይሮቢ የተቃውሞ ሰለፍ ከወጡት ሰዎች ፖሊስ አነድ ስው ገደለ እንዲሁም ሰላመዊ ሰልፍ የወጡ 100 ሰዎችን በትኗል በተመሳሳይም በ ኮስታል ታና ወንዝ ዳርቻ በምተገኝ መንደር በተከሰተው ጥቃት የተመለከቱ የአይን እማኝ እንደተናገሩት የታጠቁ ወንበዴዎች 1 ሰው ገድለው ብዙ ሰዎች ማቁሰላቸውን ተናግረዋል፡፡ ፖሊስም 2ጥቂዎችን ተኩሶ ገድሏል፡፡የውጭ ታዛቢዎች የተፈጠረው ነገር ማስረጃ ስለሌለው አስተያየት ከመስጠተት ተቆጥበዋል ነገር ግን ሁሉም ፓረቲዎች እንዲረጋጉ አሰገንዝበዋል
የምርጫ ቦረዱ መሪ እዛራ ቺሎባ እንዳሉት ከምርጫው በፊትም ሆነ ከምርጫው በኋላ ምንም አይነት የውጭ ጣልቃ ገብንት አልተፈጠረም የኛ የምርጫ አስተዳደር ስርአት ደህንነቱ የተጠበቀ ነው ሲል አያይዞም የኤሌክትሮኒክስ ድምጽ መስጫው ተሰብሯል እንዲሁም ተጭበርብሯል በሚል የተነሳውን ቅሬታ እነደሚያጣራ ለሀገሪቱ የዜና አሰራጮች ገልጸዋል፡፤
የምርጫ ቦርድ በድህረ ገጹ እነዳስቀመጠውፕሬዝዳንት ኬንያታ በ 54.3 በመቶ የመራጮች ድምጽ ለ 44.8በመቶ ተቃዋሚያቸውን ኦዲንጋን 97 በመቶ በሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች 1.4 ሚሊዮን በሚሆን የመራጭ ድምጽ በማግኘት በሰፊ ድምጽ እየመሩ እንደሆነ ዘግቧል ፡፡
ዘገባው all Africa .com