በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ በግንባታ ላይ ያሉት ከአራት ሺህ 700 በላይ የጋራ የመኖሪያ ህንጻወች በቀጣይ አመት ይመረቃሉ፡፡
በአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ ልዩ ስሙ ቦሌ ቡልቡላ ተብሎ በሚጠራ ቦታ እየተገነቡ የሚገኙት 52 ህንጻዎችንና 4ሺህ 708 የመኖሪያ ቤቶችን ግንባታ አሁን 80 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን በ2010 አ.ም ይመረቃሉ ሲል ኢንተርፕራይዙ አስታውቋል፡፡
የህንጻዎቹ ግንባታ የተጀመረው በ2006 እና በ2007 አ.ም ነበር፡፡
የግንባታውን ሂደት እያማከረ የሚገኘው የአስፓየር ኤ ኢኮም ድርጅት ፕጀክት አስተባባሪ አቶ ዳንኤል መስፍን በአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ በቅርንጫፍ አንድ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ስር በቦሌ ቡልቡላ እየተካሄዱ ባሉ ግንባታዎች ደረጃ አንድ የሆኑ 24 ኮንትራክተሮች እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
በቦሌ ቡልቡላ የቤቶቹ ግንባታ ሲጠናቀቅ በውስጡ 4ሺህ 708 አባወራ የመያዝ አቅም ያላቸው የመኖሪያ ቤቶች፤ 1ሺህ 170 የንግድ ቤቶች፤ ከሶስት ሺህ በላይ መኪና ማስቆም የሚያስችል ማቆሚያ፤ የጋራ የመጠቀሚያ ቦታዎች፤ የህጻናት መዋያና የህክምና መስጫ ጣቢያ እንደሚኖረው የኢንተርፕራይዙ የኮሚውኒኬሽን ደጋፊ የስራ ሂደት አስታውቋል፡፡
ናርዶስ ዩሴፍ

Tuesday, 29 August 2017 13:32

ኬንያዉያን የ ፕላስቲክ እቃ መያዣዎችን እንዳይጠቀሙ ታገዱ

ኬንያዉያን የ ፕላስቲክ እቃ መያዣዎችን እንዳይጠቀሙ ታገዱ

የፕላስቲክ የእቃ መያዣዎቹ ጥቅም ላይ እንዳይዉሉ እገዳ የተጣለው አካባቢን ከብክለት ለመጠበቅ ነው የተባለ ሲሆን ከዚህ በኋላም የፕላስቲክ የእቃ መያዣዎችን ሲሸጥ፣ ሲያመርት እና በእጁ ይዞ የተገኘ ሰው 38 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የገንዘብ ቅጣት እና የ4 ዓመት የእስር ቅጣት ሊተላለፍበት ይችላል ሲሉ የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታዉቀዋል፡፡
ኬንያዉያን በወር ከ24 ሚሊየን በላይ የፕላስቲክ መያዣዎችን የሚጠቀሙ ሲሆን 80 ሺህ ያህል ዜጎችም በዚህ ስራ ይተዳደራሉ አምራቾችም ታዲያ መንግስት ያሳለፈዉ ዉሳኔ እነዚህን ሰዎች ከስራ ገበታቸዉ ላይ እንዲፈናቀሉ ያደርጋል ሲሉ ተደምጠዋል
ይሁን እንጂ ባሳለፍነዉ አርብ በዋለዉ ችሎት ፍ/ቤቱ የአምራቾችን ቅሬታ ዉድቅ ማድረጉ ተሰምቷል
ኬንያ የፕላስቲክ የእቃ መያዣዎች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ስትከለክል በ10 ዓመታት ውስጥ የዘንድሮው ለሶስተኛ ጊዜ ነው ፡፡
ደቡብ አፍሪካ፣ ሩዋንዳ እና ኤርትራን ጨምሮ የተወሰኑ የአፍሪካ ሀገራት የፕላስቲክ የእቃ መያዣዎች በሀገራቸው ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ማገዳቸዉን አስታዉሶ የዘገባዉ ቢቢሲ ነዉ፡፡

Tuesday, 29 August 2017 13:31

በደቡብ አፍሪካ የሰው ስጋ መበላት መጀመርድንጋጤና ስጋት ፈጥሯል፡፡

በደቡብ አፍሪካ የሰው ስጋ መበላት መጀመርድንጋጤና ስጋት ፈጥሯል፡፡

በሀገሪቱ ስጋቱ የተፈጠረው ሻይሞያ በተባለች የደቡብ አፍሪካ ግዛት የተቆራረጠ ስጋ ተጥሎ ከተገኘ በኃላ ነው
ከመንደሩ ነዋሪዎች መካከል ዛኒል የተባለች ልጃቸው መጥፋቷንና በአምስት ሰዎች በሚመራው ሰው በላ ቡድን መበላቷ እንደማትቀር ቤተሰቦቿ ተናግረዋል፡፡
ሳይሞቱ አልቀሩም የተባሉ ሰዎችን መገኛ ፖሊስ ባፈላለገበት ወቅት በአንድ ባህላዊ የመድሀኒት ቀማሚ ቤት ውስጥ የስምንት ሰዎች ጆሮ በድስት ውስጥ ለመቀቀል ዝግጁ ሆኖ ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡
ሟች ግለሰቦች በነብሰ በሊታው በመዳኒት አዋቂ ለምግብነት የሚቀርበው የሰው ስጋ ተመጋቢዎቹን ገንዘብ ታገኛላችሁ ስልጣንና ከፍታችሁ ላቅ ይላል ጤናችሁም ይስተካከላል እያለ ሰዎችን ገድሎ ለምግብነት እንደሚያዘጋጅ የአካባቢው የአይን እማኞች ለፖሊስ ገልፀዋል፡፡
በመንደሪቱ በሰው በላው ለሞት የተዳረጉት ሰዎች ለመለየት ባደረገው ጥረት የሁለት አመት ህፃን ልጅና የአንዲት እናት አካል መገኘቱንና የሌሎቹን ቀሪ ማንነት በደም ከተጨማለቁ ልብሶቹ ላይ በተገኘ የዘረ መል ምርመራ እንለያለን ብለዋል፡፡
በመንደሪቱ ያሉት ሌሎች የባህላዊ መድሀኒት ባለ ሙያዎች የሰውየው ስራ እኛን አይወክለንም ይህን ድርጊት የፈፀመውን ሰው እንቃወማለን ብለዋል፡፡
ቢቢሲ

ከ5 ሚሊየን ብር በላይ የተገመቱ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ
በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የአዳማና የኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤቶች ግምታዊ ዋጋቸው ከ5 ሚሊየንብር በላይ የሆኑ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን አስታወቁ፡፡
ከአዳማቅ/ፅ/ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚመለክተው 2.3 ሚሊየን ብር የተገመቱ ህገወጥ ዕቃዎቹ ወደ አዳማ ከተማ ሊገቡ ሲሉ በአዳማ ከተማ በተካሄደ ኮንትሮባንድ የመከላከል ዘመቻ እንደተያዙ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎችሺሻ፣ ልባሽ ጨርቆች፣ መድሃኒቶች፣ ሽቶ እና አዳዲስ አልባሳት ይገኙበታል፡፡
በተመሳሳይ የኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤትከ900ሺ ብር በላይ ዕገ ወጥ ኤሌክትሮኒክስ፣ አዳዲስ አልባሳት፣ ከስሞቲክስ እና ጫማ በሚኒባስ እና በህዝብ ማመላለሻ መኪኖች በህገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዙ ተይዘዋል፡፡
እቃዎቹ የተያዙት በወልዲያ የመቆጣጠሪያ ጣቢያ በሐምሌ 2009 ዓ.ም. መሆኑን የቅ/ጽ/ቤቱ የደንበኞች ትምህርትና ድጋፍ ቡድን አስተባባሪ አቶ መሀመድ አህመድ ተናገረዋል፡፡
ከአፍዴራ ተነስቶ በወልድያ በኩል አዲስ አበባ ለመግባት በተሳቢ መኪና ተጭኖ ሲጓዝ የነበረው የኮንትሮባንድ እቃ ግምታዊ ዋጋው ከ3.8 ሚሊየን ብር በላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ምትኬ ቶሌራ

የአለም ባንክ ጥናት ኢትዩጲያ በ2009 ካሳየችው 8.3 የእድገት ምጣኔ የተበደረችው ገንዘብ 50 በመቶ እንደሚልቅ ያሳያል፡፡
አለም ባንክ በየአመቱ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ያሳዩ ሀገራት ዝርዝር በሚያሳይበት የአለም ኢኮኖሚ እድገት የዚህ አመት እትሙ ላይ ኢትዩጲያ ባጠናቀቅነው የበጀት አመት ኢኮኖሚዋ በ8.3 በመቶ እንዳደገ አመላክቷል፡፡ ከአለም ኢኮኖሚ እድገት ጋር ሲነጻጸርም በ2.7 በመቶ ልቆ ተገኝቷል፡፡
አለም አቀፉ ተቋም እድገቱ በተስፋፋ የመሰረተ ልማት ግንባታ ምክንያት እንደመጣ ጠቁሟል፡፡
ነገር ግን ኢትዩጲያ ባለፉት ሶስት አመታት ከ2006አ.ም እስከ 2008 አ.ም ባለው ጊዜ የብድር መጠኗ ከእድገቷ 10 በመቶ ሲልቅ በዚህ አመት ደግሞ 50 በመቶ ሆኗል፡፡
አለም ባንክ አብዛኞቹ ፈጣን እድገት የሚያስመዘግቡ ኢኮኖሚዎች ከፍተኛ የብድር መጠንእንደሚኖራቸውና ኢትዩጲያ በአሁን ወቅት በ8.5 ሚሊዩን ህዝቦቿ ላይ ከተጋረጠው የድርቅ አደጋ አንጻር ችግሩ አሳሳቢ እንደሆነ አስታውቋል፡፡
ሀገሪቱ ያለባት የብድር መጠን የኢኮኖሚውን እድገት እንዲጎትተው እና ሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ የምትሰራው ስራ ላይም የገንዘብ አቅም ችግር በመፍጠር የድርቁን ጉዳት የከፋ ሊያደርገው ይችላል ሲል ሪፖርቱ አስነብቧል፡፡
ኢትዩጲያ በ2008 በፈጸመቻቸው የብድር ስምምነቶች ምክንያት እያንዳንዱ ዜጋ ከ11ሺህ ብር በላይ እዳ እንዳለበት ከዚህ በፊት መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ናርዶስ ዩሴፍ

Tuesday, 29 August 2017 13:25

የጓታማላ ፕሬዚዳንት የተባበሩት መንግስታት የጸረ-ሙስና መርማሪ ኮሚሽን ዋና ሀላፊ ሀገሪቷን ለቀው እንዲወጡ አዘዘ፡፡

የጓታማላ ፕሬዚዳንት የተባበሩት መንግስታት የጸረ-ሙስና መርማሪ ኮሚሽን ዋና ሀላፊ ሀገሪቷን ለቀው እንዲወጡ አዘዘ፡፡
ፕሬዚዳንት ጂሚ ሞራለስ እሁድ እለት የተባበሩት መንግስታት የጸረ-ሙስና ኮሚሽን ዋና ሀላፊ ኢቫን ቫላስኩዌዝ ጎሜዝ በአፋጣኝ ሀገሪቷን ለቀው እንዲወጡ የሚያዝ ቪዲዩ ለቀዋል፡፡
የሀገሪቱ ህገ-መንግስታዊ ፍርድ ቤት ትእዛዛቸውን ቢያግደውም ፕሬዚዳንቱ ፍርድ ቤቱ የውጪ ጉዳዩችን በተመለከተ የምወስነውን ውሳኔ የመሻር መብት የለውም ብለዋል፡፤
የተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲ የፕሬዚዳንት ሞራለስን ፖለቲካዊ ያለመያዝ እና ያለመከሰስ መብታቸውን ደግፎል፡፡
የጸረ-ሙስና ኮሚሽኑ በማጣራት ላይ የሚገኘው የጓታማላ አቃቤ ህጎች ፕሬዚዳንቱ እ.ኤ.አ በ2015 ምርጫ ፈጽሞታል የተባለውን የገንዘብ አወጣጥ ግድፈት ነው፡፡
ፕሬዚዳንት ሞራለስ እሁድ እለት በማህበራዊ ድረ ገጾች የለቀቁት ቪዲዩ መርማሪው ሀላፊ የግል አጀንዳ አድርገው ነው የያዙኝ እንጂ ተቋማዊ ምርመራ አይደለም ብለዋል፡፡
የጓታማላ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሉክሬሺያ ማክ የፕሬዚዳንቱን ውሳኔ በመቃወም ከፖለቲካም ሆነ ከሞራል አንጻር ለፕሬዚዳንቱ መስራት አስቸጋሪ ነው ስትል በቲዩተር ማህበራዊ ገጽ ጽፋ ስራዋን በገዛ ፈቃዷ ለቃለች፡፡
ፕሬዚዳንት ሞራለስ ስልጣን ከመያዛቸው በፊት ተዋናይ የነበሩ ሲሆን በምንም አይነት የመንግስት መስሪያ ቤት ሰርተው አያውቁም ነበር፡፡ ለፕሬዚዳንትነት በሚወዳደሩበት ወቅትም ሙስናን ለመቃወም ቃል ገብተው ነበር፡፡

ቢቢሲ ዘግቦታል