ደቡብ ኮሪያ የቀድሞዋን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጓደኛ አሰረች፡፡

Written by on February 14, 2018

ደቡብ ኮሪያ ያሰረችው የቀድሞዋን ፕሬዝዳንት ፓርክ ጉን ኢይ የልብ ጓደኛ የሆኑትን ቹ ሱን ሲልን ሲሆን ግለሰቧ ተጠርጥረው ፍርድ ቤት የቀረቡት ከቀድሞዋ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጋር በነበራት የቆየ ጓደኝነት አማካኝነት በስልጣናቸው ላይ እንዲባልጉና በተለያዩ የሙስና ወንጀሎች ውስጥ እንዲዘፈቁ ተፅዕኖ አሳድረውባቸዋል በሚሉ ክሶች ነው፡፡ ፕሬዝዳንት ፓርክ ጉኢን ኤይ በዚህ ድርጊታቸው የሀገሪቱ ፍርድ ቤት የ20 አመት እስርም በይኖባቸዋል፡፡

ወይዘሮዎቹ በደቡብ ኮሪያ ውስጥ በተፈፀሙ ከባድ የሙስና ወንጀሎች ውስጥ የነበራቸው ድርሻ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡
ፕሬዝዳንት ፓርክ በስልጣን ዘመናቸው በወሰኗቸው ውሳኔዎችም ወይዘሮዋ ጫና በመፍጠር ሀሳቦችን ሲያስቀይሩ እና ከባድ ውሳኔዎች በእሳቸው ቀጥተኛ አማካሪነት ሲወሰኑ ነበረ፡፡ በወይዘሮዋ ላይ እነኚህን መሰል ክሶች ቢቀርቡባቸውም የቀድሞዋ ፕሬዝዳንት ጉዳዩን አጣጥለውታል፡፡


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]