ለደቡብ ሱዳን ግጭት መባባስ ኡጋንዳ እና ኬንያ ምክንያት እየሆኑ ነዉ ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወቀሰ፡፡

Written by on February 14, 2018

ለደቡብ ሱዳን ግጭት መባባስ ኡጋንዳ እና ኬንያ ምክንያት እየሆኑ ነዉ ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወቀሰ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የደቡብ ሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት ሊያቆም ይገባል ባለበት ወቅት የአፍሪካ ህብረት ዲፕሎማሲያዊ ጥረት መቀዛቀዙ ከየትኛውም ጊዜ በላይ አሳስቦኛልም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ የዘር ማጥፋት ወንጀል መከላከል ልዩ አማካሪ አዳማ ዲየንግ ኬንያና ኡጋንዳ ለደቡብ ሱዳን የሰላም እጦት መባባስ አለታዊ አስተዋጽዎ እያደረጉ ነው ብለዋል፡፡ ትኩረቱን በደቡብ ሱዳን ባደረገው የሬድዮ ፕሮግራም ላይ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ህዝቦቹን ከሰላም እጦትና ችግር መከላከል ቅድሚያ ኃላፊነቱ የወደቀው በደቡብ ሱዳን መንግስት ላይ ቢሆንም ከዚህ ባለፈ ሸክሙ ወደ ጎረቤት ሀገራትና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሊሻገር እንደሚገባ ሊታወቅ ይገባል ብለዋል፡፡ የዋና ጸሓፊው የዘር ማጥፋት ወንጀል መከላከል ልዩ አማካሪው አዳማ ዲየንግ ኬንያን እና ኡጋንዳን የከሰሱበት ዋና ምክንያት በ2ቱ ሀገራት በኩል የጦር መሳሪያ በገፍ ወደ ደቡብ ሱዳን እየገባ መሆኑን መረጃዎች በማመላከታቸው ነው፡፡

ሲጂቲኤን


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]