የባህር ጠለል ከፍታ መጨመሩ የአየር ንብረት ላይ ችግር ፈጥሯል፡፡

Written by on February 14, 2018

የባህር ጠለል ከፍታ መጨመሩ የአየር ንብረት ላይ ችግር ፈጥሯል፡፡

ከህዋ ላይ በተወሰደ ምልከታ የባህር ጠለል ከፍ ማለቱ ለአየር ንብረት ለውጥ አፋጣኝ እንዳያደርገው ተሰግቷል፡፡

አዲስ ይፋ በተደረገ ጥናት የባህር ጠለል ከፍ ማለት ወትሮም በአስደንጋጭ ፍጥነት እየተቀየረ የመጣውን የአየር ንብረት ለውጥ ወደ ከፋ ደረጃ በማድረስ ምድርን በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዳይከታት ተሰግቷል፡፡

በኮሎራዶ ዩንቨርስቲ በተካሄደ ጥናት ከ1992 እስከ 2014 ባሉት ጊዜያት የባህር ጠለል ቀይ ወይም ብርቱካናማ ቀለም በመያዙ ስጋት መፈጠሩን አስታውሰው ባሁኑ ሰዓት ደግሞ የባህር ጠለል ከህዋ ላይ ሆኖ ሲታይ ሰማያዊ ቀለም ይዟል ይህም ስጋት ነው ብለዋል፡፡

 

የጥናት ቡድኑ አባላት ባደረጉት ጥናት በውቅያኖሶች አካባቢ ያለው የባህር ጠለል በ25 ዓመታት ውስጥ 7 ሴንቲ ሜትር ከፍ ይል የነበረ ቢሆንም አሁን የከፍታው መጠን 3 ሜትር ደርሷል፡፡

ለባህር ጠለል ከፍ ማለት የግግር በረዶዎች ከተጠበቀው ፍጥነት ቀድመው መቅለጥ መጀመራቸው ፣የመሬትን ከባቢ አየር የሚቆጣጠረው ግሪን ሀውስ መጠኑ ዝቅ ማለት በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡

 

 


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]