አንድ ጥናት ኢትዮጲያ ውስጥ ከ4 ሚሊዮን በላይ አሳዳጊ አልባ ህጻናት መኖራቸውን አሳይቷል፡፡

Written by on February 13, 2018

የካቲት 6  2010

አንድ ጥናት ኢትዮጲያ ውስጥ ከ4 ሚሊዮን በላይ አሳዳጊ አልባ ህጻናት መኖራቸውን አሳይቷል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በማህበረሰብ ተኮር አማራጭ እያደጉ ያሉት የእነዚህ ህጻናት ብዛት ብቻ ወደ 5 ሚሊዮን እንደሚደርሱ ያሳያል፡፡

አንድ ህጻን የሚያድግበት መንገድ ወደ ፊት እንደ ሰው የሚኖረው ማንነት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

በኢትዮጲያ ከአጠቃላይ ህዝቡ 50 በመቶ ያህሉ እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ህጻናት ናቸው፡፡

በሀገሪቱ ተለዋዋጭ እና አስቸጋሪ በሆኑ የማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ከዚያም ባለፈ የሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ባህል ተጨምሮበት ለህጻናት ተስማሚ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ህጻናት ቁጥር ከአመት አመት እየጨመረ መጥቷል፡፡ ይህ እውነታ ደግሞ በኢትዮጲያ የሰራተኞች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከ5 አመታት በፊት ያጠናው ጥናት ላይ ሰፍሯል፡፡

በተባበሩት መንግስታት የህጻናት ኤጀንሲ ዩኒሴፍ በ1984 ኢትዮጲያን በአለም ከፍተኛ የሆነ ወላጅ አልባ ህጻናት የሚገኙባት ሀገር ሲል ሰይሟት ነበር፡፡ ይህ ነገር እየተባባሰ መምጣቱን የሚያሳየው ደግሞ ማእከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ 2005 አ.ም ላይ ያወጣው መረጃ በኢትዮጲያ በአጠቃላይ እድሜያቸው ከጨቅላነት አንስቶ እስከ 17 አመት ድረስ የሆነ 4 ሚሊዮን 885 ሺህ 337 አሳዳጊ የሌላቸው ህጻናት እንዳሉ ያሳያል፡፡

ኢትዮጲያ የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መብት ስምምነት UNCRC እና የአፍሪካ የህጻናት መብት እና ደህንነት ቻርተር ACRWCን ተቀብላ ስምምነቱን ያጸደቀች ሀገር ናት፡፡

በእነዚህ 2 ስምምነቶች ላይ በግልጽ እንደተደነገገው ስምምነቱን ተቀብለው ተግባራዊ በሚያደርጉ ሀገራት በሙሉ ለአሳዳጊ አልባው ህጻን ጥቅም፤ መልካም

አስተዳደግ እና ደህንነት የተሻለው አማራጭ የሀገር ውስጥ ጉዲፈቻ ወይም በሀገር ውስጥ የማደጎ ድርጅቶች ማሳደግ ነው፡፡

የውጪ ሀገር ጉዲፈቻም የሚፈቀደው ሁሉም ህጻኑ በሀገር ውስጥ ሊያድግባቸው የሚችሉት አማራጮች ሲታጡ ነው፡፡

በተባበሩት መንግስታት የህጻናት ኤጀንሲ ዩ-ኒ-ሴ-ፍ በቅርብ ጊዜ የተሰራ ጥናት እንደሚያሳየው በኢትዮጲያ 4.5 ሚሊዮን አሳዳጊ የሌላቸው ህጻናት አሉ፡፡

ከሴቶች እና ህጻናት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ከ2002 አ.ም እስከ 2007 ባለው 5 አመት ብቻ በተለያዩ ማህበረሰብ ተኮር የማደጎ አማራጮች በኩል እንዲያድጉ እየተደረገ ያሉት አሳዳጊ አልባ ህጻናት ቁጥር በ2002 ከነበረበት 361 ሺህ 857 ህጻናት ከ 5 አመት በኋላ ወደ 4.9 ሚሊዩን ህጻናት አድጓል፡፡

በዚሁ የ5 አመት ጊዜ ውስጥ በሀገር ውስጥ ጉዲፈቻ እንዲያድጉ ለአሳዳጊ የተሰጡት ህጻናት ብዛት ከ1347 ወደ 10387 ከፍ ብሏል፡፡

በሌላ በኩል ክልል ተሻጋሪ የሆኑት የሀገር ውስጥ ጉዲፈቻዎች ከ2ሺህ አ.ም እስከ 2006 ባለው ከነበረበት 4269 በሀገር ውስጥ በክልሎች በሚገኙ አሳዳጊዎች ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል የተወሰዱ ህጻናት ወደ 1250 በክልል አሳዳጊዎች ወደ ተወሰዱ አሳዳጊ ህጻናት ዝቅ ብሏል፡፡

ይህም ከክልል ክልል የሚደረጉ የሀገር ውስጥ ጉዲፈቻዎች ብዛት ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ በየአመቱ በ29.28 ዝቅ እያለ ሄዷል፡፡

የሀገር ውስጥ ጉዲፈቻ ፈተናዎች ሲል ከዘረዘራቸው ጉዳዮች መካከል ተቀዳሚ የሆነው ማህበረሰቡ ስለሀገር ውስጥ ጉዲፈቻ ያለው ግንዛቤ ዝቅተኛ መሆኑ ነው፡፡

የኢፌድሪ ህገመንግስት አንቀጽ 36 የህጻናት መብት እና ደህንነት ጥበቃ በተመለከተ ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብቶችን ድንጋጌዎች ባማከለ

መልኩ ወሳኝ የሚባሉ አስፈላጊ የአስተዳደር፤ የፖሊሲ እና የህግ ማሻሻያ እርምጃዎችን እንዴት መሆን እንዳለባቸው አስፍሯል፡፡

የህገ-መንግስቱ አንቀጽ 36 ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት በግልም ሆነ በህዝብ ተቋማት ለማደጎ የሚሰጡ ህጻናት በፍርድ ቤት፤ በአስተዳደር ባለስልጣናት ወይም በህግ አውጪ አካላት በኩል ማለፍ ሲኖርባቸው ህጻኑን እንዲያሳድግ የሚፈቀድለት ቤተሰብም ሆነ ተቋም መመረጥ ያለበት ታዳጊውን ከሁሉም የላቀ ጥቅም የሚሰጥ መሆኑ ሲረጋገጥ እንደሆነ ይደነግጋል፡፡

 


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]