ጽ/ቤቱ እና ባለስልጣን መ/ቤቱ ለመንገድ ጥገና ተለቋል ያሉት ገንዘብ መጠን በ 3 ሚሊዮን ብር ልዩነት አሳይቷል፡፡

Written by on February 13, 2018

የካቲት 6  2010 ዓ.ም

ጽ/ቤቱ እና ባለስልጣን መ/ቤቱ ለመንገድ ጥገና ተለቋል ያሉት ገንዘብ መጠን በ 3 ሚሊዮን ብር ልዩነት አሳይቷል፡፡

ለኢትዮጵያ የመንገድ ጥገና የሚውል ገንዘብ እንዲመድብ በአዋጅ 66/89 የተቋቋመው የኢትዮጵያ መንገድ ፈንድ ጽ/ቤት ለአዲስ አበባ የመንገድ ጥገና ለከተማዋ መንገዶች ባለስልጣን 70 ሚሊዮን ብር እንደሰጠ የጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ረሻድ መሀመድ ተናግረዋል፡፡

የጽ/ቤቱ ዳይሬክተር አቶ ረሻድ ለአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን በየአመቱ 70 ሚሊዮን ብር ለመንገድ ጥገና እንደሰጡ ቢናገሩም ዛሚ ያነጋገራቸው የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ጥዑማይ ወ/ገብርኤል ባሳለፍነው አመት ከጽ/ቤቱ 53 ሚሊዮን ብር፣ በተያዘው ዓመት ደግሞ 67 ሚሊዮን ብር እንዳገኙ አረጋግጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንገድ ፈንድ ጽ/ቤት 90 በመቶ የሚሆነውን ገቢ የሚያገኘው ከነዳጅ ታሪፍ እንደሆነ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም በሀገሪቱ የሚከናወኑ የመንገድ ጥገናዎች 15% የገንዘብ ድጋፍ በጽ/ቤቱ የሚሸፈን ነው፡፡ በአጠቃላይም በየአመቱ 2.5 ቢሊዮን ብር በላይ ያወጣል፡፡

የከተማዋ መንገዶች ባለስልጣን መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ባለስልጣኑ በ2007 በጀት ዓመት 30 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ለመጠገን አቅዶ 29 ኪሎ ሜትር እንዲሁም በ2008 በጀት ዓመት 30 ኪሎሜትር ለመጠገን አቅዶ 42 ኪሎ ሜትር ሲጠግን በ2009 በጀት ዓመት 70 ኪ.ሜ የአስፓልት መንገድ ጥገና ለማድረግ አቅዶ በግማሽ ዓመቱ 67 ኪ.ሜ ማሳካት ችሎ ነበር፡፡


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]