በሳቅ ምክንያት ለህልፈተ-ህይወት የተዳረጉ 10 ግለሰቦች

Written by on February 12, 2018

ሳቅ የደስታ ምንጭ ብቻ ሳይሆን የጤንነትም ቁልፍ እንደሆነ በርካቶች ይስማማሉ፡፡
Tought catalog.com ግን ከዚህ በተቃራኒው በሳቅ ምክንያት ለህልፈተ-ህይወት የተዳረጉ 10 ግለሰቦች ሲል አውጥቷል፡፡
እኛ ደግሞ እስቲ 4ቱን እናካፍላችሁ፡፡
1. አሌክስ ሚሼል፡- እ.ኤ.አ በ1975 በአንዱ እለት አመሻሽ ላይ kungfu kapers የተባለውን ፊልም እያየ ከፊልሙ አንዱ ትእይንት ያስቀውና ከ30 ደቂቃ በላይ በሳቅ ፍርፍር እያለ ህይወቱ አለፈ፡፡
2. ቶማይነሲን ኡም፡- እ.ኤ.አ በ2003 የከባድ መኪና ሹፌር የሆነው ይኸው ግለሰብ ካለማቋረጥ ለ2 ደቂቃ ከሳቀ በኋላ ትንሽ ልረፍ ብሎ ጋደም እንዳለ እስከመጨረሻው አሸልቧል፡፡
3. ኦሌ ቤንዜን፡- እ.ኤ.አ በ1988 የጆሮ ሀኪም የነበረው ይህ ሰው a fish called wanda የተሰኘውን ታዋቂ የኮሜዲ ዘውግ ያለው ፊልም እያየ እጅግ ይስቃል፡፡ በዚህም ምክንያት በደቂቃ ከ250- 500 ልቡ በመምታቱ ህይወቱ አልፏል፡፡
4. ክሪሲፐስ፡- በ3ኛው መ/ክ/ዘመን የነበረው ይህ የግሪክ ፈላስፋ አህያው በአቅራቢያዋ ካለው ወራጅ ያገኘችውን እንቁራሪት ስታንከባልለው ያይና በሳቅ ፍርስ ይላል፡፡ከደቂቃዎች በኋላም ህይወቱ አልፏል፡፡
Image may contain: 1 person, tree and outdoor


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


[There are no radio stations in the database]